TIKVAH-ETHIOPIA
" ድርቁ ከ1977ቱም የከፋ ነው " - የትግራይ ክልል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) በትግራይ ስላለው የድርቅ ሁኔታ ምን አሉ ? - ድርቁ በ5 የትግራይ ክልል ዞኖች ተከስቷል። - በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 ነበር። አሁን ያጋጠመን ከዚህም በላይ ነው። - በዚህ ድርቅ ምክንያት…
" እኔ እድሜዬን በሙሉ እንዲህ አይነት ድርቅ አይቼ አላውቅም "
በትግራይ ክልል፤ የኢሮብና አፅቢ ወረዳ ነዋሪዎች አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ቃላቸውን ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን የሰጡ ነዋሪዎች ምን አሉ ?
አንድ አባት ፦
" ክረምት አልነበረም ማለት ይቻላል። በጣም ጥቂት ዝናብ ነው የዘነበው። እንኳን እህል የእንስሳት መኖ አልሰበሰብንም። አካባቢያችን ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል። በድርቁ ምክንያት ለረሃብ ተጋልጠናል። ሰላም ሆኗል ብለን ብዙ ተስፋ ብናደርግም ተፈናቃዮቻችን ወደቦታቸው አልተመለሱም። እርዳታም አግኝተው አያውቁም። ድርቅ ሲጨመርበት ሁኔታው ከፍቷል። "
ሌላ አባት ፦
" እኔ እድሜዬን በሙሉ እንዲህ አይነት ድርቅ አይቼ አላውቅም። የዘንድሮው እጅግ የተለየ ነው። ከሶስት ጊዜ የማይበልጥ ዝናብ ነው የዘነበው። ምንም አይነት እህል ማብቀል አልቻልም። ቀደም ሲል አርሰን የተወሰነ እህል እንሰበስብ ነበር፤ ዘንድሮ ግን እኛም እንስሳቶቻችንም የምንበላው የለንም። በሻቢያ ሰራዊት መሰቃየታችን ሳያንስ ድርቁ እጅግ ጎድቶናል። ከረሃብ ባለፈ የመጠጥ ውሃም ችግር አለብን። በርካታ ኪሎሜትር ተጉዘን ነው የመጠጥ ውሃ የምንቀዳው ይህ ሳያንስ በሻቢያ ሰራዊት ተከበን ስላለን ችግራችን በቃላት የሚገለፅ አይደለም። "
አንዲት እናት ፦
" በክረምት ዝናብ አጥተን ነው የቆየነው። ዘንቧል ከተባለ በሳምንት አንዴ ነው። እንኳን ለኛ ለእንስሳቱ ምግብ አልሰበሰብንም። "
ሌላ እናት ፦
" ችግራችን እንሸፍነው ብልን የሚሸፈን አይደለም። በረሃብ ምክንያት እጅግ ተጎድተናል። "
በወረዳዎቹ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ እንዲሁም በመድሃኒት እጥረት ምክንያት የሞቱ ሰዎች መኖራቸው ሪፖርት የተደረገ ሲሆን የሞት አፋፍ ላይ ያሉም አሉ ተብሏል። ጠንካራ ድጋፍ ካልተደረገ ሰዎች በህይወት የመቆየታቸው ነገር አሳሳቢ መሆኑን ነዋሪዎች አመልክተዋል።
ነዋሪዎች በከፋ ችግር ውስጥ እንዲወቅዱ ያደረጋቸው ድርቁ ብቻ ሳይሆን አካባቢዎቹ ባስተናገዱት የከፋ ጦርነት ምክንያት ኢኮኖሚው በመድቀቁ፣ መሰረተ ልማት በመውደሙ መሆኑም ጭምር ተነግሯል።
* በትግራይ ያጋጠመውን ድርቅ እና ረሃብ ለመመከት በሚል ክልሉ " የረሃብ አደጋ አዋጅ " አውጆ እንተንቀሳቀሰ ይገኛል። ችግሩን በውስጥ አቅም ለመፍታት ክልሉ አሁን አቅም እንደሌለው ገልጾ ፦
- በመላው ዓለም የሚገኝ ትግራዋይ፣
- መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣
- ሁሉም ክልል ፣
- ዓለም አቀፍ ማህበረስብ ረብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ክልሉ ያቋቋመው ግብረኃይል የባንክ አካውንት በዚህ ይገኛል ፦https://t.me/tikvahethiopia/83490?single
@tikvahethiopia

#ኦዲት
#ለተከታታይ_ዓመታት ለተገኘበት በርከት ያለ የኦዲት ክፍተት ማስተካከያ ማድረግ እንደተሳነው የተገለፀው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከአመራር መቀያየር ባለፈ ጥብቅ ሪፎርም እንደሚስፈልገው የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል።
ይህንን ያስታወቀው፤ የሕ/ተ/ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2014 / 15 በጀት ዓመት ሒሳብ ኦዲት ላይ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ሲደረግ ነው፡፡
መስሪያ ቤቱ ምን አለ ?
ኮሚሽኑ ፦
📄ለሚፈጽማቸው ክፈያዎች ደረሰኝ ባለማቅረብ፣
📄ኮፒ ደረሰኝ መጠቀም፣
📃በኮፒ ደረሰኝ ሂሳብ ማወራረድ፣
📄ያልተፈቀደ ክፈያ በመፈጸም፣
📄ለተከፈለ ገንዘብ ማስረጃ ባለማቅረብ፣ እንዲሁም #በቢሊዮኖች ብር የሚቆጠር ተከፋይ እና ተሰብሳቢ ውዝፍ የኦዲት ሪፖርት ተገኝቷል።
- ከሳዑዲ ከስደት ለተመለሱ 102 ሺህ ኢትዮጵያውያን ለኪስ አበል እንዲሁም ለቤት ኪራይ 5.2 ሚሊዮን ብር ማስረጃ ሳይቀርብ ተከፍሏል። ተከፈለ ለተባለው ለዚህ ገንዘብ ሰነድ ማግኘት ባለመቻሉ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልታቻለም።
- ለምግብ ዝግጅት ድርጅት ተብሎ የተከፈለና በወጪ የተመዘገበ 2.9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ዋጋው ከ65.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 14 ሺህ ኩንታል ዱቄት " ናህሊ ዱቄት ፋብሪካ " ለተስኘ ድርጅት የተከፈለ ተብሎ የቀረበ ቢሆንም የቀረበው ደረሰኝ ግን ኮፒ ነው።
- በወጪ ሒሳብ ለተመዘገበ 79 ሚሊዮን ብር ለኦዲት ሥራ የሚፈለጉ የወጪ ማስመስከሪያዎች (ቫውቸሮች) ከደጋፊ ሰነዶች ጋር እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ማስረጃ ሊቀርብ አልቻለም።
- ያልተወራረደ 881.5 ሚሊዮን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ መኖሩ በኦዲት ሪፖርት ቢረጋገጥም፣ ከኦዲት ግኝት በኋላ የተወሰደ ማስተካከያ የለም።
➡️ በወቅቱ ያልተወራረደ 39.7 ሚሊዮን ብር ተከፋይ ሒሳብና ያልተከፈለ ሲሆን ከኮሚሽኑ መደበኛ በጀት 37.6 ሚሊዮን ብር በሥራ ላይ አልዋለም።
በተጨማሪም ፦
* ውኃ የሚያስገቡ እና ጣሪያቸው የሚያፈሱ መጋዘኖች ተገኝተዋል።
* በቆይታ ብዛት የተበላሸ ብስኩት ሳይወገድ በግምጃ ቤት ተገኝቷል።
* የቆይታ ጊዜያቸው የማይታወቅና በውስጣቸው ምን እንዳለ የማይታወቅ የታሸጉ 9 ኮንቴነሮች በመጋዘን ግቢ ውስጥ ተገኝቷል።
* የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ ፦
🔹ሴሪላክ የዱቄት ወተት፣
🔹የወይራ ዘይት፣
🔹የምግብ ዘይት፣
🔹ብዛት ያላቸውና ጊዜያቸው ያለፈባቸው ቴምሮች፣
🔹የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ተገኝቷል።
* በእህል መጋዘኖች ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያልፍ #ሁለት እና #ሦስት ወራት የቀራቸው አልሚ ምግቦች፣ ሳሙናዎችና እህሎች ተገኝቷል።
◾የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም የኦዲት ሪፖርት ላይ ለመምክር በተጠራው ውይይት አለመገኘታቸው ቋሚ ኮሚቴውን አስቆጥቷል።
በወቅቱ ውይይቱ ላይ የተገኙት ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ኮሚሸነሩ የቀሩት ሌላ ተልዕኮ ስለነበራቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ምን አሉ ?
° ኮሚሽኑ ኃላፊዎችን #ከመቀያየር ባለፈ መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልገዋል።
° በ2014 ዓ/ም የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ኦዲተሮች ለጊዜያዊ የኦዲት ሥራ የተረከቡትን ቢሮ ኦዲት አድርገው በሚወጡበት ጊዜ የኮሚሽኑ ሠራተኞች በመግባት #ሰነድ እያወጡ መሆኑን መረጃ አለኝ።
° ይህ ኮሚሽን ለፈጸማቸው ክፍያዎች ሰነድ ማቅረብ አለመቻሉ መሠረታዊ ችግሩ ነው።
° ከዚህ በፊት የበላይ ኃላፊው ቢታሰሩም ኮሚሽኑ ግን አሁንም ሰንኮፉ አልተነቀለም፣ በመሠረታዊነት ችግሩ አልተቀረፈም።
° በመጋዘኖች ውስጥ በሚገኙ ንብረቶች ከፍተኛ ችግር አለ። ገንዘቡ አንዴት እንደሚመጣ እናውቀዋለን ነገር ግን እዚህ ያለው ሥራ የተዝረከረከ ነው፡፡
° በ2013 ዓ.ም. #ድሬዳዋ እና #ሻሸመኔ በሚገኙ መጋዘኖች ከታዩ ችግሮች በመነሳት የኦዲት አስተያየት የተሰጠንባቸው ጉዳዮች በ2014 ዓ.ም በድጋሚ ኦዲት ሲደረግ በነበሩበት እንጂ ተስተካክለው አልተገኙም።
° " ደመወዝ የምንበላበት ተቋም ነው፣ ስለዚህ እዚያ ያለውንም ሥራ ልክ እንደ ቤታችን ማየት አለብን፡፡ ይህ ሁሉ ቁሳቁስ የሚገዛው በብድር ነው እናውቃለን፡፡ እዚህ አምጥተን በአግባቡ የማይውል ከሆነ፣ መሬት ላይ የሚደፋና ከጋዝ ጋር ተቀላቅሎ የሚበላሽ ከሆነ ሥራው ትርጉም አልባ ነው "
° በዚህ ውይይት ላይ ያልተገኙት #ኮሚሽነሩ የቀሩት ዕርዳታ ለማፈላለግ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ተቋሙ የተገኘውን ንብረት በተገቢው መንገድ ማስተዳደር ካልተቻለ፣ ዕርዳታ ማፈላለጉ ብቻ ትርጉም የሌለውና በቀዳዳ በርሜል ውኃ እንደመሙላት የሚቆጠር ነው።
የገንዘብ ሚኒስቴር ፤ የኢንስፔክሽን መምርያ ኮሚሽኑ በኮፒ ደረሰኝ ሒሳብ እንደሚያወራረድ በተደጋጋሚ ቢነገርም ሊስተካከል ባለመቻሉ ይህንን ያደረገ ኃላፊ መጠየቅ አለበት ብሏል።
More - https://telegra.ph/Reporter-12-14-2
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ "ሪፖርተር ጋዜጣ " መሆኑን ያሳውቃል።

ዋነኛው መክሰስ በሃሙስ ምድር ተገኝቷል፤ ከማባያ እና ማጣፈጫ ጋር እናጣጥም- ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
Thursday cannot go any better with all the pairings and dips - with #SunChips 😋 and #SunnyMoments.☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

" ባለቤቴ ፓርቲው በእግሩ እንዲቆም መስዋእትነት ከፍለው እንደዛ ሰርተው ከሌላ አካል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም " - ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ የብልጽግና ፓርቲ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ዳንዳአ መታሰራቸው " በምንም መለኪያ ትክክል አይደለም " ሲሉ ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አላማየሁ ተናገሩ። የአቶ ታዬ ባለቤት ፤ አቶ ታዬ ሙሉ ጊዜያቸውን በመስጠት…
" ውሳኔው ገፍቶ የሚመጣ ከሆነ ጎዳና ላይ ለመውጣት እንገደድ ይሆናል። " - ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ
በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ አሁን እየኖሩበት ያለበትን የመንግሥት ቤት ለቀው እንዲወጡ እንደተነገራቸው ከቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ተናግረዋል።
ምን አሉ ?
- የባለቤታቸው መታሰር መላው ቤተሰባቸው ላይ ከባድ ችግርን እንዳስከተለ ተናግረዋል።
- አቶ ታዬ ሰኞ ታኅሣሥ 01/2016 ዓ.ም. ምሽት መያዛቸውን ተከትሎ በቀጣዩ ቀን የሚኖሩበትን የመንግሥት ቤት ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው ጎዳና ላይ የመውደቅ ስጋት እንደደቀነባቸው ገልጸዋል።
- " የኪራይ ቤቶች ሰዎች ማክሰኞ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ላይ መጥተው ቤቱን በ3 ቀናት ውስጥ ለቀን እንድንወጣ መልዕክት አስቀምጠው ሄደዋል። ረቡዕ ጠዋት መልሰው በመምጣት ሐሙስ 3፡00 ላይ ቤቱን እንድትለቁ ብለውናል " ሲሉ ተናግረዋል።
- ልጆቻቸው ተማሪዎች መሆናቸውን እንዲሁም ሌላ ቤተሰብም አብረዋቸው እንደሚኖሩ ገልጸው በዚህ አጭር ጊዜ ቤት መፈለግ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው እና ሁኔታው የበለጠ እንዳሳሰባቸው አስረድተዋል።
- ባለው ሁኔታ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሆኑ ተናግረው ውሳኔው ገፍቶ የሚመጣ ከሆነ " ጎዳና ላይ ለመውጣት እንገደድ ይሆናል። " ብለዋል።
ወ/ሮ ስንታየሁ ባለቤታቸው አቶ ታዬ ደንደአ ፦
- መታሰራቸውን በምንም መለኪያ ትክክል ነው ብለው እንደማይቀበሉ።
- ሙሉ ጊዜያቸውን በመስጠት ይሄን ስርዓት መሰረት ለማስያዝ ሲሉ ከብዙ ሰዎች እና ቤተሰቦች ጋር እየተጋጩ እራሳቸውን ሰጥተው ሲሰሩ እንደነበር።
- ፓርቲው (ብልፅግና) በእግሩ እንዲቆም መስዋእትነት ከፍለው ፤ እንደዛ ሰርተው ከሌላ አካል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ እንዳልሆነ ቅሬታቸውን መግለፃቸው ይታወቃል።
#Update
ወ/ሮ ስንታየሁ ፦
* የጸጥታ ኃይሎች ሐሙስ ዕለት ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ መጥተው አስወጥተውናል።
* የተወሰኑ የቤት ዕቃዎችን እና አልባሳት ማውጣት ብንችልም ሌሎች ንብረቶች በቤቱ ውስጥ ታሽጎብናል።
* " አሁን የምትችሉትን ዕቃዎች ውሰዱ እና ሌሎች ንብረታችሁን አርብ ተመልሳችሁ ውሰዱ ብለው ነው ያሸጉት "
" በአሁኑ ወቅት በቤተሰቦቻቸው ቤት በጊዜያዊነት ተጠግተን ነው የምንገኘው።

ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎች ፤ " ጤና ሚኒስቴር በሕግ የተወሰነልንን ልዩ አበል አልከፈለንም " አሉ። የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት፤ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ማኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን…
#ጤና_ሚኒስቴር #ክስ
የፍርድ ቤት ውሳኔን በተደጋጋሚ ጣሰ የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " ለ70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ -19 ልዩ አበል እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈበት።
70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ወረርሽኝ #ልዩ_አበል እንዲሰጣቸው በመሰረቱበት ክስ መሠረት ገንዘቡን እንዲከፍል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ጥሷል የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " አሁንም ከንግድ ባንክ አካውንቱ #እየቆረጠ_እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጤና ባለሙያዎቹ ገለጻና ከተጻፈው ደብዳቤ መረዳት ችሏል።
የጤና ባለሙያዎቹ ተወካይ የፍርድ ሂደቱ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
* ፍርድ ቤት ለባንክ ሲያዝ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
* የፋይናንስ ክፍሉ ኃላፊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ድክመት ለፍርድ ቤት #ታስረው ቀርበው እንዲያስረዱ ቢታዘዝም ጉዳዩን እንዲያስፈፅም የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ መስሪያ ቤቱ ድርስ በመሄድ ቢጠይቅም እረፍት እንደወጡና እስከ ሰኞ (ያለፈው ሳምንት ሰኞ) እንደሚመጡ አሳውቀው ነበር። ከዚያ በኋላም ፍርድ ቤት መጥተው አያውቁም።
* ታስረው እንዲቀርቡም #ከሁለት_ጊዜ_በላይ ነው የታዘዘው።
* ፍርድ ቤት በራሳቸው እንዲፈፅሙ ግን በተደጋጋሚ (ከአምስት ጊዜ በላይ) ትዛዝ ሰቶ ነበር።
* ሰዎቹ በፍፁም ለህግ ተገዢ አለመሆናቸውን እና እምቢተኝነታቸውን በተደጋጋሚ ጊዜ አሳይተውናል።
* ለፍርድ ቤት ውሳኔ ያላቸው ንቀት በቃላት የሚገለፅ አይደለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ይሄንን የጤና ባለሞያዎች መረጃ በማደራጀት ሂደት የጤና ሚኒስቴርን ምላሽ እና ማብራሪያ ለማካከት ብዙ ቢደክምም ምላሽ ሰጪ አላገኘም።
አሁንም #በአካልም ይሁን #በስልክ ምላሽ ሰጣለሁ የሚል የሚኒስቴር መ/ቤቱን አካል ለማስተናገድ ዝግጁ ነው።
ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-14
የመረጃው ዝግጅት በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

Telegraph
Tikvah-Ethiopia
#ጤና_ሚኒስቴር #ክስ የፍርድ ቤትን ውሳኔን በተደጋጋሚ ጣሰ የተባለው ጤና ሚኒስቴር ለ70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ልዩ አበል እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈበት። 70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ - 19 ልዩ አበል እንዲሰጣቸው በመሰረቱበት ክስ መሠረት ገንዘቡን እንዲከፍል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ጥሷል የተባለው ጤና ሚኒስቴር አሁንም ከንግድ ባንክ አካውንቱ እየቆረጠ…
#Oromia
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ሰላማዊ ዜጎችን ያልለየ ግድያ በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ይፈጸማል ሲል ከሷል።
በመግለጫው ምን አለ ?
- በኦሮሚያ ተደጋጋሚ ግድያ እና የጅምላ እስሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሳያቋርጥ ይፈጸማል።
- ህዳር 30 እና ታኅሣሥ 01 ቀን 2016 ዓ.ም. በአቡና ግንደበረት እርጃጆ፣ ጫፌ ኤረርና ፊኖ ቀበሌያት 8 ንጹሃን ዜጎች በጠራራ ጸሃይ ተገድለው ሁለት ሰዎች ቆስለዋል።
- በቄሌም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ውስጥ ጸሎት ላይ እያሉ ከመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እንዲወጡ ተደርገው የተገደሉ 9 አማኞች በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ነው።
- ከቀናት በፊት በአጋምሳ "ቆርቆቤ' በሚባል ቦታ ላይ መንግስት በስልጣን ላይ እያለ የፋኖ ታጣቂዎች ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል። የአገምሳ ወጣቶች እህል ለመሰብሰብ በሲኖትራክ መኪና ወደ ምእራብ ጎጃም ሲጓዙ በተፈፀመው ጥቃት ከ13 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
- በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ሲርካ ወረዳ በሚገኙ መንደሮች በዋጂ ራፋሳ፣ ቢዱ ባላ፣ ሄላ አመጃ፣ ሄላ ጠሬታ፣ ገለቤ አማጃ፣ ማካራራ፣ ሶጂዪ ሳዲ፣ ጋላቤ ሁሉል እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመክፈት ህፃናትን ጨምሮ ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፣ ብዙ ቤቶች ተቃጥለዋል።
- የመንግስት ወታደሮች ህዳር 15 በደምቢ ዶሎ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት የሰዎችን ህይወት ቀጥፈዋል።
- ህዳር 13 ቀን 2016 በቡኖ በደሌ ዞን ጨዋቃ ወረዳ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ተማሪዎችን ጨምሮ 52 ሰዎች ተገድለዋል።
ለኦነግ ፓርቲ መግለጫ የመንግስት ምላሽ ምንድነው ?
ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ፦
* መንግስት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚወሰድው እርምጃ አይኖርም።
* በንጹሃን ዜጎች ላይ ርምጃ የሚወስደው አሸባሪው የሸኔ ቡድን ነው። በቅርቡ ሽርካ ወረዳ በርካታ ንጹሐንን የቀጠፈውን አሰቃቂ ጥቃት የፈፀመው ይኸው ቡድን ነው። ከግድያ ባለፈ በአከባቢው የነዋሪዎችን ቤት አቃጥሏል።
* ንጹሃን ዜጎችን ከጥቃት ለመጠበቅና የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ የሚረዳ ወታደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
* እርምጃዎቹ በታጣቂዎች ላይ ያነጣጠሩ ብቻ ናቸው። ለአብነትም በቡኖ በደሌ ወረዳ ጨዋቃ ወረዳ የተወሰደው ሸማቂውን ቡድን ሙትና ቁስለኛ አድርጓል። እርምጃው ታጣቂ ቡድኑ ለጥቃት ሲዘጋጅ የተወሰደ ነው።
* ለአሸባሪ ቡድን የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ወንጀል በመሆኑ ድጋፍ የሚሆኑት ሴሎቹ ላይ እርምጃ ይወሰዳል እንጂ ንጹሐንን መንግስት አይገድልም።
* በሺ የሚቆጠሩ ያሏቸው የታጣቂ ቡድኑ አባላት ለመንግስት እጅ ሰጥተው የታሃድሶ ስልጣና እየወሰዱ ነው።
" ለመሆኑ ሰዎች የሚገድሉት በመንግሥት የፀጥታ ኃይል ብቻ ነው ? " በሚል ለኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።
አቶ ለሚ ፦
" ለሚፈፀሙ ለሁሉም ግድያዎች መንግስት ኃላፊነት መውሰድ የሚኖርበት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት ብቸኛው ተቋም እሱ በመሆኑ ነው።
የታጠቀ ኃይል እኮ መንግስት አልሆነም፡፡ የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግስት ነው። " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ባለቤት ዶቼቨለ ሬድዮ እንዲሁም መግለጫው ከኦነግ ማህበራዊ ትስድር ገፅ የተገኘ መሆኑን ይገልጻል።

" ማንኛውም ግለሰብ እኔ ከልጆቼና ከቤተሰቦቼ ጋር እራሴ አወርዳለሁ ካለ #አይገደድም " - የአ/አ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር
በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የማህበር ቤቶች፣ ሪል ስቴት ያሉባቸው አካባቢዎች ላይ ጫኝ እና አውራጆች በሚጠይቁት ያልተመጣጠነ ክፍያና በሚፈጥሩት ግብግብ በርካቶች እንደሚማረሩ ይታወቃል።
" እቃዬን እኔ እራሴ አወርዳለሁ " ሲባልም አንዳንድ ጫኝ እና አውራጆች ከአፃያፊ ቃላት ውርወራ ጀምሮ ለግብግብ እና ፀብ እስከማጋበዝም ይደርሳሉ።
" መንግስት እስካደራጀን ድረስ ባለቤቱ ፈለገም አልፈለገም እቃውን የምናወርደው እኛ ነን " እስከማለትም ይደርሳሉ።
አንዳንዴም እቃዎች እንዲጎዱ ፣ እነሱ ካላወረዱት እዛ አካባቢ ላይ በነፃነት ለመንቀሳቀስ ስጋት እንስከመሆንም ይደርሳል።
በዚህ ላይ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ይቀርፋል፣ ነዋሪዎችንም ከምሬት እና እንግልት ያታደጋል የተባለው መመሪያ ማንኛውም ህገወጥና ነዋሪዎችን የሚያማርሩ ተግባራትን ይከለክላል።
" ግለሰቡ እኔ ከልጆቼ፣ ከቤተሰቤ ጋር ሆኜ አወርዳለሁ ካለ አይገደድም ፤ እራሱ ማውረድ ይችላል። ማህበራቱም እኛ ነን የተደራጀነው ማስወረድ አትችሉም ማለት አይችሉም " ሲሉ አቶ ማስረሻ ሃብቴ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አማካሪ ተናግረዋል።
የባለቤቱን መብት መጠበቅ የማህበራቱ ግዴታ እንዳሆነ ገልጸዋል።
በስምምነት እቃው የሚወርድ ከሆነ ደግሞ ጫኝ እና አውራጅ ማህበሩ ሙሉ ኃላፊነት ለእቃው ይወስዳል ብለዋል።
አቅምን ያላገናዘበ ፣ ከእቃው ጋር ያልተመጣጠነ ክፍያም እንዳይኖር የዋጋ ተመን መውጣቱን አቶ ማስረሻ ገልጸዋል።
" ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ተቀምጦለታል " ያሉት አቶ ማስረሻ " የራሱ የሆነ ርቀት አለው ለምሳሌ ከተሽከርካሪ ከወረደበት 50 ሜትር የመጀመሪያ ዋጋ አለ ከዛ በኃላ እያጨመረ ይሄዳል። ኮንዶሚየም ላይ የሚወጣ ከሆነ እስከ ብሎክ ስር 50 ሜትር ከሆነ ከታች ወደላይ ዋጋው እያጨመረ ይሄዳል። " ብለዋል።
ቢሮው ተግባራዊ ስለተደረገው መመሪያ በጫኝ እና አውራጅ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች እና ማህበራት የ2 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

#አቢሲንያ_ባንክ
ሁሉም የሚመርጠን በምክንያት ነው! ባሉበት ሆነው የአፖሎ ዲጂታል ባንክን በመጠቀም አነስተኛ ብድር ያለምንም ማስያዣ በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ይውሰዱ፡፡
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Apollodigitalbank #loan #apolloloan #instantloan
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ

እስከ 55% የሚደርስ ቅናሽ ከጥሪ ማሳመሪያ ስጦታ ጋር!
ከመደበኛ ጥቅሎቻችን እስከ 55% ቅናሽ የተደረገባቸውን ልዩ የቴሌብር ወርሃዊ የድምጽ እና ዳታ ጥቅሎች ከጥሪ ማሳመሪያ ስጦታ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ (http://onelink.to/fpgu4m) አቅርበናል!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

ፎቶ፦ 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ነው የሚገኘው የተባለው የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት #ወደመጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል።
ፕሮጀክቱ በውስጡ ፦
- በዓድዋ ጦርነት የተሰዉ ጀግኖችን የሚዘክር ሙዚየም፣
- የመዝናኛ ሥራዎች፣
- ካፍቴሪያዎች፣
- ሲኒማ ቤቶችና ሁለገብ አዳራሾችን
- የህፃናት መጫወቻ
- አንድ ሺህ (1000) መኪና ማቆም የሚያስችል ፖርኪንግ
- የንግድ ቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።
የዓድዋ ድል የተበሰረበት ነጋሪት በሙዚየሙ ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን #የአጼ_ምኒልክ እና #እቴጌ_ጣይቱን የሚዘክር ሃውልትም ይቀመጣል ተብሏል።
በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል የተባለው ይኸው ፕሮጀክት የተወሰኑ ሥራዎች ብቻ እንደቀሩት ተገልጿል። በ45 ቀናት ውስጥም ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል ተብሏል።
Credit - AMC & EPA