TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጅግጅጋ ከሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን በተገኘው መረጃ በጅግጅጋ ከተማ የ9 ዓመቷን ልጅ #ደፍረው_ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 ተጠርጣሪዎች በአባቷ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ናቸው። በልጅቷ አባት ቤት ውስጥ ይሰሩ ነበር ከተባሉት ከአራቱ ተጠርጣሪዎች አንዱ ላይ በዋናነት ምልክቶች እንደሚታዩ የክልሉ መንግሥት አሳውቋል። ከሚታዩት ምልክቶች አንዱ ፤ ልጅቷን ሲደፍሯት የጥፍሮቿ ምልክት እንዲሁም…
#ጅግጅጋ

" እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ " - አባት

በጅግጅጋ ከተማ የተደፈረችው ልጅ አባት ምን አሉ ?

አባት ኡጋስ አረብ በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ልጃቸው በራሳቸው ሰራተኞች ከተደፈረች በኃላ መገደሏን ገልጸዋል።

ለቢቢሲ ሶማሊ ክፍል አባት ኡጋስ አረብ ፦

" እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ። እለኔ ልጅ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሕይወታቸው ለጠፋ ሁሉ ፍትሕ እንዲሰፍን እጠይቃለሁ።

በወቅቱ መኝታ ቤቴ ውስጥ ተኝቼ ነበር። ቤት ውስጥም ከእኔ ውጭ ትልልቅ ሰዎች አልነበሩም።

ልጄ ጋር ሄጄ ሳያት እየተነፈሰች አልነበረም ደረቷንም በመጫን እንድትተነፍስ ለማድረግ ሞከርኩ።

አንገቷንም ሳየው ገመድ ተጠምጥሞባት ታንቃለች። ገመዱን ቆርጬ ወደ ሐኪም ወሰድኳት።

ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አፋፍሰን ብንወስዳትም ሕይወቷ አልፏል።

በሞባይል ጥገና ሱቄ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ አራቱ ሠራተኞቼ በድርጊቱ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አንደኛው ሠራተኛዬ ጠፍቷል። " ሲሉ ተናግረዋል።

Via BBC Somali

@tikvahethiopia
#ጋብቻ

እየተጠናቀቀ ባለው በ2015 ዓ/ም የጋብቻ ፍቺ የፈፀሙ እና የተመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ባለትዳሮች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር #በእጥፍ እንደበለጠ ታውቋል።

የአ/አ ሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በሰጡት ቃል፤ " በ2015 ዓ/ም በጀት አመት 4,696 ሰዎች ፍቺ አስመዝግበዋል ፤ አምና መጥተው ያስመዘገቡት 2,937 ሰዎች ነበሩ " ብለዋል።

ምዝገባው ነው የጨመረው እንጂ ፍቺው ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል ሲሉ ዳይሬክተሩ አክለዋል።

የፍቺ ሁኔታ ከእጥፍ በላይ ጭማሪ ቢያሳይም ሂደቱ ፍርድ ቤትን ጨምሮ በተለያየ መንገድ የሚከናወን በመሆኑ ትክክለኛውን ቁጥር ለማውቅ አዳጋች እንደሆነ አቶ ዮሴፍ ገልጸዋል።

" ፍ/ቤት ላይ የሚፈፀመውን ፍቺ እዛው ወቅታዊ ምዝገባውን የማከናወን ስራ በዚህ አመት አቅደን አልተሳካም ሚቀጥለው አመት እየተነጋገርን ነው ፍርድ ቤት ሆነን ምዝገባ የሚከናወንበት ሁኔታ ይመቻቻል ብለን እንጠብቃለን። " ብለዋል።

" በዚህ መንገድ ትክክለኛውን ዳታ ፍቺ እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ ነው የሚለውን ውሳኔ ለመስጠት እንችላለን " ያሉት አቶ ዮሴፍ " አሁን ላይ ግን የኛ ምዝገባ ሰው ፍልጎ ፍቺውን በተለያየ አግባብ ለንብረት ክፍፍል ፣ ከመታወቂያ ዲጂታላይዝ መደረግ ጋር ተያይዞ የጋብቻ ሁኔታ ፍቺ የማስባል እና ሌሎች ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ... በዛ ምክንያት እኛ ጋር ምዝገባው ከአምና ከፍ ብሏል የሚል ድምዳሜ ነው የያዝነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#ቪኦኤ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋብቻ እየተጠናቀቀ ባለው በ2015 ዓ/ም የጋብቻ ፍቺ የፈፀሙ እና የተመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ባለትዳሮች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር #በእጥፍ እንደበለጠ ታውቋል። የአ/አ ሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በሰጡት ቃል፤ " በ2015 ዓ/ም በጀት አመት 4,696 ሰዎች ፍቺ አስመዝግበዋል ፤ አምና መጥተው ያስመዘገቡት 2…
#ጋብቻ

አሳስቢውን የጋብቻ ፍቺ ለመግታት ወደ ጋብቻ ከማምራት በፊት የጋብቻን መርህ ፣ ዓላማ ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል ሲሉ የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪ ባለሞያው ተናገሩ።

የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪ አቶ ይመስገን ሞላ ትዳራቸውን ለማትረፍ ምክር ፈልገው የሚመጡ ቤተሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪው ምን አሉ ?

" የችግሩ አይነት እየበዛ እየጨመረ መጥቷል። በዚህም ቢሯችን የምናስተናግደው እንኳን አብዛኛው ችግር ሲገጥማቸው ለምክር የሚመጡ ናቸው ለመገንባት ከሚመጡ ይልቅ።

በሀገራችን ምክንያት ተብለው የሚሰጡ አሉ፦
- የመጀመሪያው በወሲብ አለመጣጣም ይባለል ፣
- በገንዘብ እጥረት ይባለል አብዛኛው የሚፋታው ግን ገንዘብ ሲያገኝ ነው፣
- የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት / የጓደኛ ጠልቃ ገብነት ይባለል ይህም ቢሆን የግንኙነቱን ስስ መሆን ያሳያል፣
- የኮሚኒኬሽን ችግር ይባላል ፣
- አሁን እየጨመረ የመጣው የእምነት ጉዳይ ይነሳል በሁለቱ መካከል አለመተማመን አለ ምክንያት የሚባሉት እነዚህ ናቸው።

ለእኔ ግን ከዚህም በላይ ተጨማሪ ምክንያቶች አሉ ፦
- ያለን መንፈሳዊ እሴት መበላሸት አንድ ነገር ነው ፤
- በጾታዊ አክራሪነት የመጣው የወንድ እና የሴት ፆታ መገፋፋት ፣ አለመቀባበል በሁለቱ መካከል ያለው መተባበር ሳይሆን መፎካከር ስላለ፣ እንደ ባል እና ሚስት ሚናቸውን አለማወቃቸው ምክንያት ናቸው።

መጋባት ይፈልጋሉ ተዋደን ይሆናል ብለው መዋደድ ግን የጋብቻ መሰረት አይደለም ወይም ፍቅር ስላለ ጋብቻ መሰረት አያገኝም ውጤታማም አይሆንም። የጋብቻ መርህ አላማ፣ የጋብቻን ምንነት መረዳት ይጠይቃል። የነዚህ ሁሉ ድምር ውጤቶች ጋብቻ እንዳይፀና ቤተሰብ እንዲፈርስ ያደርጋል።

ወደ ጋብቻም ወደ ቤተሰብም የገቡ ሰዎች አስበው አይገቡበትም፤ ገብተው ምን እንደሚያደርጉ፣ ከመግባታቸው በፊት ምን መዘጋጀት እንዳለባቸው ስለማያውቁ ጋብቻው እንዳይዘልቅ ቤተሰብም እንዲፈርስ ዋነኛ ምክንያት ይሆናሉ። "

ባለሞያው ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ወደ ትዳር የሚገቡ #ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው ከጋብቻ በፊት ስልጠና የመውሰድ ልምድም እያደገ ነው ብለዋል። ይህ ፍቺን ለመቀነስ ሚና እንዳለው ጠቁመው ከምንም በላይ ግን ቤተሰብ ልጆችን ሲያሳድግ አርያ መሆን አለበት ብለዋል።

ባለሞያው ፦

" ጋብቻ ብዙ ጊዜ እኛም ሀገር አይተን እንደሆነ ስመረቅ፣ ቤት ስገዛ ፣ስራ ስይዝ ብለው condition ያስቀምጣሉ ጋብቻ ግን Condition ሳይሆን Qualification ነው የሚጠይቀው። የበቃች ሚስት የበቃ ባል ለመሆን እራሱን አስቀድሞ ማዘጋጀት አለበት።

ለምሳሌ ፦ ባልነት ለበሰለ ወንድ ነው ኃላፊነት ለመሸከም ለበቃ ወንድ ነው ሚስትነትም እንደዛው ስለዚህ ከመዋደድ ያለፈ የመጋባት ምክንያትና ኃላፊነት የመወጣት አቅም ይጠይቃል። አንድ ወንድ ባል የሚሆነው ብስለቱና ብቃቱ ነው ወንድነቱ ብቻ ባል አያደርገውም። ስለዚህ ይህን ለማድረግ በግል እራስን መገንባት አለበት።

ወላጆች ልጆቻቸውን ለራሳቸው ጥሩ ልጅ፣ ለዛ ቤት ደግሞ ጥሩ ባልና ሚስት እንዲሆኑ፤ ሲወልዱ ጥሩ አባት እና እናት እንዲሆኑ ሞዴል መሆን አለባቸው።

አሁን የሚታየው የጋብቻ መፍረስ፣ የፍቺው ብዛት፣ የልጆች መጎዳት ትላንት ያልተሰራው ስራ መዘዝ ነው። ነገም እንደዚያ ይቀጥል ከተባለ ዛሬ እያንዳንዳችን የራሳችንን ቤት ጠብቀን ልጆቻችንን ለጋብቻ ማብቃት (የራሳችንን ጋብቻ በመጠበቅ)፣ ልጆቻችን እንዲሰለጥኑ ማድረግ ጋብቻን አውቀው እንዲኖሩ ማድረግ መፍትሄ ነው " ብለዋል።

ፁሁፍ በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት።
Credit፦ ቪኦኤ (አስማማው አየነው)

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

አቢሲንያ ባንክ ለዕድሮች ባዘጋጀው ዕድል ለመጠቀም አሁኑኑ ወደ ቅርንጫፎች ጎራ ይበሉ።

ለበለጠ መረጃ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡፡ https://www.bankofabyssinia.com/saving-account/

#Edir #BankofAbyssinia  #BankingService  #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዲሱ ዓመት፣ በ07 መስመራችን ማርሻችንን ወደ ስኬት እንቀይር!

#GearUp #FutherAheadTogether
#Amaharic #Russia

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በሞስኮ የሚገኙ ት/ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀምራሉ ተባለ።

በዚህም የአማርኛ ቋንቋ አንዱ ሆኖ ይሰጣል።

የሞስኮ ትምህርትና ሳይንስ ክፍልን ዋቢ በማድረግ ስፑትኒክ እንደዘገበው ፤ ሩሲያ ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ #አማርኛ እና #ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ት/ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ባሳወቀችው መሰረት ትምህርቱ መሰጠት ይጀምራል።

እንደ ዘገባው ከሆነ " 1517 " የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል።

" 1522 " የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል።

ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች።

ሩሲያ በቀጣይ በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻለች።

በመቀጥልም #ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው።

ሌላኛዋ ሀገር ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ማስተማር እንደምትጀምር ከዚህ ቀደም መግለጿ ይታወቃል።

አማርኛ ቋንቋ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ሆኖ ይሰጣል ተብሏል።

መረጃው የ #አልዓይን (ስፑትኒክ) ነው።

ስፑትኒክ አፍሪካ ፦ https://www.facebook.com/100091796831512/posts/pfbid02Zf2NYdkBuBFDA8UDxBbtf5ZBGbRVPjYGUWzgeLVL365qBrKQgthGS622GJqo2PNul/?app=fbl

@tikvahethiopia
#መቐለ

በወርሃ ጳጉሜን የተጠየቀው የተቋውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይችል የመቐለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የከተማው አስተዳደር ይህንን ያስታወቀው በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፓለቲካ ፓርቲዎች በጥምር ከጳጉሜ 2 አስከ 4 /2015 ዓ.ም በተከታታይ የአደባባይ የተቋወሞ ስልፍ እንዲካሄድ ላስተላለፉት ጥሪ በሰጠው ምላሽ ነው።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ  (ባይቶና )  ውድብ ናፅነት ትግራይ የተባሉ የፓለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ነሃሴ 23 /2015 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ " መሰረታዊ ለውጥ " በሚል መሪ ቃል ሁሉም የህብረተሰበረ ክፍል የሚሳተፍበት የተቋውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። 

የከተማው ዋና መንገዶች በመዞር ሮማናት በተባለው የመቐለ አደባባይ እንደሚጠናቀቅ በተገለፀው የተቋውሞ ሰልፍ  ፦
- የትግራይ ግዛት ማስከበር ፣
- የተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች እንደሚያነሱ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ገልፀዋል ፓርቲዎቹ። 

የመቐለ ከተማ አስተዳደር የፓርቲዎቹን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ  ነሃሴ 25/2015 ዓ.ም ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ  ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በኢፌዴሪ አዋጅ ቁጥር  3/1991 የተቀመጠ መብት ቢሆንም የተመረጠው ጊዜ አዲስ አመትና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚበዙበት በመሆኑ ለማስተናገድ እቸገራለሁ ብሏል።

የከተማው አስተዳደር ለተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ፀጥታ የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት እንዳለበት በመጥቀስ ፤ ይሁን እንጂ በበዓሉ በሚኖረው የህዝብና የመኪና ሰፊ እንቅስቃሴ ምክንያት በሚፈጠር የስራ መደራረብ ምክንያት የቀረበውን ጥያቄ ማስፈፀም አልችልም ብሏል።

የተቋውሞ ሰልፉን የጠሩ ሶስቱ ፓርቲዎች የከተማ አስተዳደሩ ላወጣው መግለጫ ይፋዊ የመልስ መግለጫ ባይሰጡም በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ስልፉ እንደሚደረግ እየገፉበት ነው ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

More : @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia
#itel_Mobile
አይቴል ሞባይል አዲሱ ምርቱ የሆነውን S23+ ሞዴል በኢትዮጵያ አስተዋወቀ!

ጥራት ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከሚያቀርቡ ታላላቅ ኩባያዎች አንዱ የሆነው አይቴል ሞባይል አዲሱ የሆነውን እና የላቁ ፈጠራዎችን እጅግ ከዳበሩ ግልጋሎቶች ጋር የያዘውን አይቴል S23+ ሞዴል በኢትዮጵያ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በይፍ አስተዋውቋል።

6.78 ኢንች ትልቅ ኤፍ.ኤች.ዲ. አሞኦሌድ ከርቨድ ስክሪን ዲዛይን ጋር የተመረተው አዲሱ አይቴል S23+ አስገራሚ ምስልን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ሲሆን ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ በፍጥነት እና ያለ እንከን እንዲሰራ የሚያስችለው 16Gb ራም ከ 256Gb የሜሞሪ አቅም ያካተተ ነው። 18ዋት የፍጥነት ቻርጅ የማድረግ አቅም ያለው ባለ 5000 mhA ባትሪ የያዘው ይህ ሞዴል አገልግሎትን ያለ ማቋረጥ እየሰጠ ቀኑን ሙሉ ያለ ስጋት እንድንጠቀም ያስቸለናል።

አይቴል ሞባይል
#ItelMobile #ItelEthiopia #S23+
Follow Us : Facebook Instagram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዘመናዊ ግብይት
ወደ አዲስ ዓመት!
የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበትን በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጣቸው።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሰሪዎች ፌዴሬሽን በሚል ስያሜ የሀገሪቱ የሆቴል እና መሰል አገልግሎት ባለቤቶችን አባል አድርጎ ሲሰራ የነበረው  አሁን ስያሜውን የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን በማለት ሰይሟል።

የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ትላንት እና ዛሬ የተደረገ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበትን በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጧዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ አስራ አንድ የቦድር አባላትንም የመረጠ ሲሆን ፦

- ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት - ፕሬዝደንት - ከሀዋሳ

- አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን - ተም/ ፕሬዝደንት - ከባህር ዳር

- አቶ ቴዎድሮስ ደበላ - ም/ ፕሬዝደንት - ከጅማ

- አቶ ዘውዱ በላይ - ዋና ጸሀፊ - ከቢሾፍቱ ሆነው ተመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማኢ አቶ ወርቁ ታምራት (ከባህር ዳር) ፣ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ (ከአዲስ አበባ) ፣ አቶ አየነው ሀብቴ (አርባምንጭ)፣ አቶ አለማየሁ ድንቁ (ከሀረር)፣ ኢንጂ መሀመድ አህመድ (ከጅማ) ፣ ወ/ሮ ሂሩት ጸጋዬ (ከድሬዳዋ) የቦርድ አመራር ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ዩሀንስ ወልደጊዮርጊሰ (ከላሊበላ) የሂሳብ ሹም ሆነዋል።

በፌዴሬሽኑ ህገ ደንብ መሰረት ለዘርፉ ባደረጉት አስተዋጽዎ እና በፈጠሩት የሥራ ዕድል የፌዴሬሽኑ የበላይ ጠባቂ እና የክብር አባላትንም ሰይሟል።

በዚህም ፦

👉 ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ - የበላይ ጠባቂ - ከሀይሌ ሆቴሎች
👉 አቶ ጀማል አህመድ - የክብር አባል - ከሸራተን ሆቴሎች
👉 አቶ ታዲዎስ ጌታቸው - የክብር አባል ከኩሪፍቱ ሆቴሎች
👉 አቶ በላይን ክንዴ - የክብር አባል - ከኢትዮጵያ ሆቴሎች
👉 ወ/ሮ ጸደይ አስራት - የክብር አባል - ከካልዲስ ካፌ እና ሬስቶራንት
👉 አቶ ትዕዛዙ ኮሬ - ከዮድ አቢሲኒያ የባህል ማዕከል እና ሆቴሎች
👉 አቶ በቀለ ሞላን (ቤተሰቦቻቸው) - የምግዜም የክብር አባል ያደረገ ሲሆን በትላንት ውሎውም የሀገሪቱ የሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ያለውን አቅም፤ ያለበትን ተግዳራቶች እንዲሁም ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች ከሀገር አቀፍ ደረጃ በማስጠናት የቀረብ ሲሆን የፌዴሬሽኑም የቀጣይ አምስት አመታት የሚሰራበትን ስትራቴጂክ ፕላን ቀርቦ በመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በአባላቱ እና በባለድርሻ አካላት አስገምግሞ ጉባኤው አጽድቆታል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊውን ህዝባችን ይዘን በያዝነው የግዜ ሰሌዳ ሰልፉን እንደምናካሂደው ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን " - ሶስቱ ፓርቲዎች

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ፣ ትግራይ ውድብ ናፅነት ትግራይ ለመቐለ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ሰጡ።

ፓርቲዎቹ ፤ በቀን 24 ቀን 2015 ዓ.ም በትግራይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት " ኪዳን ንሱር ቦቆስ ለውጢ " በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜን 2 እስከ 4 /2015 ዓ.ም በመቐለ ሮማናት አደባባይ ለሚያካሂዱት ሰላማዊ ሰልፍ የከተማ አስተዳደሩ እንዲያውቀውና አስፈላጊውን ፀጥታ የማስከበር ስራ እንዲሰራ ደብዳቤ ልከው እንደነበር አስታውሰዋል።

የከተማው አስተዳደር የተላከውን ጥያቄ አስመልክቶ የላከውን ደብዳቤ ደርሷቸው በሚገባ መመርመራቸውን ገልጸዋል።

ፓርቲዎቹ በደብዳቤው ላይ እንደተገለፀው " በሰልፉ የፀጥታ ስራ ማስከበር ተፈጥሮአዊ ግዴታችሁ መሆኑ መቀበላችሁ ወስደነዋል " ብለዋል።

" ይሁን እንጂ ሰላማዊ ሰልፉ በስመ በዓልና የፀጥታ አስከባሪ ቁጥር ማነስ ' ማስፈፀም አንችልም ' ማለታችሁ ውድቅና የማንቀበለው ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

ፓርቲዎቹ " ሰላማዊውና ለውጢ ፈላጊውን ህዝባችን ይዘን በያዝነው የግዜ ሰሌዳ እንደምናካሂደው ልናረጋግጥላችሁ " እንፈልጋለን ብለዋል።

አክለውም ፤ " በበኩላችን የበዓል ግዚያት ያላችሁት በተለምዶ ይሁን ብለን ፤ ህዝባችን የተለመደውን በዓል ማክበር ካቆመ ሦስት አመት እንደሆነው ፤ በዓል ማክበር ይቅርና በህልውና ጥያቄ ውስጥ እንደሚገኝ ፤ በማያባራ ጥፋት እንጂ  ፤ እንደ የስርአቱ ተጠቃሚ አካላት ተመችቶት እንዳልሆነ እንረዳለን " ሲሉ ገልጸዋል።

በመሆኑም "  የፀጥታ ስራ እንድታከናውኑና ትኩረታችሁን ደግሞ ከሰርአቱ ከሚሰነዝር ጥቃት ህዝቡ መታደግ መሆን እንዳለበት ደግመን እንገልፃለን " ብለዋል።

መረጃው የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

Via @TikvahEthiopiaTigrigna

@tikvahethiopia