" በጊዜ ገደቡ ምላሽ ካልሰጠ ወደ ክሥ እናመራለን " - የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም
የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ቤቶቻቸው ለፈረሱባቸው ሰዎች አቤቱታዎች፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
ተቋሙ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፈረሳ ጋራ ተያይዞ፣ ከ100 ሺሕ በላይ አቤቱታዎችን እንደተቀበለ፣ ከዚኽ ቀደም ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርመራ ዲሬክተር አቶ ቶሌራ በላይ፣ የከተማ አስተዳደሩ፥ ለአቤቱታዎቹ ምላሽ እንዲሰጥ በደብዳቤ እንደተጠየቀ ገልጸዋል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር፣ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ፣ ጉዳዩ ወደ ክሥ እንደሚያመራ፣ የምርመራ ዲሬክተሩ አቶ ቶሌራ በላይ አመልክተዋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የሸገር ከተማ አስተዳደር ያለው ነገር የለም።
ከዚህ ቀደም ግን በሰጠው " ለእንባ ጠባቂ ተቋም 100 ሺሕ አቤቱታዎች መቅረባቸውን አላውቅም " ብሎ ነበር።
የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሸገር ከተማ፣ " ሕገ ወጥ ግንባታ " በሚል እየተካሔደ ካለው የቤቶች ፈረሳ ጋራ የተያያዙ፣ 100 ሺሕ አቤቱታዎችን እንደተቀበለ ማሳወቁ አይዘነጋም።
አሁን ደግሞ፣ እንባ ጠባቂ ተቋሙ፥ የሸገር ከተማ አስተዳደር ለአቤቱታ አቅራቢዎቹ ምላሽ እንዲሰጥ፣ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ እንደጠየቀው ማስታወቁን ሬድዮ ጣቢያው አመልክቷል።
@tikvahethiopia

#iCog
AI ኮድ ያድርጉ!
የወደፊቱን አብረን እንተዋወቅ። የiCog-ACC ክረምት ካምፕ ሦስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ ተጀምሯል። ክረምቱን ከiCog-ACC ጋር
-AI
-ሮቦቲክስ
-እንዲሁም የተለያዩ አስደሳች የኮዲንግ ኮርሶች ኮድ ያድርጉ።
አሁኑኑ ይመዝገቡ።
ለአዲስ አበባ (በአካል)-5,500 ETB
ለክልል ከተሞች-4000ETB
ለኦንላይን-4000ETB ብቻ
ለመመዝገብ: በስልክ ቁጥራችን +251904262728/251901379478 በመደወል
ዌብሳይታችንን በመጎብኘት https://icogacc.com/register
ወይም ቴልግራም ቦት ይጠቀሙ @iCogACCsummercamp_bot
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችንን ይከተሉ
Facebook: facebook.com/icogacc
Instagram: instagram.com/icogacc
Twitter: twitter.com/icog_acc
Linkedin: linkedin.com/company/icog-anyone-can-code/

#ልዩ_ዕቃ
2 in 1 Hobby Lobby Brand የጁስ Juice እና የቡና መፍጫ የጉልበት መጠኑ አስተማማኝ የሆነ ዕቃ ፤ ዋጋ 2600 ብር ብቻ ከነፃ ዲሊቨሪ ጋር እና ከዋስትና ጋር ቴሌግራም ቻናል @LeyuEka
👉 2 ዕቃ ከ1 ሺ ብር በላይ የሚተመኑ ዕቃዎች ሲገዙ ስጦታ🎀 አዘጋጅተናል
0933334444 @LeMazez_z
0944109295 @Lemaze_z
0946242424 @Le_Mazez
አድራሻ✅
⭕️ቁጥር 1 ልደታ ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገባ ብሎ አህመድ ህንፃ ላይ 1ኛፎቅ 105B
⭕️ቁጥር 2 __ 22 ጎላጎል ህንፃ አጠገብ
የ NOAH ህንፃ ግራዉንድ የሱቅ ቁጥር G 15 ልዩ ዕቃ የሚል ይደዉሉልን👆

" ትስስሩ ከዚህ እስከ የመን የሚደርስ ነው "
ባቲ ከተማን እንደ መሻገሪያ አድርጎ ለአመታት የዘለቀውና አሁንም ትኩረት የተነፈገው የህገወጥ የሰዎሽ ዝውውር ጉዳይ አሁንም አሳሳቢ ነው።
ባቲ ከተማ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረስብ ዞን የምትገኝ ሲሆን ከደቡብ ወሎ ዞንና ከአፍር ክልል ይዋሰናል።
እንዲሁም ኮምቦልቻ ባቲ ሚሌን አቋርጦ ጂቡቲ ድረስ የሚዘልቀው የፈደራል መንገድ ያቋርጣታል።
በዚህም የተነሳ መነሻቸው ከሰሜን ወሎ ፤ ከደቡብ ወሎ ፤ ሰሜን ሸዋና ከኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ተነስተው በርካታ ዜጎች በህገወጥ ደላሎች ተጠልፈው ከአገር ለውጣት እንደመሻገሪያነት የሚጠቀሙባት ከተማ ናት።
በዚህ ጉዳይ የባቲ ከተማ አስተዳር ፓሊስ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ ኢንስፔተር ዑመር መሐመድን አነጋግረናል።
ባቲን ከተማ ለዚህ ህገወጥ ጉዞ እንዴት ተመራጭ አርጋት ?
" ከአማራ ክልል ከተማችን ወደ ጂቡቲ መውጫ በር ካላቸው ከተሞች አንዶ በመሆኗ ነው ለዚህ ሕገወጥ ጉዞ ተመራጭ የሆነችው ። "
በዚህ የወንጀል ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረግ ጥረት ካለ ?
" ይህ ድርጊት በጣም ስፊና ትስስሩም ከዚህ እስከ የመን እንደሚደርስና ለዚህም ጉዞ ምልመላ የሚያርጉት ከዚያው ከአካባቢያቸው ጭምር ስለሆነ ችግሩን ከባድ ያረጋዋል።
ከተለያየ አካባቢ ያሰባሰቧቸውን ባቲ ደጋንና ኮምቦልቻ በማስቅመጠት ጉዞ ያደርጋሉ ፤ ግንኝነታቸው በስልክ ብቻ ስለሆነ እነዚህን ወጀለኞች ለመያዝ ከባድ ያደርገዋል።
ነገር ግን በእኛ ከተማ ሁነው በተለያዩ ምርመራዎች የያዝናቸውንና በማስረጃ ጭምር ክስ የመስረትንባቸው ወጀለኞች የፍትህ አካላት እኛ በማናቀው መንገድ በመሳጠር ቅጣቱን በተገቢው ሁኔታ ተፈፃሚ እንዳይሆንና ፍትህን የማጎደል ደካማ ስራ ይስራሉ በዚህ ድካማችን ዋጋ ያጣል። "
ወንጀሉን ካጎራባች ዞኖችና ወረዳወች ጋር በቅንጂት ለመስራት የተደረገ ጥረት ካለ ?
" እንደ ከተማ አስተዳደር ከደቡብ ወሎ ዞን ከቃሉ ወረዳ ጋር በስፍት እስራለን።
ወጀለኞች የመያዝ ለጉዞ የሚጠቀሙበት ተሽከርካሪዎች የመያዝና ኦፕሬሽኞችን የመስራት ስራዎች እስራለን በኛ አቅም ደረጃ። "
ይህ አስከፊና እስከ ህይወት ማጣት የሚደርስ አደገኛ ጉዞ ህብረተስቡ እንዲገነዘበው ከግብረስናይ ድርጂቶች ጋር በመተባበር ምን የተስራ ስራ አለ?
" ይህ ስራ ለመስራት ምንም አይነት የግብረ ስናይት ድርጅት በአካባቢያችን የለም በኛ አቅም ደግሞ ይህ ማድረግ በጣም ይከብዳል ፤ ለዚህ ተብሎ የሚስጥ በጀት የለም። በአጠቃላይ ይህ ትልቅ ትኩረት የሚሻ ሆኖ ግን ምን ትኩረት ያልተስጠው ጉዳይ ነው ስለዚህ የክልል ይሁን የፈደራል አካላት ችግሩ አይተው ትኩረት ቢሰጠው። "
መረጃው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ - ባቲ ቤተሰብ ተላከ ነው።
ፎቶ ፦ በዚህ መንገድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ በባቲ ከተማና በቃሉ ወረዳ ፓሊሶች በቁጥጥር የዋለ ዜጎች ምስል ባቲ ፓሊስ ጽ/ቤት

#ትግራይ
በኮሮና ቫይረስ እና በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች እንዲፈተኑ የሚያስችል ዕድል ማመቻቸቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ እንዳስታውቀው የ2012 ዓ.ም የ12 ክፍል አገራዊ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በመተባበር የማካካሻ ትምህርት በመስጠት እንዲፈተኑ ይደረጋል።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ አራቱ ዩኒቨርስቲዎች በመተባበር በያዝነው የክረምት ወቅት ፤ ለፈተና የሚያግዝ የማጠናከሪያ ትምህርት /SUPPLEMENTARY TUTORIAL / በመስጠት እዲፈተኑ ቅድመ ዝግጅት አጠናቋል።
በዚህም ፦
1. የደቡብና ደቡባዊ ምስራቅ ዞኖች የ12 ክፍል ተማሪዎች - በራያ ዪኒቨርስቲ
2. የመቐለ ከተማ አስተዳደር የ12 ክፍል ተማሪዎች - በመቐለ ዪኒቨርስቲ
3. የምስራቃዊ ዞን እንዲሁም የእገላ ፣ ኣሕፈሮም ፣ እንትጮ ፣ ሓሓይለ ፣ ቆላ ተምቤን ፣ ቀይሕ ተኽሊ ፣ ዓብዪ ዓዲ ፣ ጣንቋ ምላሽና የጭላ ኣበርገለ ወረዳ የ12 ክፍል ተማሪዎች - በዓዲግራት ዪኒቨርስቲ
4. የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዲሁም ጭላ ፣ ታሕታይ ማይጨው ፣ ዓዴት ፣ ናዕዴር ፣ የኣክሱም ከተማ ፣ የዓድዋ ከተማ ፣የዓድዋ አከባቢ ወረዳ ፣ ኣሕሳኣ ፣ ራማ ዓዲ ኣርባዕተ ፣ እንዳባፃሕማ ፣ ማይቅነጣልና እምባስነይቲ ወረዳ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች - በኣክሱም ዪኒቨርስቲ
5. በተለያዩ አከባቢዎች ሚኖሩ የምዕራባዊ ዞን ተፈናቃይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከሚኖሩበት ወረዳ አቅራቢያ ባለው ዩኒቨርስቲ የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።
ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎች የሚቀበሉበት የግዜ ሰሌዳ በተመለከተ ፡
• ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ከሃምሌ 28 - 29 /2015 ዓ.ም ባለው ግዜ
• ራያ ዩኒቨርስቲ ሃምሌ 23 /2015 ዓ.ም
• አክሱም ዩኒቨርስቲ ሃምሌ 26 /2015 ዓ.ም
• መቐለ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ ይገለፃል ተብሏል።
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ይህንን በመገንዘብ በተጠቀሰው ግዜ በዩኒቨርስቲዎቹ ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝተው እንዲመዘገቡ ማሳሰቢያ ተለልፏል።
የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የተመለሙ መምህራንና ርእሰ መምህራን በተጠቀሰው ግዜ ወረዳና ዞናቸው በተመደበበት ዩኒቨርስቲ ሪፓርት እንዲያደርጉ ተብሏል።
በተቀመጠው የግዜ ሰሌዳ ሪፓርት ያላደረገ ተቀባይነት አያገኝም የተባለ ሲሆን ፈተናው መውሰድ ያላባቸው የ2012 ዓ.ም የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ጥሪ ተላልፏል።
ተማሪዎችና መምህራን ወደ ተጠቀሱት ዩኒቨርስቲዎች ሲመጡ ፦
- ብርድ ልብስና አንሶላ
- የትምህርት ቁሳቁስ
- የተማሪ መፅሃፍ
- ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎችና መፃህፍት ይዘው እንዲመዘገቡ ተብሏል።
መረጃው የመቐለ ቲክቫህ አባል ነው።
#TikvahEthiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ መግለጫው ምን አለ ? በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት…
" በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ።
ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው።
ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያኗ የገጠማት ፈተና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ በተለያየ ምክንያት #እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ ተብሏል።
ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤው እንዲገኙ በድጋሜ ጥሪ ተለልፏል።
በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳስቧል።
መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት / EOTC TV ነው።

#ጥምረት . . የፊልም ፌስቲቫል . . ለሁሉም
ዩኤስኤይድ ከፕሮሎግ ማርኬቲንግ ጋር በመተባበር ጥምረት የተሰኘ የፊልም ፌስቲቫል ከሐምሌ 25 እስከ 28 ድረስ ለዕይታ ያቀርባል።
📽 በአዲስ አበባ፦ የጣሊያን ባህል ማዕከል፣
📽 በአዳማ፦ ኦሊያድ ሲኒማ
📽 በባህር ዳር፦ ሙሏዓለም አዳራሽ ያካሂዳል።
ይኽ የፊልም ፌስቲቫል ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን የሚያንሸራሽሩበት መድረክ ጭምር በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።
📣 መግቢያው #በነጻ ነው።
ቀድመው ይመዝገቡ ፦ https://forms.gle/wjNi3Dk5ssNpsZ9s7
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉 https://t.me/TimretEth

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የፀጥታ_ችግር
ዘላቂ ሰላም ያልተገኘለት እና ዛሬም ድረስ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው ቀጠና መፍትሄው ምንድነው ?
• ከ2010 ዓ/ም አንስቶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ንብረት ወድሟል። እርቅ ለመፈፀም ተሞክሮ ዘላቂ ሰላም አልመጣም።
• ከሰሞኑ በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል ፤ እርቅ ለመፈፀም ጥረት እየተደረገ ነው።
• ዛሬ ወደ ገበያ በሚያቀኑ ሰዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ ተጎድተዋል።
በደቡብ ክልል መን፤ በጉራጌ ዞን በመስቃን እና ማረቆ መካከል በተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግሮች እየተከሰቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ ንብረት ሲወድም ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ሲስተጓጎሉ ፣ የመንግሥት ስራም ሲበደል በአጠቃላይ በቀጠናው ከፍተኛ ተፅእኖ ሲደርስ ቆይቷል።
በአካባቢው ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም የዕርቅ ጥረቶች ተደርገውም ያውቃሉ።
ከሰሞኑን ደግሞ በዚሁ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ጉዳትም ደርሷል።
አንድ ስለ ጉዳዩ አውቃለሁ ያሉ የቤተሰባችን አባል ፤ " መስቃን እና ማረቆ ባንተ ወረዳ ይሄን ያክል ቀበሌ አለኝ አንተ የለህም የኔነዉ ያለኝ ባንተ ወረዳ እየተባባሉ ግጭት ከተጀመረ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ እስከ ዛሬዉ ቀን ሰዉ ከመሞትና ቤት ንብረት ከመቃጠልና ከመዘረፍ አልቆመም " ብለዋል።
እኚሁ የቤተሰባችን አባል ፤ በዞኑ እንዲሁም በክልሉ ያሉ አመራሮች ለችግሩ ምንም አይነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ እንዳልቻሉ ፤ ካቅማችን በላይ ነዉ ብለዉም ለከፍተኛ አካል ለፌደራል መንግስት የሰጡት / ያስረከቡት ነገር እንደሌለ አስረድተዋል።
ከሰሞኑንም በዚሁ ቀጠና ላይ የሰዎች ህይወት መቀጠፉን ንብረት መውደሙን አመልክተዋል።
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-29

#እንድታውቁት
" ኢንፎኔት ኮሌጅ " ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን ሙሉ የትምህርት ማስረጃ እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያስረክብ የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳሰበ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ " ኢንፎኔት ኮሌጅ " በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በቴ/ሙ ዘርፍ እውቅና ፍቃድ በማግኘት ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ነገር ግን ኮሌጁ በባለስልጣኑ የእውቅና ፍቃድና እድሳት መመሪያ መሰረት ህጋዊ የቤት ኪራይ ውል ማቅረብ ባለመቻሉ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ #ፍቃድ_የሌለውና ፍቃዱም በባለስልጣን መ/ቤቱ #መሰረዙን ሚያዝያ 12/2014ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ እንዳሳወቀው አመልክቷል።
" ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና እየሰጠ አለመሆኑን " በቀን 11/11/2015 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ ቁጥር ኢንፎ/2910/15 ገልፀውልናል " ያለው መ/ቤቱ ኮሌጁ ቀደም ሲል እውቅና ፍቃድ በነበረው ወቅት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን ሙሉ የትምህርት ማስረጃ እስከ ነሐሴ 17 / 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያስረክብ ቀነ ገደበ አስቀምጠናል ብሏል።
ኮሌጁ በተቀመጠው ጊዜ ይህን መፈፀም ካልቻለ በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርገውም ባለስልጣን መ/ቤቱ አስጠንቅቋል።

#ExitExam
ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚተገበረው አስገዳጅ መመሪያ ምን ይላል ?
(የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን)
" ከቀጣዩ ዓመት 2016 ዓ/ም ጀምሮ እያንዳንዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።
የግል ተቋማቱ 25 በመቶ ተፈታኞቻቸውን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት ፕሮግራሙ #ይሰረዛል።
በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው። "
NB. ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት ያመጡት 12,422 ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ናቸው።
Credit : #FBC

#CBE
ኢትዮ-ዳይሬክት (EthioDirect)
• በሞባይል ስልክዎ
• የቪዛ እና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም
• ያለምንም ክፍያ
• ከውጭ ሀገራት
• ወደ ሀገር ውስጥ
• ቀጥታ ወደተቀባዩ ሂሳብ
• ገንዘብ የሚልኩበት የሞባይል መተግበሪያ!
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
=============
የEthioDirect መተግበሪያን ከPlay Store ወይም ከApp Store በማውረድ የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ!
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡- https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአይፎን ስልኮች፡- https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491

#ሳፋሪኮም_ኢትዮጵያ
በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡትን የሳፋሪኮም ቲክቶክ ጥቅሎችን በመጠቀም አዳዲስ ቪዲዮዎችን እየሰራን ለምንወዳቸው ሰዎች እንላክ፣ ዘና ፈታ እንበል!
አሁኑኑ ወደ *777# በመደወል ጥቅላችንን እንግዛ!
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ
ከሐምሌ 24-ነሃሴ 24 'የዘወትሯ ኢትዮጵያ' በሚል ርዕስ ሀገራዊ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ተዘጋጅቷል፡፡ የኢትዮጵያን አንድነትና የጋራ የአኗኗር ዘይቤዎች የሚያሳዩ የፎቶግራፍ ስብስቦችን ያዋቀረው ይህ የፎቶ ኤግዚቢሽን በአራት የተለያዩ ከተሞች የሚደረግ ይሆናል፡፡
በመጪው ሰኞ ሐምሌ 24/2015 በባህር ዳር ከተማ በድምቀት የሚከፈተው ይህ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለአምስት ተከትታይ ቀናት እስከ ሐምሌ 28/2015 አርብ ድረስ የሚዘልቅ ይሆናል፡፡
በቀጣይ ከነሃሴ 3-7/2015 - ድሬዳዋ ላይ ከዚያም ሐዋሳ ላይ ከነሃሴ 12-16/2015 መዳረሻውን አድርጎ ከነሃሴ 20 -24/2015 ደግሞ አዲስ አበባ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
በተዘረሩት ቀናት ላይ በፎቶ አውደርዕዩ ላይ በመገኘት የዘወትሯን ኢትዮጵያ አብረውን ይቃኙ! ኑ! ግሩም ተሰጥኦ ባላቸው የፎቶ ባለሙያዎች የተቀነጨቡትን የማህበረሰባችንን ገጽታዎች በጋራ እንመልከት፣ በጋራ እናድንቅ!
#የዘወትሯኢትዮጵያ #ተጓዥየፎቶግራፍአውደርዕይ

ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ በኣካል ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አደረገ።
ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምከንያት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ሲያደርገው የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው ፦
- ሶስተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበሩ መደበኛ (Regular) የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች፣ ሁሉም የሕክምና ትምህርት ክፍል (Medicine department) ተማሪዎች እና ሁሉም መደበኛ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ነሐሴ 2 እና 3 ቀን 2015 ዓ/ም ፤
- ሁሉም የክረምት(summer) ቅድመ-ምረቃና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ነሐሴ 4 እና 5 ቀን 2015 ዓ/ም፤
- ሁሉም የኤክስቴንሽን (Extension) ቅድመ-ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ነሐሴ 6 እና 7 ቀን 2015 ዓ/ም ፤
- 1ኛና 2ኛ ዓመት የነበሩ መደበኛ (Regular) የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መስከረም 10 እና 11 ቀን 2016 ዓ/ም፤
- በትግራይ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውጪ ተመድበው የመሄድ ዕድል ያላገኙ ወይም ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ኣስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ከላይ ከላይ በተገለፀው መሰረት በየተመደቡበት ግቢ በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።
ተማሪዎች ሪፖርት የሚያደርጉት የት ግቢ ነው ?
• ከሕብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ ተማሪዎች በስተቀር ሁሉም የዋና ግቢ ተማሪዎችና የዓድዋ ግቢ ተማሪዎች በኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ
• የጤና ሳይንስ ግቢ ተማሪዎችና ሁሉም መደበኛና ክረምት የሕብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ ተማሪዎች በኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ግቢ
• የኣከሱም ዩኒቨርሲቲ ሽረ ግቢ ተማሪዎች በሽረ ግቢ