TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሶማሌላንድ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈፀም መብትን የሚደግፍ እና የሶማሊያን መንግሥት ጣልቃ ገብነትን ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፏል። ሶማሌላንድን የራሴ አካል ናት የምትለውን ሶማሊያ እያቀረበች ያለውን የይገባኛል ጥያቄ #ውድቅ በማድረግም "የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነትና ነጻነቷ የተረጋገጠ ነው " ብሏል። የሶማሊያው…
#Update

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ የሁለትዮሽ ስምምነት ለማድረግ " የሶማሊያ ፍቃድ "አያስፈልገኝም ፤ አልጠይቅምም " አለች።

ከሶማሊያ ተነጥላ ሶስት አስርት ዓመታት እንደሆናት የገለፀችው ሶማሌላንድ፤ ሶማሊያ የምታቀርበው " የኔ አካል ናት " የሚለው የባለቤትነት ጥያቄ ፍፁም ሀሰት ነው ስትል ገልጻለች።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን በሶማሊላንድ የወደብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት አንድ ሀገር ከሌላ ሀገር ጋር ከሚደርገው #የሊዝ_ኮንትራቶች የተለየ አለመሆኑን አመልክታለች።

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፤ ሶማሊያ የመግባቢያ ስምምነቱን በተመለከተ ያየዘችውን አቋም እና ያወጣቻቸውን መግለጫዎች ሁሉ #ውድቅ አድርጋለች።

ከዚህ ባለፈ ሶማሌላንድ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማድረግ የሶማሊያን ፈቃድ ትፈልጋለች የሚባል ማንኛውም ሀሳብ ፍፁም ውሸት ነው ስትል ገልጻለች።

ሶማሊላንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ጋር የራሷን ነጻ የሆነ ግንኙነት ስታደርግ እንደነበርና አሁንም የምትቀጥል መሆኑን ገልጻ ከአሁኑ የመግባቢያ ስምምነት በፊት በርካታ ዓለም አቀፍ እና የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በተሳካ ሁኔታ መፈፀሟን አስታውሳለች።

ከእነዚህ ከተፈፀሙ ዓለም አቀፍ እና የሁለትዮች ስምምነቶች መካከል አንዳቸውም ከሶማሊያ ፈቃድ አልተጠየቁም ወይም አልተቀበሉም ብላለች።

ሶማሌላንድ ባለፉት 33 ዓመታት የሶማሌላንድ እና የሶማሊያ #ተቃራኒ ሁኔታዎችን ብዙ ይናገራሉ ስትልም ገልጻለች።

ሶማሌላንድ ፤ በአፍሪካ ቀንድ የበለፀገ ዲሞክራሲ እና የመረጋጋት ምልክት ሆና የውስጥ ጉዳዮቿን፣ አስተዳደሯን እና ምርጫዋን ያለአለም አቀፍ ድጋፍ በብቃት በመምራት ላይ እንደሆነች አመልክታችለች።

" ሀገራችን እና የባህር ዳርቻዋ ያለማቋረጥ / በወጥነት ከዘረፋ፣ ከሽብርተኝነት እና ከሽፍታነት የፀዱ ናቸው። " ስትል አክላለች።

በአንፃሩ ሶማሊያ ላለፉት 33 ዓመታት ከውስጥ ሽኩቻ፣ ሙስና እና ሽብርተኝነት ጋር ስትታገል፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በተደጋጋሚ " የወደቀች / የከሸፈች ሀገር " ስትባል እንደነበር እና ለራሷ ጥበቃ የዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሃይል ያስፈለጋት ሀገር መሆኗን ሶማሌላንድ ገልጻለች።

" ሶማሊያ ብዙ ጊዜ ' ብርቅዬ አፍሪካዊ ተአምር ' እየተባለች በሚነገርላት በሶማሌላንድ ላይ ያልተገባ አረዳድ እንዲኖር ከማድረግና መሠረተ ቢስ የባለቤትነት ጥያቄ ከማቅረብ ይልቅ፣ የራሷን ቤት ብታስተካክል ይመረጣል " ብላለች።

" እርግጥ ነው፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን ከፍተኛ ልዩነት ይገነዘባል " ያለችው ሶማሌላንድ " እኛ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት የምናደርገውን አስተዋጽኦ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደንቀው ነው " ስትል ገልጻለች።

ሶማሌላንድ እንደፈለገችው በነፃነት ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመመሥረት ሉዓላዊ መብቷን ከማስጠበቅ ወደ ኋላ ባትልም፣ ከሶማሊያ ጋር እንደ #ጎረቤት ገንቢ ውይይት ለማድረግና ሰላማዊ በሆነ መንገድ አብሮ ለመኖር ቁርጠኛ ነኝ ብላለች።

ሶማሊያ ፤ እንደ አንድ የራሷ ግዛት በምትቆጥራት ሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈረመውን ስምምነት " ዋጋቢስ " በማለት ውድቅ ያደረገች ሲሆን የኢትዮጵያ ድርጊት ሉዓላዊነቴን ፣ ግዛታዊ አንድነቴ የሚዳፈር ነው ብላለች።

የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድም ስምምነቱን ተከትሎ ወደ ተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጋር በመደወል ውይይት አድርገዋል።

በአሁን ሰዓት ደግሞ በኤርትራ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲም ወደ ግብፅ መጥተው የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
ሚና ፈርኒቸር .. ከዘመኑ ጋር 🤌

ሚና ፈርኒቸር መጪውን በዐል በማስመልከት
KSA4O የሚለውን code ይዞ ለመጣ ደንበኛ ከታህሳስ 20- ጥር 11 የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ከነጻ ትራንስፖርት 🚚እና 4 አመት ዋስትና ጋር ልዪ ቅናሽ አዘጋጅተናል🎄

☎️ 0924245151  /0932325151

Telegram👉 https://t.me/minafurniture

Facebook👉 https://www.facebook.com/Minafurnitur?mibextid=LQQJ4d

TikTok👉 www.tiktok.com/@minafurniture

Instagram👉 https://www.instagram.com/mina.furniture1?igsh=OGQ5ZDc2ODk2ZA==
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይፈለጋል #Wanted " ... ሟች ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ፤ ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው የተባለ ግለሰብ መሆኑን ገልጿል። ግለሰቡ #እጁን_እንዲሰጥም ፖሊስ አሳስቧል። ፖሊስ ተጠርጣረው ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አስተላልፏል።…
#ይፈለጋል #Wanted

ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጠሪው እንደተያዘ በማስመሰል የሚያሰራጩት መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው ሳይያዝ እንደ ተያዘ አድርጎ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ እንዳልሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅም ሆነ ማነኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 15 ሺህ 592 ሰራተኞች ፈተና ወስደዋል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመንግስት ሰራተኞች የብቃይ ምዘና ፈተና በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ፈተናውን 15 ሺህ 592 ሰራተኞች ፈተናቸውን ወስደዋል። ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት…
#Update

የሰራተኞች ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የተሰጠው ፈተና #ውጤት ይፋ ሆኗል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ፈተናን በሚመለከት በዛሬው ዕለት መግለጫ ተሰጥቷል።

በዚህ መግለጫም ፤ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተናው የወሰዱት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ቁጥር 15 ሺህ 151 መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ውስጥ የአመራሩ ቁጥር 4 ሺህ 213 ሲሆን የፈተውን ማለፊያ ውጤት ያመጡት 1 ሺህ 422 ናቸው። ይህም 34 በመቶው አመራሮች አልፈዋል። አመራሩ ለማለፍ ከ60 በመቶ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናውን የወሰዱ የሠራተኞች ቁጥር 10 ሺህ 257 ሲሆኑ ያለፉት 5 ሺህ 95 ናቸው ተብሏል። ይህም 50 በመቶ ነው። ሰራተኞች ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣት አለባቸው።

ለፈተና ከተቀመጡት አጠቃላይ ቁጥር 681 የሚሆኑት በተለያየ የስነ ምግባር ጥሰት ከፈተና ውጪ መሆናቸውን እና 441 የሚሆኑት ደግሞ በፈተና ስፍራ ያልተገኙ መሆናቸው ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከኢፕድ እና ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ልማት ቢሮ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሶማሌላንድ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈፀም መብትን የሚደግፍ እና የሶማሊያን መንግሥት ጣልቃ ገብነትን ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፏል። ሶማሌላንድን የራሴ አካል ናት የምትለውን ሶማሊያ እያቀረበች ያለውን የይገባኛል ጥያቄ #ውድቅ በማድረግም "የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነትና ነጻነቷ የተረጋገጠ ነው " ብሏል። የሶማሊያው…
ሶማሊያ እና ኤርትራ ምን መከሩ ?

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ አቅንተው የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ ጉብኝታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በማብራሪያቸውም ፤ " ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ኤርትራ ለኛ እንደ ቤታችን ናት " ብለዋል።

ወደ ኤርትራ የሄዱት ፦
- ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች ባለችበት በሶማሊያ ሽብርተኝነትን መዋጋት ዙሪያ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ገለጻ ለማድረግ፤
- ከሰሞኑ በቀጠናው እየተስተዋለ ስላለው ተለዋለዋጭ ሁኔታ ላይ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ገለጻ ለማድረግ፤
- በአካባቢው ስለላለው ሁኔታ የሶማሊያን አቋም ለፕሬዜዳንት ኢሳያስ ለማስረዳት ነው ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " ኤርትራ ሁልጊዜም ከሶማሊያ ጎን ናት፤ ለዚህም እናመሰግናለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ኤርትራ የሶማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ስትደግፍ ቆይታለች ይህም የኤርትራ ዓለም አቀፍ አቋም ፤ አሁንም ይህንን አቋም ክቡር ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ደግመውኛል፤ ለዚህም እናመሰግናለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኤርትራ መንግሥት ምን አለ?

የኤርትራ መንግሥት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ባለፉት ሁለት ቀናት በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ እና ጥልቅ ውይይት አድርገዋል ብሏል።

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ መስማማታቸውን እና በቅርቡ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ መግለጫ እንደሚያወጣ አስታውቋል።

NB. የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ኤርትራ በነበሩበት ወቅት የግብፁ መሪ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ አድርገውላቸዋል። የኢትዮጵያ እና የራስ ገዟ ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኃላ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በቅድሚያ ስልክ ደውለው የተነጋገሩ ከአል ሲሲ ጋር እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰራተኞች ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የተሰጠው ፈተና #ውጤት ይፋ ሆኗል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ፈተናን በሚመለከት በዛሬው ዕለት መግለጫ ተሰጥቷል። በዚህ መግለጫም ፤ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተናው የወሰዱት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣…
#AddisAbaba #Exam

ለአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች ፣ ባለሞያዎች / ሠራተኞች የተሰጠውን የቴክኒክ እና ባህሪ ብቃት ፈተና የማለፊያ ነጥብ አምጥተው ያለፉ #የክዋኔ_ክህሎት ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ሳይችሉ ቀርተው #ያላለፉት ደግሞ #የአቅም_ግንባታ_ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪ የማለፊያ ውጤት ያላመጡት ዝቅ ብለው እንደሚመደቡ ፤ አሁን ላይ #ስንብት የሚባል ነገር እንደሌለ ፤ ስንብት የሚፈፀመው መጨርሻ ላይ ሁሉ ነገር ከተጠናቀቀና ሌላ አማራጭ ከጠፋ ብቻ መሆኑ ተነግሯል።

የፈተናው ውጤት፦

👉 የቴክኒክና የባህሪ ብቃት ምዘና ፈተናውን የወሰዱ አመራሮች፣ ባለሙያዎች / ሠራተኞች አጠቃላይ ቁጥር 15 ሺህ 151

ፈተናውን የወሰዱት አመራሮች ቁጥር 4 ሺህ 213 ፤ የፈተውን ማለፊያ ውጤት ያመጡት 1 ሺህ 422 ፤ ፈተናውን ያላለፉ አመራሮች 2,791 ፤ በአጠቃላይ ፈተናውን ያለፉት 34 በመቶ አመራሮች ብቻ ናቸው።

NB. አመራሮች ለማለፍ ከ60 በመቶ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸው ነበር።

ፈተና የወሰዱ የሠራተኞች ቁጥር 10 ሺህ 257 ፤ ፈተናውን ያለፉት 5 ሺህ 95 ናቸው። 5,162 ሠራተኞች አላለፉም። ያለፉት 50 በመቶ የሚሆኑት ናቸው።

NB. ሰራተኞች ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸው ነበር።

#AAU #KotebeUniversityofEducation

@tikvahethiopia
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://t.me/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#SafaricomEthiopia

አሪፍ እና ሰፋ ያለ ስክሪን ያለዉን Samsung A34 አቅራቢያችን ካሉ የሳፋሪኮም ሱቆች እንግዛ::

#SafaricomEthiopia #Furtheraheadtogether
EU_Cotonou and Samoa Agreement_merged.pdf
1.8 MB
#CotonouAgreement (እ.ኤ.አ 2000 የተፈረመ)

#SamoaAgreement (እ.ኤ.አ 2023 የተፈረመና የኮቶኑ ስምምነት ተከታይ)

PDF ፋይሉን በመክፈት ሁለቱንም ስምምነት ማንበብ ይችላሉ። የሚፈልጉትን ቃላትም 🔍 Search የሚለውን በመጫን በመፃፍ መፈለግ ይችላሉ።

ከእስከ 179 ገፅ ያለው የ #CotonouAgreement ሲሆን ከዛ በታች ያለው አዲሱ ስምምነት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
EU_Cotonou and Samoa Agreement_merged.pdf
#SamoaAgreement

ከወር በፊት ሀገራችን #ኢትዮጵያን ጨምሮ አጠቃላይ 79 የአፍሪካ እና የካረቢያንና ፓስፊክ ሀገራት / 48 ከአፍሪካ፣ 16 ከካረቢያን፣ 15 ከፓስፊክ / ሳሞአ ላይ አንድ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የተፈረመው ስምምነት " #የአፍሪካ#የካረቢያን እና #የፓስፊክ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጋር የሚያደርጉት የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር " የሚል ነው።

ስምምነቱ 22 ዓመታትን የዘለቀው " የኮቶኑ ስምምነት " ቀጣይ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህ ስምምነት ግን ብዙ ጥያቄ ተነስቶበታል። 

በቅድሚያ ስምምነቱ ላይ ጥያቄ እና ከፍተኛ ጥርጣሬ የተነሳው #ካረቢያን አካባቢ ነው። 

ስምምነቱ ፤ በካሪቢያን አካባቢ ከባህል እና ከእሴቶች ጋር የማይጣጣሙ ህጎችን በካሪቢያን ህዝብ ላይ ይጭናል በሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው በቅድሚያ የገለፁት ፦
- በትሪንዳድ እና ቶቤጎ የሚገኘው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን 
- የጃማይካ ጥምረት ለጤናማ ማህበረሰብ (JCHS) ናቸው።

በትሪኒዳድ የሚኖሩ አንድ #የሃይማኖት_አባት በሀገር ውስጥ በሚገኝ መገናኛ ብዙሃን ላይ ቃለ ምልልስ ካደረጉ በኃላ ነው ስምምነቱ ላይ #ህዝባዊ_ትችት የመጣው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባት የስምምነት ሰነዱ ' የአውሮፓ ህብረት ' " የእኛ ያልሆነን ርዕዮተ ዓለም " በአስገዳጅነት እንዲጭን የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የጃማይካ ጥምረት ለጤናማ ማህበረሰብ (JCHS) ደግሞ " ተቀባይነት የሌለውን / ውድቅ የተደረገውን አጠቃላይ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ትምህርተ ሥርዓተ ወደ ጃማይካ የመማሪያ ክፍሎች እንደሚመልስ እና የጃማይካውያንን መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ይጎዳል ፤ ከሀገሪቱ ባህልም ያፈነገጠ ነው " በሚል ጠንካራ ተቃውሞ አስምቷል።

እንዚህ አካላት፤ " በማዕቀብ ሰበብ እና ውል በማሰር " ህዝብ የማይቀበለውን #ከባህል_ያፈነገጠ ተግባር ያለማምዳል ፤ ይጭናል በሚለው ነው የተቃወሙት።

በ ' ሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲንስ ' ከዚህ ከባለ 400 ገፆች የሳሞአ ስምምነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስጋት ተሰቅስቅሶ ነበር። እሱም ስምምነቱ ፦
- ሀገሪቱ በፅንስ ማቋረጥ ፣
- በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ 
- በLGBTQ መብቶች ላይ ሀገሪቱ ህጎቿን ለማሻሻል #ትገደዳለች የሚል ነው።

ይህ ጉዳይ እና ስጋት በካረቢያን አካባቢ ከተነሳ በኃላ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ መናጋገሪያ ሆኖ ወደ አንዳንድ #የአፍሪካ_ሀገራት ተሰራጭቷል።

በተለይ ደግሞ በናይጄሪያ፣ በናሚቢያ፣  በታንዛኒያ ... የመሳሰሉ ሀገራት ውስጥ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስምምነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲገልጹ ነበር።

ምንም እንኳን በርካታ ሀገራት ስምምነቱን #በሰዓቱ ቢፈርሙም አንዳንድ ሀገራት ግን ሰነዱ ላይ ዘግይተው ነው የፈረሙት።

ለአብነት ሰነዱን ዘግይተው ከፈረሙት ውስጥ በሰነዱ ላይ በቅድሚያ ከዜጎቿ ጥያቄ የተነሳባት #ጃማይካ አንዷ እና ዋነኛዋ ስትሆን እነ ፦
* ቦትስዋና፣
* ናሚቢያ፣
* ሰኔጋል፣
* ታንዛኒያ፣
* ሶማሊያ፣
* ሩዋንዳ ዘግይተው ከፈረሙት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

➡️ ጥያቄ እና ስጋት በተነሳባቸው ሀገራት ምን ምላሽ ተሰጠ ?

➡️ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ጉዳዩ ምን ተባለ ?

➡️ ስምምነቱን በተመለከተ ፤ " ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግብረሰዶም እንታደግ ማህበር " ምን አለ ?

➡️ በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያን መስፋፋት ምን ያህል አስከፊና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ አጠቃላይ ያለውን ሁኔታ ዳሷል ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-10

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ‘ልጆቼን ልያቸው’ ብሎ ማታ ሲመጣ ከሁለት አቅጣጫ ተተኮሰበት ሞተ። " - የመተሃራ ነዋሪ ከታህሳስ 19/2016 ዓ/ም ወዲህ ባሉት ቀናት ብቻ በተለያዩ ቦታዎች ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን፣ ከአሥር በላይ ተጓዦች መታገታቸውን፣ እንዲሁም ስምንት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን የዓይን እማኞችና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አንድ…
#Update

" እግዚአብሔር አምላክ አትሙቺ ያላት ነብስ ሆናነው እንጂ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበርን " - ከእገታ የተለቀቁ ግለሰብ

ታህሳስ 19 ለቁልቢ ንግስ በዓል ወደ ቁልቢ ደርሰው ሲመለሱ በታጣቂዎች የታገቱ 11 ሰዎች መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም አንድ የተለቀቀ ታጋችን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

አንድ ከእገታው ነፃ የሆነ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ ግለሰብ ፤ ወደ ቁልቢ ሲሄዱና ሲመለሱ ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልጿል።

ታህሳስ 17 ወደ ቁልቢ ሲሄዱ ከወለንጪቲ ወጣ ባለ ቦታ ዘረፋ የተፈፀመባቸው ሲሆን ሲመለሱ ታህሳስ 19 በታጣቂዎች ጥቃት ተከፍቶባቸዋል።

አስተያየት ሰጪው ፤ " ዋናውን የአዋሽ ፓርክ በር አልፈን ያልታወቁ ታጣቂዎች ተኩስ ከፈቱና የነበርነው 19 ሰዎች ነበር ከ19ኙ 5 ሰዎች ህይወቱ አልፎ እዛው አስክሬናቸው ከመኪናው ጋራ ተቃጠለ። እኛ በህይወት ያለነውን 11 ሰዎች ውረዱ ... ውረዱ ብለው አስወርደውን በማናቃቸው ኃይሎች ታግተን በጣም እሩቅ የሚባል 10 ሰዓት የሚፈጅ እግረ መንገድ ወደማናቅበት ተራራማ አካባቢ ከተቱን " ብለዋል።

አጋቾቹ እገታውን ከፈፀሙ በኃላ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ የጠየቁ ቢሆንም ታጋቾች ግን አቅም እንደሌላቸው ነግረዋቸዋል። በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙ ተመላክቷል።

ታጣቂዎቹ ሲጠይቁ የነበረው ገንዘብ ከ100 ሺህ ብር አንስቶ እስከ 250 ሺህ ብር የሚደርስ መሆኑን የገለፁት ከእገታ ነፃ የሆኑት ግለሰብ " እኛ ይህን ገንዘብ ማግኘት አንችልም አቅማችን አይፈቅድም አልናቸው በጨረሻ ተስፋ ሲቆርጡ ገርፈው ለቀቁን " ብለዋል።

" ምሽት 4 ሰዓት ነው የተነሳነው ነግቶ ነው ከወልጪቲ ወጣ ብለን ቤተሰብ ጋር ደውለን በኮንትራት መኪና ወደቤት የሄድነው " ሲሉ አክለዋል።

ታጣቂዎቹ ሲለቋቸው ስለነበረው ሁኔታ ለማንም እንዳይናገሩ እንዳስጠነቀቋቸው የገለፁት እኚሁ ስሜ አይገለፅ ያሉ ግለሰብ  በወቅቱ በጥይት እጇን የተመታች ባለቤቱን ጨምሮ 3 ሴቶች ሳይታገቱ መቅረታቸውን አመልክተዋል።

" እግዚአብሔር አምላክ አትሙቺ ያላት ነብስ ሆናነው እንጂ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበርን። የሚለበስ ነገር የለ፣ የነበርነው በቲሸርት ነው ብርዱ ውርጩ ዝናቡ ከነድብደባው ከፍተኛ ስቃይ ነበር። ከእኛ መሃል አንድ ልጅ ግንድ ላይ አስረው የደበደቡት እጅግ በጣም ተጎድቷል፤ ከአንገቱ እስከ እግሩ ቁስል ብቻ ነው። እሱን ሆስፒታል እንዲሄድ አድርገናል። " ሁኔታውን ገልጸዋል።

አጋቾቹ እነማን ናቸው ? በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ " ከ20 በላይ ፤ 25 ወይም 30 ይጠጋሉ። የተወሰኑት ፀጉር አላቸው ፤ የወታደር ልብስ የበከተ አይነት ሬጀር ያደረጉ ነበሩ፤ ግማሾቹ ጭንብል አላቸው። ያስፈራል በጣም። ስለማንነታቸው አይነግሩንም ነበር። ወስደው ሁለት ተራራ መሃከል ባለ ዋሻ ውስጥ አስገቡን ለሽንት ብቻ ነበር የሚወጣው ፤ ግማሹ ኦሮሚኛ፣ ግማሹ አፋርኛ በቃ ድብልቅልቅ ያለ ቋንቋ ነው የሚሰማው ይሄ ነው የሚባል አይደለም። ድብልቅልቅ ያለ ነው። የሚጠራሩትም በኮድ ስም ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ታግተው ከተለቀቁት መካከል የአንዱ ቤተሰብ የሆኑ አባት ሁሉም ታግተው የተለቀቁ የአካል እና ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ ከተማ የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አለ ?

ትላንት እንዲሁም ዛሬ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ብዙ ተከታይ ያላቸው ገፆች እና ግለሰቦች ፤ " በአዲስ አበባ የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳለ፣ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተደረገ እንደሆነ፣ 4 ኪሎ አካባቢ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ የሚገልፁ መረጃዎች " እያዘዋወሩ ይገኛሉ።

መሰል መረጃዎችን እያሰራጩ የሚገኙት ገፆች እና ግለሰቦች ሶማሊያን እንደግፋለን በሚል የሚንቀሳቀሱ የሶማሊያ አክቲቪስቶች ሲሆኑ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ዜጎችም ሲያጋሯቸው መመልከት ተችሏል።

አንዳንድ የግብፅ ገፆችም እና ግለሰቦችም ተመሳሳይ መልዕክቶችን ሲያሰራጩ የነበረ ሲሆን የእነሱንም መልዕክቶች አንዳንድ የኢትዮጵውያን ዜጎች ሲያጋሯቸው ነበር።

እነዚህ አካላት እያሰራጩ ስላሉት ጉዳይ ምልከታ ያደረግን ሲሆን የተባለው አይነት ነገር አዲስ አበባ ውስጥ ፈፅሞ እንደሌለ ለማረጋገጥ ችለናል።

ዛሬ 4 ኪሎን ጨምሮ መላው አዲስ አበባ ላይ በመዟዟር ምልከታ አድርገናል። ምንም አይነት ያልተለመደ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም ፣ ተኩስ የሚባልም ነገር የለም።

አዲስ አበባ በተመለከተ እየወጡ ያሉት መረጃዎች በጠቅላላ ሀሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጠናል።

መሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ያሉት ሆን ተብለው ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ለመጣል እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

በተለይ ኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኃላ ሶማሊያን በመደገፍ የተለያዩ ብዙ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች እና ገፆች ኢትዮጵያን በተመለከተ የተፈበረኩ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሆነ ለማታዘብ ተችሏል።

ከዚህ ባለፈ በሶማሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እንዲደርስ የሚቀሰቅሱ ፅሁፎችን ሲያጋሩ ታይተዋል።

እነዚህ የውጭ ሀገር ሰዎችና በርካታ ተከታይ ያላቸው ገፆች የሚያሰራጯቸውን መልዕክቶች የሚያጋሩ የሀገራችን ሰዎችም ስለመኖራቸው መረዳት ተችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቅኝት

" ኢትዮጵያውያን ከሶሚሊያ ይውጡልን " እስከ " ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት ይነጠቅ " ዘመቻ !

ከሰሞኑን #የሶማሊያ እና #የግብፅ አክቲቪስቶች እንዲሁም " ሶማሊያን ነው የምንደግፈው " የሚሉ የኢትዮጵያ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ዘመቻ ከፍተዋል።

ጉዳዩ ኢትዮጵያ የባህር በር ለመጠቀም እድል ይሰጣታል ከተባለውና ከሶማሌላንድ ጋር ካደረገችው የመግባቢያ ስምምነት በኃላ የመጣ ነው።

ከስምምነቱ ማግስት ጀምሮ የሶማሊያ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ መግለጫ የማውጣት፣ አጉል ዛቻ የማድረግ ፣ ኢትዮጵያውያን እንደ * ወራሪ * እንዲታዩ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር።

የሀገሪቱ ብሄራዊ የመንግሥት የዜና አውታሮች እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣  አክቲቪስቶች እንዲሁም የግብፅ ሰዎች #የተናበበ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ ይከትልናል ያሉትን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ።

ቀላል የማይባል የተከታይ ቁጥር ያላቸው ገፆች #ነጭ_ውሸት ከማሰራጨት ባለፈ ኢትዮጵያውን እንዲጠቁ የማድረግ ዘመቻ እያደረጉ ነው።

ለአብነት ፤ " አዲስ አበባ ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት እየተደረገ ነው ፣ መዲናዋ በተኩስ እየተናጠች ነው ፣ የሀገሪቱ መንግሥት  ለሁለት ተከፋፍሏል ፣ እርስ በእርሱ እየተዋጋ ነው፣ ኢትዮጵያ በሁሉም መልኩ ተዳክማለች " የሚሉ ነጭ ውሸቶችና እና ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ስራዎች እየሰሩ ይገኛሉ።

እንዲሁም " ኢትዮጵያውያን ሶማሊያ ውስጥ ምን ይሰራሉ ? ፣ ጠራርገን እናስወጣቸው፣ ወደ ሀገራቸው እንሸኛቸው ፣ ወራሪ ናቸው " የሚሉ ለጥቃት የማመቻቸትና የጥላቻ ቅስቀሳዎችን ከዚህ አለፍ ሲልም የግድያ ዛቻዎችን እስከማስተላለፍ ደርሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንድትፈጥር ላደረጉት ስራ የተሰጣቸው ዓለም አቀፉ " የኖቤል የሰላም ሽልማት " እንዲነጠቁ የሶማሊያ ሰዎች ዘመቻ ማድረግ ጀምረዋል።

ዘመቻው በብሄራዊ የሶማሊያ ቴሌቪዥን ጣቢያ እና ብሄራዊ ዜና አገልግሎት ጭምር ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት ሰዎች እንዲፈርሙት እየተደረገ ይገኛል።

ይህንን ዘመቻም የግብፅ አክቲቪስቶችም አብረው እያሟሟቁት ይገኛሉ።

NB. የኖቤል የሰላም ሽልማት አንዴ ከተሰጠ እንደማይሻር / እንደማይነጠቅ ይታወቃል፤ በስቶክሆልምና በኦስሎ ያሉት የሽልማት ሰጪ ኮሚቴዎች አንድም ጊዜ ሽልማትን ለመሻር/ ለመንጠቅ አስበው አያውቁም።

በአጠቃላይ የሶማሊያ ሰዎች " የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኖቤል ሽልማት ይነጠቅ " ከማለት አንስቶ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እንዲከፈት ፣ በአዲስ አበባ እና ክልል ያለው ህዝብ እንዲሸበር በማህበራዊ ሚዲያ እየሰሩ ያሉትን ዘመቻ የግብፅ ሰዎችም ሲደግፏቸው ታይቷል።

በዚህ የሶማሊያ እና የግብፅ ሰዎች የጋራ የሚመስል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ #የሀገራችን_ዜጎችም ሲሳተፉ መመልከት ተችሏል።

በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ፤ ኢትዮጵያ ማንንም ባልወረረችበት ፣ የሰው ሀገር ባላጠቃችበትና ፍትሃዊ ጥያቄ በመጠየቋ ብቻ የሀገራችን ዜጎች ሆነው ከሶማሊያ እና ግብፅ ጋር በማበር የሚያደርጉት ድርጊት እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

" የኖቤል ሽልማት ማሻር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣን ማስወረድ ፣ የሀገሪቱን መንግሥት መቀየር ይህ ሁሉ #ኢትዮጵያውያንን ብቻ የሚመለክት ነው " ያሉ ሲሆን " በሀገር ውስጥ የቱንም ያህል ተቃውሞ፣ ቅሬታ ቢኖረን እንዴት ከሌላ ሀገር ሰዎች ጋር ለዛውም ለኢትዮጵያ መልካም ከማያስቡ ሰዎች ጋር እናብራለን ? ይህ ተገቢ አይደለም መታረም አለበት ፤ ማንኛውም የውስጥ ጉዳዮች በውሥጥ ማለቅ አለባቸው " ብለዋል።

#ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia