TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉት 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ናቸው " - ቃሊቲ ማረሚያ ቤት

ከቃሊቲ ማረሚያ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ነበሩ የተባሉ ታራሚዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት  መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉር የከባድ ውንብድና ወንጀል ፍርደኛ ታራሚዎች መሆናቸው ተነግሯል።

ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃና የደኅንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ ለኤፍ ቢ ሲ የሰጡት ቃል ፦

" ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ላይ ማረሚያ ቤቱ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ለማምለጥ ሙከራ ካደረጉ ፍርደኞች መካከል ከዚህ በፊት #አምልጦ ከጣልያን ሀገር በኢንተርፖል ተይዞ የመጣ ታራሚ ይገኝበታል።

ሌሎችም በተደጋጋሚ ከጤና ጣቢያ ፣ከመኪና ላይ ጭምር ለማምለጥ ሞክረው የተያዙ ፍርደኞች አሉ።

ማረሚያ ቤቱ  ዛሬ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ቀጠሮ የነበራቸው ታራሚዎችን አጅቦ በማቅረብ መደበኛ ስራውን ሲሰራ ውሏል።

ታራሚዎቹ  ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ ተገቢ የሆነ  የክትትልና የቁጥጥር ስራው ይቀጥላል። "

Credit : #FBC

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ባላችሁበት ሆናችሁ የአፖሎ ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ፊታችሁንና መታወቅያችሁን ስካን በማድረግ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በማስገባት 5 ደቂቃ ባልፈጀ ጊዜ ውስጥ የአቢሲንያ ባንክ አካውንት መክፈት ትችላላችሁ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#AddisAbaba

ሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ስራ እየተከናወነ ሲሆን በዚህም " የንግድ ቤቶቻችን ያላግባብ ፈርሰዋል  ንብረቶቻችን በአጠቃላይ ተወስደዋል " ያሉ የአካል ጉዳተኞች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት " ይሄንን ግፍ እና በደል አቤት ለማለት ቅሬታችንን ለማቅረብ በሄድንባቸው የመንግሥት ተቋማት በጸጥታ አካላት ማዋከብ እና እንግልት እየደረሰብን ነው። " ብለዋል።

እንደዜጋ ተመልክቶ ምላሽ ሊሰጠን ፈቃደኛ የሆነ የመንግስት አካል የለም ሲሉ አሳውቀዋል።

" እንለምን አይደለም ያልነው እንስራ እንጂ ፤ እራሳችንን ችለን መንግስትን እናግዝ እንጂ መንግስትን አግዙን እርዱን አላልንም " የሚሉት እኚህ ወገኖች " ለራሳችን እና ለቤተሰባችን ጉሮሮ መሸፈኛ ከዛም አልፎ ሌሎች የስራ ዕድል የፈጠርንበት ረጅም የድካም አመታት አሳልፈን በአካል በጉዳተኝነታችን የሚደርስብንን ተፅዕኖ ተቋቁመን የገነባነውን ነገር ነው እንደቀልድ በሌሊት መተው አፍርሰውብናል " ሲሉ አስረድተዋል።

" እየተከናወነ ያለው የንግድ ቤቶች ፈረሳ ሕጋዊ ሥርዓትን ባልተከተለ መልኩ ነው " የሚሉት አካል ጉዳተኞቹ  " በተለይ አገራችን ከዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች የመብት ኮንቬንሽን ከፈረመችው ስምምነት ውጭ  ነው " ብለዋል።

ይህም አካል ጉዳተኞችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ የከተተ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት በአፋጣኝ ተገቢውን ምላሽ ከሚመለከተው አካል ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት እንደ ወንጀለኛ አካል ጉዳተኞችን በየመስሪያ ቤቱ እየተከታተሉ የሚያሸማቅቁ የሚያንገላቱ የሕግ አካላት መኖራቸውን በመጠቆም " በሀገራችን የሕግ የበላይነት ካለ በህግ አምላክ መብታችንን አስከብሩልን ለማለት እንወዳለን " ብለዋል።

ለመሆኑ የንግድ ቤቶች የፈረሱት የት ነው ?

" ሰላም ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች ንግድ አክስዮን ማኅበር " በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ከረሜላ ፋብሪካ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የ181 አባላቱ የንግድ ቤቶች እንደነበሩ ገልጿል።

ቦታው በ2001 ዓ.ም. አካል ጉዳተኞቹ በጊዜያዊነት እንዲሠሩበት የተሰጣቸው እንደነበር የገለፀው ማህበሩ አባላቱ ላለፉት 15 ዓመታት ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ሲያስተዳድሩበት መኖራቸውን አመልክቷል።

ባለፈው ሳምንት ግን " ከሸራ የተሠሩ ንግድ ቤቶች ይፍረሱ " ተብሏል በሚል፣ የንግድ ቤቶቹ መፍረሳቸውን አሳውቋል።

መንግሥት እና ኢሰመኮ ምን አሉ ?

የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች፣ የሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፤ ከንግድ ቤቶች ፈረሳ ጋር በተያያዘ ቀረበ ስለተባለው ቅሬታ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ ፤ ከንግድ ቤቶች ፈረሳ ጋር በተያያዘ ከ160 በላይ የሚሆኑ አካል ጉዳተኞች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ቅሬታ እንዳቀረቡለት አሳውቋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ካለው የንግድ ቤቶች የማፍረስ ሂደት ጋር በተገናኘ የንግድ ቤቶቻቸው ያላግባብ እንዲፈርሱ መደረጉን፣ ንብረታቸው መወሰዱን እንዲሁም ቅሬታቸውን ለማቅረብ በሄዱባቸው የመንግሥት ተቋማት በጸጥታ አካላት ማዋከብ እና እንግልት የደረሰባቸው መሆኑን ለኮሚሽኑ አስረድተዋል። 

ኮሚሽኑ ፤ ቅሬታቸውን ተቀብሎ የክትትል እና የምርመራ ሥራዎችን በአፋጣኝ እንደሚጀምር እና ግኝቶቹንም እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

Credit : የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፣ ኢሰመኮ፣ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ
ቪድዮ ፦ በወረቀት

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

አሁንም በተለያየ ምክንያት የጋራ መኖሪያ ቤት ውል ላልተዋዋሉ የቤት ባለዕድለኞች የመጨረሻ እድል ተሰጠ።

የቤት እድለኞችን ውል የማዋዋል ጊዜም እስከ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም ድረስ ተራዝሟል።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን  ፤ የ14ኛው ዙር የ20/80 እና የ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት እሰከ ግንቦት 30/2015 ባሉ የስራ ቀናት /ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ/ መራዘሙን አሳውቋል።

ከጥር 1 ጀምሮ እስከ ግንቦት 7 ተጠቃሚውን ሲያዋውል መቆየቱን ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ማስታወቂያ የገለፀ ሲሆን አሁንም በተለያየ ምክንያት ያልተዋዋሉ የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞችን የመጨረሻ እድል ለመስጠት ሲባል እሰከ ግንቦት 30 ማራዘሙን ገልጿል።

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያልተዋዋለ የቤት እደለኛ #ቤቱን_እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ለኮርፖሬሽኑ ተመላሽ እንደሚሆን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቀሪዎቹ 3 ሺህ 69 ቤቶች ከሁለት ወር በኃላ ጨረታ ይወጣባቸዋል " - ኮርፖሬሽኑ የ4ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ጨረታ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾችን ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን 5 ሺህ 397 ቤቶች ለጨረታ ቀርበው 2 ሺህ 328 ቤቶች አሸናፊ እንደተገኘላቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የ4ኛ ዙር…
#Update

የ40/60 ንግድ ቤቶች ጨረታ ወጣ።

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ ከተማ አስተዳደሩ በ40/60 ፕሮግራም በተለያዩ ክ/ከተሞች ያስገነባቸፍን 3310 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግንቦት 17/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም. ባሉት 28 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ፣ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ እስከ 6 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብና የማይመለስ ብር 400 በመክፈል መግዛት ይችላል ሲል ገልጿል።

የጨረታ ሳጥን ሰኔ 19/2015 ከምሽቱ 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ሰኔ 20/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራጮች በተገኙበት ይከፈታል ተብሏል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የጨረታ ሰነድ የት ነው የሚሸጠው ?

- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ

- ሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች ብሎክ 4

- የካ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ

- አራዳ ክ/ ከተማ ግቢ ውስጥ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ቢሮ ቁ/G03

- 40/60 ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት

- 40/60 አያት 49 ማዞርያ ብሎክ 21 ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት

@tikvahethiopia
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀል ችሎት አስታውቋል።

የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ፣ ፍ/ቤቱ በይፋ ክሥ ከመሠረተበት ካለፉት 22 ዓመታት ጀምሮ በሽሽት ላይ ነበር።

በተመድ የተቋቋመው ችሎት፣ ሥራውን ለሩዋንዳ በማስረከቡ፣ ካይሼማ፥ ለሩዋንዳ ተላልፎ እንደሚሰጥ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ካይሼማ ያለበትን ለሚጠቁም፣ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

ሌላው የዘር ማጥፋቱ ጠንሳሽ የተባለው ፌሊሲን ካቡጋ፣ ከ26 ዓመታት ሽሽት በኋላ ከሦስት ዓመት በፊት በፈረንሳይ ውስጥ መያዙ ይታወቃል።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ፣ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

#ቪኦኤ #ሩዋንዳ #Genocide

@tikvahethiopia
#ethio_telecom

የኢትዮ ቴሌኮምን አዲስ ሲም ካርድ ይበልጥ ተሻሽለው  ከቀረቡት የሲም ካርድ ማስጀመሪያ ጥቅሎች ጋር ሲገዙ ከ15 ብር የአየር ሰዓት በተጨማሪ እስከ 3 ጊ.ባ የሚደርስ የዳታ ስጦታ እንዲሁም ለአንድ ወር የሚያገለግል የጥሪ ማሳመሪያ አገልገሎት በነፃ ያገኛሉ

ሁሌም የተሻለውን፤ ምርጥ ምርጡን ለናንተ!
#SPECIALOFFER!!!  #buyandgetbonus
#Update

በ " ሸገር ከተማ " እየተካሔደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ተግባር በመቃወም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

እንደ ሀሩን ሚዲያ ዘገባ ፤ በተቃውሞው ሰልፎቹ የከተማ አስተዳደሩ እየሄደበት ያለው አካሔድ #ትክልል_አለመሆኑን እና #በአስቸኳይ እንዲያቆም የተጠየቀ ሲሆን ያፈረሳቸውንም መስጂዶች ይቅርታ ጠይቆ መልሶ እንዲገነባ ተጠይቋል።

በአንዋር መስጂድ በነበረው ተቃውሞ የፀጥታ ኃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን ኃይል ስለመጠቀማቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ በደረሰው መልዕክት የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ለማወቅ ችሏል።

እስካሁን በከተማ አሰተዳደሩ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

በአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ካለው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ ገልጾ የጁመዐ ኹጥባ በሸገር ከተማ የተደረገውን መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻን በማውገዝ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

እንደ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት መረጀ ፤ በአስተዳደሩ እስካሁን ከ19 በላይ መስጂዶች ፈርሰዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ መፃፉና በደብዳቤው በሸገር ከተማ እያፈረሱ ስላሉ መስጂዶች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ማስታወሻ 1.  https://t.me/tikvahethiopia/78657?single

ማስታወሻ 2. https://t.me/tikvahethiopia/78541?single

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
#ሸገር

" እየፈረሱ ያሉት ቤቶች #አሁንም በመንግስት መዋቅር ዉስጥ ባሉ ሃላፊዎች ይሁንታ የተሰሩ ስህተቶች መሆናቸዉን እናምናለን " ሲሉ የሸገር ከተማ ከንቲባ አስታወቁ፡፡

በቅርቡ የተቋቋመውን የሸገር ከተማ ተከትሎ በተለይ ከቤት ፈረሳ ጋር ተያይዞ በርካታ ቅሬታዎች ከመነሳታቸው ባሻገር ዜጎች በመንግስት አካላት ፍቃድ ቤቱን እንደገነቡ ቢገልጹም መፍትሄ ማግኘት እንዳልቻሉ ይገለጻል፡፡

ፍቃዱን የሰጡ የመንግስት አካላት አሁንም በሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው የዜጎች ቤት እንዲፈርስ እያደረጉ ነው የሚለው ቅሬታም በተደጋጋሚ ጊዜ ይነሳል፡፡

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ከአሃዱ መድረክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሸመ አዱኛ  ፤ ባለፈው የመንግስት መዋቅር ውስጥ በነበሩ የስራ ሃላፊዎች ስህተት ቤቶቹ እንደተሰሩ እንደሚያምኑ አስታዉቀዋል፡፡

#አሁንም እነዛ ሃላፊዎች በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን በመግለጽ ሆኖም ግን ለሰሩት ስህተት እርምጃ አለመወሰዱ ጥያቄ እያሥነሳ ቢሆንም ካለፈው ይልቅ ስለ ወደ ፊቱ በማሰብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለዉ መሰል ስህተቶች እንዳይደገሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቤት እየፈረሰባቸው ያሉ ዜጎች ለሚያነሱት ጥያቄ ምንም እንኳን በከተማዋ አስተዳደር ህገ ወጥ ስለሆናችሁ ነው የሚል ምላሽ ቢሰጣቸውም #ከመንግስት_አካላት ፍቃድ አግኝተው እንደሰሩ እየገለጹ ያሉ ግን በርካቶች ናቸው፡፡

Credit : Ahadu Mederk

@tikvahethiopia