TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል። ሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታህሳስ ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ? - ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም - ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም - ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም…
#እንድታውቁት

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።

ሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።

@tikvahethiopia
የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ መቼ ነው ?

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

44ኛው የአባል ሀገራቱ የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከመሪዎች ጉባዔ ቀደም ብሎ የካቲት 6 እና 7 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ሕብረት የ2024 መሪ ቃል " ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት " የሚል ነው።

የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ (አዲስ አባባ) እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam2016

ከጥቂት ቀናት በኃላ የሚሰጠውን ሀገር አቀፉን የመውጫ ፈተና " ካለንበት ዩኒቨርሲቲ / ተቋም በርካታ ኪሎ ሜትሮችን ርቀን ተጉዘን እንድንፈተን #መመደባችን ተነግሮናል " ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።

ቅሬታቸውን ካሰሙት መካከል የተወሰኑት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጥቁር አንበሳ ' ስኩን ኦፍ ሜዲስን ' ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ የካቲት 6 /2016 ዓ/ም መሰጠት የሚጀምረውን ፈተና ለመፈተን ከአዲስ አበባ ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሚርቀው ወሎ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደቡ እንደተነገራቸውና ጉዳዩ ፍፁም ያልጠበቁት ዱብእዳ እንደሆነ አስረድተዋል።

" የምርቃት ቀናችን 10 ቀናት እየቀሩት የመውጫ ፈተና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ420 ኪ/ሜ ርቀን በወሎ ዩኒቨርስቲ እንደምንፈተን ተነግሮናል፤ ይህ ፍፁም ያጠበቅነውና ያልተለመደ ነው " ብለዋል።

ከተቋማችን እጅግ ርቀን ፈተናውን እንድንወስድ ተመድበናል ያሉት ተማሪዎች ፤ " ላለፉት 8 ዓመታት እዚህ ቀን ላይ ለመድረስ ከነቤተሰቦችን ከፍተኛ መስእዋትነት ከፍለናል፤ ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፈናል " ያሉ ሲሆን ቤተሰቦችም የልጆቸውን ድካም ፍሬ ለማየት እየተጠባበቁ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ተመራቂዎቹ ፦
- አሁን ባለው ሁኔታ ረጅም ጉዞ ማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ እየታወቀ፤
- ለምርቃት የቀረው አጭር ቀን ሆኖ ሳለና በርካታ ካምፓሶች በአዲስ አበባ እያሉ፤
- የብሄራዊ የመውጫ ፈተናው በኦንላይ እንደሚሰጥ እየታወቀ፤
- የደህንነታችን እና በዚህ የምርቃት ወቅት የቤተሰብ ኢኮኖሚ ጉዳይ ፍፁም ታሳቢ ሳይደረግ ለምን እንደዚህ ያለው ውሳኔ እንደተላለፈ በፍፁም ሊገባን አልቻለም፤ ማብራሪያም ሊሰጠን የወደደ አካል የለም ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም " ይህ ወደ ሌላ ቦታ ሄዳችሁ በኦንላይ የሚሰጠውን ፈተና ትወስዳላችሁ " የሚለው ነገር ተገቢ ባለመሆኑ እርምት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ከ ' ስኩል ኦፍ ሜዲስን ' ተመራቂዎች በተጨማሪ የተወሰኑ የምህንድስና ተማሪዎችም ተመሳሳይ ቅሬታቸውን አድርሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመራቂ ተማሪችዎች ጋር በውስጥ የደረሰ የመፈተኛ username ፣ password  እንዲሁም የመፈተኛ ጣቢያ (ዩኒቨርሲቲ) የያዘ ፋይል ደርሶት ተመልክቷል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማት ተመራቂዎች መሰል ቅሬታዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰዋል።

አንዳንድ ተመራቂዎች አሁን ካሉበት ዩኒቨርሲቲ ርቀው እንደሚፈተኑ በተወካዮቻቸው በኩል እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

በተመሳሳይ እነዚህ ተመራቂዎች ፤ በዚህ ወቅት ወደሌላ ቦታ እንዲጓዙ ተደርገው የኦንላይን ፈተና የሚወስዱበት ምክንያት ምንም ግልፅ እንዳልሆነላቸውና ይህ ነገር ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ማሰብና ማስተካከል እንደሚገባ አስገንዘበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችን ለማነጋገርና መረጃ ለመስጠት ጥረት ያደርጋል።

በአመቱ አጋማሽ ላይ የሚሰጠው የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ተራዝሞ ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል።

በዚህ ሳምንት የሞዴል ፈተና ይሰጣል።

@tikvahethiopia
“ ወደ 10 የሚደርሱ ደጋፊዎችና አባላቶች ታስረዋል” - አቶ ጀሚል ሳኒ

የጎጎት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጀሚል ሳኒ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “በአመራር ደረጃ ሦስት ከፍተኛ አመራሮች እስር ላይ ናቸው። ደጋፊዎች የተለያየ ቦታ ይታሰራሉ። ቁጥራቸው አንዱ ሲታሰር ሌላው የመፈታት ሁኔታዎች አሉ” ብለዋል።

“ወደ 10 የሚደርሱ ደጋፊዎችና አባላቶች ታስረዋል” ያሉት ኃላፊው፣ “ኪዚያ በተጨማሪም አካባቢው ላይ የፓርቲያችን አባላቶች ባይሆኑም ወጣቶችን የማሳደድ፣ የማሰር (በተለይ የክልል ጥያቄ ጋር አክቲቭ ሆነው ሲሳተፉ የነበሩትንም የአካባቢው ወጣቶች አሳሳዶ የመያዝ) ሂደቶች አሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

የታሰሩ ሰዎችን ለማስፈታት ፓርቲው ምን ያህል ጥረት አድርጓል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም አቶ ጀሚል፣ “አብዛኛው እስሩ ፖለቲካል የሆነ እስር ነው ብለን ነው የምናስበው። ብዙ ጊዜ የፖለቲካ እስር ባለቤት አይኖረውም” ብለዋል።

አቶ ጀሚል አክለውም፣ “አሁንም አቃቢ ህጎች ‘ክስ እጃችን ላይ ምንም የለም’ ሲሉ ሁለት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ‘ይሄ ነው’ ነው ብለው በጥፋትም መልክ ወይም በክስም ቢሆን ያቀረቡት ነገር የለም” ሲሉ አስረድተዋል።

አቶ ጀሚል ሳኒ ስለ ጉዳዩ በዝርዝር ምን አሉ ?

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-06

@tikvahethiopia
#አሁን

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

በስበስባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን በምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች እየቀረበላቸው ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

@tikvahethiopia
#BeledHawo

በደቡባዊ ሶማሊያ ፤ ጌዶ ክልል ፣ በሌደሀዎ በተባለ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ኢትዮጵያውያን እና አንድ ሶማሊያዊ መገደላቸውን ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።

በዚህ ምክንያት በርካቶች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተነግሯል።

ታጣቂዎቹ ሌሊት ኢትዮጵያውያን ወደ ሚኖሩበት ቤት በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 3 ሴቶች እና 3 ወንዶችን ሲገድሉ 1 ሶማሊያዊም መገደላቸው ተነግሯል።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በሶማሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተወካይ በሰጡት ቃል ፤ ቅዳሜ ሌሊት 6 እሁድ 1 በተለያየ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል ብለዋል።

" ከተገደሉት መካከል ሁለቱ ሕጻናት ሲሆኑ ፣ እናት እና አባቷ ተገድለውባት ብቻዋን የቀረች ሕጻንም አለች " ሲሉ አክለዋል።

" የተገደሉት ሰዎች ወደ አገራቸው ተመልሰው በሥነ ሥርዓት ቀብራቸው እንዲፈጸም እንፈልጋለን። መንግሥት ይህን ማድረግ ይችላል። ለተገደሉትም ፍትሕ እንዲሰፍንም እንፈልጋለን " ሲሉ አክለዋል።

ጥቃቱ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ እንደሆኑና በርካቶች ወደ አገር ቤት መመለስ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።

የበለደሀዎ አስተዳዳሪ አብዲራሺድ አብዲ ፤ ግድያው ሌሊት 9 ሰዓት መፈጸሙን እንደታወቀ አመልክተዋል።

ግድያ መፈፀሙ የታወቀው የአካባቢው የፀጥታ ባልደረቦች የተኩስ ድምጽ ከሰሙ በኋላ ሲሆን 7 ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን አስረድተዋል።

" ማቾቹ በአጠቃላይ ለሥራ የመጡ ስደተኞች ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአካባቢው ሆስፒታል የሚሠራ አንድ ዶክተር በሰጠው ቃል በጥቃቱ የተገደሉ የ6 ኢትዮጵያውያን አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ መምጣቱን አረጋግጧል።

በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 6 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውንም ገልጿል።

ምንም እንኳን እስካሁን ከግድያው ጀርባ ማን እንዳለ ያልታወቀና ኃላፊነት የወሰደም አካል የሌለ ቢሆንም የአካባቢው አስተዳዳሪ " ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት ገዳዮቹ #የአልሸባብ አሸባሪዎች ናቸው " ብለዋል።

" እስካሁን አልተያዙም። ለምን ስደተኞን ዒላማ አደረጉ ለሚለው ጥያቄ፣ ይህ ግድያ በመላው አገሪቱ ከሚፈጸመው ግድያ የሚለይ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው የቢቢሲ ሶማልኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። በስበስባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን በምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች እየቀረበላቸው ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ። @tikvahethiopia
#Update

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት መካከል ፦

" ... ዋናው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሥራ አጥነት ነው።

አብዛኛው ሰው cause ኖሮት አይደለም። ሥራ ፍለጋ ይሄዳል ያግታል ብር ይጠይቃል።

ዓላማ መር ትግል ሳይሆን እገታ መር ትግል ነው ያለው።

ይሄን ደግሞ በርከት አድርጎ ሥራ በመፍጠር ወጣቱ ወደ ሥራ እንዲሄድ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ተግባሩ ነው ጥረት እየተደረገ ነው ማጠናከር ይኖርብናል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት መካከል ፦ " ... ዋናው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሥራ አጥነት ነው። አብዛኛው ሰው cause ኖሮት አይደለም። ሥራ ፍለጋ ይሄዳል ያግታል ብር ይጠይቃል። ዓላማ መር ትግል ሳይሆን እገታ መር ትግል ነው ያለው። ይሄን ደግሞ በርከት አድርጎ ሥራ በመፍጠር ወጣቱ ወደ ሥራ እንዲሄድ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ተግባሩ…
#Update

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሀገራዊ ሰላምና ፀጥታ ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ " መንግሥት በቀጣይነት ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል " ብለዋል።

" ሕግ ማስከበር አጠናክረን እንቀጥላለን " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጡ የሚለውን ጉዳይ አንስማማም አንቀበልም አናደርግም። መንግሥት ነን አቅም በፈቀደ መጠን ሕግ ለማስከበር እንሰራለን " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ሕግ ለማስከበር ስንሰራ በየአንዳንዷ ሰከንድ ለሠላም ዝግጁ የሆነ ኃይል ካለ በራችን ክፍት ነው " ያሉ ሲሆን " ለውይይት ለሠላም፣ ለንግግር ክፍት ነን። ሕግ የማስከበሩን ሥራ ከንግግር እና ከውይይት ውጭ እንዲሆን አንፈልግም " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ እና ትግራይ ድርቅ ባስከተለው #ረሃብ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ምን ያህል ሰዎች ድርቅ ባስተከተለው ረሃብ ሞቱ ? በትግራይ ክልል ፤ በማዕከላዊ ዞን 334 ሰው ከድርቁ ጋር በተያያዘ የሞተ ሲሆን ከዚህ ዞን ውስጥ የተቋሙ ቁጥጥር ቡድን ካየው የአበርገሌ ወረዳ 91 ሰው መሞቱን እና ከደቡብ ምስራቅ…
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህ/ተ/ም/ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ፤ " እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

" በትግራይ የተወሰነ አካባቢ ፣ በአማራ የተወሰነ አካባቢ ፣ በኦሮሚያ ፣ ምስራቁ ክፍልም እንዲሁ ድርቅ አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህ ምንም ጥያቄ የለውም ፤ ይህን ግን ማየት ያለብን እንደ ፖለቲካ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ድርቅን መንግሥት አላመጣውም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " environmental crisis አለ ችግኝ እንትከል ሲባል ችግኝ ምን ያደርጋል ብለን ፤ ድርቅ እና ረሃብ አለ ስንዴ እናምርት ስንል ስንዴ ምን ያደርጋል ብለን ድርቅ መጣ ብለን ብንጮህ ትርጉም የለውም ትርጉሙ ተባብሮ ሰው እንዳይሞትብን ማድረግ ነው " ብለዋል።

በቦረና በተደረገ ርብርብ ምንም እንኳን ከብቶች ቢሞቱም ሰው አልሞተም ፤ በሶማሌ ክልልም እንዲሁ በርብርብ ሰው እንዳይሞት ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁንም ትግራይ ፣ አማራ ፣ ኦሮሚያ ተርቦ እዚህ በልተን ማደር አንችልም ተባብረን ሰው እንዳይሞትብን ማድረግ አለብን ፤ ግን ድርቅን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ የምንጠቀም ከሆነ ጥፋት ነው " ብለዋል።

" ባለፉት 4 ወራት ወደ ትግራይ 500 ሺህ ኩንታል እህል በዋነኝነት በመንግሥት እና በተወሰኑ ደጋፊዎች ተልኳል ይህ ሶስት አራት ወር ሰው በምግብ እጥረት እንዳይሞት ያደርጋል። የትግራይ መንግስትም ያለውን resource / እህል ውስንም ቢሆን የከፋ ችግር ያለበት ቦታ ማድረስ አለበት፤ ያለው እህል በትክክል ካልተሰራጨ ችግር ሊያመጣ ይችላል " ብለዋል።

" ያለው resource በቂ ካልሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አቅም እያለውና የኢትዮጵያ ህዝብ በልቶ እያደረ አንድም ቦታ በረሃብ የሚሞት ሰው አይተን ዝም አንልም፤ ባለን አቅም ህዝባችንን አግዘን ይህችን ጊዜ እንዲሻገር እናደርጋለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

" መንግሥት ለድርቅ ትኩረት አልሰጣም " የሚባለውን አስተያየትም አጣጥለውታል ሰው እንዳይሞት በዋነኝነት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያወጣ ነው ብለዋል።

" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት ሚሞት ሰው የለም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ያለው ችግር ረሃብ እና አብሮ የሚመጣ በሽታ አለ በትግራይ ብቻ ሳይሆን ደቡብ ምዕራብ አካባቢ ብትወስዱ አዲስ የወባ ባህሪ አለ ያ የወባ ባህሪ በጥቂት ቀናት ሰው ይገድላል ከዚህ ቀደም የሚሰጡ መድሃኒቶችም ፈውስ አላመጡለትም ወባ ሲጨመር ፣ ተቅማጥ ሲጨመር በምግብ እጥረት እላዩ ላይ በሽታ ሲጨመር ሰው መቋቋም አቅቶት ሊሞት ይችላል " ብለዋል።

" ይሄ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ የሚሆን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምንም ጊዜ በላይ በታሪክ ተምርቶ የማያውቅ ምርት አለ " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ይህ ሁሉ እያለ ምርት አምራች አርሶ አደሮች " ወንድምህ ተርቦ እየሞተ ነው " ሲባሉ ዝም ይላሉ ብላችሁ አትጠብቁ ፤ መንግሥት እንኳን ባያደርግ ህዝቡ ተረባርቦ ሰው እንዳይሞት ጥረት ያደርጋል ብለዋል።

፣ መንግስት የሚራብበት ዜጋ ካለ ፕሮጀክት አጥፎ ህዝቡ በረሃብ እንዳይሞት ከህዝቡ ጋር የሚችለውን ሁሉ ይሰራል " ሲሉ ተናግረዋል።

በቅርቡ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ይፋ ባደረገው ሪፖርት በትግራይ እና በአማራ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ምክንያት 372 ሰዎች መሞታቸውን ፤
23 ህፃናት በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት ተገቢዉን ዕድገት ባለማግኘታቸዉ ሞተው መወለዳቸውን ማረጋገጡ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህ/ተ/ም/ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ፤ " እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ሲሉ ተናግረዋል። " በትግራይ የተወሰነ አካባቢ ፣ በአማራ የተወሰነ አካባቢ ፣ በኦሮሚያ ፣ ምስራቁ ክፍልም እንዲሁ ድርቅ አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህ ምንም ጥያቄ…
#ድርቅ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርቅን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ " አሁን የተከሰተው ከ77ም ያልተናነሰ ነው " በሚል ከዚህ ቀደም የተሰጡ አስተያየቶችን ኮነኑ።

" የሚታረስ መሬት እያለን የሰው ጉልበት እያለን ድህነንት እና ልመናን ጌጥ አናድርገው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ተቸግረዋል ሊያልቁ ነው ሲሉን እንደ ሽልማት አንውሰደው ኮሮና መጣ ሊረግፉ ነው አሉ ረገፍን እንዴ ? አልረገፍንም ሟርት ነው። ጦርነት ስንጀምር ታስታውሳላችሁ ረሃብ ረሃብ ረሃብ አሉ እውነት ነው እንዴ ? " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአንድ በኩል መዘናጋት የለብንም ችግር ሲመጣ ተረባርባን እንፍታው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " 6 ወር ያልፍና የታለ የሞተ ሰው ፣ የተባለው የታለ ሲባል ማፍር ያመጣል " ብለዋል።

" አንዳንዱ ከ77 ያልተናነሰ ድርቅ አለ ይላል ማለትም 1 ሚሊዮን ገደማ ሰው ይሞታል ማለት ነው ፤ አንድ ሚሊዮን ካልሞተ እየዋሸ ነው ሰውየው እኛ ደግሞ 1 ሚሊዮን ሳይሆን አንድም እንዳይሞት አቅማችን በፈቀደ እንፍጨረጨራለን ከአቅም በላይ ከሆነስ ? እሱ ምን ይደረጋል " ብለዋል

አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ከተረባረበች ቢያንስ ሰው እንዳይሞት የማድረግ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።

ከወራት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) ፤ በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 እንደነበርና አሁን ያጋጠመው ከዚህም በላይ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ፤ " በትግራይ ረሃብ እና ሞት እያንዣበበ ነው "  ያሉ ሲሆን ከ1977 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ ድርቅ ነው የተከሰተው ሲሉ ተናግረው ነበር።

በእድሜ የገፉ አዛውንቶችም በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው መሬት እህል አላበቅል እንዳላቸውና ሁኔታው ከ1977 የከፋ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት መካከል ፦ " ... ዋናው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሥራ አጥነት ነው። አብዛኛው ሰው cause ኖሮት አይደለም። ሥራ ፍለጋ ይሄዳል ያግታል ብር ይጠይቃል። ዓላማ መር ትግል ሳይሆን እገታ መር ትግል ነው ያለው። ይሄን ደግሞ በርከት አድርጎ ሥራ በመፍጠር ወጣቱ ወደ ሥራ እንዲሄድ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ተግባሩ…
" በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ የዜጎች #እስር ጉዳይ ነው።

" እስር በዝቷል " በሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው መልስ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እውነቱን ለመናገር አሁን እንዳለው anarchy ፣ ስድብ ፣ጥፋት እስር ቢበዛ ኖሮ ፓርክ ሳይሆን እስር ቤት ነበር የምንገነባው " ያሉ ሲሆን " በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ " ብለዋል።

ምሳሌ ብለውም ፤ ሸራተን ጀርባ ብዙ ተለፍቶበት ተሰርቷል ያሉትና ስራ ከጀመረ 15 ቀን ገደማ በሆነው መንገድ ላይ ቆመው ሽንት የሚሸኑ ሰዎች ጠቅሰዋል።

" እነዚህ ሰዎች ቢታሰሩ አገባብ አይደለም ወይ ? " ሲሉ ጠይቀው " ለማጥፋት ነው የሚመስለው እንጂ ካልጠፋ ቦታ እንደዛ አይነት ቦታ ላይ ሄዶ እንደዛ አይደረግም " ብለዋል።

" እኛ እስር ቤት ሳይሆን ፓርክ ነው እየገነባን ያለነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ከሆነ የእስር ጉዳይ የተነሳው ... ከተያዘው አብዛኛው ሰው ተምሮ ወጥቷል። " ብለዋል።

በሺህ የሚቆጠር ሰው ከእስር እንደወጣ የገለፁት ዶ/ር ዐቢይ " አሁን በጣም በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው እስር ቤት ያሉት። እነሱም እየተጣሩ፣ እየተማሩ ሊፈቱ ይገባል ፤ ሰው እስር ቤት አቆይቶ መቀለብ ለድሃ መንግሥት አያዋጣም። አስተምሮ መመለስ ያስፈልጋል " ብለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " የታሰሩ ሰዎች እዚህም እዚያም አሉ " ያሉ ሲሆን " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚመራው ኃይል እየመረመረ እያወያየ እያሰለጠነ አብዛኛዎችን ይፈታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ መሆንም ያለበት እንደዛ ነው። " ብለዋል።

" ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ከዚያ ጋር አብሮ የሚጨፈለቅ ፣አብሮ የሚታይ ነገር ካለ መፈተሽ ጥሩ ነው " ብለዋል።

" እንደው እንከን የለውም የመንግስት አሰራር ብሎ መሄድ ጥሩ አይደለም። የምንፈጥረው ስህተት ካለ እየመረመርን ማስተካከል አለብን። ካጠፋን ይቅርታ መጠየቅ አለብን። " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ሀገር ሲፈርስ ዝም ብለን አናይም፤ ስራችን መጠበቅ ስለሆነ ሀገር ጠባቂ ነን ብለን ደግሞ ጥፋት የምናመጣ ከሆነ መጠየቅ አለብን። በጣም በርካታ ሰዎች እኛ ውስጥ ሆነው የሚሰርቁ የሚያጠፉ አሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" #መለዮ ለብሰው ሰላም ማስከበር ሲገባቸው ጥፋት ላይ የሚሳተፉ ሰዎች አሉ " በማለት የተናገሩት ጠ/ሚኒስትሩ " ብዙዎቹ ይያዛሉ እነሱም ይጠየቃሉ። 100% የተሟላ ባይሆንም በውስጥ የእርማት ስራዎች በስፋት ይሰራሉ " ብለዋል።

@tikvahethiopia