TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

" በመቐለ ከተማ ከ184 ሄክታር በላይ የመንግስትና የህዝብ መሬት መጭበርበሩ በጥናት ተረጋግጧል " - የከተማዋ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ

በትግራይ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ከተሞች ህገ ወጥነት ተንሰራፍቶ በርካታ ወንጀሎች መፈፀማቸው የመቐለ ከንቲባ ይትባረክ ኣማሃ ገለፁ።

ከንቲባው ፤ የመንግስትና የህዝብ መሬት ዘረፋና የፀጥታ መደፍረስ ዋነኛ ተጠቃሽ ችግሮች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

የመሬት ወረራው የተካሄደው ለምቶ ወደ ተጠቃሚዎች ለመተላለፈ በተዘጋጀ ፤ በእርሻና በመንግስት ክፍት ቦታ ፤ ከገጠር ወደ ከተማ በተካለለና በተቀሙ የኢንቨስትመንት መሬቶች መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ ፤ " በህገወጥ ተግባሩ 3337 ሰዎች ተሳትፈዋል " ብለዋል።

" በመሬት ወረራው የተሳተፉ ህገወጦች በህግ እንዲጠየቁ የህዝቡ ጥያቄ ጭምር ነው " ያሉት ከንቲባ ይትባረክ " ከእርምጃው በፊት የተወረረው መሬት ማጥናት ፣ ቦታዎቹ የሰነዱ ፋይሎች ድህንነት ማረጋገጥ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር ተገብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሳሳቢ የሆነውን የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ለመፍታት እየተሰራ  መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ በተካሄደው ጥናትና ክትትል በቡድን የሚዘርፉ ፣ ህገ-ወጥ ሕትመት የሚያካሂዱ ፣ የመሬት ፕላን ሰርተው የሚሸጡ ፣ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ የፎርጅድ ገንዘብ ማተምያ ማሽንና የተለያዩ ህገ ወጥ ገንዘቦች እጅ በፈንጅ ተይዘዋል ብለዋል።

የመሬት ወረራ ሆነ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራት ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑ ያብራሩት ከንቲባው ህዝቡ መረጃና ሰነዶች ከመስጠት እስከ መመስከር ንቁና ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃውን የመቐለ ቲክቫህ አባል የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢትዮጵያውያን በፀሎት እንዳይለዩን " - ጉዳፍ ፀጋይ

የዓለም የወርቅ እና ብር ሻምፒዮኗ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ዛሬ ምሽት በ10,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ለሀገራችን የመጀመሪያ ሜዳሊያን ለማስገኘት ከቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች።

ከውድድሩ አስቀድሞ ሀሳቧን ያካፈለችው ጉዳፍ ፤ " የራሳችን ጥረት እና ልፋት እንዳለ ሆኖ ሁሉም ነገር የሚያምረው ፈጣሪ ሲጨመርበት ነው ፣ ህዝባችን ሁሌም ከጎናችን ነው አሁንም እንዲሆን እንፈልጋለን ፤ በፀሎት አይለየን " ብላለች።

" የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ነው መግለፅ ያቅተኛል ፤ በየትኛውም ቦታ የተለየ ክብር ነው የሚሰጠኝ ፣ ከዚህ በላይ መስራት እንዳለብኝ የቤት ስራ ሰጥቶኛል። የህዝቡን ፍቅር ለመግለፅ እቸገራለሁ " ስትል ገልጻለች።

ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በ10,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ ፣ ለምለም ሀይሉ ተካፋይ ይሆናሉ።

#TikvahSport

More 👇
https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

አቶ እንዳሻው ዛሬ በቀጠለው ጉባኤ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም በሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበው ሰርተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ-መንግስት በጉባኤው አባላት በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል። ዛሬ ጠዋት በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ በጀመረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-መንግስት አጽዳቂ ኮሚሽን ጉባኤ የቀረበው ረቂቅ ህገ-መንግስት በ10 ተቃውሞ በ2 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል  ረቂቅ ህገ-መንግስቱ 11 ምዕራፎች፣ 141 ዋና ዋና አንቀጾች…
#Update

የቀድሞው የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ " ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "ን በርዕሰ መስተዳደርነት እንዲመሩ ተሾሙ።

የ44 ዓመቱ ገልማሳ አቶ ጥላሁን ከዚህ ቀደም ፦
- በሃዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የጤና ጣቢያ ኃላፊ፣
- በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን የውባ ደብረፃይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፣
- በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን ንግድ እና ኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊ፣
- በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን የድርጅት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፣
- የቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፣
- በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የግብርና እና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እንዲሁም የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ
- የደቡብ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ሆነው መስራታቸው ተገልጿል።

አመራሩ በትምህርት ደረጃቸው በከተማ ልማት አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም በተመደቡበት ቦታ ህዝባቸውን #በንፅህና በእኩልነት የመሩ ናቸው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ።

ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው።

በዚህም መሠረት :-

- የም ዞን

- ምስራቅ ጉራጌ ዞን

- ጠምባሮ ልዩ ወረዳ

- ቀቤና ልዩ ወረዳ

- ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል በሞሽኑ ቀርቦ ፀድቋል።

የምክር ቤቱ ጉባኤም ተጠናቋል፡፡

መረጃው የደ/ሬ/ቴ/ድ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ትላንት ለስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ / አዲስ አበባ የመጡት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ሄደዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ። ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው። በዚህም መሠረት :- - የም ዞን - ምስራቅ ጉራጌ ዞን - ጠምባሮ ልዩ ወረዳ - ቀቤና ልዩ ወረዳ - ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው…
#NewsAlert

የደቡብ ኢትያጵያ ክልላዊ መንግስት አዲስ ዞን እና የወረዳ አስተዳደር መዋቅርን ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት ፦

- የአማሮ ፣ የደራሼ ፣ የባስኬቶ፣ የቡርጂ፣ የአሌ ልዩ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው እራሳቸውን ችለው #በዞን ይደራጃሉ።

- በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ እንዲደራጅ ተወስኗል።

- የደቡብ ኦሞ ዞን በሁለት ዞን እንዲደራጅ ተወስኗል።

• ከደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ፣ የሐመር፣ የበና ጸማይ ፣የሰላማጎ፣ የኛንጋቶም የዳሰነች ወረዳ እና የቱርሚ ከተማ አስተዳደር በጋራ #በዞን የሚደራጁ ይሆናል።

• ከደቡብ ኦሞ ዞን የደቡብ አሪ፣ የወባ አሪ የባካ ዳውላ ፣ የሰሜን አሪ ወረዳዎች እንዲሁም የጂንካ ከተማ አስተዳደር እና የገሊላ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በጋራ ሆነው #በዞን ይደራጃሉ ተብሏል።

መረጃ የክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
ቴሌግራም ላይ በኮፕ ቻፓግራም https://t.me/ChapagramBot የግብይት ክፍያ መፈፀም ተቻለ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በ " ደቡብ ኢትዮጵያ " እና በ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ " ክልሎች ምስረታ ጉባኤ ላይ የተደረጉ ሹመቶችን በተመለከተ ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia