TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኬንያ መንግሥት የኮንጎ ብራዛቪል ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ ኬንያ መግባት እንደሚችሉ ውሳኔ አሳለፈ።

የጎረቤት ሀገር ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊልያም ሩቶ ከትላንት ጀምሮ በኮንጎ ብራዛቪል ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደርጉ ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንት ሩቶ በጉብኝንታቸው ለሀገሪቱ ፓርላማ ንግግር አድርገዋል።

ሩቶ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ከዛሬ ጀምሮ የኮንጎ ብራዛቪል ዜጎች ኬንያ ለመግባት ቪዛ እንደማያስፈልጋቸው አሳውቀዋል።

ይህን ውሳኔ መተላለፉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ንግድ፣ ቢዝነስ ፣  የሃሳብ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚረዳና ግኝኑነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልጻዋል።

ፕሬዝዳንቱ ፤ የአፍሪካ አገሮች በመሠረተ ልማት አውታሮች መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ፣ የንግድ እንቅፋቶችን እና የቪዛ ገደቦችን #በማስወገድ ነፃ የንግድ አቅምን ማጎልበት አለባቸው ብለዋል።

በ " ትሬድስ " ይቀላቀሉን ፦ threads.net/tikvahethiopia

@tikvahethiopia
" የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይጠየቅልን " - ተፈናቃይ ወገኖች

ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት የተፈናቀሉ ዜጎች ፤ የክልሉ መንግሥት እንዲጠየቅ እንደሚፈልጉ ተናግሩ።

" የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንዲጠይቀን እንፈልጋለን " ያሉት ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች ናቸው።

ተፈናቃዮቹ ይህን የጠየቁት ፤ ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት በዞኑ ተገኝቶ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ነው።

ተፈናቃዮች ምን አሉ ?

" ኦሮሚያ ክልል፤ ተወልደን ያደግንበት፣ ትዳር መስርተን ልጆች የወለድንበት፣ ኃብትና ንብረት ያፈራንበት ክልላችን ሆኖ ሳለ ከክልላችን ስንፈናቀል የክልሉ መንግስት የት እንደወደቅን መጠየቅ አለመቻሉ አሳዝኖናል።

ከክልላችን ስንፈናቀል ከ60 ዓመታት በላይ ያፈራነውን ኃብትና ንብረት ይዘን መውጣት አልቻልንም።

ድጋፍ ከመንግስት መጠበቅ ሰልችቶናል መንግስት የጸጥታውን ጉዳይ በፍጥነት ይፍታልንና ወደ ክልላችን መመለስ እንፈልጋለን።

የዕለት ደራሽ ምግብ እጥረት ገጥሞናል ፤ እጥረቱ በተለይም በሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ የሚመለከተው አካል በፍጥነት ይድረስልን። " ብለዋል።

ተፈናቃዮችን ሄዶ የተመለከተው ቡድን ለተፈናቃዮቹ በተለይም ደግሞ ሕፃናት፣ ሴቶችና አረጋዊያን በዕለት ደራሽ የምግብ አቅርቦት እጥረት ምክንያት ከመጎዳታቸው በፊት የሚመለከታቸው አካላት የተሟላ የዕለት ደራሽ ምግብ ሊያቀርቡላቸው ይገባል ሲል አሳስቧል።

በመጠለያ ጣቢያዎቹ የመፀዳጃ እና ሻወር ቤቶችን ተዘዋውሮ በተመለከተበት ወቅትም መፀዳጃና ሻወር ቤቶች  ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ቢሆኑም፤ በመጠለያ ጣቢያዎቹ ያለው የተፈናቃይ ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ተጨማሪ መፀዳጃና ሻወር ቤቶች መገንባት እንዳለበት አሳስቧል።

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ በዞኑ ከ44 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ አሳውቋል።

ያጋጠመውን የዕለት ደራሽ ምግብ እጥረት ለመፍታት ዞኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የከፋ ችግር እንዳይደርስ እየሰራ መሆን ገልጿል።

አስተዳደሩ ፤ የችግሩን ስፋትና ክፋት ለማስረዳት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቢነጋገርም ለችግሩ እልባት እንዳልተሰጠው አሳውቋል።

ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋምና ወደ ቀያቸው ለመመለስ ቋሚ ኮሚቴው ሚናውን እንዲወጣ ተጠይቋል።

Via HoPR

@tikvahethiopia
#ቴክኖ

የላቁ ፈጠራዎችን እጅግ ከዳበሩ ግልጋሎቶች ጋር የያዘው አዲሱ Tecno Camon 20 Series ለተጠቃሚዎች እጅጉን የላቀ አገልግሎትን ዘመኑ ከድረሰበት ዲዛይን ጋር ይዞ ቀርቧል !

ዘመኑ ያፈራውና ከፍተኛ አቅም እንዳለው የሚነገርለትን ፕሮሰሰር የያዘው ካሞን 20 Series ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ በፍጥነት እና ያለ እንከን በመስራቱ በሞባይል ስልክ በመጠቀም ብዙ ስራዎችን ለሚሰሩ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ያደርገዋል።

45ዋት የፍጥነት ቻርጅ የማድረግ አቅም ያለው ባለ5000 ሚሊአሚፒር ባትሪ የያዘው ይህ ሞዴል አገልግሎትን ያለ ማቋረጥ እየሰጠ ቀኑን ሙሉ ያለ ስጋት እንድንጠቀም ያስቸለናል።

#CamonSeries #TecnoMobile #TecnoEthiopia

(ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ)
#COOP

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ @coopbankoromia ደንበኞች ኮፔይ ኢብርን በመጠቀም በቀላሉ ነዳጅ እንዲሞሉ በማድረግ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የነዳጅ ማደያ ሠራተኞችን ሸለመ::

በ1ኛው ዙር የ55 ኢንች ሶኒ ቴሌቪዥን፣ ልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ስማርት ስልኮች እና ታብሌቶች የተሸለሙት ባለሞያዎች ፊንፊኔ፣ ዲሬዳዋ፣ ሃፈቴሳ፣ ቦቴ እና ቢሻን ጉራቻ ከሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች መሆን ችለዋል። ሽልማቱ ለሁለተኛና ሶስተኛ ዙር ይቀጥላል።
@coopbankoromia
#ትግራይ #መቐለ

" ስካይ ማይክሮፋይናንስ አ/ማ " የተሰኘ የቁጠባና የብድር የፋይናንስ ተቋም በይፋ ተመሰረተ።

የስካይ ማይክሮፋይናንስ ሰብሳቢ አቶ ግርማይ ካሕሳይ በይፋዊ የምስረታ ፕሮግራም ባሰሙት ንግግር ተቋሙ በመላ አገሪቱ መንቀሳቀስ የሚያስችለው ፍቃድ ከብሄራዊ ባንክ ማግኘቱንና ዘመኑ በሚጠይቀው ቴክኖሎጂ በመታገዝ የቁጠባ ፣ የገቢ ወጪ እንዲሁም ገንዘብ የመቀበል እና የማስተላለፍ የሃዋላ  አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል ።

የአንድ አክስዮን የሽያጭ ዋጋ አንድ ሺ ብር መሆኑና በግለሰብ 10,000 ፤ በተቋም 30,000 አክስዮኖች መግዛት እንደሚቻል ያብራሩት ሰብሳቢው ፤ ተቋሙ  በሚቀጥሉት ስድስት ወራት መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል። 

የትግራይ ክልል የፋይናንስ ፎረም አስተባባሪና የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ  ዶ/ር መብራህቱ መለስ " የፋይናንስ እንቅስቃሴ በድህረ ግጭት ወቅት " በሚል ርእስ ባቀረቡት ፅሁፍ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ የፋይናንስ ተቋማት ምስረታ በመላ አገሪቱ መስፋፋቱንና ፤ በትግራይ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ  59 ቢሊዮን ብር የቆጠቡ ፤ ከ70 ሚሊዮን ብድር መስጠት የቻሉ 1074 ቅርንጫፍ ያላቸው 44 የፋይናንስ ተቋማት እንደነበሩ ገልፀው ፤ ተቋማቱ በተካሄደው ጦርነት ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርገዋል ብለዋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የፋይናንስ ዘርፉ በክልሉ መነቃቃት ማሳየት እንደጀመረ የዚሁ ማሳያ ስካይ ጨምሮ 45 የግል የፋይናንስ ተቋማት በምስረታ ላይ መሆናቸው ዶ/ር መብራህቱ አስታውቀዋል።

ባለፉት ሶስት የጦርነት አመታት የትግራይ የፋይናስ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱንና ይህንን ለማዳንና ክልላዊና አገራዊ ፋይዳው እንዲጎለብት የፌደራል መንግስት የተለየ ትኩረት መስጠት ይገባዋል ብለዋል ዶ/ር መብራህቱ መለስ።  

የምስረታ ፕሮግራሙ ተሳታፊ  ወ/ሮ ለምለም ሃይሚካኤልና አቶ አስገዶም አሰፋ በሰጡት አስተያየት የተበታተነ ፋይናንስ በቁጠባ መልክ በማሰባሰብ መልሰው ለአገርና ህዝብ እድገት ብድር በመስጠት ኢኮኖሚው የሚደገፉ የግል የፋይናንስ ተቋማት የመንግስት ልዩ ትኩረትና ጥበቃ ይሻሉ ።  

በስካይ ማይክሮፋይናንስ አ/ማ ይፋዊ የምስረታ ፕሮግራም ባለ አክስዮኖች የሃይማኖት መሪዎች :  በፋይናንስ ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ተቋማት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ለማወቅ ችለናል።

@tikvahethiopia
" በየትኛውም ዓለም ፤ በየትኛውም ሀገር ዋነኛው ቀጣሪ የግሉ ዘርፍ ነው " - አቶ ንጉሱ ጥላሁን

በአፍሪካ ሀገራት የስራ እድል ፈጠራዎች ላይ ባሉ ፈተናዎች እና ምቹ ሁኔታዎች ላይ የሚመክር የስራ ፈጠራ ማድረክ በአ/አ አፍሪካ ህብረት ግቢ ውስጥ ተጀምሯል።

ትላንት በነበረው መድረክ ላይ የተሳተፉት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በየአመቱ 2 ሚሊዮን አዳዲስ ስራ ፈላጊዎች እየተፈጠሩ ነው ብለዋል።

ለስራ ፈላጊ ዜጎች በተለያየ የስራ ዘርፍ ስራ ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ በውጭ ሀገርም ትልቅ እድል እንዳለ አሳውቀዋል።

አቶ ንጉሱ ፤ " በየአመቱ በእቅድ ተይዞ ነው የሚሰራው።

ለምሳሌ በ2015 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ100 ሺህ ዜጎች በውጭው አለም ለመፍጠር ነው የታቀደው፤ ከዙህ ውስጥ 85 በመቶ በቤት ውስጥ ስራ 15 በመቶ skilled የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የዓመቱን ማጠቃለያ እንገመግማለን የአመቱን እቅድ እንደምናሳካ መረጃዎች ያሳያሉ።

ከዛ ባሻገር በውጭ ሀገር ገበያ በርካታ ፍላጎት አለ፤ 2 ሚሊዮን ያህል የስራ ገበያ ፍላጎት አለ።

በአንዳንድ ሀገራት ተወዳዳሪ ሆነን እስከተገኘን ድረስ ዋናው ብቃት ያለው ሰው ፣ ታታሪ ፣ ታማኝ ፣ ምርታማ የሆነ ፣ ስነምግባር ያለው ፤ ብቃት ያለው ተወዳዳሪ የሆነ ሰው ማዘጋጀት ከቻልን ሰፊ እድል አለ " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአዲሱ በጀት ዓመት የመንግሥት አዲስ ሰራተኞች የስራ ቅጥር እንደሌለ በገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ የተደረገውን ውሳኔ በተመለከተ አቶ ንጉሱ ተጠይቀው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ንጉሱ ፤ ስራ መፍጠር ያለበት መንግሥት ብቻ ነው የሚለው የቆየ አስተሳሰብ መቀየር አለበት ብለዋል።

" እኔ ምረዳው እውነታውም ጭምር መንግሥት ዋነኛ ስራ ቀጣሪ አይደለም። በየትኛውም ዓለም ፤ በየትኛውም ሀገር ዋነኛው ቀጣሪ የግሉ ዘርፍ ነው። መንግሥት የግሉ ዘርፍ ሁኔታዎችን እንዲመቻቹለት ማድረግ ነው የሚጠበቅበት ፤ ይሄንን የስራ እድል ለመፍጠር የማያስችሉ ፖሊሲዎች ፣ መመሪያዎችን አሰራሮችን ማውጣት ፣ የገንዘብ አቅርቦት እንዲሟላ ማድረግ ፣ የቴክኖሎጂ ትስስር ሽግግር እንዲኖር ማድረግ ፣ መሰረተ ልማት ማሟላት ፣ የገበያ ትስስር እንዲኖር ማድረግ የመንግስት ድርሻ ነው " ሲሉ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል።

" እነዚህ ሁሉ የተሟሉ ሲሆኑ ፤ አገልግሎት ሲሟላ የግሉ ዘርፍ ይስፋፋል ያድጋል ፣ ኢንቨስትመንት ይሰፋል በዚህ ምክንያት የስራ እድል ይፈጠራል መንግሥት ሁሉንም ጀምሮ የሚጨርስ አይደለም። ዘንድሮ 3.1 ሚሊዮን የስራ እድሎች ተፈጥረዋል እስካሁን ከዚህ ውስጥ በመንግሥት መ/ቤቶች እና ተቋማት የተቀጠረው በጣም ዝቅተኛ ነው ከ3.1 ሚሊዮኑ መቶ ሺህ የማይሞላ ወደ 92 ሺህ ያህል ነው ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ ያለው ፤ በመንግሥት የስራ ዘርፍ ያሉት እድሎች ውስን ናቸው ጥቂቶች የሚገቡባቸው ናቸው ፤ ይልቁንም መንግሥት ማድረግ ያለበት ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮ በርካታ ዜጎች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው የሚያስችሉ ኢንተርፕራይዞች እንዲሰፉና እንዲያድጉ ማድረግ ነው " ብለዋል።

አቶ ንጉሱ ፤ " በባለፈው ዓመት ከለየነው 6 ሚሊዮን የስራ ፈላጊ ፤ ወደ 650 ሺህ አካባቢው ምሩቅ ነው ፤ ይሄንን ምሩቅ ከቴክኒክና ሙያ እና ከዩኒቨርሲቲ የተመረቀ መንግሥት ሁሉም ቦታ ላይ አስገባዋለሁ ቢል ቦታው የለውም ፤ ይሄን ሁሉ ምሩቅ እና ስራ ፈላጊ መንግሥት ማድረግ ያለበት አሰልጥኖ አብቅቶ የገንዘብ አቅርቦት አመቻችቶ የስራ ቦታ አመቻችቶ የስራ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅበታል። " ሲሉ ተደምጠዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተፈታኞች ፈተናውን ያለምንም ጭንቀትና ስጋት በጥንቃቄ ስሩ " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ያለምንም ጭንቀትና ስጋት ተረጋግተው እንዲወስዱ መልዕክቱን አስተለልፏል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

በዚህ መልዕክቱ ፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በተማሩት የትምህርት መስክ ከፍተኛ ግንዛቤ ያላቸውን ተመራቂዎች ለማፍራት እንዲቻል የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። ከእነዚህም መካከል አንዱ የመውጫ ፈተና መስጠት እንደሆነ አመልክቷል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ በየትኛውም የትምህርት መስክና ከየትኛውም የአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው የሚወጡ ተማሪዎች በኦንላይን የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ እየሰራ መሆኑና የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ቀንም በአገር አቀፍ ደረጃ ሰኔ 30 ቀን በጤናና ተጏዳኝ መስኮች መሰጠት መጀመሩን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ፈተናው በኦንላይን እንዲሰጥ ሲያደርግ በየደረጃው ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ የቆየ መሆኑንና አስፈታኝ ተቋማትም  ያደረጉትን ዝግጅት መገምገሙን ጠቁሟል።

ባደረገው ክትትልና ግምገማም ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት  ተቋማት ፈተናውን ለመስጠት በሚያስችል ዝግጅትና ቁመና ላይ መሆናቸውን እንዳረጋገጠ ገልጿል።

በተጨማሪ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የፈተና አዘገጃጀቱን በበላይነት ሲመራና ሲከታተል መቆየቱን ጥያቄዎቹ በየዘርፉ መምህራን እንዲዘጋጁና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ መስራቱን አስገንዝቧል።

ይህ የመውጫ ፈተና ሁሉንም  የቅድመ ምረቃ ድግሪ የሚሸፍን ነው ያለው ሚኒስቴሩ ፤ በዲጂታል መሰጠቱ ልዩ ያደርገዋል ብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ገልጾ ለተፈታኝ ተማሪዎችም ጥያቄዎቹ የተዘጋጁት በቆይታቸው ከተማሯቸው ርዕሰ ጉዳዮች መሆኑን ተገንዝበው ያለምንም ጭንቀትና ስጋት በጥንቃቄ እንዲሰሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
" ጥቃቱ በጣም አሳዛኝ ነው ለማን እንደሚነገርም አይታወቅም " - የአይን እማኝ

ትላንት ምሽት ላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ መተከል ዞን፣ ግልገል በለስ ከተማ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በትንሹ ከ6 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአንይ እማኞች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ አሳውቀዋል።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መጎዳታቸው ተነግሯል።

አንድ የአይን እማኝ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ጥቃቱ በከተማው አቅራቢያ የተፈፀመ መሆኑንና የ6 ሰዎች አስክሬን ሲነሳ በአይናቸው መመልከታቸውን ገልጸዋል።

" እኛም የህግ አካል አልደረሰልንም ፤ በአይን ያየሁት የ6 ሰው ሲነሳ ነው ፤ መኪና ላይ ያለው ወደ መንደር 7 ሄዷል ስንት እንደሆነ አላወኩም " ብለዋል።

ሌላ አንድ የአይን እማኝ ደግሞ ታጣቂዎቹ በፈፀሙት ጥቃት ከዚህም ከፍ የሚል መሆኑን ገልጸዋል። እስከ ጥዋት ድረስ አስክሬን ሲሰበሰብ የቆሰሉ ሰዎችን የማንሳት ስራ ሲሰራ ነበር ብለዋል።

" ህዝብ እና ሽፍታ አንድ ላይ እየተቀመጠ የከባድ መሳሪያ ይዘው ይንቀሳቀሳሉ ፣ ሹፌር አስቁመ ይዘርፋሉ ፣ ህዝብን ይገድላሉ፣ ያስራሉ ይደበድባሉ ትላንት ደግሞ ህዝብን አዘናግተው ብዙ ሰው ፈጁ ፤ የገደሏቸው ሰዎች አስክሬን ሲለቀም ነበር ፤ እነሱ ቤት ገብተው የገደሉበት ቦታ ሌላው ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታል ገብተው እየታከሙ ነው ፤ መለስተኛ ጉዳትም የደረሰባቸው አሉ ፤ ብዙ የሞቱ አሉ አስክሬናቸው ሲለቀም ነበር ከሰፈርም ከቤት ውስጥም እና በጣም አሳዛኝ ነው ለማን እንደሚነገርም አይታወቅም " ብለዋል።

የአይን እማኞቹ ጥቃቱን የተፈፀሙት በቅርቡ ከትጥቅ ትግል እራሳቸውን አግልለው በከተማው ቅርብ ርቀት በሚገኘው " ቻይና ካምፕ " የሰፈሩ ታጣቂዎች መሆናቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ጠቁመዋል።

ጥቃቱን በተመለከተ የክልሉ / የዞኑ ኃላፊዎች ምላሻቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ ጥረት ቢደረግም አለመሳካቱን ሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

ከዚህ ቀደም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን በመተከል ዞን ፤ በሁለት ወረዳዎች 90 የታጣቂ አባላት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ትጥቃቸውን ለመንግስት ማስረከባቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ሲቢኢ ብር
ለፈጣን፣ ቀላል፣ አስተማማኝ የነዳጅ ክፍያ አገልግሎት!

***************

 ወደ ሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Quick Pay’ በመግባት ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ መርጠው
• የነዳጅ ቀጂውን የተመዘገበ ስልክ ቁጥር፣
• የሚገዙትን የነዳጅ ክፍያ መጠን፣
• የነዳጅ አይነት፣
• የሰሌዳ ቁጥርዎን፣ እና
• የሚስጥር ቁጥርዎን አስገብተው ክፍያውን በማከናወን ነዳጅ መቅዳት ይችላሉ፡፡

 ወይም ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው
• ሲቢኢ ብር የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ߹
• የሰሌዳ ቁጥርዎን ፣
• የሚቀዱትን ነዳጅ የገንዘብ መጠን አሳውቀው ግብይቱን ሲያስጀምሩ በሚደርስዎት አጭር መልእክት መሠረት የገንዘብ መጠኑን ትክክለኛነት አረጋግጠው የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት እና ክፍያውን በመፈፀም ነዳጅ መቅዳት ይችላሉ።

ስለሲቢኢ ብር አገልግሎት በቂ መረጃ ለማግኘት ወደ 951 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ!

*********************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787