TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AliBirraa

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ " ጋርመንት " አካባቢ ባለው አደባባይ የተገነባው የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ መታሰቢያ ሐውልት ተመርቋል።

በሐውልቱ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል ፦

Rabbi moo namumaa
Kan seera jallisee ?
Haati teenya takkaa
Maaltu addaan nu baasee ?

አምላክ ወይንስ ሰው ፤
ሕግን ያጣመመው ?
የአንድ እናት ልጆች ነን ፤
የሚለያየን ማን ነው ?

Photo Credit : Alamudin Mustefa ፣ FBC ፣ EBC

@tikvahethiopia
#OLF50

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የ50ኛ ዓመቱን ለማክበር ዝግጅት ላይ ይገኛል።

ኦነግ ፤ እኤአ 1973 ሐምሌ 01 የተመሰረተ ሲሆን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በአንጋፋነቱ ይጠቀሳል።

ድርጅቱ 50ኛ ዓመቱን በአገር ውስጥና በተለያዩ አገራት በድምቀት ለማክበር ማቀዱን አሳውቋል።

ይህንን የ50ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ ወቅት አቶ ዳውድ ኢብሳ ፤ በፓርቲው የትግል ሂደት ውስጥ የተሰው ጓዶቻቸውን አስታውሰው አመስግነውአቸዋል፡፡

ስለወቅታዊ አገራዊ ፖለቲካ እና የፓርቲያቸው ይዞታ ማብራሪያም ሰጥተዋል። ለአሁናዊው በተለይም የኦሮሚያ አለመረጋጋት መነሻ ያሉትንም ሃሳብ አስቀምጠዋል፡፡

አቶ ዳውድ ምን አሉ ?

" በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል በእኤአ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ሰምምነት ተደርሶ ነበር፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት ጦርነት ቆሞ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ) በህዝቡ መሃል ሆኖ በነጻነት የፖለቲካ እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን፤ ለዚህም ሙሉ መብት አለው የሚል ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር  (ኦነግ) ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተመሳሳይ ነገር እንደሚፈቅድ ነው የተስማማው፡፡ የስምምነታችን አስኳሉ ይህ ነው፡፡

ከዚህ ጋር የተያያዙ የሰራዊታችንና ሰላም ጉዳይም በስምምነቱ ውስጥ ነበር፡፡

አሁን ላይ ይህ መከዳቱ ነው ላለፉት አምስት (5) ዓመታት በኦሮሚያ የቀጠለውን ጦርነት ያስከተለው፡፡  ለትግራይ ጦርነት እና አሁን በአማራ ክልል እየተስፋፋ ላለውም ቀውስ መሰረት የሆነው።

ስምምነቱ ላይ ተግዳሮት መግጠሙን ተከትሎ ፓርቲያችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ወከባ ደርሷል።

...ስምምነታችንን በመሻር ነው መንግስት በደቡብ እና ምዕራብ እንዲሁም በመሃከለኛው አከባቢ ያሉ የኦነግ ሰራዊት ላይ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ተኩስ የከፈተው፡፡

ይህን በማድረግ ሂደት ውስጥ ሽማግሌዎችም በመሃል ገብተው ፤ የቴክኒክ ኮሚቴ በሚባልም ጥረቶች ሲደረጉ የነበረው፡፡ ያም አልሆነም ጦርነቱ ቀጠለ፡፡  መንግስት በተለያዩ ጊዜያት ይህን ሰራዊት አጠፋዋለው በሚል በተደጋጋሚ መግለጫ ሲያወጣ ነበር፡፡ ያ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡

ያ ጦርነት ጫካ ብቻ ሳይሆን እዚህ ከተማ ውስጥ የኦነግ ጽ/ቤቶችን በመዝጋትና አመራሮቹን በማሰር የፓርቲውን እንቅስቃሴ በመግታትም ጭምር የተደረገ ነበር፡፡

አሁንም እንደ እኛ እምነት በኦሮሚያ ሰላም የሚሰፍነው መንግስት ከዋናው ባለጉዳይ ከእኛ ጋር ተቀምጦ ያ ስምምነታችን ሲከበር ነው ብለን እናምናለን፡፡ "

Credit : ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OLF50

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አለው ?

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፤ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ አማካኝነት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው  መግለጫ ወቅት ፓርቲው መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ ስለሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) የታጠቀ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው እንደሆነ ማብራሪያ ሰጥቷል።

አቶ ዳውድ ኢብሳ ምን አሉ ?

" የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር አሁን ላይ ግንኙነት አለው ወይ ለሚለው፤ ያ ሰራዊት የፖለቲካ ጥያቄ ያለው ሰራዊት ነው፡፡

አባላቶቹን ለምን እንደሚታገል አስተምሮ ነው ወደ ጦር የሚያሰማራው፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ደግሞ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ይህን ትግል #በሰላማዊ መንገድ እያካሄደ ነው፡፡

ይህ መንግስት አለመግባባቱ በተፈጠረ ጊዜ ኦነግን ገመድ ውስጥ አስገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን ነው የጠየቀው፡፡ ትጥቅ አልፈታም ያለው ያ ሰራዊት የኔ ነው ወይስ አይደለም እንድንል፡፡

በወቅቱ ከአባገዳዎች ጋር ሆነን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ባደረግነው ጉባኤ መንግስት ስምምነቱን አፍርሷል ብለን በማመናችንና ጦሩን ማስገባት ስርዓት ስላለው እኛ በወቅቱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ለአባገዳዎች ሰጥተን ነው ከመሃል የወጣነው፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከጦሩ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡

ያን ተከትሎ በምርጫ ቦርድ በሕጋዊ መሰረት ብንንቀሳቀስም ይሄው ቤት ውስጥ እስከመታገት የሚደርስ ጫና ደርሶብናል፡፡ የኦነግ እንቅስቃሴ ግን በተለያየ መንገድ ቀጥሏል እንጂ አይገታም፡፡

አሁንም የምንጠይቀው መንግስት ሰላም እንዲወርድ ተቀምጦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ግደታውን ይወጣ።

በኦሮሚያ ለሁሉም ዜጋ እኩል ክብር እንዲሰጥና መከባበር እንዲሰፍን እንጠይቅላለን። "

@tikvahethiopia
የተማሪዎች ምረቃ እና የመውጫ ፈተና ማለፍ / አለማለፍ ለምን አይነጣጠልም ?

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዜዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው ፦

" የ Graduation Ceremony ጉዳይ ፤ በጣም ብዙ ስብሰባ እያደረግን ነው የምንሰራው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ።

አንዳንድ ጊዜ መመሪያዎችም ሲወጡ ተሳትፈንበት ፣ ተወያይተን ጠይቀን አንዳንድ ጊዜ compromise አድርገው win win situation እየተደረገ ነው የወጣው።

Graduation (ምረቃ) እስከ ዛሬ የነበረው ምን ነበር ? ይሄ የመውጫ ፈተና (exit exam) ታሪክ ከመምጣቱ በፊት፤ በአዋጅ መሰረት አንድ ተማሪ የተወሰነ ፕሬግራሙን አሟልቶ የትምህርት ቤቱ ሴኔት approve አድርጎት ልጁ Graduate ማድረግ ይችላል ሲባል Graduate ያደርጋል ፤ ዲግሪውን ያገኝ ነበር።

አንዳንዶቹ ደግሞ ለመርዳት ብሎ walk የሚያደርጉ ይባላሉ ፤ walk የሚያደርጉ ማለት በዛ ዓመት አንድ class ስለቀረችው ልጁ next year ድረስ ከሚቆይ ለበዓሉ አብሮ ይሳተፍ ምክንያቱም አንድ ዓመት ለመሳተፍ ለምን ይቆያል ቤተሰብ አሉት፣ ለቤተሰቡ almost ጨርሻለሁ ብሎ ሊሆን ይችላል አንድ class ነች ያገኛታል ተብሎ ሲታሰብ አብሮ walk እንዲያደርግ ይድረጋል ፤ ይሄም አብሮ ይሳተፋል ፤ የፎቶ ዕድል ያገኛል።

ይሄ ማለት ፎቶግራፍ እና ጋዎን ስለለበሰ ልጁ Graduate አድርጓል ማለት አይደለም። የceremonyውን part አብሮ ይሳተፍ ምንም ለውጥ የለውም የሚል ነገር ነበር እኛ ለምሳሌ (ዩኒቲ) walk ማድረግ አቁመናል ቆይቷል እኛ ጋር ለምረቃ የሚገባው ልጅ የሴኔትን approval አግኝቶ የት/ቤቱን ፖሊሲ አክብሮ ከጨረሰ Graduate ያደርጋል፤ ceremony ላይ ይሳተፋል።

አሁን exit exam መጥቷል ፤ ይህ ሲመጣ መጀመሪያ ላይ ሲነገር የነበረው ኃላም ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው ' ምረቃ የምትባለዋ ነገር exit exam ላለፈ ልጅ ብቻ ነው ' አሉ ምን ማለት ነው ምረቃ የምትሰጠው ከሆነ ዲግሪውን እየሰጠኸው ስለሆነ ያ የሚሆነው exit exam ሲያልፍ ነው።

ስለዚህ exit exam ያለፈ ተማሪ ከሆነ ብዥታ የለም።

አሁን Situation የመጣው የexit exam ውጤት ሳይሳካለት ቢቀር / ቢሳካለት የሚለውን ትተን እኛ ceremony ላይ የኛን የሴኔት ጉዳይ የጨረሰ ሴኔት approve ያደረገው ግን exit exam ላይ ያልተሳካለት አብሮ በዓሉ ላይ ቢያከብር ምን አለበት ? የሚል ነው።

እኛ ያደረግነው አዎ እነዚህን ሰዎች እናሳትፋቸዋለን፤ የኛን የሴኔት ጉዳይ የጨረሱ ከሆኑ exit exam ብቻ ያለፉትን አናደርግም ለበዓሉ፤ ለበዓሉ አብረው ይሳተፉ። ይሄ ቅርብ ጊዜ ያደረግነው ነው።

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተገናኝነት ለምንድነው exit exam ያለፉትን ብቻ የምታደርጉት እነዚህም ቢሳተፉ ምን አለበት ? ብለን ይሄ የናተ ጉዳይ ነው አለን ትምህርት ሚኒስቴር እኔ አቋሜ exit exam ተፈትኖ ምረቃ የሚለው ዲግሪ ስትሰጠው ነው አሉ።

እኛ የምናደርገው ግን ceremony ይሳተፋል፣ walk ያደርጋል ፤ ዲግሪውን ግን አያገኝም። እንኳን ዲግሪ temporary የሚባለውን አንሰጠውም። በዚህ ተስማምተናል።

ምረቃት ላይ ከባችለር ውጭ የexit exam የማይመለከታቸው የማስተርስ ተመራቂዎችም ይሳተፋሉ ፤ በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ላይ የጨረሱ exit exam አይመለከታቸውም እነሱም በሴኔቱ ውሳኔ መሰረት ይሳተፋሉ። ሶስተኛው exit exam ይወስዳል የተባለው ሴኔቱን ካሟላ በምረቃ በዓሉ ላይ እንዲሳተፍ እናደርገዋለን። "

@tikvahethiopia
Audio
#ይደመጥ

- የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ጉዳይ እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስጋት

- የተማሪዎች ምረቃ እና የመውጫ ፈተና መያያዝ

- የሬሜዲያ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ

- የትምህርት ጥራት እና ፈተና

እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮች የተዳሰሰበት " ፋና ቴሌቪዥን " ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ከላይ በድምፅ ፋይል ተያይዟል።

ፋይሉ 13 MB ነው።

Credit - #FBC

@tikvahethiopia
#advertorial

(Harmony Hills Academy)

በሦስት ካምፖሶቹ ከቅድመ መደበኛ (Pre KG) እስከ 12 ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምረው ሀርመኒ ሂልስ አካዳሚ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት ወላጆች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል

ትምህርት ቤቱ በ2008 ጀምሮ 270 ተማሪዎችን ይዞ የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ በሦስት ቅርርንጫፎቹ 2300 ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኝ ሲሆን ከ300 በላይ ቋሚ ሰራተኞች አሉት።

ትምህርት ቤቱ በከተማ ደረጃ ሞዴል በሚሆን መልኩ በአካቶ ትምህርት የልዩ ፍላጎት (Special Needs) ተማሪዎችን በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን ከ48 በላይ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

ትምህርት ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ በከተማ ደረጃ በደረጃ ሦስት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2014 የቅድመ መደበኛ ት/ቤቱ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የልምድ መቅሰሚያ ሆኖ የዋንጫና የሰርተፊኬት ሽልማት አግኝቷል።

በተመሳሳይ ተማሪዎቻችን በከተማ ደረጃም ሆነ በክፍለ ከተማ ደረጃ ተወዳዳሪዎችና በተለያዩ ውድድሮች አሸናፊዎች ጭምር ናቸው።

ትምህርት ቤቱ በመጪው የትምህርት ጊዜም ባሉት ውስን ቦታዎች ከሐምሌ 1 ጀምሮ የተማሪዎች ምዝገባ የሚያደርግ ሲሆን በጎሮ እንዲሁም በሰሚት በሚገኙት ት/ቤቶቻችን መጥተው መጎብኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ 0938979797 / 0911437536 /0911202059 ይደውሉ።
" . . . እኛ ከፓርላማው በታች ከሆነው ከምርጫ ቦርድ ጋር የምንጨቃጨቅበት ምክንያት የለም " - ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ " ሕወሓት " ን ሕጋዊ ሰውነት ጥያቄ እንደገና እንዲመልስ ለማድረግ ከመንግሥት ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ " ሕወሓት " ን እንደገና ላለመመዝገብና ሕጋዊ ዕውቅና ላለመስጠት ያሳለፈው ውሳኔ፣ ትክክል ያልሆነና ፖለቲካዊ መሆኑን የገለፀው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ ጉዳዩ በቅርቡ በንግግር ዕልባት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አሳውቋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለተከተ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሥር የማኅበራዊ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት ለሪፖርተር ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ፕሮፌሰር ክንደያ ምን አሉ ?

" ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከምርጫ ቦርድ ጋር ቴክኒካዊ ንግግር የሚያደርግበት ምክንያት የለም።

ከዚያ ይልቅ ጉዳዩ ፖለቲካዊ ስለሆነ ከመንግሥት ጋር በተጀመረው ፖለቲካዊ ውይይት ይፈታል። "

ይህም ሆኖ ምርጫ ቦርድ የ " ሕወሓትን ዕውቅና አልመልስም " ቢል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድና ለመሞገት ወይም እንደ አዲስ ፓርቲ ለመመዝገብ ጥረት ታድርጋላችሁ ወይ ? ተብሎ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት፦

" ሁለቱም አማራጮች አይሆኑም።

እኛ የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት የተፈራረምነው ከመንግሥት ጋር ነው፡፡ ይህ ጉዳይም የስምምነቱ አንድ አካል ነው፡፡

የአገሪቱ ከፍተኛ የሥልጣን ባለቤት ፓርላማው ሕወሓትን ከሽብርተኝነት መዝገብ ሰርዟል፡፡

እኛ ከፓርላማው በታች ከሆነው ከምርጫ ቦርድ ጋር የምንጨቃጨቅበት ምክንያት የለም።

ጉዳዩ ፖለቲካ ነውና ከመንግሥት ጋር ንግግር ጀምረንበታል፤ ከመንግሥት ጋር ጥሩ መግባባት ያለን በመሆኑ በቅርቡ ይፈታል ብለን እንጠብቃለን። "

ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ ምን ነበር ? በዚህ ይመልከቱ ፦  https://t.me/tikvahethiopia/78399

@tikvahethiopia
የ ' ቅጥር ደመወዝ ' አልበቃ ቢላት ፤ ፊቷን ወደ " ሊስትሮነት " ያዞረችው የምህድስና ምሩቋ ምንታምር በለጠ ፦

" ስሜ ምንታምር በለጠ እባላለሁ።

በሊስቶር ስራ ነው የምተዳደረው አዲስ አበባ፤ ቦሌ አካባቢ ።

የተወለድኩት በአማራ ክልል ፣ ዳንግላ ከተማ ነው። ተወልጄ የተማርኩትም እዛው አካባቢ ነው።

እናት አባቶቼ አቅመ ደካማ ነበሩ። አሁን ላይ በህይወት የሉም ሁለቱም። እህቶች እና ወንድሞች አሉኝ።

ዩኒቨርሲቲ የገባሁት በ2007 ዓ/ም ነው በ2011 ዓ/ም በቴክስታይል ኢንጂነሪንግ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቄያለሁ።

ከተመረቅኩ በኃላ ስራ ፍለጋ ነበር የወጣሁት ፤ ስራ ቶሎ ማግኘት ከባድ ስለነበር ወደ ሐዋሳ ነው የሄድኩት።

ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገባሁ፤ በ2500 ብር ደመወዝ ስራ ጀመርኩ የስራ ድርሻዬ የጥራት ደረጃ ማስጠበቅ ቁጥጥር ነበር እሰራበት የነበረው ጨርቃ ጨርቅ ነው፣ ጋርመት ቲሸርቶች ሱሪ ይሰራል እሱ ላይ ጥራት መቆጣጠር ነበር የኔ ስራ።

እዚያ ሁለት ዓመት ሰራሁ ፤ ከዛ በጦርነቱም በ #AGOA / አጎዋ ምክንያት እየቀነሱ ነበር ድርጅቶቹ ሰራተኞችን ፤ ከእሱ ወጥቼ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።

አዲስ አበባ መጥቼ እንደጠበኩት ስራ አላገኘኹም። እየፈለኩኝ ነበር አንዳንድ ቦታዎችም ገብቻለሁ ፤ ደሞዝ የማይሰጥ ድርጅትም አጋጥሞኝ ያውቃል፤ ብዙ ተግዳሮቶችን አሳልፌያለሁ።

ሰው ቤት በተመላላሽነት ምግብ መስራትም ጀምሬ ነበር መጨረሻ ላይ ሊስትሮ / ጫማ ማስዋብ ጀመርኩ።

ዲግሪ ይዣለሁ ፤ ያሳፍራል ዲግሪ ጥቅም የለውም፤ በዲግሪ ስራ ማግኘት አልቻልኩም። ባገኝም ህይወቴን Survive የማያደርግ  ፣ የቤት ኪራይ የማይከፍል ፣ ቤተሰብ የማያስተዳድር ፣ ህይወቴን የማይቀይር ደመወዝ ነው ያለው።

ቤተሰብ መርዳት ቀርቶ እራስን መቀየሪያ የለም ፤ እኔ ዩኒቨርሲቲ ስማር የገዛሁትን ልብስ ነው እስካሁን የምለብሰው ፤ ምናልባት ይሄን ሊስትሮ ከሰራሁ በኃላ ልገዛ እችላለሁ።

ከጥዋቱ 11:30 ከቤቴ እወጣለሁ ፤ ታክሲ ይዤ እዚህ ስራ ቦታዬ ላይ 12:30 ደርሳለሁ ፤ ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:40 ድረስ ስራ ቦታዬ ላይ እገኛለሁ።

ደስ ብሎኝ ነው የምሰራው፤ የራሴ መመሪያ አለኝ ፤ በጥዋት ተነስቼ መጥቼ እሰራለሁ፤ ለኔ መስሪያ ቤቴ ድርጅቴ ነው።

ወጣቱ ተስፋ መቁረጥ የለበትም ፤ ያኔ ተስፋ ቆርጬ እራሴን አልጎዳሁም አማራጭ ሳጣ ወደ ሊስትሮ ዝቅ ብዬ መስራት እንዳለብኝ አእምሮዬ ነገረኝ ፤ ይህንን በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ይሄን ወጥሬ ስለምሰራ እራሴን ለመቀየረ፣ ወደዓላማዬ ፣ ወደ መንገዴ ያስገባኛል።

ከዚህ በኃላ የተሻለ ነገር መስራት አስባለሁ። ከዚህ ቀጥሎ ከሞያዬ ጋር ስለሚያያዝ ወደ ፋሽን ፣ ጋርመንት ፣ ስፌት ሞያ ሰልጥኜ ፣ ትንሽዬ ማሽንም ይሁን ገዝቼ ወደዛ የማዘንበል እቅድ አለንኝ። "

Credit : BBC AMHARIC

@tikvahethiopia