TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tecno_Pop8 !

እያንዳንዱ ምስል በቀለማት ታጅቦ በከፍተኛ ጥራት ቁልጭ ብሎ እንዲታይ 6.6 ኢንች ሰፊ ስክሪን ከ90Hz  ሪፍሬሽ ሬት ጋር በማጣመር አዲሱ Pop 8 ከTECNO ሞባይል ቀርቦሎታል።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Pop8 #TecnoMobile #TecnoEthiopia
#ግሎባል_ባንክ_ኢትዮጵያ

ቀለል ያለ ጥያቄ በመገመት ይሸለሙ!

የሽልማቱ ሕግጋትና ደንቦች፤

1. የሚያሸልመውን ትክክለኛ ጥያቄ ምላሽ የምንቀበለው በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/Globalbankethiopia123 ብቻ ነው፡፡
2. የጥያቄውን ትክክለኛ ምላሽ ለሚያገኙ ቀዳሚ 10 ተወዳዳሪዎች ሽልማቱን የምንሰጥ ይሆናል፡፡
3. ትክክለኛውን ምላሽ ከጎል አስቆጣሪዎቹ ጋር በትክክል ለሚገምቱ መላሾች ተጨማሪ ቦነስ ሽልማት ያገኛሉ፡፡
4. ተወዳዳሪዎች ሽልማቶቹን ለማሸነፍ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የቴሌግራም ገፅ ተከታይ መሆን አለባቸው፡፡
5. የጥያቄውን ትክክለኛ መልስ የምንቀበለው እስከ ቅዳሜ ማታ 1፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
6. ከአንድ በላይ ግምት መስጠት ለሽልማት ብቁ አያደርግም፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡
https://bit.ly/3TkrrXD

ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚ ናቸው፡፡
መልካም ዕድል!

ለጋራ ስኬታችን
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም አዲሱ የክልል አደረጃጀት ተከትሎ የተለያዩ አስተዳደሮች እና መዋቅሮች መልሶ መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ሂደት ጋር የሚነሱ የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ አቤቱታዎችን፣ እንዲሁም ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

ይህ በተመለከት ከላይ የተያያዘውን መግለጫ ልኮልናል።

@tikvahethiopia
#TOYOTA

ቶዮታ / Toyota ዓለም አቀፍ የመኪና አምራች ኩባንያ በዓለም ገበያ በዋነኝነት #በአሜሪካ የተሸጡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎቹን  ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ አዟል።

ቶዮታ እንዲሰብሰቡ ያዘዘው ከ2020 እስከ 2022 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተመረቱ ተሽከርካሪዎችን ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የ " ኤርባግ " ደህንነት ችግር አለባቸው ተብሏል።

ከ2020 እስከ 2022 ወደ ገበያ የቀረቡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች (በዋነኝነት #አሜሪካ) ከ " ኤርባግ " ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለባቸው ተደርሶበታል።

ችግሩ በፊት ለፊት ተሳፋሪ መቀመጫ በኩል በስህተት ከተሰራ የ " ኤርባግ ሴንሰር " ጋር የሚያያዝ ሲሆን ምናልባትም በአደጋ ጊዜ " ኤርባጉ " አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል። ይህ አደጋ በሚፈጠር ጊዜ ኩዳቱ እንዲጨምር ያደርጋል።

ቶዮታ የትኞቹ ሞዴሎች ይሰብሰቡ አለ ?

#ቶዮታ

ኮሮላ (2020 - 2021)
ራቭ4 ፣ ራቭ4 ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ሃይላንደር፣ ሃይላንደር ሃብሪድ (2020 - 2021)
አቫሎን ፣  አቫሎን ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ካምሪ፣ ካምሪ ሃብሪድ (2020 - 2021)
ሴና ሀይብሪድ (2021)

#ሌክሰስ

ES250 (2021)
ES300H (2020-2022)
ES350 (2020-2021)
RX350 (2020-2021)
RX450H (2020-2021) የተሰኙ ከ2020 እስከ 2022 ላይ የተመረቱት የ " ኤርባግ " ችግር ስላለባቸው ይሰብሰቡ ብሏል።

ከላይ የተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች ያላቸው ሰዎች ኤርባጋቸውን #እንዲያረጋግጡ እና ችግር ካጋጠማቸው እስከ ቀጣዩ የካቲት ወር ድረስ እንዲመልሱለት ቶዮታ ጥሪ አቅርቧል።

የቶዮታ ተሽከርካሪዎች ችግር እንዳለባቸው የታወቀው የጃፓን ትራንስፖርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተሽከርካሪ እምራች ኩባንያዎች ላይ ባደረገው #ምርመራ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የቶዮታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል።

ምርመራው ከቶዮታ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ዳይሀትሱ በተሰኘው ኩባንያ ላይም ተመሳሳይ ችግር መታየቱን ገልጿል።

ከ87 ዓመት በፊት ኪቺሮ ቶዮታ በተባለ ግለሰብ የተመሰረተው ቶዮታ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በዓመት 10 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ይገኛል።

ከ360 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ቶዮታ ኩባንያ 300 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳለው የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።

#ጥቆማ ፦ ከደህንነት ጋር በተያይዘ በተለይም በአሜሪካ እንዲሰበሰቡ የታዘዙ ተሽከርካሪዎችን ቼክ ለማድረግ https://www.nhtsa.gov/recalls በዚህ አድራሻ መጠቀም ይቻላል። የመኪናውን መለያ ቁጥር (VIN) በማስገባት ማወቅ ይቻላል።

Credit - #AlAiN / #Reuters / #Toyota_News_Room

@tikvahethiopia
#ትግራይ

ከገረብ ሰገን ግድብ ለመቐለ ከተማ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ መጋቢ የሆነው ማእከላይ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ማስተላለፍያ ትራንስፎርመር (ቮልቴጅ KO-9) #ተሰረቀ። 

ስርቆቱ የተፈፀመው ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም ንጋት ላይ ነው ተብሏል።   

ስርቆቱ እስከ አሁን " ማንነታቸው ባልታወቁ ዘራፊዎች " መፈፀሙ ነው የተሰማው።

የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ግርማይ ግደይ ለሚድያዎች በሰጡት መረጃ ፤ በቅርቡም ወደ ጋምራና ጨለቆት የሚባሉ የመቐለ ዙሪያ አከባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያስተላልፍ ትራንስፎርመር ተዘርፏል።

ከገረብ ሰገን ግድብ ለመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ውሃ ለማቅረብ የሚያገለግለው ጨምሮ በወራት ውስጥ 3 ትራንስፎርመር መዘረፋቸውን የተናገሩት አቶ ግርማይ ፤ የአሁኑ የትራንስፎርመር ስርቆት በርካታ የከተማዋ አከባቢዎች ለመጠጥ ውሃ እጦት ይዳርጋል ብለዋል። 

የትራስፎርመር ስርቆቱ ከግድቡ አጠገብ የሚገኘው የመለስ ስራ አመራር አካዳሚ የኤሌክትሪክ አግልግሎት እንዲቋረጥ ምክንያት መሆኑም አክለው አስታውቀዋል። 

በተደጋጋሚ ጊዜ በኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ ትራንስፎርመሮችና ገመዶች የሚፈፀም ስርቆት የመከላከል ጉዳይ ለፀጥታ ሃይሎች ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት ባለሞያው ፤ ህዝቡ ተደራጅቶ አከባቢውንና የመንግስትና የህዝብ ንብረት በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

በጦርነቱ ጊዜ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የነበሩ ትራንስፎርመሮች ላይ በርካታ የስርቆትና የማበላሸት ተግባራት ሲፈፀም እንደነበረ መረጃውን የላከልን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiaTigrigna
                                      
@tikvahethiopia            
#ጥቁር_አንበሳ👏

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመርያው የአንጎል የደም ስር ክሊፒንግ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የአንጎል የደም ስር ክሊፒንግ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ህክምና የተደረገላት ታካሚ ከአዲስ አበባ በጥቂት ርቀት ላይ የምትኖር ሲሆን ድንገት በዕለት ሥራዋ ላይ ሳለች ከፍተኝ የራስ ህመም ይሰማት እንደጀመረና ከዚያም እራስዋን ስታ መውደቋን ታሪኳ ያስረዳል።

ህክምና ተቋም እንደደረሰችም በተደረገላት ምርመራ በአንጎልዋ ውስጥ የደም ቧንቧ መፈንዳት ምክንያት የደም መፍሰስ እንደተከሰተና የፈነዳዉን የደም ቧንቧ በቅዶ ጥገና ህክምና ባስቸኳይ ካልተስተካከለ ለሞት የሚዳርጋት መሆኑን ይነገራታል።

በወቅቱ ታካሚዋ ህክምናውን ውጭ ሀገር ወይንም የግል የህክምና ተቋም ላይ ከፍላ መታክም ስላልቻለች ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መላኳን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በኒውሮሰርጀሪ ዲፓርትመንት አስተባባሪነትና የአንጎል ደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ህክምና ከፍትኛ ልምድ ባካበቱት ዶ/ር ቶማስ ቦጋለ የሚመራ የህክምና ቡድን ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም ሶስት ስዓት ከግማሽ በወሰደ የቀዶ ጥገና የተስተካከለ የአንጎል የደም ዝውውር እንዲኖራት ማድረግ ችሏል።

ይህ ህክምና ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ደረጃ በመንግስት ሆስፒታሎች ሲሰራ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ታካሚዋ በተደረገላት ህክምና እጅጉን እንደተደሰተች ገልጻ፥ ባሁኑ ስኣት ከህመምዋ አገግማ ወደ ቤትዋ መመለስ ችላለች።

ለሌሎች ግንዛቤ ለመፍጠር ያግዝ ዘንድ በቀዶ ጥገና ወቅት የተወሰዱ ፎቶዎችን ለማጋራት ታካሚዋ ፍቃድዋን የሰጠች ሲሆን ፤ በቀዶ ጥገናው ላይ የተሳተፉ አባላት ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

➡️ ዶ/ር ቶማስ ቦጋለ (የአንጎል ውስጥ የደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም)

➡️ የነርቭ ቀዶ ሕክምና ሬዝደንት ዶ/ር መሃሪ ፣ ዶ/ር ፒኔል ፣ ዶ/ር ዳዊት እና ዶ/ር ብዙአየሁ

➡️ ስክራብ ነርስ ፦ ነርስ ኢብራሂም፣ ሲስተር ሶስና እና ሲስተር መንበረ

➡️ ዶ/ር ቦንሳ (አንስቴዚዮሎጂስት)

➡️ አንስቴዚዮሎጂ ሬዝደንት፦ ዶ/ር ማህደር ፣ ዶ/ር እየሩስ እና ዶ/ር ውበት

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል (ቀዶ ጥገናውን ካከናወኑ የጤና ባለሞያዎች) ነው ያገኘው።

Via  @TikvahethMagazine
#Tecno_Pop8

በየትኛውም የሞባይል ጌሞች እየተዝናኑ አስደሳች ቆይታ እንዲኖሮት፣ ምርጫዎ አዲሱ ፖፕ 8 ሲሪየስን ያድርጉ! 

በመረጡት የሞባይል ጌሞች እየተዝናኑ እንከን የለሽ ጊዜ ለማሳልፍ ኦክታ ኮር ፕሮሰሰር ( Octa core A53 processor )፣  በ90Hz ሪፍሬሽ ሬት ጥራት ያለው ምስል የሚያሳይ ሰፊ 6.6 ኢንች እስክሪን እና እረጅም የአገልግሎት ጊዜ ከሚሰጠው በባለ 5000mAh ባትሪ አንድላይ በማቀናጀት የተመረተው አዲሱ ቴክኖ ፖፕ 8’ን ምርጫዎ ያድርጉ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Pop8 #TecnoMobile #TecnoEthiopia
#CBE
በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ!
EthioDirect
===========
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ መላክ ይችላሉ፡፡
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
===========
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም  App Store በማውረድ  አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491

***  
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!  
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh  
• Telegram፡- https://t.me/combankethofficial
#AddisAbaba

ጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰጠው የዕውቅና ፍቃድ ታገደበት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ባገኘው መረጃ ትምህርት ቤቱ ፦

- በሀገር አቀፍ እና በከተማ አስተዳደሩ የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ባለማድረጉ ተማሪዎች ከአማርኛ ትምህርት ውጭ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚማሩ መሆኑ ከፍተኛ የስርዓተ ትምህርት ጥሰት በመሆኑ፤

- ት/ቤቱ በትምህርት ቢሮ በተዘጋጀው ካላንደር መሰረት እየተጠቀመ ባለመሆኑ፤

- ት/ቤቱ በራሱ ያዘጋጀው የአሰራር መመሪያዎች ከመንግስት ፖሊሲ መመሪያና ደንቦች ጋር ተናባቢ ያልሆነና የሚጣረስ በመሆኑ፤

- የትምህርት ክ/ጊዜ ስርጭት በተሻሻለው የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት ባለመሆኑ እና ከስርዓተ ትምህርቱ ውጪ የሆኑና በሚመለከተው አካል ያልፀደቁ የማስተማሪያ መጽሐፍት ለማስተማሪያነት እየተጠቀመ በመሆኑ የማስጠንቀቂ ደብዳቤ ተልኮለት እንደነበር ተገልጿል።

በዚህም በ15 ቀናት ውስጥ ማስተካከያ በማድረግ አፈፃፀሙን በሪፖርት እንዲያሳውቅ የተጠየቀ ቢሆንም በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መሰረት ትምህርት ቤቱ ምላሽ እንዳልሰጠ ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

በተሰጠው የጊዜ ገደብ ማስተካከል ስላልቻለ ከ12/04/2016 ጀምሮ ለትምህርት ቤቱ የተሰጠው የዕውቅና ፍቃድ የታገደ መሆኑን ተገልጿል።

በትምህርት ቢሮም ሆነ በትምህርት ፅ/ቤት በኩል ለትምህርት ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች በሙሉ እንዲቋረጡ ታዟል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑን የባለስልጣን መ/ቤቱ የካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቅዱስ ሚካኤል ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እውቅና ሰርዟል።

ፍቃዱ የተሰረዘው ፦
° ከአሰራር ውጭ በወርሃዊ ክፍያና በመመዝገቢያ ያደረገው ጭማሪ፤
° ትምህርት ቢሮ ያወረደውን የተማሪዎች ሪፖርት ካርድ ባለመስጠት፣
° የአፋና ኦሮሞ ትምህርት በትምህርት ቢሮ በወጣለት ስርዓት ያለመፈፀሙ
° በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የታተሙ መፅሀፍትን በመተው በራሱ ያሳተማቸውን ለወላጆ በመሸጡ
° ሁሉንም አይነት ስርዓተ ትምህርት ይዘት ጥሰት ፈፅሞ በመገኘቱ ማስተካከያ እንዲያደርግ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም የእውቅና ፍቃዱ ታግዶ ቆይቷል። በኃላም ማስተካከያ ስላልወሰደ ከታህሳስ 5 / 2016 ጀምሮ ታግዶ የቆየው እውቅና ፈቃድ መሰረዙን ቅርጫፍ ፅ/ቤቱ አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦ አፖሌ ግሎባል አካዳሚ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተመሳሳይ የእውቅና ፍቃዱ ተሰርዞበታል።

ትምህርት ቤቱ ፦
* ከመደበኛ ትምህርት አገልግሎት ክፍያና መመዝገቢያ ውጭ ለመፅሀፍትና ለኮሚኒኬሽን ዲያሪ በሚል 2 ሺህ ብር ከወላጅ በመሰብሰቡ
* 3 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ለማስተማር 3 ክፍሎች የተፈቀደለት ሆኖ በራሱ ውሳኔ 3 ክፍሎችን በመጨመሩ፣
* 5 የአስተዳደር አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን በማጠፍ የመማሪያ ክፍል እንዲሆኑ በማድረጉ
* ያልተፈቀዱ ክፍሎችን ለማስፋት በሚል ዓላማ የተማሪዎችን ማሸለቢያ ክፍል በመቀየር አመቺ ባልሆነ የፍራሽ ክምችት በሚገኝበት ጠባብ ቦታ ማድረጉ ... ሌሎችንም ችግሮች እንዲያስተካክል በደብዳቤ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኃላ የእውቅና ፍቃዱ ታግዶ ነበር። በኃላም የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ ከታህሳስ 08/2016 ጀምሮ ታግዶ የቆየው እውቅና ፍቃድ መሰረዙን ቅ/ፅቤቱ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እውቅናው ከታገደው የጊብሰን ትምህርት ቤት እንዲሁም እውቅናቸው ከተሰረዘው የቅዱስ ሚካኤል  ት/ቤትና አፖሎ ግሎባል አካዳሚ ማባራሪያ የሚያገኝ ከሆነ ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቡና ደርሷል! የቡና ቁርሱም ቀርቧል- ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
Stage All Set with Coffee and Snacks at the Ready - with #SunChips 😋 and #SunnyMoments. 😋

Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia