TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የምንሰጠውን ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማው የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ላይ #ጥብቅ_እርምጃ ይወሰዳል " - ወ/ሪት ራሄል ሃይለ የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ በመቐለ የተደረገው የታክሲ አገልግሎት ማቋረጥና አድማ " ህጋዊ አይደለም " ብሏል። ቢሮው ከመቐለ የትራንስፓርት ፅህፈት ቤትና ፓሊስ በጋራ ' አካሄድኩት ' ባለው ግምገማ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች ቀድም…
#Update

በመቐለ ከተማ በአድማ ምክንያት ለአንድ ቀን ተቋርጦ የነበረው የታክሲ አገልግሎት ዛሬ በከፊል ሲሰጥ ውሏል።

የታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ለአንድ ቀን የጠሩት ስራ የማቆም አድማ " ሰርአት አልበኝነት ነው " ያሉት ተጠቃሚዎች ፤ " መንግስት አፋጣኝና ወቅቱ የሚዋጅ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል " ብለው ነበር። 

ለምለም ኪሓ ፣ ሓወልትና ህዳሴ የተባሉ ሦስት የታክሲ ማህበራት ህዳር 3/2016 ዓ.ም በማህተም አስደግፈው ባወጡት የጋራ መግለጫ የተፈፀመው ስራ የማቆም አድማ " ከእውቅናችን ውጭ የተፈፀመና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው " በማለት ውድቅ አድርገውታል።  

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሪት ራሄል ሃይለ ህዳር 3/2016 ዓ.ም ለሚድያ በሰጡት መግለጫ ፤ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የማቋረጥና አድማ የመምታት ደርጊቱ ችላ ተብሎ የማይታለፍ ህጋዊ እርምጃና ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን በመገንዘብ ስራቸው ይቀጥሉ ዘንድ መክረው ነበር።

የመንግስትን ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማ የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ግን ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉም ምክትል ኃላፊዋ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።

በዚሁ መሰረት የመቐለ ታክሲዎች ህዳር 4/2016 ዓ.ም ከሰአት በኃላ በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
                      
@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ  ህዳር 05-6 /2016 እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ፈተናው በ46 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን ዘጠና ሺ ሰባ ተማሪዎች ለመፈተን ተመዝግበዋል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#StockMarket ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የ ' ስቶክ ማርኬት ' ስራ እንደሚጀመር ተገለፀ። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚጀምረውን የ ' ስቶክ ማርኬት ' ለመደገፍ ከወዲሁ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል። ስቶክ ማርኬት በከፍተኛ ደረጃ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይደግፋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " በጣም ብዙ ሰው ሃሳብ አለው ገንዘብ የለውም፤ ጥቂት ሰዎች ደግሞ ገንዘብ አላቸው ሃሳብ…
#StockMarket

(የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችን በቅርበት በሚከታተሉት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ድረገፅ ከሰጡት ቃለምልልስ የተወሰደ)

ስቶክ ገበያ ምንድነው ?

ለስቶክ ማርኬት ‘ የድርሻ ገበያ ’ የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን።

ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ ያቀርባሉ።

ሰዎች ይህን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነ መጠን ያላቸውን ድርሻ መልሰው በመሸጥ ወይም ከትርፍ ክፍፍል ትርፋማ የሚያደርግ አሠራር ነው።

ስቶክ ማርኬት ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል ?

የስቶክ ገበያ በዋናነኝነት ለኢትዮጵያ የሚከተሉትን ጥቅሞች ይዞ ይመጣል።

1. የካፒታል ገበያ

በርካታ የአገር ውስጥ ባንክ እንዲሁም ኢንሹራንሶች ሲመሠረቱ እና ከምሥረታቸውም በኋላ የአክሲዮን ድርሻዎችን ሲሸጡ ቆይረዋል።

የስቶክ ገበያን ከዚህ የተለየ የሚያደርገው ፤ ይፋዊ በሆነ መልኩ ተደራጅቶ ቁጥጥር እየተገደረገበት በግልጽ መገበያየት ማስቻሉ ነው።

የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ እውን ሲሆን ፤ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች ሲቋቋሙም ሆነ ማስፋፋት ሲፈልጉ አክሲዮን ለመሸጥ ይከተሉት የነበረውን ረዥም መንገድ ያሳጥርላቸዋል።

እነዚህ ኩባንያዎች ሲቋቋሙ ስቶክ ኤክስቼንጅ ስላልነበረ በጣም ረዥም ሂደት በማለፍ ለእያንዳንዱ ሰው እየዞሩ ነው ሼር የሚሸጡት።

ይህ ረዥም ጊዜ እና ገንዘብ ይወስዳል። አዋጭም አይደለም።

የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ አንዱ ጥቅም አዲስ ለመሚሠረቱም ሆነ ለነባር ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን መፍጠሩ ነው።

ካፒታል ማሰባሰብ ለሚፈልጉ ስቶክ ገበያ መልካም አማራጭ ነው።

ጥሩ ሐሳብ ኖሯቸው የካፒታል እጥረት ላለባቸው ሰዎች ይጠቅማል።

ዛሬ ላይ ከባንክ ብድር ማግኘትም ቀላል አይለደም። ለዘመድ ወይም ለጓደኛ ሼር የመሸጥ ሂደት ቀላል አይደለም። ስቶክ ማርኬት አዲስ ለሆኑም ይሁን መስፋፋት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን ይፈጥራል።

2. ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል

የስቶክ ገበያ ፣ ፍትሐዊ እና ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ ሀብት ማከፋፈል የሚችል ሥርዓት ነው።

በአሁኑ ጊዜ ግዙፍ መንግሥታዊ ኩባንያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ እየተሸጋገሩ ነው።

እነዚህ ከመንግሥት ወደ ግሉ የሚዘዋወሩት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሲገዙ የቆዩት ጥቂት ግለሰቦች እና ኮርፖሬሽኖች ናቸው። ስቶክ ማርኬት ሲመጣ ግን መንግሥት የሕዝብን ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከፋፈል ይችላል።

ስቶክ ማርኬት ላይ 1 ሼር በአምስትም፣ በአሥርም ዶላር ሲሸጥ ሁሉም የየአቅሙን በመግዛት ኢትዮጵያ ያካበተችውን ሀብት ማከፋፈል ይቻላል።

እነዚህ ወደ ግሉ ዘርፍ የሚዘዋወሩ ኩባንያዎች ወደ ስቶክ ገበያው ሲገቡ፣ ሁሉም የአቅሙን ያህል ባለቤት ይሆናል። ይህም የሀብት ክፍፍልን ያመጣል።

3. ቁጠባ እና የኢንቨስትመንት አማራጭን ማስፋት

የቁጠባ ባህልን ከፍ ያደርጋል። ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ኪሳራ አያስከትልም ብለው በሚያስቡት ዘርፍ ላይ ብቻ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ይገኛሉ።

ገንዘብ ያላቸው ሰዎች #የቤቶች_ልማት ላይ ብቻ ትኩረት ሲያደርጉ ይታያል። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ደግሞ ተጎድቷል። ይህም ኢንቨስት የሚደረግባቸው ዘርፎችን ውስን በማድረግ የቁጠባ አለመመጣጠን ይፈጥራል።

ስቶክ ማርኬቱ ግን ውጤታማ በሆነ መንገድ ካፒታል በሁሉም ዘርፎች ላይ ማሰራጨት ያስችላል።

4. ግልጽነት

የድርሻ ገበያዎችን በቀላሉ፣ ግልጸኝነት በሰፈነበት መልኩ መግዛት እና መሸጥ ማስቻሉ ነው።

ምን ያህል ሼር በምን ያህል ዋጋ ለገበያ እንደቀረበ ግልጽ ነው።

ሰዎች ስልካቸው ላይ በሚጭኑት መተግበሪያ በቀላሉ የገበያ ድርሻዎችን መግዛት እና የገዙትንም መሸጥ ይችላሉ።

የባንክ ባለ አክሲዮኖች ዓመት ጠብቀው ትርፍ ከመከፋፈል ውጪ በቀላሉ ያላቸውን አክሲዮን መሸጥ አይቻላቸውም።

ስቶክ ማርኬት ሲሆን በቀላሉ አክሲዮን የመሸጥ ዕድል ይዘረጋል።

በስቶክ ገበያ ትርፍና ኪሳራ እንዴት ያጋጥማል ?

ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ስቶክ ገበያ ምንድን ነው ? እንዴትስ መሸጥ እና መለወጥ ይቻላል ? የሚለውን እንመልከት።

ስቶክ ገበያን በቀላል ቋንቋ ለመረዳት የምጣሄ ሀብት ባለሙያዎች አዘወትረው የሚጠቀሙትን ቀላል ምሳሌ እንውሰድ። 'ሀ'፣ 'ለ' እና 'ሐ' የሚባሉ ሦስት ምናባዊ የሞባይል ስልክ አምራች ኩባንያዎችን አሉ አንበል።

እርስዎ 6 ዶላር አውጥተው ከእያንዳንዱ ኩባንያ የሁለት ዶላር የገበያ ድርሻ ይገዛሉ።

'ሀ' ለገበያ ያቀረበው ሞባይል ስልክ ባትሪ እየፈነዳ ሰዎችን ለጉዳት እየዳረገ መሆኑን የሚያመለክት ሪፖርት መውጣት ይጀምራል።

የ'ለ' ኩባንያ የሆነው ምርት ደግሞ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ከተጠቃሚዎች ቅሬታ ይደርሰዋል።

የ'ሐ' ምርት የሆነው ሞባይል ስልክ ግን በአግባቡ ይሠራል።

ይህ በገበያ ላይ ያጋጠመው ክስተት በሦስቱ ኩባንያዎች ስቶክ ገበያ ዋጋ ላይ ለውጥ ያመጣል። የአንድ ኩባንያ ምርት ጥራት ሲወርድ የዚያ ኩባንያ ፈላጊዎች ይቀንሳሉ።

በተቀራኒው አንድ ኩባንያ ትርፍማ የሚያደርገውን ውሳኔ ወስኖ ትርፍ ሲያጋብስ፣ የትርፉ ተቋዳሽ መሆን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከፍ ይላል።

በዚህ መሠረት ባትሪው እየፈነዳ ሰዎችን ለአደጋ እያጋለጠ ያለው የሞባይል ኩባንያ ድርሻ በከፍተኛ መጠን ሊወርድ ይችላል።

በሁለት ዶላር የገዙትን ድርሻ መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ ከግማሸ ባነሰ ዋጋ እንኳን የሚገዛዎትን ላያገኙ ይችላሉ።

ይህ ሞባይል አምራች ኩባንያ ሲከስር እርስዎም የኩባንያው ባለድርሻ እንደመሆንዎ ኪሳራ ያጋጥምዎታል።

ስለዚህ በኩባንያ 'ሀ' ላይ ያደረጉት ኢንቨስትመንት ኪሳራን ያስከትላል።

የ 'ሐ' ምርት የሆነው ስልክ ግን በገበያ ተፈላጊነቱ ሲጨምር የኩባንያው ዋጋም ከፍ ይላል።

ምናልባት በሁለት ዶላር የገዙትን የኩባንያውን ድርሻ፣ አሁን ላይ በ4 ዶላር ሸጠው ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ።

@tikvahethiopia
" የተደፈረችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት " - ብፁዕነታቸው

ድርጊቱ የተፈፀመው ህዳር 1 ቀን ምሽት ላይ ነው።

መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ የቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ በደብሩ ለሁለት ቀን በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ኅዳር 1 ምሽት ጉባኤው ተጠናቆ ምዕመናን ሲባርኩ " ማንነቱ ባልታወቀ " ግለሰብ በጥይት ተመተዋል።

በኃላም ወደ ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ገብተዋል። በአሁን ሰዓትም በህክምና ክትትል ላይ ናቸው።

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተፈፀመው ድርጊት " የተደፈረችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት " ብለዋል።

ብፁዕነታቸውን ይህን ያሉት መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ በሆስፒታል ተገኝተው ከጎበኙ በኃላ ነው።

ሀገረ ስብከቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እንደሚነጋገር የገለፁት ብፁዕነታቸእ " ለአገልጋዮች ነገ ዋስትና እንዲኖራቸው መሠራት አለበት " ሲሉ አስገንዝበዋል።

በተፈጸመው ድርጊት የተደፈረችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናትም ብለዋል ብፁዕነታቸው።

ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን በፖሊስ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

@tikvahethiopia
#Update #USAID

የአሜሪካ መንግሥት በዓለም አቀፉ የተርድዖ ድርጅቱ USAID አማካኝነት በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካቢዎች ለሚገኙ ሰዎች ያቀርበው የነበረውና አቋርጦት የነበረውን የምግብ እርዳታ ከ15 ቀናት በኋላ ዳግም ሊጀምር እንደሆነ አስታውቋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ስታቀርብ የቆየችው የምግብ እርዳታ ላልተገባ ዓላማ እንደዋለ ከገለጸች በኋላ ማስተካከያ እስከሚደረግ በሚል በሁሉም አካቢዎች የነበረውን የምግብ እርዳታ ባለፈው ዓመት አቋርጣ ነበር።

USAID ትናንት  ባወጣው መግለጫ ተቋርጦ የቆየው እርዳታ ከኅዳር 21/2016 ጀምሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ድርጅቱ የምግብ እርዳታው ላልተገባ አላማ እንዳይውል ያደረገውን ማሻሻያ በቀጣዩ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙከራ ይደረግበታል ብሏል።

በዚህ የሙከራ ጊዜ በUSAID ፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በአጋሮች የሚተገበረውን የአዲሱን አሰራር ውጤታማነት በተከታታይ እንደሚቆጣጠርና እንደሚገመግም አስታውቋል።

በኢትዮጵያ አቋርጦት የቆየውን እርዳታ ለመጀመር ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችና ድርድር ሲደረግ መቆየቱን USAID ገልጿል።

አዲሱ አሰራር የእርዳታ ተደራሽነትን ለመቆጣጠርና ለመከታተል ያግዛል የተባለ ሲሆን ይህንኑ አሰራር ለመተግባር የሚያስችል ለውጦች ለማደረግ የኢትዮጵያ መንግሥት መስማማቱን ተገልጿል።

በተጨማሪ መንግሥት ያልተስተጓጎለ የእርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት ለመፍቀድ ቁርጠኛ ነው ብሏል።

(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር 6 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሬሜዲያል ተማሪዎችን እንደማያስተናግዱ አሳወቀ።

በ2015 ዓ.ም  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲያስተካክሉ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ፦
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ
6. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ መሆኑን አሳውቋል።

Via MoE / @tikvahuniversity
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ይጠቀሙ!!

ወደ ባንክ መሔድ ሳያስፈልግዎ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የኢንተርኔትና የሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ጊዜና ገንዘብዎን ይቆጥቡ ፡፡

መተግበሪያውን ከፕሌይስቶር ላይ ለማውረድ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ። https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ofss.dgbb

USSD *9335# በአማራጭነት መጠቀም ይችላሉ

ለተጨማሪ መረጃና አገልግሎት የባንካችንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ፦https://t.me/Globalbankethiopia123

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን !!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia

የ07 ቅምሻ ኮንሰርት መግቢያውን በ250 ብር በM-PESA ሳፋሪኮም አፕ ፤ በአጭር የጥሪ ኮድ *733# ወይም ከM-PESA ሳፋሪኮም ሱቆች ሲገዙ የከፈሉት 250 ወደ M-PESA አካውንትዎ ተመላሽ ከመሆኑም በተጨማሪ ነፃ የ5GB የሳፋሪኮም ዳታ ጉርሻ ያገኛሉ።

መግቢያውን በM-PESA ሳፋሪኮም ሱቆች ማግኘት ይችላሉ።
በዕለቱ የ07 ቅምሻ ኮንሰርት መግቢያ በር ላይ 500 ብር ነው። ኮንሰርቱ ላይ እንገናኝ!

ፕለይ ስቶር/ አፕ ስቶር - https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
ጋዜጠኛው ለሰዓታት ከታሰረ በኃላ ተለቀቀ።

የቀድሞ የቢቢሲ ሬድዮ የትግርኛ ፕሮግራም ባለደረባ ጋዜጠኛ ደስታ ገ/መድህን ህዳር 4/2016 ዓ.ም ምሽት 4:00 ሰዓት አከባቢ ከታሰረ በኃላ ዛሬ ማምሻውን መለቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

ጋዜጠኛ ደስታ ገ/መድህን ለእስር የተዳረገው ህዳር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመቐለ በመካሄድ ላይ ያለውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ፤ የህወሓትና የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ጥምር ስብሰባ አስመልክቶ "ሬድሲ ኦቭዘርቨር" ለተባለ የዩቱብ ቻናል ካስተላለፈው ዘገባ በኃላ ነው። እስሩም ከዚህ ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ተነግሯል።

ይህንኑ መረጃ የጋዜጠኛ ደስታ ገ/መድህን ባለቤት ወ/ሮ ወይኒ ኣብራሃ አረጋግጣለች።

" ትናንት ህዳር 4/2016 ዓ.ም ደስታን በቅርበት የሚያውቀው ሰው በስልክ ደውሎ ሊያገኘው እንደሚፈልግ ነገረው፤ ከዛ በኃላ የደስታ ሞባይል ሊሰራልኝ አልቻለም። ዛሬ ህዳር 5/2016 ዓ.ም ጠዋት ተደውለሎኝ ወደ ታሰረበት ቦታ ሄጀ አገኘሁት። Red Sea Observer ለተባለ ዩቲዩብ ቻነል በሰራው ዘገባ እንዳሰሩት ለማወቅ ችያለው..." ስትል ገልጻለች።

ጋዜጠኛው ሰዓታትን ካፈጀ እስር በኃላ ማምሻውን ምንም ክስ ሳይመሰረትበት መለቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

ምንም እንኳን ከእስር ቢለቀቅም ስልኩ፣ ላፕቶፑ እና የማስታወሻ ደብተሩ በፖሊስ እጅ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ለጋዜጠኛው የእስር ምክንያት ሊሆን ይችላል የተባለው የድምፅ መረጃ አግኝቶ አዳምጦታል።

ለ "Red sea Observer" የትግርኛ ከፍል እንደተሰራ የሚያትተውና በራሱ በጋዜጠኛ ደስታ ገ/መድህን ድምፅ በትግርኛ ቋንቋ የተነበበው ዘገባ ከአንድ ቀን በፊት ህዳር 4/2016 ዓ.ም ወደ ዩቲዩብ የተጫነ ሆኖ 10 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ርዝማኔ አለው።

ይህ " የህወሓትና ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ አመራርሮችና አዛዦች ምን ተወያዩ ?" በሚል የጥያቄ ርእስ የተሰጠው ዘገባ የህወሓትና ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ አመራሮችና አዛዦች በወቅታዊው የቀይባህር ወደብ አጠቃቀም ዙሪያ በፅሁፍ የተደገፈ ጥልቅ ወይይት ማካሄዳቸው ያትታያል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ፤ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችና የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ አመራሮች ጥምር ስብሰባ ህዳር 2/2016 ዓ.ም ጀምሮ በዝግ በመካሄድ ላይ ሲሆን እስከ አሁን ስለስብሰባው ለሚድያ የቀረበ ይፋዊ መረጃ የለም።

አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩና በህወሓተ የተዘጋጁ ፅሁፎች ቀርበው ወይይት እየተካሄደባቸው እንደሆነ ቢገልጹም፥ ስለ ጹሁፎቹ ይዘት በሚመለከት ያሉት ነገር የለም።

ጋዜጠኛ ደስታ ገ/መድህን በ2013 ዓ.ም ቢቢሲ ሬድዮ የትግርኛ ፕሮግራም ለቆ ወደ ትግራይ ሃይሎችን ተቀላቅሎ የነበረ ሲሆን፥ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ ድግሞ ለተለያዩ አለምአቀፍ ሚድያዎች የዘገባና የማስተባበር ስራ ሲሰራ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ያጠናከረው መረጃ ያመለክታል።

* ጋዜጠኛውን አግኘትን አነጋግረን አስተያየት ካለው የምናቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia
የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ወደ ቲክኒክና ሙያ መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ የመግቢያ ነጥቡን ይፋ ያደረገው ረቡዕ ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ላምበረት በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

መግለጫውን የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 5 የመቁረጫ ነጥብ ወንድ ከ218፣ ሴት 199 በላይ፣ የታዳጊ ክልል (የአርብቶ አደር አካባቢዎች) ወንድ ከ192፣ ሴት 187 በላይ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ (ሁሉንም ክልሎች ታሳቢ ያደረገ ነው)  ብለዋል።

ደረጃ 3 እና 4 ወንድ ከ173፣ ሴት 163 በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ ከ157፣ ሴት 156 በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ነው ተብሏል።

ተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 1 እና 2 ወንድ 172፣ ሴት 162ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 156፣ ሴት 155ና ከዚያ በላይ ነው።

ማኅበራዊ ሳይንስ ደረጃ 5 ወንድ 179፣ ሴት 170ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 166፣ ሴት 162፣ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ ነው።

ደረጃ 3 እና 4 በማኅበራዊ ሳንይንስ ወንድ 149፣ ሴት 147፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 138፣ ሴት 137ና ከዚያ በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ሆኗል።

ደረጃ 1 እና 2 በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 148፣ 146፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 137፣ ሴት 136፣ አካል ጉዳተኞች 129ና ከዚያ በላይ መሆኑን አስረድተዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም፣ "በ2016 ዓ.ም 844 ሺሕ 384 የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደዋል። ከእነዚህ ውስጥ በእኛ ምልከታ 632 ሺሕ 587 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ይመጣሉ የሚል ግምት አለን" ነው ያሉት።

የሰው ሃይል ለመቀበል የተሻለ ዝግጁነት አላቸው ያልናቸውኝ የመንግሥትና የግል የቴኪኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን ፈትሸናል ያሉት ሚኒስትሯ፣ እስካሁን ባለው ከ28 ሺህ በላይ የሚሆኑ አሰልጣኞች፣ ወደ 1ሺሕ 400 ገደማ የተሻለ ብቃት ያላቸው ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሉ ብለዋል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
ሰላም ይስበኩ፤ ይሸለሙ!

ዝርዝር መረጃዎችን ይመልከቱ - https://www.cardeth.org/am/peace-messaging
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

ቅዳሜ ህዳር 08 2016 ዓ.ም 12ኛ ዙር የግራፊክስ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ይጀምራል። ቀድመው ይመዝገቡ!
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ15 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ

Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
#MoH

የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና ምዝገባ ተጀመረ።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ2016 የትምህርት ዘመን በ21 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች አመልካቾችን ተቀብሎ እንደሚያሰለጥን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና /ERMP/ መግቢያ ፈተና በመስጠት አወዳድሮ እንደሚያሰለጥን የገለፀ ሲሆን የህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ያላቸውና የስፔሻሊቲ ስልጠና መውሰድ የሚፈልጉ ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጿል።

ምዝገባው ከዛሬ ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ /ም የሚጀምር ሲሆን ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚያበቃ አሳውቋል።

አመልካቾች የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ www.moh.gov.et/ermp ላይ በመግባትና ለመሰልጠን በሚፈልጉት የስፔሻሊቲ ትምህርት ላይ በመመዝገብ መወዳደር እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተመዝጋቢዎች ምዝገባውን ከመጀመራቸው በፊት ዝርዝር መረጃዎችንና መመሪያዎችን በዚህ ይመልከቱ ተብሏል👇
https://www.moh.gov.et/site/initiatives-4-col/ermp

@tikvahethiopia