TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጋምቤላ . . . ኦሮሚያ

" በአካባቢው #ሰላም አስፍኛለሁ " - የሀገር መከላከያ ሰራዊት

ይህ ከጋምቤላ ወደ ሸበል ደንቢዶሎ የሚወስደው መንገድ ላለፉት 3 ዓመታት በፀጥታ ችግር ተዘግቶ ቆይቷል።

በዚህም ምክንያት ፤ ዜጎች ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግር ሲገጥማቸው ነበር።

አሁን ላይ ግን ሀገር መከለከያ ሰራዊት መንገዱ ለኅብረተሰቡ አገለግሎት መስጠት እንዲችል የሰላም ማስከበር በመስራት መንገዱ እንዲከፈት ማድረጉን አሳውቋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት " በቀጠናው የተሰጠኝን የሰላም ማስከበር ግዳጅ በአግባቡ በመወጣት በአካባቢው ሰላም አስፍኛለሁ " ብሏል።

ማኅበረሰቡ በስፋት የሚገናኝበት እንዲሁም የገበያ ትሥሥሩን የሚያጠናክርበት መንገድ ዳግም በሰላም መደፍረስ እንዳይዘጋ የመንግሥት ኃላፊዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የመከላከያ ሰራዊቱ አስገንዝቧል።

በዚህ ቀጠና ባለፉት 3 ዓመታት በነበረው ግጭት ሕዝቡ ክፉኛ የተጎዳ ሲሆን በተለይ የመንገዱ መዘጋት በሕዝቡ  #የኢኮኖሚያዊ እና #ማኅበራዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ቀውስ አስከትሏል።

#GambellaPressSecretariat

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#4freemarket

#አስፈላጊ_ምርቶች ፤ በተመጣጣኝ_ዋጋ

ለተጨማሪ ማብራሪያ የቴሌግራም ገፃችን : https://t.me/forfreemarket

አነስተኛ የልብስ እና ጫማ ማጠቢያ
👉 ለጫማ ለልብስ ቦታ የማይዝ
👉 ለፓንት፣ ቦክሰር እና ካልሲ
👉 ለቲሸርት
 👉ለዳይፐር

አድራሻ ፦ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ
ስልክ፦ 0911255787፣ 0983360606
ጥራት መለያችን ነው!
" ብሩህ ኢትዮጵያ "

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፤ " ማሰልጠን ፣ መሸለም ፣ ማብቃት " በሚል መርህ የሚያካሄደው እና በሁሉም ክልሎች ከወረዳ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው " ብሩህ ሀገር አቀፍ የንግድ ሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር " ከ200 የክልል ተወዳዳሪዎች እሸናፊዎቹን የሚለይበት መርሐ ግብር እየተዘጋጀ ይገኛል።

የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንዲሁም ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆኑ ወጣቶችን የመፍጠር ተልዕኮን አንግቦ በ2013 ዓ.ም የተጀመረው የፈጠራ ሥራ ውድድር በዚህ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህ ዓመት ከየክልሉ የተመዘገቡት 1016 የፈጠራ ሃሳቦች ሲሆኑ ከዩኒቨርሲቲዎች 127 ናቸው ተብሏል።

ለውድድሩ የመመልመያ መስፈርትና ፎርማቶችን በማዘጋጀት ለ1240 ወረዳዎች፣ ለ98 ዞኖች ለፖሊቴክኒክ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች በየክልሎቹ አማካይነት እንዲሰራጭ የተደረገ ሲሆን ውድድሩ ይፋ ከተደረገበት እስከ ሚያዚያ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ከተማ አስተዳደሮች እና ክልሎች ከወረዳ ጀምረው አወዳድረው የተሻለ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን በማበረታታት በፌደራል ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ዝግጁ እንዳደረጉ ተገልጿል።

ከየክልሉ ያለፉት 200 ተወዳዳሪዎች ከዛሬ ግንቦት 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተዘጋጀላቸው ቡራዩ ተሰጥዖ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የማሰልጠኛ ካምፕ ( Boot camp) የሚገቡ ይሆናል ተብሏል።

በቆይታቸው ኢንተርፕርነርሺፕ፣ ሃሳብን ወደተግባር መቀየር እና የንግድ አመሰራረትን በተመለከተ ስልጠና ይሰጣቸዋል።

ካምፕ ከገቡት ተወዳዳሪዎች መካከል በየደረጃው ተወዳድረው አሸናፊ የሚሆኑትን 50 ምርጥ ሀሳቦች በፌዴራል ደረጃ በመሸለም ብሩህ ኢትዮጵያ 2015 ውድድር የሚጠናቀቅ ይሆናል።

እስካሁን በተካሄዱ 7 ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ውድድሮች በአጠቃላይ 2,412 አመልካቾች የተሳተፉ ሲሆን ለ400 ሃሳብ ባለቤቶች ወይም 552 ወጣቶች (343 ወ፤ 129 ሴ) የቡትካምፕ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡በአጠቃላይ ለ 167 ምርጥ ሃሳቦች የ 1,518,00 ዶላር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

" ብሩህ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኃሳቦች ውድድር " ፕሮግራም በኢትዮጵያ በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ እና በማህበረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ቁልፍ ችግሮችን ለመፍታትና የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚችሉ አዳዲስ ሀሳቦች ይዘው የሚመጡ ወጣቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ የውድድር መርሐ ግብር ነው።

@tikvahethiopia
" ይህ ድርጊት መቼም ይፈፀም መቼ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል "

ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በታጠቁና የፀጥታ ኃይሎችን ልብስ በለበሱ አካላት እጅግ ዘግናኝ የግፍ ግድያዎች ሲፈፀሙ በቪድዮ ታይቷል።

ከምንም ነገር በላይ እጅግ በጣም አሳዛኙ ተግባር ደግሞ የሚሰሩትን ዘግናኝ ስራ ልክ በጎ ነገር እንዳደረጉና መልካም እንደሰሩ በቪድዮ ቀርፀው ማሰራጨታቸው ነው።

ቪድዮውን ሚቀርፃቸው ሌላ ሶስተኛ ወገን ሳይሆን ደግሞ እራሳቸው ገዳዮቹ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በቪድዮ ህዝብ ዘንድ ደርሶ በታዩት ብቻ (ሌሎች በቪድዮ ያልታዩ ብዙ ግፎች ይኖሩ ይሆናል) እጅግ በርካቶችን ቁጣ ውስጥ የከተተ ሲሆን የድርጊቱ ፈፃሚዎች ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ ሲጠየቅ ነበር።

ከሰሞኑን ደግሞ ከዚህ ቀደም ያልታየ አንድ እጅግ በጣም ዘግናኝ ቪድዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተዘዋወረ ይገኛል።

ቪድዮው ፤ ላይ በቁጥር አራት (ከቪድዮ ቀራጩ ውጭ) የፀጥታ ኃይሎችን ልብስ የለበሱ የታጠቁ አካላት ሁለት ሰዎችን ጫካ ውስጥ አስገብተው እጃቸውን የኃላ የፊጥኝ አስረው በጥይት ደብድበው ሲገድሏቸው ይታያል።

ወደ ኃይላ የፊጥኝ ታስረው የነበሩትን ግለሰቦች የገደሉት በቪድዮው እንደታየው ሁለቱ ሲሆኑ አንድ የሬድዮ መገናኛ በእጁ የያዘ ሰው ደግሞ " በለው " ብሎ ትዕዛዝ ሲሰጥ ይታያል።

ድርጊቱ / ቪድዮ መቼና የት ? ቦታ ላይ የተፈፀመ / ተቀረፀ ለሚለው የተሟላ መረጃ ለጊዜው ማግኘት ባይቻልም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ እና በአግባቡ በተሟላ ሁኔታ በታጠቁ አካላት ስለመፈፀሙ የሚያጠራጥር አይደለም።

የፀጥታ ኃይሎች ስለታጠቁ ብቻ ይህንን ግፋዊና ከስርዓት ውጭ የሆነ አረመኔያዊ እርምጃ መውሰዳቸው በርካቶችን ያሳዘነ እና ያስቆጣ ሆኗል።

የሚመለከተው የመንግሥት አካል ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ስለጉዳዩ ማብራሪያ ሊሰጡበት ይገባል።

ይህ ድርጊት መቼ ? የት ? ተፈፀመ ፤ የተገደሉት ግለሰቦችስ እነማን ናቸው ? ፍትህ ተገኝቷል ወይ ? የሚለው መልስ ያሻል ፤ ድርጊቱ መቼም ይፈፀም መቼ ግን ተጠያቂነት ሊሰፍን፤ የማስተማሪያ እርምጃ ሊወሰድ የግድ ይላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... በከተማው የንጥቂያ እና ዝርፊያ ወንጀሎች #መባባስ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ እያስነሳ ነው " - የጋምቤላ ፖሊስ በጋምቤላ ከተማ በሞተር ሳይክሎች ላይ የሰዓት ገደብ ተጣለ። በጋምቤላ ከተማ በተሽከርካሪ የሚፈፀም ስርቆትና ዝርፊያን ለመከላከል ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች ላይ እገዳ መጣሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ…
በወንጀል ድርጊት የተማረሩት ነዋሪዎች  . . .

በጋምቤላ ከተማ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መፍትሄ ያገኙ ዘንድ በጋምቤላ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠየቁ።

አንድ ነዋሪነቱ በጋምቤላ ከተማ የሆነ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ በከተማው ማታ እንዲሁም በቀን ሳይቀር ዘረፋና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች መበራከቱን ገልጸው የጋምቤላ ክልል መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

" ቀን ላይ እንኳ ከዋናው አስፓልት በቀር አብዛኞቹ ቦታዎች ላይ ሰው ብቻውን ለመሄድ እስከሚሰጋ ድረስ ነው ወንጀል የተበራከተው "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

ሌላ የጋምቤላ ቲክቫህ አባል ፤ በከተማው የወንጀል ድርጊት እጅግ መስፋፋቱን በመግለፅ እንደ ከዚህ ቀደሙ በነፃነት ወጥቶ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ሆኗል ሲል ገልጿል። በመሆኑም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የከተማው ደህንነት እንዲጠበቅ ማድረግ ይገባል ሲል አስገንዝቧል።

ሌሎችም የቤተሰቦቻችን አባላት በከተማ ዝርፊያ፣ ንጥቂያ እና ሌሎችም ወንጀሎች መስፋፋታቸውን በመጠቆም አስቸኳይ እና አስተማማኝ መፍትሄ እንዲበጅ ጥሪ አቅርበዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የጋምቤላ ፖሊስ ፤ በጋምቤላ ከተማ የንጥቂያና ዝርፊያ ወንጀሎች #መባባሱንና ይህም በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ እያስነሳ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

በተለይ በተሽከርካሪ የሚፈፀም ስርቆትና ዝርፊያን ለመከላከልም ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች ላይ እገዳ ጥሏል።

እንደ ፖሊስ መረጃ በከተማዋ እየተስፋፋ በመጣው የዝርፊያና መሰል ወንጀሎች በዋናነት ተጠቂዎቹ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ናቸው።

Via @tikvah_eth_BOT

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

ሳዑዲ አረቢያ ከነዳጅ ምርቷ በቀን 1 ሚሊዮን በርሜል እቀንሳለሁ ማለቷን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ተነገረ።

ሌሎች የዓለማችን ነዳጃ አምራች አገራትም በተመሳሳይ የነዳጅን ዋጋን ለማረጋጋት በማሰብ የምርት አቅርቦታቸውን ለመቀነስ ተስማምተዋል ተብሏል።

ሳዑዲ አረቢያ በቀጣዩ ሀምሌ ወር በየቀኑ 1 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከምርት አቅርቦቷ ላይ እንደምትቀነስ የገለጸች ሲሆን የነዳጅ ላኪዎች ሀገራት ማህበር ወይም ኦፔክ+ እንደ አውሮፓውያኑ በ2024 ዕለታዊ የነዳጅ አቅርቦት በ1.4 ሚሊዮን በርሜል እንደሚቀንስ ገልጿል።

ኦፔክ+ የዓለምን 40 በመቶ የነዳጅ ፍላጎት የሚያሟላ ሲሆን ውሳኔው በዓለም የነዳጅ ምርት ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።

የሳዑዲን ውሳኔ ተከትሎ በእስያ ገበያ የደፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ 2.4 በመቶ አሻቅቦ በበርሜል 77 ዶላር ሆኗል።

የሳዑዲ ኢነርጂ ሚንስትር ልዑል አብዱላዚዝ ቢን ሰልማን ፤ የነዳጅ ምርት አቅቦቱን የመቀነሱ ውሳኔ አስፈላጊ ከሆነ ከሃምሌም በኃላ #ሊራዘም ይችላል ብለዋል። ውሳኔው የዓለም የነዳጅ ዋጋን እንደሚያረጋጋ ገልጸዋል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#መቐለ

አምባሳደር ማይክ ሀመር ትግራይ ክልል፣ መቐለ ይገኛሉ።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ለመነጋገር ዛሬ መቐለ ገብተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሀመር መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ በትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና በአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በትግራይ ቆይታቸውም በፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀም፣በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከክልሉ ቴሌቪዥን በተገኘው መረጃ ፤ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ጋር ​​ተወያይተዋል።

@tikvahethiopia
#ጋዜጣዊ_መግለጫ : " በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል " - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋዜጣዊ_መግለጫ : " በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል " - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን @tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር (Enforced Disappearance) እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ (incommunicada Detention) ሰዎችን ጉዳይ ሲከታተል ከቆየ በኃላ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

ኢሰመኮ ምን አለ ?

- በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን ተረጋግጧል።

- አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን፣ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ሌሎች ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው፡፡

- ከተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው፡፡

ምሳሌ ፦

#1

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በማስገደድ ተሰውረው ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ከተለያየ የጊዜ መጠን መሰወር በኃላ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የተገኙ ሲኖሩ፣ አስገድደው በተሰወሩበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ " ገላን " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የቀድሞው ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ተይዘው እንደቆዩ ለማወቅ ተችሏል። በአስገድዶ መሰወሩ ወቅት ተፈጽሟል ስለተባለ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ ወይም #የማሰቃየት ተግባር ኮሚሽኑ ምርመራውን ቀጥሏል።

#2

በአማራ ክልል በባሕር ዳር እና በደብረ ብርሃን ከተማ የአስገድዶ መሰወር ሰለባዎች የሆኑ ሰዎችን ጉዳይ ኮሚሽኑ ሲከታተል ቆይቶ ነበር። ከነዚህም ውስጥ አንድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል " ከሠራዊቱ ከድቷል " በሚል በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ወረብ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወላጅ #አባቱን " ልጅህን አምጣ " በሚል ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በግዳጅ ተወስደው ተሰውረው ከቆዩ በኋላ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለቀዋል፡፡

#3

አንድ የቀድሞ የ " ሶማሊ  ክልል  ልዩ  ኃይል " አባል ታኅሣሥ 6 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ከቢሮ ተደውሎለት ለሥራ ጉዳይ ቢሮ እንዲመጣ ተጠርቶ ከሄደ በኋላ በዕለቱ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጅምሮ ስልኩ የተዘጋ ሲሆን ከዚያ ቀን ጀምሮ የት እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

#4

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ቢያንስ #ሰባት ሰዎች የአስገድዶ መሰወር ድርጊት ሰለባ መሆናቸው ለኢሰመኮ አቤቱታ ቀርቦ ክትትል እየተደረገባቸው ነው።

ከእነዚህ መካከል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው ይገኝበታል፡፡

ይህ ግለሰብ ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በወረዳው ፖሊስ ከሌሎች ሦስት ጓደኞቹ ጋር ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ ከገባ በኋላ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሌሎቹ ታሳሪዎች ተለይቶ ነቀምት ከተማ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወሩ ለቤተሰብ የተነገረ ቢሆንም ከዚያ ቀን ጀምሮ ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

በተመሳሳይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የምሥራቅ ወለጋ ዞን የኦፌኮ አስተባባሪ የሆነ ሌላ ሰው ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ ከሚሠራበት መሥሪያ ቤት በመንግሥት #የደኅንነት_ኃይሎች ተይዞ ነቀምት ከተማ በሚገኘው የጸጥታ ቢሮ ውስጥ ታስሮ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት እንደነበረና እጁ በሰንሰለት በመታሰሩ ምክንያት ከቤተሰብ የሚሄድለትን ምግብ ተቀብሎ መመገብ ሲያቅተው ሰዎች የተመለከቱት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ግለሰቡ ከጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሊገኝ አልቻለም።

ቡራዩ በተለምዶ " አሸዋ ሜዳ " ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ተይዞ በቡራዩ ወረዳ 3 ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውሎ የቆየ አንድ ሰው ከሁለት ወራት የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ በኋላ አንድ ቀን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ (ቀነ በትክክል አልታወቀም) ከሌሎች እስረኞች ተለይቶ መወሰዱ የታወቀ ቢሆንም ፣ ከዚያን ቀን ጀምሮ ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ቁጥራቸው ከሃያ ያላነሱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ ሱሉልታ ወረዳ ፣ ለገጦ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ፣ ልዩ ስሙ " ረቡዕ ገበያ " ፣ 04 ቀበሌ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ በመምጣት አንድ ሰው ይዘው የሄዱ ሲሆን፤ በማግስቱ ቤተሰቦቹ ታሳሪውን ለመፈለግ ወታደሮቹ ይኖሩበት ወደነበረው ደርባ ቶኒ፣ አበባ ልማት ካምፕ ቢሄዱም ወታደሮቹ የተያዘው ግለሰብ ያበትን ሁኔታ ሊያሳውቁ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን፤ ይልቁንም ለመጠየቅ የሄዱ ሰዎች እስር እና ማስፈራርያ የደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። የተያዘው ግለሰብም እስከ አሁን ድረስ ያለበት ሁኔታ እና ቦታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

(ሙሉ መግለጫው በዚይ 👉 https://t.me/tikvahethiopia/78928?single ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DigitalLottery አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል። 3 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0102013522 ሆኖ ወጥቷል። 👉 3 ሚሊዮን ብር - 0102013522 👉 1,200,000 ብር - 0100663609 👉 800 ሺህ ብር - 0100706800 👉 400 ሺህ ብር - 0100750353 (ተጨማሪ የዕጣ…
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።

3 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 011851289 ሆኖ ወጥቷል።

👉 3 ሚሊዮን ብር - 0111851289
👉 1,200,000 ብር - 0111137546
👉 800 ሺህ ብር - 0112042798
👉 400 ሺህ ብር - 0110682365
👉 250 ሺህ ብር - 0111989047

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

ምንጭ፦ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia