አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።
እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።
አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።
ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።
አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/
አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia

" የሚቀበለንን አጥተናል " - የቀድሞ የደቡብ ክልል ሰራተኞች
ከቀድሞዉ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወደተለያዩ ቦታዎች የተበተኑ የመንግስት ሰራተኞች የሚቀበለን አጣን እያሉ ነዉ።
የደቡብ ክልል ለሁለተኛ ጊዜ ወደሁለት ማለትም የደቡብ ኢትዮጵያና የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተብሎ መከፈሉን ተከትሎ በቀድሞዉ የደቡብ ክልል ስር የነበሩ ሰራተኞች ወደአራቱ ክልሎች መደልደላቸዉ ይታወሳል።
ይሁንና ከአራቱ ክልሎች መካከል በሲዳማና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የተመደቡ ሰራተኞች ክልሉ አልተቀበለንም ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚሉት የሲዳማ ክልል በሲዳምኛ ቋንቋ የመጻፍና የማንበብ ክሂል ሲጠይቅ የደቡብ ምእራብ ክልል በበኩሉ የምፈልገዉን የሰራተኛ መጠን ይዤ ሄጃለሁ አሁን ላይ የምፈልገዉ ጽዳትና የመላላክ ስራ ነዉ በማለት የተመደቡትን ሰራተኞች መቀበል አልቻሉም።
ይህን ጥያቄ ይዘዉ ካሁን በፊት ወደተቋቋመዉ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ቢሄዱም ምላሽ የሚሰጣቸዉ አካል ያጡት የቀድሞ ደቡብ ኢትዮጰያ ሰራተኞች የሚመለከተዉ አካል አቤቱታቸውን እንዲሰማቸዉ ጥሪ አቅርበዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ምላሽ ለማግኘት ያደረገዉ ጥረት አልተሳካም። ምላሽ እንዳገኘን እንልካለን።

የሰቆጣና አካባቢው የሚፈፀመው ዝርፊያ !
• " ስርቆቱ በዚህ ከቀጠለ ለህበረተሰቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማድረስ እንቸገራለን " - የሰቆጣ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ
• " የመብራት ሃይል ገመድና የውሃ ቧንቧዎችን ሲሰርቁ የተያዙ 5 ግለሰቦችን በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል " - የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መመሪያ
• " የተዘረፈ ንብረት ስለመኖሩ አላውቅም " - ፖሊስ መምሪያ
ሰቆጣ ከተማ እና አካባቢው ላይ ማንነታቸው አልታወቁም በተባሉ ግለሰቦች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ መስመሮች ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው ተብሏል።
ይህን ያለው የሰቆጣ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ነው።
8 የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮች ተሰርቀው ተወስደዋል ያለው ማዕከሉ በብር ሲገመት 8 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።
ማዕከሉ ፤ በተለያዩ ግዚያት የተዘረፉትን መሰረተ ልማቶች ለሚመለከተው የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ቢያሳውቅም አጥፊዎችን አሳዶ በመያዝ ረገድ መፍትሄ አልተገኘም ብሏል።
ተዘርፈው ከተወሰዱት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ፋጥዝጊ ክሬችር፣ እርሻ ምርምር የዝቋላ መገንጠያ፣ ባር ኪዳነምህረትና ቄቫ በተባሉ አከባቢዎች አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ይገኙበታል።
ወንጀለኞች ተይዘው ለህግና ለፍርድ ካልቀረቡና የስርቆት ዘረፋ በዚሁ ሂደት ከቀጠለ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድርግ እንደሚቸገርም አገልግሎቱ አሳውቋል።
የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መመሪያ በበኩሉ የመብራት ሃይል ገመድና የውሃ ቧንቧዎችን ሲሰርቁ የተያዙ 5 ግለሰቦችን በህግ እንዲጠየቁ መደረጉን ገልጿል።
የስርቆት ድርጊቱ ሊቆምና ሊቀነስ ባለመቻሉ የፀጥታ መዋቅሩ ይበለጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚጠይቅ ወቅት ነው ብሏል።
እየወደሙ ያሉ መሰረተ ልማቶችን ለማስቆምና ዘረፋን ለመከላከል ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ ለመስራት ጥረት እንደሚደረግም አመልክቷል።
ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር የንብረቱ ባለቤት ሆኖ ካልጠበቀ ተፈላጊውን አገልግሎት ማግኘት እንደማይቻል አስገንዝቧል።
የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ደግሞ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ስለመዘረፉ ምንም አይነት መረጃ እንዳልደረሰውና " የተዘረፈ ንብረት ስለመኖሩ አላውቅም " ብሏል።
በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ህዝብን የሚጎዱ በመሆናቸው ከፖሊስ ኦፊሰሮች ጋር በመነጋገር በተቻለ መጠን ጥበቃ ይደረጋል ሲል ገልጿል።
ማንኛውም ቦታ ላይ ፖሊስ ሊመደብ ስለማይቻል በመሰረተ ልማቶች ላይ ማህበረሰቡ የራሱን ጥበቃ በማድረግ የድርሻውን እንዲወጣ አሳስቧል።
መረጃው ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

በመላው ዓለም ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል ?
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ወይም በምህጻረ ቃሉ ናሳ ከሰሞኑ አንድ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
የተቋሙ ማስጠንቀቂያም በሚቀጥለው ሳምንት በተለይም በፈረንጆቹ ጥቅምት 10 እና 11 ባሉት ቀናት ውስጥ ከባድ የጸሀይ መብረቅ ወይም ሞገድ ሊከሰት ይችላል ብሏል።
ይህን የናሳን ማስጠንቀቂያ መሰረት በማድረግ በመላው ዓለም ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል የሚሉ ዜናዎች በዓለም ላይ በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።
ይህ ዜና በስፋት መሰራጨቱ ያሳሰበው ናሳም ኢንተርኔት በመላው ዓለም ይቋረጣል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ አክሎም በሚቀጥለው ሳምንት በጸሀይ ሀይል ምክንያት ይፈጠራል በተባለው መብረቅ የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቋረጥ የሚችልበት ምንም አይነት ግልጽ ስጋት የለም ብሏል።
የአሜሪካ መንግሥት ንብረት የሆነው ናሳ ስለ ጠፈር ሳይንስ የተለያዩ ጥናቶችን እና ግኝቶችን ለመላው ዓለም በማቅረብ ይታወቃል።
Credit - #AlAin_Amharic

#እንድታውቁት
ቅዳሜ የሚከበረው " #የኢሬቻ_ሆራ_ፊንፊኔ በዓል " ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።
ከነገ ዓርብ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቅ ድረስ ፦
- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
- ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ
- ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
- ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
- ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
- ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ
- በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ
- ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ
- ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ
- ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
- ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ
- ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ
- ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ
መንገዶች ከነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡
በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52- 63-02/03 ፣ 011-542-40-77፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987 ፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀም እንደሚችል ተገልጿል።

#አቢሲንያ_ባንክ
በዚሞል፣ በዴልቨር አዲስ ወይም በትኩስ ዴሊቨሪ ምግብ አዘው ለመክፈል ሲዘጋጁ ድንገት እጅዎ ላይ ካሽ ባይኖር ምን ያደርጋሉ? አቢሲንያ ባንክ ሁሌም ባለ መላ ነው። በቪዛ ካርድዎ ላይ ከፊት እና ጀርባ የሚገኘውን ቁጥር ብቻ በመጠቀም ክፍያዎን ኦንላይን መፈጸም ይችላሉ።
አጠቃቀሙን ለማየት የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/BoAEth/1018

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) የተፈታኞች ምዝገባ ዛሬ ያበቃል።
GAT ለመውሰድ የማመልከቻው ጊዜው ዛሬ መስከረም 25/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 እንደሚያበቃ ይጠበቃል።
በቀሩት ሰዓታት በ https://portal.aau.edu.et የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖርታል ላይ በመግባት ምዝገባ ማድረግ ይቻላል።
በተያያዘ ከመስከረም 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የድህረ ምረቃ የመለማመጃ የመግቢያ ፈተና (Mock Exam) ዛሬ እንደሚያበቃ ይጠበቃል።
ዋናው የመግቢያ ፈተናው ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ እንደሚሰጥ ይታወቃል።
ምስል ፦ Mock Exam (ዲላ እና ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ)
Via @tikvahuniversity

#USAID #ETHIOPIA
የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ተራድ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ አቋርጦት ከቆየው የምግብ እርዳታ ውስጥ ለስደተኞች የሚሰጠውን ድጋፍ መልሶ ለመጀመር ወስኗል።
የምግብ እርዳታ አቅርቦትን መልሶ ለመጀመር የተደረሰው ውሳኔ ሁሉንም የእርዳታ ፈላጊዎች የሚመለከት ሳይሆን ለስደተኞች የሚደረገውን እርዳታ ብቻ መልሶ በመጀመር ላይ ያተኮረ ነው።
ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው የኢትዮጵያ መንግሥት እና አጋሮቹ የስደተኞች የምግብ እርዳታ አቅርቦት መዋቅር ላይ ለውጦችን በማድረጋቸው ነው ብሏል።
" የኢትዮጵያ መንግሥት የስደተኞች የምግብ እርዳታን የማጓጓዝ፣ የማከማቸት እና የማሰራጨት ኃላፊነትን ለሌሎች አጋሮች በማስተላለፉ " እርዳታውን ለመጀመር ወስነናል ብሏል።
በእርዳታ ስርጭቱ ላይ የተደረገው ለውጥ አቅርቦቶችን በትክክል ለተጠቃሚዎች መድረሳቸውን ለመቆጣጠር በሚያስችል ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል።
የእርዳታ ምግብ እደላው በፍጥነት የሚጀመረው ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ በሚገኙት 28 የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ለተጠለሉ ስደተኞች ነው።
ድርጅቱ " የምግብ እርዳታ በሚያስፈልግባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ድጋፉ ለታለመላቸው ተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ማረጋገጫ አስክናገኝ ድረስ ተቋርጦ ይቆያል " ብሏል።
የምግብ እርዳታው ቢቋረጥም የጤና እና የአልሚ ምግቦች እርዳታዎችን ጨምሮ ሌሎች የአሜሪካ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦቶች ግን ይቀጥላሉ ተብሏል።
USAID የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚያደርገው ድጋፍ ለታለመላቸው ተጠቃሚዎች ብቻ እንደሚደርስ ማረጋገጫ እስከሚያገኝ ድረስ እንደማይጀምር አሳውቋል።

" ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም " - ነዋሪዎች
በአማራ ክልል ባህር ዳር እና ጎንደር ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ነዋሪው የዋጋ ንረቱን መቋቋም አልቻለም።
የባህር ዳር ነዋሪው አቶ አለሙ ይርዳው ባለፈው ሳምንት ጤፍ ለመግዛት ወደ ገቢያ በወጡበት ወቅት ከወር በፊት በ10 ሺህ ብር የገዙት ጤፍ በሺዎች ብር ጨምሮ እንዳገኙት ገልጸዋል።
እኚሁ ነዋሪ ከ6 እና 7 ወር በፊት አንድ ኩንታል ጤፍ 6,700 ብር ገደማ መግዛታቸውን አስታውሰው አሁን 13,000 ብር መባሉን ገልጸዋል።
" በጣም ደንግጫለሁ ፤ ከእጥፍ በላይ ነው የጨመረው ዝቅተኛው ጤፍ 11 ሺህ 500 እና 12 ሺህ 500 ነው የሚባለው እኔ የገዛሁት 13 ሺህ ብር ነው " ብለዋል።
ለምን በዚህ ልክ እንደጨመረ ነጋዴዎችን ጠይቀው የተሰጣቸው ምላሽ " ከትራንስፖርት አንፃር አቅርቦት የለም ፣ በየቀኑ መንገድ ይዘጋል " የሚል እንደሆነ ገልጸዋል።
ከጤፍ በተጨማሪ ሽንኩርት አንድ ኪሎ 110 ብር እንደገዙ አመልክተዋል። ቲማቲምን ጨምሮ ሌሎችም የዕለት ዕለት ግዢዎች ላይ ዋጋ ጨምሯል ብለዋል።
" 13 ሺህ ብር ጤፍ ተገዝቶ እንዴት መኖር እንደሚቻል አይገባኝም ፤ በተለይ መካከለኛ እና ዝቅተኛ እንደኔ አይነት ገቢ ያላቸው የወር ደሞዝተኞች መኖር የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። " ሲሉ አክለዋል።
ይህንን እየፈጠረ ያለው አንደኛው ወቅታዊው የመንገድ መዘጋት ነው ፤ በተጨማሪ ስግብግብ ነጋዴዎች ወቅቱን ተጠቅመው ሰው እንደተቸገረ አውቀው በከፍተኛ ዋጋ እየሸጡ በመሆኑ ነው ብለዋል።
አማራ ክልል በተለይ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ጤፍ አምራች ቢሆንም የአካባቢው ነዋሪ በዚህ ዋጋ ለመሸመት መገደዱ አስደንጋጭ ነው ያሉ ሲሆን ለዚህ ምክንያት እየሆነ ያለው ግጭት በፍጥነት ካልቆመ ህዝቡ በኑሮ ይጎዳል ብለዋል።
አንድ ስማቸው እንዲገልፅ ያልፈለጉ ከምዕራብ ጎጃም አዴት እና ጎንጂ ቆለላ ጤፍ አምራች አካባቢዎች ጤፍ እያመጡ የሚሸጡ ነጋዴ ፤ በወቅታዊ ግጭት ምክንያት አርሶ አደሩ ምርቱን ወደገበያ እንደማያወጣ ገልጸዋል።
" አርሶ አደሩ በሰላም ውለን መግባት ስላልቻልን ምርቱን እያወጣ አይደለም። ነጋዴው ደግሞ ያገኘውን ይዞ ይመጣል " ብለዋል።
እኚሁ ነጋዴ ጤፍ 12 ሺህ ብር እየሸጡ እንደሆነ ተናግረዋል።
የጎንደር ነዋሪ የሆኑት ይፍቱ ስራማረው ፤ የዋጋ ንረቱ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው ብለዋል።
" እውነት ለመናገር እንኳን በሁለት ዓመት ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ እንኳን ከፍተኛ ጭማሪ ነው ያለው። 30 እና 20 ብር ስንገዛው የነበረው እቃ አሁን 100 ቤት ውስጥ ነው።
ሽንኩርት ከግርግሩ በፊት ከ50 - 55 ብር ነበር አሁን ሱቅ ውስጥ እስከ 120 ብር ዋና ገበያ እስከ 80-100 ብር ይሸጣል።
ሞኮሮኒ ፓስታ ከአንድ ወር በፊት ነው የጨመሩት የ20 ብር ጭማሪ አለው ፤ ጤፍ 115 ብር - 120 ብር ይባላል በኪሎ ፤ አቅርቦትም ስለሌለ ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።
አዘዞ ከተማ የሚኖሩት የችርቻሮ ነጋዴዋ ወ/ሮ አለሚቱ ደሴ ፤ ጤፍን ጨምሮ ሌሎች እህሎች ተወዷል ብለዋል።
" የገበያው ሁኔታ በጣም ከባድ ነው ለሻጭም ለገዢም ... ቀይ ጤፍ 90 ብር ነው ፣ ነጭ ጤፍ 100 ብር አሁን ላይ ነው በጣም የጨመረው 60 እና 70 ብር ነበር ፤ ግጭት ከጀመረ አንስቶ እስከ 100 ብር ገብቷል። ሽንኩርትም እስከ 100 ብር እየተሸጠ ነው። " ብለዋል።
እህል እየተቀበሉ ያሉት የገጠሩ ማህበረሰብ ይዞ ሲመጣ እነድሆነ የገለፁት ወ/ሮ አለሚቱ " ባለው ችግር የገጠሩ ነዋሪዎች እንደልባቸው መንቀሳቀስ አልቻሉም " ሲሉ ገልጸዋል።
https://telegra.ph/VOA-10-06
መረጃው ከቪኦኤ ሬድዮ የተወሰደ ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል