TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

ቅዳሜ የሚከበረው " #የኢሬቻ_ሆራ_ፊንፊኔ በዓል " ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

ከነገ ዓርብ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቅ ድረስ ፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ

- ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ

- ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

- ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

- ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ

- በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ

- ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ

- ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  አትላስ ሆቴል አካባቢ

- ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ  የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

- ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ

- ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ

- ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ

መንገዶች ከነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52- 63-02/03 ፣ 011-542-40-77፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987 ፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀም እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በዚሞል፣ በዴልቨር አዲስ ወይም በትኩስ ዴሊቨሪ ምግብ አዘው ለመክፈል ሲዘጋጁ ድንገት እጅዎ ላይ ካሽ ባይኖር ምን ያደርጋሉ? አቢሲንያ ባንክ ሁሌም ባለ መላ ነው። በቪዛ ካርድዎ ላይ ከፊት እና ጀርባ የሚገኘውን ቁጥር ብቻ በመጠቀም ክፍያዎን ኦንላይን መፈጸም ይችላሉ።
አጠቃቀሙን ለማየት የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/BoAEth/1018
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) የተፈታኞች ምዝገባ ዛሬ ያበቃል።

GAT ለመውሰድ የማመልከቻው ጊዜው ዛሬ መስከረም 25/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 እንደሚያበቃ ይጠበቃል።

በቀሩት ሰዓታት በ https://portal.aau.edu.et የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖርታል ላይ በመግባት ምዝገባ ማድረግ ይቻላል።

በተያያዘ ከመስከረም 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የድህረ ምረቃ የመለማመጃ የመግቢያ ፈተና (Mock Exam) ዛሬ እንደሚያበቃ ይጠበቃል።

ዋናው የመግቢያ ፈተናው ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል ፦ Mock Exam (ዲላ እና ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ)

Via @tikvahuniversity
#USAID #ETHIOPIA

የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ተራድ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ አቋርጦት ከቆየው የምግብ እርዳታ ውስጥ ለስደተኞች የሚሰጠውን ድጋፍ መልሶ ለመጀመር ወስኗል።

የምግብ እርዳታ አቅርቦትን መልሶ ለመጀመር የተደረሰው ውሳኔ ሁሉንም የእርዳታ ፈላጊዎች የሚመለከት ሳይሆን ለስደተኞች የሚደረገውን እርዳታ ብቻ መልሶ በመጀመር ላይ ያተኮረ ነው።

ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው የኢትዮጵያ መንግሥት እና አጋሮቹ የስደተኞች የምግብ እርዳታ አቅርቦት መዋቅር ላይ ለውጦችን በማድረጋቸው ነው ብሏል።

" የኢትዮጵያ መንግሥት የስደተኞች የምግብ እርዳታን የማጓጓዝ፣ የማከማቸት እና የማሰራጨት ኃላፊነትን ለሌሎች አጋሮች በማስተላለፉ " እርዳታውን ለመጀመር ወስነናል ብሏል።

በእርዳታ ስርጭቱ ላይ የተደረገው ለውጥ አቅርቦቶችን በትክክል ለተጠቃሚዎች መድረሳቸውን ለመቆጣጠር በሚያስችል ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል።

የእርዳታ ምግብ እደላው በፍጥነት የሚጀመረው ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ በሚገኙት 28 የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ለተጠለሉ ስደተኞች ነው።

ድርጅቱ " የምግብ እርዳታ በሚያስፈልግባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ድጋፉ ለታለመላቸው ተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ማረጋገጫ አስክናገኝ ድረስ ተቋርጦ ይቆያል " ብሏል።

የምግብ እርዳታው ቢቋረጥም የጤና እና የአልሚ ምግቦች እርዳታዎችን ጨምሮ ሌሎች የአሜሪካ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦቶች ግን ይቀጥላሉ ተብሏል።

USAID የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚያደርገው ድጋፍ ለታለመላቸው ተጠቃሚዎች ብቻ እንደሚደርስ ማረጋገጫ እስከሚያገኝ ድረስ እንደማይጀምር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም " - ነዋሪዎች

በአማራ ክልል ባህር ዳር እና ጎንደር ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ነዋሪው የዋጋ ንረቱን መቋቋም አልቻለም።

የባህር ዳር ነዋሪው አቶ አለሙ ይርዳው ባለፈው ሳምንት ጤፍ ለመግዛት ወደ ገቢያ በወጡበት ወቅት ከወር በፊት በ10 ሺህ ብር የገዙት ጤፍ በሺዎች ብር ጨምሮ እንዳገኙት ገልጸዋል።

እኚሁ ነዋሪ ከ6 እና 7 ወር በፊት አንድ ኩንታል ጤፍ 6,700 ብር ገደማ መግዛታቸውን አስታውሰው አሁን 13,000 ብር መባሉን ገልጸዋል።

" በጣም ደንግጫለሁ ፤ ከእጥፍ በላይ ነው የጨመረው ዝቅተኛው ጤፍ 11 ሺህ 500 እና 12 ሺህ 500 ነው የሚባለው እኔ የገዛሁት 13 ሺህ ብር ነው " ብለዋል።

ለምን በዚህ ልክ እንደጨመረ ነጋዴዎችን ጠይቀው የተሰጣቸው ምላሽ " ከትራንስፖርት አንፃር አቅርቦት የለም ፣ በየቀኑ መንገድ ይዘጋል " የሚል እንደሆነ ገልጸዋል።

ከጤፍ በተጨማሪ ሽንኩርት አንድ ኪሎ 110 ብር እንደገዙ አመልክተዋል። ቲማቲምን ጨምሮ ሌሎችም የዕለት ዕለት ግዢዎች ላይ ዋጋ ጨምሯል ብለዋል።

" 13 ሺህ ብር ጤፍ ተገዝቶ እንዴት መኖር እንደሚቻል አይገባኝም ፤ በተለይ መካከለኛ እና ዝቅተኛ እንደኔ አይነት ገቢ ያላቸው የወር ደሞዝተኞች መኖር የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። " ሲሉ አክለዋል።

ይህንን እየፈጠረ ያለው አንደኛው ወቅታዊው የመንገድ መዘጋት ነው ፤ በተጨማሪ ስግብግብ ነጋዴዎች ወቅቱን ተጠቅመው ሰው እንደተቸገረ አውቀው በከፍተኛ ዋጋ እየሸጡ በመሆኑ ነው ብለዋል።

አማራ ክልል በተለይ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ጤፍ አምራች ቢሆንም የአካባቢው ነዋሪ በዚህ ዋጋ ለመሸመት መገደዱ አስደንጋጭ ነው ያሉ ሲሆን ለዚህ ምክንያት እየሆነ ያለው ግጭት በፍጥነት ካልቆመ ህዝቡ በኑሮ ይጎዳል ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገልፅ ያልፈለጉ ከምዕራብ ጎጃም አዴት እና ጎንጂ ቆለላ ጤፍ አምራች አካባቢዎች ጤፍ እያመጡ የሚሸጡ ነጋዴ ፤ በወቅታዊ ግጭት ምክንያት አርሶ አደሩ ምርቱን ወደገበያ እንደማያወጣ ገልጸዋል።

" አርሶ አደሩ በሰላም ውለን መግባት ስላልቻልን ምርቱን እያወጣ አይደለም። ነጋዴው ደግሞ ያገኘውን ይዞ ይመጣል " ብለዋል።

እኚሁ ነጋዴ ጤፍ 12 ሺህ ብር እየሸጡ እንደሆነ ተናግረዋል።

የጎንደር ነዋሪ የሆኑት ይፍቱ ስራማረው ፤ የዋጋ ንረቱ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው ብለዋል።

" እውነት ለመናገር እንኳን በሁለት ዓመት ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ እንኳን ከፍተኛ ጭማሪ ነው ያለው። 30 እና 20 ብር ስንገዛው የነበረው እቃ አሁን 100 ቤት ውስጥ ነው።

ሽንኩርት ከግርግሩ በፊት ከ50 - 55 ብር ነበር አሁን ሱቅ ውስጥ እስከ 120 ብር ዋና ገበያ እስከ 80-100 ብር ይሸጣል።

ሞኮሮኒ ፓስታ ከአንድ ወር በፊት ነው የጨመሩት የ20 ብር ጭማሪ አለው ፤ ጤፍ 115 ብር - 120 ብር ይባላል በኪሎ ፤ አቅርቦትም ስለሌለ ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

አዘዞ ከተማ የሚኖሩት የችርቻሮ  ነጋዴዋ ወ/ሮ አለሚቱ ደሴ ፤ ጤፍን ጨምሮ ሌሎች እህሎች ተወዷል ብለዋል።

" የገበያው ሁኔታ በጣም ከባድ ነው ለሻጭም ለገዢም ... ቀይ ጤፍ 90 ብር ነው ፣ ነጭ ጤፍ  100 ብር አሁን ላይ ነው በጣም የጨመረው 60 እና 70 ብር ነበር ፤ ግጭት ከጀመረ አንስቶ እስከ 100 ብር ገብቷል።  ሽንኩርትም እስከ 100 ብር እየተሸጠ ነው። " ብለዋል።

እህል እየተቀበሉ ያሉት የገጠሩ ማህበረሰብ ይዞ ሲመጣ እነድሆነ የገለፁት ወ/ሮ አለሚቱ " ባለው ችግር የገጠሩ ነዋሪዎች እንደልባቸው መንቀሳቀስ አልቻሉም " ሲሉ ገልጸዋል።

https://telegra.ph/VOA-10-06

መረጃው ከቪኦኤ ሬድዮ የተወሰደ ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም #ቴሌብር

በፍቅር እና በደስታ የተሞላ ልዩ የኢሬቻ በዓል እየተመኘን፤ እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ያዘጋጀናቸውን የኢሬቻ የሞባይል ጥቅሎች ከሰፊው ገበታችን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም በ*999# ለራስዎ ይግዙ፤ ለሚወዷቸው በስጦታ ያበርክቱ!

መልካም በዓል!
TIKVAH-ETHIOPIA
#የፀጥታ_ችግር ዘላቂ ሰላም ያልተገኘለት እና ዛሬም ድረስ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው ቀጠና መፍትሄው ምንድነው ? • ከ2010 ዓ/ም አንስቶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ንብረት ወድሟል። እርቅ ለመፈፀም ተሞክሮ ዘላቂ ሰላም አልመጣም። • ከሰሞኑ በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል ፤ እርቅ ለመፈፀም ጥረት እየተደረገ ነው። • ዛሬ ወደ ገበያ በሚያቀኑ ሰዎች…
#ማረቆ #መስቃን

- " እስከ 2,868 የቤተሰብ አባላቶች የተፈናቀሉበት ሁኔታ ነው ያለው " - የምሥራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር

- " አንድ ቤተሰብ ላይ ተሰብስበው ቡና እየጠጡ ወደ ሰባት ሰው ተመትቷል። እናትና ልጅ ሞትዋል " - የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳደር

- " ጉዳዩን በተመለከተ ግምገማ እየተደረገ ነው ሲጠናቀቅ እናሳውቃለን " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

በመስቃንና ማረቆ ብሔረሰብ መካከል በተፈጠረው ግጭት " እስከ 2,868 የቤተሰብ አባላቶች የተፈናቀሉበት ሁኔታ ነው ያለው" ሲሉ የምሥራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ጀማል አወል ገለጹ።

ዋና አስተዳዳሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " አሁን በቅርቡ ባለን መረጃ መሠረት ከማረቆ ልዩ ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች እስከ 2,868 የቤተሰብ አባላቶች የተፈናቀሉበት ሁኔታ ነው ያለው " ብለዋል።

ግን በሁለቱም ወረዳዎች ደግሞ የሁለቱ ም ብሄሮች ተሰባጥረው በሰላም የሚኖሩበት ሁኔታ ስላለ የብሄር ግጭት ነው ለማለት ያስቸግራል ያሉት አቶ ጀማል፣ "ችግር በተፈጠረባቸው አካቢባቢዎች ግን ተፈናቅለው ወደ ምሥራቅ መስቃንና ሌሎች አካባቢዎች የመጡ አሉ " ሲሉ አክለዋል።

" #ከጥር_7_ቀን_2014 ዓ.ም ወዲህ ( እርቀ ሰላሙ ከተፈጸመ በኋላም ) ከ34 ያላነሱ ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ተፈጽሞ ለሞት የተዳረጉበት ሁኔታ አለ። በሁለቱም ወገን ሰው እየሞተ ነው " ብለዋል።

" መስቃንና ማረቆ አካባቢ ያለው ግጭት 4 ዓመታትና ከዚያ በላይ ያስቆጠረ ግጭት ነው " ያሉት አቶ ጀማል " በሕዝብና ሕዝብ መካከል የነበሩ አለመግባባቶች በአካባቢው ባህል መሠረት ጥር 7 ቀን 2014 ዓ.ም ግጭቱ የተፈታበት ሁኔታ ነበር። ከዚያ በኋላም በጣም የተሻሻሉ ሁኔታዎች ነበሩ። በሒደት ግን አንዳንድ እርቀ ሰላሙ እንዲጸና የማይፈልጉ አካላት በተለያዩ ጊዚያቶች ግለሰቦች፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች፣ ሕጻናት፣ ፖለቲካውን በቅጡ የማያውቁ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃቶች እያደረሱ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ግጭቱ እንደገና አገርሽቷል " ነው ያሉት።

ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል የግጭቱን ዋነኛ ምክንያት እንዲያስረዱ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ለውጡን ተከትሎ የመልካም አስተዳደር ችግርን አሳበው በሚነሱ ጥያቄዎችን ሽፋን አድርገው ሁለቱን ብሄረሰቦች ቅራኔ ውስጥ ያስገቡ አካላቶች አሉ " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት በተለይ ከእርቀ ሰላሙ በፊት ከሁለቱም ወገኖች ወደ 86 ሰዎች የሞቱበት ሁኔታዎች ናቸው ያሉት " ሲሉ አክለዋል።

" በማረቆ ወንድሞች ወገን ዘጠኝ / 9 ቀበሌዎች ወደ ምሥራቅ መስቃን ወረዳ ተከልለውብናል በሚል የሚነሱ ጉዳዮች አሉ" ያሉት አቶ ጀማል፣ "ዞሮ ዞሮ ዋነኛ መነሻው ግን እነዚህ ቀበሌዎችን መሠረት ያደረገ አይደለም በእኔ እምነት " ሲሉ ገልጸዋል።

የቀበሌ ጥያቄዎች ካሉ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ሳይሆን በሕግ አሰራር መቅረብ ይችል ነበር ብለው፣ ዋነኛው ምክንያቱ ግን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ግጭቱ እንዲፈጠርና እንዳይቆም ይፈልጋሉ ያሏቸው የታጠቁ አካላትን ተወቃሽ አድርገዋል።

አክለውም ፣ " የፖለቲካ ቁማሮች በመሠረታዊነት አሉ። ከዚያ ባሻገር ጥቅማቸው ይቀርብናል ብለው የሚያስቡ የታጠቁ አካላቶች ይህ ግጭት እንዳይቆም የሚጥሩበት ሁኔታዎች አሉ " በማለት ተናግረዋል።

ችግሩን እንዲቆም ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲጠየቁም፣ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችን በተመለከተ የክልሉ መንግሥት ተወያይቶ የመግባባት ደረጃ ላይ እንደተደረሰ፣ የተኩስ ልውውጥ በመሠረታዊነት እንዲቆም አቋም እንደተወሰደ፣ አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጸጥታ መዋቅር ባደረገው ድጋፍ ግጭቱን በየቀኑ እንዲከታተል ሊደረግ መሆኑን አስረድተዋል።

" አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአካባቢው የጽጥታ ሁኔታ ጥሩ ስላልሆነ (ማታ ማታ ስለሚተኮስ) ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል እንዲገባ የተደረገበት ሁኔታ አለ " ሲሉም አክለዋል።

በተጨማሪም፣ በመስቃን ወረዳ በሚኖሩ የማረቆ ብሄረሰብ ተወላጆች ሰሞኑን ተፈጸመ በተባለ ጥቃት ሁለት ሰዎች እንደሞቱና ሌሎች እንደቆሰሉ ተነግሯል።

የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳደር አቶ ንጉሴ መኬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ " አንድ ቤተሰብ ላይ ተሰብስበው ቡና እየጠጡ ወደ ሰባት ሰው ተመትቷል። እናትና ልጅ ሞትዋል። ህጻናት ሴት ናቸው። ተሰብስበው ቡና እየጠጡ ነው ጉዳት የደረሰባቸው " ሲሉ ለቪኦኤ አረጋግጠዋል።

#ሰሞኑን በተፈጸመ ጥቃት የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን በተመለከተም የምሥራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር አቶ ጀማል አወል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ባለፈው ሀሙስ ማረቆ ልዩ ወረዳና መስቃን ድንበር በቼ የሚባል ቀበሌ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ቤት ላይ በተቀመጡ ሰዎች የመሳሪያ እሮምታ ከፍተው ጉዳት አድርሰዋል። አንድ ሕጻን ልጅና እናት የሞቱበት ሁኔታ ነው ያለው። ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በሕክምና ላይ እንዳሉ ነው መረጃው ያለኝ " ብለዋል።

አክለውም፣ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም በማረቆ ልዩ ወረዳ ዲዳ ሚደሬ በሚባል ቀበሌ በባጃጅ ላይ የነበሩ የማረቆ ብሄረሰብ ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ ይህን ተከትሎ በመስከረም 15 እና 16 ቀን 2016 ዓ.ም በመስቃንና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች ድንበር ላይ ዲባ ሀዲቦ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር አስረድተዋል።

አያይዘውም መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም በነበረው ግጭት ስድስት ሰዎች፣ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም አምስት ሰዎች እንደተገደሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ግጭቱን ለማስቆም ምን እየተሰራ እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የማዕከላዊ እትዮጵያ ክልል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሽመልስ በበኩላቸው " ጉዳዩን በተመለከተ ግምገማ እየተደረገ ነው ሲጠናቀቅ እናሳውቃለን " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

መረጃው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
በኦሮምያ ክልል በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች " አልታወቁም " በተባሉ የታጠቁ ኃይሎች በጥይት መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የተገደሉት አገልጋዮች ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።

ግድያው የተፈጸመው መስከረም 23 ቀን 2016  ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ሲሆን የተገደሉት አንድ ካህን (አባ ተክለአብ) እና ዲያቆን (ቀሲስ መሰረት) ሲሆኑ ሁለት ካህናትና አንድ ምእመን በታጣቂ ኃይሎቹ ታግተዋል።

የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው አንድ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን ያልጠቀሱ ምዕመን " በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ በተደጋጋሚ ጊዜ ካህናትና  ምእመናን ላይ ጥቃቶች ይደርሳሉ ፤ በዚህም ምክንያት በርካታ ምእመናን አካባበቢውን እየለቀቁ ተሰደዋል። " ብለዋል።

የመስከረም 23 ግድያና አፈና በተመለከተ የሚመለከተው የጸጥታ  አካላት የወሰደው እርምጃ  ይኖር እንደሆነ ተጠይቀው የጸጥታ  አካላት የደረሱት ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ ነው ብለዋል።

የተገደሉት ካህን እና ዲያቆን ዛሬ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል። የቀሲስ መሠረት የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዳማ ናዝሬት ቦኩ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ሲፈጸም የአባ ተክለ አብ የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዳማ ናዝሬት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ተፈጽሟል፡፡

በቀብር ሥርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ አባቶች ፣ በርካታ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።

መስከረም 23 የታገቱ ሁለት አገልጋዮችና ተጨማሪ በልዩ ልዩ ሥራ የሚተዳደሩ ግለሰቦች እስካሁን አለመለቀቃቸውንና የት እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ተነግሯል።

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ ቤት በተፈፀመው ግፍ ማዘኑን ገልጾ ከሚመለከተው አካል ጋር በጉዳዩ ዙሪያና ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ እየተነጋገረ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሚዲያዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
" ከአባ ገዳ አርማ ውጭ ማንኛውም አይነት የፖለቲካ ድርጅት አርማ ይዞ መገኘት አይቻልም " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

ነገ ቅዳሜ እና እሁድ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ማንኛውንም የፖለቲካ ድርጅት አርማ ይዞ መገኘት እንደማይቻል ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፤ ከአባገዳ አርማ ውጪ የገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ አርማ በበዓሉ ላይ ይዞ መገኘት እንደማይቻል አሳስቧል።

ኢሬቻ የአንድነትና የወንድማማችነት በዓል እንደሆነ ያስገነዘበው የክልሉ መንግሥት በዓሉ ያለ እምነትና ብሄር ልዩነት በአንድ ላይ ፈጣሪ የሚለመንበትና የሚመሰገንበት ነው ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፤ በኢሬቻ በዓል ላይ ከባህላዊ አከባበሩ ተቃራኒ የሆኑ ተግባራት መፈፀም እንደማይቻል አሳስቧል።

ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ  ፁህፎችና መልዕክቶችን ይዞ መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አስጠንቅቋል።

ግብረ ኃይሉ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች #ፍተሻ መኖሩን ተገንዘበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነገ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይኖር በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

ቢሮው በአምስት በሮች እንግዶችን በመቀበል ፦
- በጀሞ 3 ፣
- በቃሊቲ ቶታል፣
- ቱሉ ዲምቱ፣
- የካ ጣፎ፣
- አየር ጤና፣
- አዲሱ ገበያና ሳንሱሲ የከተማ አውቶብስ ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ፣ የታክሲና ሀይገር ተሸከርካሪዎችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ስራውን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

ነገ በአዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል የበዓሉ ታዳሚዎች እየገቡ ሲሆን በየአካባቢውን የተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ወጣቶች በባህላዊ ልባሰቸው አሸብርቀው በየጎዳናው ላይ እየተዘዋወሩ ባህላዊ ጨዋታዎች እየተጫወቱ ለነገው በዓል እየተዘጋጁ ናቸው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ይኖሩናል።

@tikvahethiopia