TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ • " ከ13,000 በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው " - የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት • " በሰሃላ ወረዳ 94 በመቶ ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች፣ 45 በመቶ ከአምስት ዓመት በታች ሕጻናት በምግብ እጥረት ተጎድተዋል " - የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በአበርገሌና…
#አማራ #ዋግኽምራ

" ዞኑ ከነበሩት 33 አምቡላንሶች አሁን ላይ 9 አምቡላንሶች ብቻ ነው ያሉት። … የህፃናትና የእናቶች የህክምና አገልግሎት አደጋ ውስጥ ነው " - የዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ

ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ፦
* የመድኃኒት፣
* የትራንስፖርት፣
* የሕክምና መሣሪያዎች እጥረት በማጋጠሙ በዞኑ የሚገኙ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ፈተና እንደሆነባቸው በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ ምን አሉ ?

- ዞኑ ከነበሩት 33 አምቡላንሶች አሁን ላይ ዘጠኝ አምቡላንሶች ብቻ ነው ያሉት። በሰርቪስ፣ በሥራ ጫና ከጥቅም ውጪ ሆነዋል። 

- በተፈለገና ባለቀ ሰዓት ወቅቱን ጠብቆ መድኃኒት ለመግዛት እንቅስቃሴዎች ገድበውናል። የሴኩሪቲ ችግር በጣም አሳሳቢ ነው። ሪፈራሎች በሚፈለገው መልኩ እየተንቀሳቀሱ አይደለም። ስለዚህ በእናቶችና በህፃናት የጤና አገልግሎት ጠቅላላ አደጋ ውስጥ ነው። 

- ሰውከፍሎ መታከም አልቻለም። የጤና መድህን ሽፋናችን ዝቅተኛ ነው። ራሳቸውን ሰርቫይብ ማድረግ ያልቻሉ፣ ለመከላከያ፣ ለልዩ ኃይል ለሌሎች ቁስለኞች ሁሉ ጠቅላላ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የጤና ተቋማት ናቸው ያሉት። እየጠፉ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ግን ደግሞ በትግል እንደምንም እየተቋቋምን ማኅበረሰቡን ለማዳረስ እየሞከርን ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጸጥታው ችግር በድርቅ ለተጎዱት ምን ጉዳት አስከተለ ? ሲል ጠይቋል።

° ይህ ሁኔታ በተለይ በዞኑ በድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች እያሳደረው ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው።

* ኮሌራ ተከስቶብናል። እንደ ጤና ተቋማት ትልቅ ሥጋት፣ ከባድ ወረርሽኝ ላይ ነው ያለነው። ቁጥር አንድ ተጋላጭ የሚባሉት ህፃናት፣ ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች ናቸው። 

° ከኅዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የልየታ ሥራ በሁሉም ወረዳዎች አሰርተን ነበር። በዚያ መሠረት አስደንጋጭ ቁጥር ነው ያገኘነው። ከለየናቸው ነፍሰጡር፣ አጥቢ እናቶች 81 በመቶ የሚሆኑት አጣዳፊ መካከለኛ የምግብ እጥረት ያለባቸው ናቸው።

° እንደ ዞን ከለየናቸው ህፃናት 45 በመቶዎቹ አጣዳፊ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር ያለባቸው ናቸው። ይህ ቁጥር ከተቀመጠው ስታንዳርድ በላይና አስደንጋጭ ነው። አስደንጋጭ ከመሆኑም በላይ አሁን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች በጣም ዘገምተኛ ናቸው ብለዋል።

የዋግኽምራ ብሄረሰብ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፦
☑️ 95 በመቶ እናቶች በምግብ እንደተጎዱ፣
☑️ የህፃናት የረሃብ መጠን 15 በመቶ ከደረሰ እንኳ ከስታንዳርድ በላይ እንደሆነ ነገር ግን ከ30 በመቶ በላይ ህፃናት በምግብ እጥረት እንደተጎዱ ገልጾ ነበር።

አሁን የጤና መምሪያ ኃላፊው በገለጹት መሠረት ደግሞ የህፃናቱ የምግብ እጥረት ጉዳት ወደ 45 በመቶ ከፍ ብሏል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ፤ በተለይ የጸጥታው ችግር ከድርቁ ጋር ተያይዞ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ፈተና መሆኑን፣ ድርቅ፣ ጦርነት፣ ወረርሽኝ በዞኑ መደራረባቸውን ገልጾ እስካሁን ድጋፍ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው፣ አሁንም መንግሥት፣ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ከችግሩ ውስብስብነት አንፃር ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተረድተው #እርዳታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናክሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #Eurobond ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ በወቅቱ ያልከፈለችው ለምንድነው ? ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም። የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ የቀረበው ከ9 ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም ነበር። ኢትዮጵያ ይህንን ቦንድ ሸጣ ከገዢዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘች ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው…
#Update

ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ወለድን በቀነ ገደቡ መክፈል ባለመቻሏ ዕዳቸውን መክፈል ካልቻሉ አገራት ተርታ እንደተመደበች ሮይተርስ የዜና ወኪል አስነብቧል።

ኢትዮጵያ ትናንት ሰኞ ታኅሳስ 15/ 2016 ዓ.ም. መክፈል የነበረባትን የ33 ሚሊዮን ዶላር ባለመክፈሏ ዕዳዋን መክፈል ያልቻለች ሶስተኛዋ የአፍሪካ አገር መሆና መመዝገቧ ተገልጿል።

ከ10 ዓመት በፊት በታኅሣሥ 2007 ዓ.ም. የ1 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ሽያጭ አድርጋ ላገኘችው ብድር የወለድ መክፈያ ጊዜያው ከሁለት ሳምንት በፊት ታኅሣሥ 1/2016 ዓ.ም. ነበር።

ከመክፈያ ጊዜው ቀነ ገደብ በኋላ የነበረው የ14 ቀናት የእፎይታ ጊዜም እንዲሁ ተጠናቀቋል።

ከዚህ ቀደም መንግስት ወለዱን እንደማይከፍል ማስታወቁ ይታወሳል።

የገንዘብ ሚኒስቴር የማሻሻያ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ሂንዣት ሻሚልም ፤ ክፍያው አለመፈጸሙን እና የሚከፈል አለመሆኑንም ማረጋገጣቸውን ብሉምበርግ ዛሬ ማለዳ ዘግቧል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ ዕዳቸውን መክፈል የማይችሉ (Sovereign default ውስጥ ከገቡት) ሁለት የአፍሪካ አገራት ጎራ ተሰልፋለች። ዕዳቸውን መክፈል የማይችሉ የተባሉት ሁለት የአፍሪካ አገራት #ጋና እና #ዛምቢያ ናቸው።

ገንዘብ ሚኒስቴር ከጥቂት ቀናት በፊት በዚህ ጉዳይ በሰጠው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ዕዳዋን የማትከፍለው፤ የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ እጥረት ሳለልባት ሳይሆን ሁሉንም አበዳሪዎች " በእኩል ለማስተናገድ " በሚል መሆኑን ተናግሯል።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋም ከቀናት በፊት ከፋና ቴሌቭዢን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ይህንን የክፍያ ጉዳይ አንስተው ነበር።

ዶ/ር ፍፁም ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ ወለድንያልከፈለችው የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ችግር ስላለባት አይደለም።

- በዓመት በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች ከውጭ ለምናስገባው ዕቃ የምንከፍል ሀገር ነን ስለዚህ 30 ሚሊዮን ዶላር [ገደማ] ገንዘብ ተቸግረን አይደለም ያልከፈልነው ኢትዮጵያ እንዲያውም ብድሯን በጣም በመክፈል የምትታወቅ አገር ናት በችግር ውስጥም ቢሆን።

- ወለዱ ያልተከፈለው ሁሉም አበዳሪ እና ተበዳሪ ተመሳሳይ አይነት አያያዝ ነው ሊያዝ የሚገባው በሚል ምክንያት ነው።

መረጃውን ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ሮይተርስ እና ብሉምበርግን ዋቢ በማድረግ ነው ያስነበበው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #ቁልቢ #ሀዋሳ

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓልን ተከትሎ ፤ ከታህሳስ 17 እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት ባሉት ቀናት ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል ነው ተብሏል።

ታህሳስ 19 የሚከበረው ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ጊዚያዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል አሳውቀዋል።

ለበዓሉ የሚያቀኑ አሽከርካሪዎች አካባቢው ዳገት፣ ቁልቁለት እና ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚበዛው ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የትራፊክ ህግና ደንብ አክብረው እንዲያሽከረክሩ ማሳሰቢያ ተለልፏል።

ከታህሳስ 17 እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት ባሉት ቀናት ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪ ፦

- የጸጥታ አካላት ቋሚና ተንቀሳቃሽ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ።

- በበዓሉ ወቅት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ሲያዙ ፈጣን ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል ጊዜያዊ ፍርድ ቤት በአቅራቢያ ተቋቁሟል።

- ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ተቋቁሟል።

የበዓሉ ታዳሚዎች ንብረቶቻቸውን #በጥንቃቄ እንዲይዙ መልዕክት ተላልፏል። ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳይ ካጋጠመ በአቅራቢያ ላለ የፀጥታ አካል ጥቆማ መስጠት ይቻላል።

በተመሳሳይ ፤ በሀዋሳ ለሚከበረው የቅዱስ ገብርዔል ዓመታዊ የንግስ በዓልን አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ብሎም ደህንነታቸው ተጠብቆ በከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ሁሉም አካል በትብብር እየሰራ ነው ተብሏል።

ስርቆት፣ ያለአግባብ ዋጋ ጭማሪ ፣ ማጭበርበር እንዳይፈፀም የጥንቃቄ ስራ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በዓሉ በሚከበርበት ዕለትና ሥፍራ ወንጀል ተፈፅሞ ቢገኝ አፋጣኝ ፍትህ የሚሰጥ ጊዜያዊ ችሎት መሰየሙ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መምህራን #ትግራይ " ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " ሲሉ የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን  በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። መምህራኑ " መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን " ያሉዋቸው እንዲመለሱላቸው ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።  መነሻቸው ሽረ ስታድዮም በማድረግ በከተማዋ…
#ትግራይ #መቐለ #መምህራን

" ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበል የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው " - መምህራን

በመቐለ ከተማ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ፤ " 17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም " ብለው የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።

ተማሪ ሄመን ሰለሙን በመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የሓየሎም መለስተኛ ትምህርት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፤ ታህሳስ 13 /2016 ዓ.ም በትምህርት ቤትዋ የወላጆች በዓል ከተከበረ በኃላ ከትምህርት መአድ መስተጓጎሏን ተናግራለች።

ምክንያቱ ደግሞ የትምህርት ቤትዋ መምህራን " 17 ወራት ዉዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም " ብለው የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ነው።

የተማሪ ሄመን ሰለሙን አስተያየት በመቐለ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ በ10 ሺዎች  የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይጋሩታል።

ተማሪዎቹ ትምህርት ካቆሙ ቀናት ተቆጠረዋል።

እንደ ተማሪ ሄመን የመሰሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ፤ በከተማው በግል ትምህርት ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ጠዋት ተንስተው ወደ እውቀት ገበያ ሲያመሩ በማየት አዝነው ሲበሳጩ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ታዝቧል።

የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ መምህራም ፤ " ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበሉ የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው " ብለዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለመቐለ ኤፍ ኤም ቃሉን የሰጠው የመቐለ ከተማ አስተዳደር ፤ " መምህራኑ ጥያቄያቸው ሳይሆን ፤ ለጥያቄያቸው መፍትሄ ብለው የወሰዱት እርምጃ ጎጂ ነው " ብሎታል።

የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው ፤ " መምህራኑ ጥያቄ ማንሳታቸው እንደ ችግር የሚቆጥር ባይሆንም ፤ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ተማሪዎች በመቅጣት ጥያቄያቸው ለመፍታት መፈለጋቸው ግን የከፋ የስህተት መንገድ ነው " ብለዋል።

ምሁራን ፤ " መምህራኑ ስለ ደመወዛቸው መጠይቅ ብቻ ሳይሆን የህፃናት ተማሪ ልጆቻቸው ቀጣይ አድልም ከግምት ማስገባት ነበረባቸው " ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

በመቐለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምህሩ መምህራን ስለወሰዱት ስራ የማቆም እርምጃ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጫ አሰጣለሁ ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ተከታትሎ ያቀርባል። 

ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም ፤ " ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " በማለት  የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን  በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃቸው መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው ከመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ እና ከመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
                                   
@tikvahethiopia            
🎁እጥፍ ድርብ የበዓል ስጦታ!🎁

መጪውን አዲስ ዓመት (2024) አስመልክቶ ባህርማዶ ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶችዎ ከ 99 ብር ጀምሮ የሞባይል አየር ሰዓት ወይም ጥቅል በአጋሮቻችን በኩል ሲላክልዎ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ200% ስጦታ ይበረከትልዎታል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ #መቐለ #መምህራን " ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበል የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው " - መምህራን በመቐለ ከተማ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ፤ " 17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም " ብለው የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ተማሪ ሄመን ሰለሙን በመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የሓየሎም መለስተኛ ትምህርት የ8ኛ ክፍል…
#Update 

ባጋጠመው የበጀት እጥረት ውዙፍ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መክፈል አለመቻሉን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታውቋል።

ከፌደራል መንግስት ያልተላከ በጀት ጨምሮ የ300 ሚሊዮን ብር የበጀት ጉድለት አለበኝ ብሏል የጊዚያዊ አስተዳደሩ በፋይናንስና ሃፍት አሰባሰብ አስተዳደር ቢሮ በኩል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ። 

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ምሕረት በየነ እንዳሉት ፤ የተላከው በጀት ከ4 ዓመት በፊት እንደሆነ በማስታወስ ከደመወዝ እድገትና ሌሎች ጋር ተያይዞ የመጣው ለውጥ የፈጠረው የበጀት እጥረት ውዙፍ ደመወዝ ለመክፈል አዳጋች አድርጎታል ፤ የበጀት ክፍተቱ ለመሙላት ከፌደራል መንግስት ብድር ተጠይቆ መልስ እየተጠበቀ ነው ብለዋል። 

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ፤ ከውዙፍ ደመወዝ መከፈል ጋር ተያይዞ የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ በተለይ የመቐለ የመንግስት ትምህርት ቤቶች መምህራን ሁኔታውን በመረዳት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። 

መምህራኑ የሚያቀርቡት የውዙፍ ደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለፌደራል መንግስት ተደጋጋሚ ጥያቄ በማቅረብ ላይ ነው ያሉት የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ መምህራኑ የጊዚያዊ መንግስቱ ጥረት በመገንዘብ ወደ ትምህርት መአድ እንዲመለሱ መጠየቃቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                 
@tikvahethiopia            
#አማራ

" ከ2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ ናቸው "

በጸጥታ ችግር ከ2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ በታጣቂዎች መካከል በክልልሉ በሚስተዋለው የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ ምን ያህል ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን፣ ከ2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ገልጸውልናል።

አቶ ጌታቸው ቢያዝን ምን አሉ ?

- በክልሉ የሚስተዋለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር የተማሪዎች የምዝገባ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳሳደረ ነው።

- እንደ ክልል 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግበን ማስተማር ነበረብን ፤ አሁን ላይ ግን እነዚያን ተማሪዎች መዝግበን በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት ማምጣት አልቻልንም።

- አሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ያልተመዘገቡ አሉ። ይሄ ተሳትፎን በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል። ተሳትፎን ይጎዳል ማለት መማር የሚገባቸውን ተማሪዎች የትምህርት ዕድል እንዳያገኙ እያደረግን ነው ማለት ነው። በሕይወታቸው ጭምር እየፈረድን ነው ማለት ነው።

- ከተሳትፎው ባሻገር የትምህርት ጥራቱ ላይም ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው፤ ጉዳቱ በአጠቃላይ አስከፊ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጸጥታው ችግር ሳቢያ ምን ያህል መምህራን ከመማር ማስተማር ሥራቸው ውጪ ሆኑ ? ሲልም ጠይቋል።

አቶ ጌታቸው ፦ " በ2,000 አካባቢ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መምህራን ከሥራ ውጪ እንደሆኑ ተናግረዋል። ነገር ግን መምህራኑ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

የጸጥታ ችግር በትምህርት ተቋማት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በተመለከተም ማብራሪያ ጠይቀናቸዋል።

አቶ ጌታቸው ፦ " በግጭት ወደ 42 ትምህርት ቤቶች የወደሙ አሉ። ጉዳቱ ከፍተኛ ነው። አሁን ከዚህ ለመውጣት ርብርብ እያደረግን ነው። " ሲሉ መልሰዋል።

በክልሉ የመማር ማስተማር አገልግሎት ሳይሸራረፍ እየተሰጠባቸው ያሉና በጸጥታው ምክንያት አገልግሎቱን የማይስጡ ምን ያህል የትምህርት ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄም ፦

" በእኛ ክልል ወደ 10,000 አካባቢ ትምህርት ቤቶች አሉ። ከ10,000 አካባቢ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ወደ 2,000 አካባቢ የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች በአንድም ይሁን በሌላ በጸጥታው ችግር አፌክት ሆነዋል። ወደ መደበኛ ሥራ ለመመለስ ነው እየሰራን ያለነው። " ሲሉ መልሰዋል።

በክልሉ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳቶች በዘርፉ ከማስከተሉ ባሻገር በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ውድመት ከደረሰባቸው 400 በላይ ትምህርት መካከል ሙሉ ለሙሉ ወደሙ የተባሉ የ1,000 ትምህርት ቤቶችን ግንባታ ለማከናወን እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ወቅት አሁናዊው ጦርነት መከሰቱ ሌላ ችግር እንደሆነባቸው፣ ሆኖም ግን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በየ ወረዳዎችና ዞኖች ውይይት እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

በአማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚደረጉ የተኩስ ልውውጦች በንጹሐን ላይ ሞትና ጾታዊ ጥቃቶች መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከዚህ በፊት መግለጹና የተኩስ ልውውጡ እንዲቆም ማሳሰቡ አይዘነጋም።

ዘገባውን ያዘጋጀው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#EHRC

" በወልቂጤ ከተማ ጥቅምት 02 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተከሰተው ሁከት እና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ለተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ እና ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል " - የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)

ከኢሰመኮ የተላከ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
" ' አክሲዮን እናሻሽጣለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችና ግለሰቦች ህገወጥ ናቸው " - የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፤ " የአክሲዮን ድርሻ እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆኑ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ይወቅልኝ አለ።

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ የካፒታል ገበያ አማካሪ አቶ አሰፋ ስሞሮ ፤ " በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ከአክሲዮን ገበያ ጋር በተገናኘ #የድለላ ስራ እየሰሩ ያሉ #ህገወጥ ግለሰቦች መኖራቸውን መረጃውን አለን ነገር ግን አንዳቸውም ከባለስልጣኑ ፈቃድ አላገኙም " ብለዋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ለጊዜው ፈቃድ መስጠት አለመጀመሩን የገለጹት ባለሙያው የፈቃድ መመሪያው ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን በማንሳት በሚደረጉ ቀጣይ ውይይቶች ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በአሁኑ ወቅት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ውጪ " አክሲዮን እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆነ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል ሲል አስገንዝበዋል።

በተቀመጠው አዋጅ መሰረት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች በሚል መጠሪያ ተቋሙ ፈቃድ እንደሚሰጥ በመግለጽ አስፈላጊው ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግባቸው እንደሚሆኑም ከአሁኑ ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣኑ በይፋ ፈቃድ መስጠት ሲጀምርም በመሰል ህገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ ግለሰቦችን በህግ #ተጠያቂ እንደሚያደርግም አሳውቋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ #የአሃዱሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia