TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤት በምን ይታያል ? " ነገ ጥዋት 12 ሰዓት ላይ በዌብሳይት እና በSMS ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይቻላሉ። " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ @tikvahethiopia
#ሙሉ_መግለጫ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የሰጠው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጥዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታትሎ መረጃዎችን ያደርሳል።

More - @tikvahuniversity @tikvahethmagazine

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት።

ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው።

ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። "

ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ?

- በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
• ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

- በማታ የተፈተኑ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

- በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

- በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

- በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ

" በጸጥታ ችግር በሙሉና በከፊል የወደሙ 287 ትምህርት ቤቶች ለ2016 የትምህርት ዘመን ጥገና ያስፈልጋቸዋል" ሲል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዘነበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "በጸጥታ ችግር በሙሉና በከፊል የወደሙ 287 ትምህርት ቤቶች ለ2016 የትምህርት ዘመን ጥገና ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል።

"እንደሚታወቀው ክልሉ ከዚህ በፊት መተከልና ከማሽ ዞኖች አካባቢ የነበረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ በሙሉና በከፊል የወደሙ ትምህርት ቤቶች አሉ" ያሉት አቶ ምትኩ፣ "እነዚህን ትምህርት ቤቶች መልሶ የመገንባት አሁን ማኅበረሰቡ የጀመረው ሥራ አለ። መንግሥትም ደግሞ ራሱን አስችሎ ከባለ ሃብቶች፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ ትምህርት ቤቶችን የመጠገን ሁኔታ አለ" ሲሉ ተናግረዋል።

ወደሙ የተባሉት ተቋማት የት አካባቢ እንደሆነ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም፣ በከማሽ፣ መተከል ዞኖች እዲሁም በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ መሆኑን ገልጸው፣ የወደሙት ትምህርት ቤቶች ብላክ ብርድ፣ ወንበር፣ ቤተ መጻሕፍት፣ አጋዥ መጻሕፍት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ውድመቱን ተከትሎ ምን ያህል ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ እንዲገልጹ ላቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ምትኩ፣ "ወደ 50ሺሕ ገደማ ሕፃናት ናቸው በዚህ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑት" ብለዋል።
50 ሺሕ ገደማ ሕፃናት ሲባል በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ ቤተሰቦቻቸው በኢኮኖሚ ችግር ላይ በመሆናቸውና አብዛኛዎቹ ግን በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ናቸው ሲሉ አክለዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ደረሰ ከተባለው የትምህርት ቤቶች ውድመት በተጨማሪ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶች በመውደማቸው 2.4 ሚሊዮን ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን፣ 1,218 ትምህርት ቤቶች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ቢከፈቱም 722ቱ እንዳልተከፈቱ መረጃዎች የክልሉ ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ወቅቶች ሲገልጽ ተስተውሏል።

በአፋር ክልል ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ 65 ትምህርት ቤቶች አምስቱ መልሶ ግንባታ እንደተደረገላቸው፣ በከፊል ከወደሙት 694 ትምህርት ቤቶች መካከል 34ቱ እንደተጠገኑ እንዲሁም በ2016 የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከታቀደው 245 ሺሕ ተማሪዎች እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የተመዘገቡት 126 ሺሕ ተማሪዎች መሆናቸው ተመላክቶ ነበር።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-09

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ውጤት እንዴት መመልከት ይቻላል ?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በዌብ ሳይት 👉 https://eaes.edu.et/

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም 👉 https://t.me/eaesbot

#MoE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ብስክሌት፣ የባለ አራት እግር እና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት አንስቶ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ተጣለ። የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ለሞተር ብስክሌተኞች፣ የባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ ባሰራጨው መልዕክት ከዛሬ መስከረም 14/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም…
#እንድታውቁት

በሞተር ብስክሌት፣ በባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ከማክሰኞ መስከረም 29 /2016 ጀምሮ ተነስቷል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፍቃዱ የሚመለከታቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው ፤ የሞተር ሳይክሎችም በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ህጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ (GPS) ያስገጠሙትን ብቻ ነው ብሏል።

ከትራንስፖርት ቢሮው ህጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከጥዋት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

የ2015 የትምህርት ዘመን ፈተና ውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው eaes.et ላይ እስከ ጥቅምት 5/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ብቻ ማቅረብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ብቻ ሳይሆን ኦርጂናሉ ሠርቲፊኬት እስኪደርሳቸው ድረስ ጊዜያዊ ሠርቲፊኬታቸውን በሶፍት ኮፒ መውሰድ አልያም ማተም እንደሚችሉ አገልግሎቱ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከጥዋት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ። የ2015 የትምህርት ዘመን ፈተና ውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው eaes.et ላይ እስከ ጥቅምት 5/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ብቻ ማቅረብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ብቻ ሳይሆን ኦርጂናሉ ሠርቲፊኬት…
#Result

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ሲል ገልጿል።
    
👉 በዌብ ሳይት፡- eaes.et
👉 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
👉 ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል " ውጤት እንገልጻለን " ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

እንዴት ውጤት ልመልከት ?

በዌብ ሳይት ለማየት ፦

1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፦

1. 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በመላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።

በቴሌግራም ቦት ፦

1. @eaesbot ይፈልጉ

2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ፡፡

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አፖሎ ለደንበኞች አነስተኛ ብድር ያለምንም ማስያዣ በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ መስጠት መጀመሩን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ብድሩን ለማግኘት የአፖሎ መተግበሪያዎን ያዘምኑ (update)
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/BoAEth/1018
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተፈታኞች ከሚያስቀጣ ተግባር ተቆጥባችሁ ተረጋግታችሁ ተፈተኑ " - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።  ፈተናው ነገ መስከረም 29 ጀምሮ ጥቅምት 2 ይጠናቀቃል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለፈተናው አስፈላጊው ሁሉ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን በይፋ አሳውቋል። የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ለትግራይ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት…
በትግራይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል።

9 ሺህ 514 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

6 ሺህ 513 ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሲሆን 3 ሺህ 1 የሚሆኑት ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው፡፡

ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በመቐለ ፣ በኣክሱም፣ በዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ነው።

Via Tigray Television

@tikvahethiopia