TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ቢሯቸው ወስጥ በስራ ላይ እያሉ በጥይት ተመተው  የተገደሉት የአቶ አለባቸው አሞኜ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።

በአ/አ ከተማ የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኜ ዛሬ ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙን ከክ/ከተማው ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አቶ አለባቸው ፤ እድሜያቸው 33 የነበረ ሲሆን ባለትዳር እንዲሁም የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ አቶ አለባቸውን የገደላቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑንና በቁጥጥር ስር መዋሉን ማሳወቁ ይታወሳል።

ፎቶ፦ የቂርቆስ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የዘማሪት ሂሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር ሰኞ ግንቦት 7 ይፈፀማል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ባገኘው መረጃ ፤ የዘማሪት ሂሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር በጴጥሮስ ወ ጳውሎስ የሚፈፀም ይሆናል።

መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን  ፤ " ዘማሪት ሂሩት በቀለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም ሞት እንደሚያድን አምነው በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሕይወት አጥቢያ ሲገለገሉና ሲያገለግሉ ቆይተው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ወደ ጌታቸው እቅፍ ተሰብስበዋል " ብላለች።

ስርዓተ ቀብሩን ለማስፈፀም የተቋቋመ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ደግሞ ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ ሻላ መናፈሻ ጀርባ በሚገኘው የዘማሪት ሂሩት በቀለ ቤት ሽኝት እንደሚደረግ እና በወዳጅነት አደባባይም የሽኝት ስነስርዓት እንደሚከናወን ገልጿል።

በወዳጅነት አደባባይ በሚኖረው ስነስርዓት ላይ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አማካኝነት የፀሎት ስነሥርዓት እንደሚደረግ ተነግሯል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፤ ለዘማሪት ሂሩት በቀለ ቤተሰቦች እና ለወደጅ ዘመዶች በጠቅላላ መጽናናት የተመኘች ሲሆን ሁሉም በጸሎት አብሯቸው እንዲሆን አሳስባለች።

ዘማሪት ሂሩት በቀለ ትላንት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#UNHR

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝና አፈጻጸም የሚከታተለውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም አቀፍ ስምምነቶች አካላት (United Nations Human Rights -Treaty Bodies) በመባል የሚታወቀው የገለልተኛ ባለሙያዎች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አስከባሪ አካላት የሚፈጸሙ ማሰቃየትና እንግልቶች፣ በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩና ተጠርጣሪዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ እንዲያደርግ አሳሰበ፡፡

የሰብዓዊ መብት ም/ቤቱ የፀረ ማሰቃየት ኮሚቴ ይህን ያስታወቀው ኢትዮጵያን ጨምሮ በብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ካዛኪስታን፣ ሉክሰምበርግና ስሎቫኪያ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ የተናጠል ግምገማ ማጠቃለያ ሪፖርት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ይፋ ባደረገበት መግለጫ ነው፡፡

በመግለጫው ምን አለ ?

በኢትዮጵያ በፖሊስ መኮንኖች ፣ በእስር ቤት ጠባቂዎች እና ሌሎች ወታደራዊና የፀጥታ ኃይሎች በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በማቆያ ማዕከላት ፣ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ በወታደራዊ ካምፖችና በግልፅ በማይታወቁ ወይም #በሚስጥራዊ እስር ቤቶች ቅሬታ አቅራቢዎች የሚደርስባቸው ስቃይና እንግልት እጅጉን አሳስቦኛል ብሏል።

አሁንም ቢሆን በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚስተዋሉ ማሰቃየት ወይም እንግልት ቅሬታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ገለልተኛ፣ ምቹና ሚስጥራዊ ዘዴ አለመኖሩንና አሁናዊው የምርመራ አካላት ሁኔታ ተፈላጊው ገለልተኝነት እንደሚጎለው ግንዛቤ መወሰዱን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አስከባሪ አካላት የሚደርሱ ማሰቃየቶችና ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እንግልቶችን በተመለከተ የቀረቡ ቅሬታዎች፣ በገለልተኛ አካል እንዲጣሩና ተጠርጣሪ ድርጊት ፈጻሚዎችንና ድርጊቱን እንዲፈጸም ያዘዙና በቸልታ የተመለከቱ የሥራ ኃላፊዎች ለሕግ ቀርበው #እንዲጠየቁ እና #እንዲቀጡ ጠይቋል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ የተገኘው የአርቲስት ዳዊት ፍሬው አስክሬን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል። ትላንት በሮም ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፍታት እንዲሁም የአስክሬን ሽንት ፕሮግራም ተካሂዷል። የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ግንቦት 6 /2015 ከቀኑ 6 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት  ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈፀም ሲሆን…
#Update

የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ።

የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

አርቲስት ዳዊት ፍሬው በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ትምህርቱን 'ሜጀር ክላርኔት' በማድረግ የተመረቀ ሲሆን የአልቶ ሳክስፎን እና ክራር ተጨዋችም ነበር።

በአስደናቂ ክላርኔት ጨዋታው የሚታወቀው ዳዊት ፍሬው በሙዚቃ ትምህርት ቤት ቆይታው፣ የታላላቅ ሙዚቃ አቀናባሪዎች /ኮምፖዘሮችን/ የክላርኔት ሥራዎች ተጫውቷል።

በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ አልበሞችንም ለአድማጮች ማቅረብ ችሏል።

አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ውስጥ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ መገኘቱ ይታወሳል።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ትንንሽ ልጆችን ፤ ህፃናትን ከጀርባቸው በማሸከም የሚፈፀመው ልመና በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ...

ከላይ አንዲት ትንሽ ልጅ ፤ ህፃን በጀርባዋ ተሸክማ በመኪና የሚያልፉ ሰዎችን ስትልመን የሚያሳየውን አጭር ቪድዮ የላከልን አንድ በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

ቪድዮውን የቀረፀው ፤ " ለቡ መብራት ሀይል " መሆኑን ገልጾ በዚህ አካባቢ እንደዚህ አይነት አለማመን በጣም እየተበራከተ ነው ብሏል።

" የሚያሳዝነው የሚታዘሉት ህፃናት ቀኑን ሙሉ ተኝተው ነው የሚዉሉት። አንገታቸው እንዲህ ስብር ብሎ ማየት በጣም ያስጨንቃል በተለይ ደግሞ ልጅ ላለው ሰው " ሲል ስሜቱን ገልጿል።

" እንደሚመስለኝ የሚያሰማራቸው ሰው አለ " ያለው የኸው ቤተሰባችን " አዛዮቹ ራሱ በጣም ህፃናት ናቸው።  እባካችሁ ! የሚመለከታችሁ አካላት ክትትል አድርጉ " ሲል መልዕክቱን አስተለልፏል።

ሌሎች የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በዛው አካባቢ " በለቡ መብራት "  ፤ ህፃናት በማይችል አቅማቸው ከጀርባቸው ህፃን ተሸክመው ሲለምኑ ተመልክተው በፎቶ አስደግፈው መልዕክታቸውን ልከዋል።

እነሱም ቢሆን እነዚህን በጣም ትንንሽ ልጆችን ፣ ህፃናት አሸክሞ የሚያሰማራ አካል ሊኖር እንደሚችል በመጠርጠር ክትትል ቢደረግ እና የህፃናቱን ህይወት መታደግ ቢቻል እንዲኩም ጎዳና ላይ ላሉ ህፃናትም መፍትሄ ቢፈለግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Via @tikvah_eth_BOT

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ በቆቦ ከተማ እና ራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ 29 አርሶ አደሮች የትራክተር ባለቤት ሆነዋል።

አርሶ አደሮቹ ፤ #አማራ_ባንክ ባመቻቸው የብድር አገልግሎት የትራክተር ባለቤት መሆን እንደቻሉ ተነግሯል።

ባንኩ ባመቻቸው የብድር አገልግሎት የተገዙት ትራክተሮች ከአርሶ አደሮቹ ጋር ርክክብ ተፈፅሟል።

አርሶ አደሮቹ የመለዋወጫ እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦትን መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲያመቻችላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

አማራ ባንክ ፤ " የህዝብ ባንክ እንደመሆኔ  መጠን ከዚህም በላይ የተሻለ ነገር ለማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀራርቤ እየሰራሁ ነው " ብሏል።

አሁን አርሶ አደሮች ትራክተር እንዲያገኙ የተደረገበት የራያ ቆቦ አካባቢ #በጦርነት ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።

ፎቶ ፦ የራያ ቆቦ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን

@tikvahethiopia
ሲቢኢ ብር - ለቀላል፣ ፈጣን፣ አስተማማኝ የነዳጅ ግብይት!
=================
ደንበኞች ወደ ነዳጅ ማደያ ከመምጣታቸው አስቀድመው

• የሲቢኢ ብር አገልግሎታቸው በአግባቡ እንደሚሠራ ቢያረጋግጡ፣
• ሲቢኢ ብርን መጠቀም ካልጀመሩም ወደ *847# በመደወል፣ ወይም የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ በራሳቸው ተመዝግበው፤ እና
• በሲቢኢ ብር አካውንታቸው በቂ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጠው ቢመጡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

ስለ ሲቢኢ ብር አገልግሎት በቂ መረጃ ለማግኘት ወደ 951 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ!
*********************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
" ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " -  ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ (የኢሮብ ወረዳ ነዋሪ) #እናት

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚገኙ የኢሮብ ወረዳ ነዋሪዎች እርዳታ መቋረጡን ተከትሎ የከፋ ችግር ላይ መሆናቸው ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ በጦርነቱ ምክንያት ከቄያቸው ተፈናቅለው ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ።

" የሰብዓዊ እርዳታ ካቆመ ብዙ ጊዜ ተቆጥሯል " ያሉት ወ/ሮ ትብለፅ ልጆቻውን ለመመገብ መቸገራቸውን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ፤ " በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅዬ በመጠለያ ውስጥ ነው ያለሁት፤ እርዳታ ብዙም አላገኝም ነበር  ፤ አሁን ደግሞ ካቆመ ብዙ ጊዜ አልፎታል። በዚህ ሁኔታ ቤተሰብ ለማስተዳደር በጣም ከባድ ነው በፈጣሪ ኃይል ነው ያለነው። " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እርዳታ ቆሟል ፤ ይህ ከፍተኛ ስጋት ነው ያሳደረብን " የሚሉት ወ/ሮ ትብለፅ " ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " ሲሉ ምን ያህል አስከፊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አስረድተዋል።

ቀድሞውኑም ችግር ላይ የነበሩት እነዚህ ዜጎች አሁን ላይ እርዳታ ማቆሙ የከፋ ችግር ላይ ጥሏቸዋል።

አንዲት የኢሮብ ነዋሪ በሰጠችው ቃል " በአሁን ሰዓት ለህፃናት #ወተት ለመስጠት ቀርቶ አንድ ዳቦም ቢሆን አይናቅም ለእኛ ትልቅ እርዳታ ነው ፤ እርዳታ ወደዚህ መምጣት ካቆመ ብዙ ወራት አልፏል ረሃብ ላይ ነው ያለነው " ስትል ሁኔታውን ገልጻለች።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ አሁን ላይ የተገኘው ሰላም በጣም እንደሚያስደስት ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

" ህዝባችን ወደቦታው ተመልሶ ሰርቶ እንዲበላና ከእርዳታ ጠባቂነት እንዲላቀቅ የሚመለከታቸው አካላት በጋር መስራት አለባቸው " ሲሉ መልዕልት አስተላልፈዋል።

የኢሮብ ነዋሪዎቹ በአካባቢያቸው የኤርትራ ኃይሎች እንደሚንቀሳቀሱ በመጠቆም ይኸው ኃይል ከአካባቢው ለቆ እንዲወጣ እንዲደረግ የሚመለከታቸው አከላት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia