TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ... በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚደረግ የቤት ማፍረስ ዘመቻ ጋር በተገናኘ ቤት የፈረሰባቸው ዜጎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት ፦ • " ... #ቤት_ለመፈለግ እንኳን በቂ ጊዜ አልተሰጠም በዚህም እቃችንን ወደ ምናውቃቸው ሰዎች አሽሽተናል ፤ መጠለያ አጥተው ሜዳ ላይ የወደቁም ጎረቤቶችም አሉ። ቤት ለመከራየት እንኳን የቤት ኪራይ በዚህ ምክንያት ጨምሯል።" • " የዚህኛው…
የቤት ማፍረስ ዘመቻው ቀጥሏል።

አዲስ በተመሰረተው ሸገር ከተማ አሁንም የቤት ፈረሳ ዘመቻው መቀጠሉን የየአካባቢው ነዋሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

መንግሥት ቤቶችን እያፈረሰ የሚገኘው " ህገወጥ ነው " በሚል እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጿል።

ቤት እየፈረሰባቸው ያሉ ወገኖች ስለጉዳዩ ምን ይላሉ ?

⮕ በርካታ ቤቶች ናቸው እየፈረሱ ያሉት፤ እነዚህ ቤቶች ከገበሬ የተገዙ እና ረጅም ዓመታት ጭምር ሰዎች ሲኖሩባቸው የነበሩ ናቸው።

⮕ ከፈረሱት ቤቶች ውስጥ ዜጎች ለዓመታት ለፍተው የሰሯቸው ይገኙበታል።

⮕ ምትክ ቦታ/ ማረፊ ሳይመቻች ነው ሜዳ ላይ የተጣልነው።

⮕ መንግስት ዛሬ ላይ ህገወጥ ነው እያለ የሚያፈርሰው ቤቶቹ ሲገነቡና ይህን ሁሉ ዓመት ሲኖርባቸው የት ነበር ?

⮕ በአንዳንድ ቦታዎች ቤት የሚፈርሰው በለሊት ጭምር ነው፤ ሰዎች በተኙበት ምንም ሳይዘጋጁ እንዲፈርስባቸው ይደረጋል።

⮕ እየፈረሱ ካሉት ቤቶች መካከል አንዳንዶቹ የመብራት የውሃ ክፍያ፣ የአፈር ግብርም የፈፀሙ ናቸው።

⮕ ከቤት ማፍረስ ዘመቻው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ቤቶችን ማንነትን/ ብሔርን ለይቶ ማፍረስም ይስተዋል።

⮕ የሰብዓዊነት ጉዳይ ጭራሽ ከምንም የማይቆጠርበት ሁኔታ ነው እየተፈጠረ ያለው ፤ ነፍሰ ጡር እና በእድሜ የገፉ እናቶች እንዲሁም ህፃናትን ጨምሮ በርካቶች #ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እቃ እንኳን እንዳይወጣ ላያቸው ላይ ቤታቸው ፈርሷል።

ስለሚፈርሱ ቤቶች ከዚህ ቀደም የከተማው ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ ምን ምላሽ ሰጥተው ነበር (አንከር ለተሰኘ ሚዲያ)?

➣ የሚፈርሱት ለአንድ ከተማ ፀር የሆኑ ህገወጥ ግንባታዎች ናቸው።

➣ ህገወጥ ግንባታዎችን እናፈርሳለን ህጋዊ ከተማ መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን።

➣ በአስተዳደር ችግር ፣ ጠንካራ የሆነ አስተዳደር በፊት አለመኖር ምክንያት የግንባታ እና የመሬት ባለቤትነት፣ የግንባታ ፍቃድ ሳይኖር መብራት ማውጣት ይሄ ስራ አሁን ከሚፈለገው የከተማ ሂደት ጋር የማይሆኑ ነገሮች ነው የተፈጠሩት እነሱ በመኖራቸው አይፈርሱም የሚል ሳይንስ የለም። አንድ ሰው በስርዓት ካርታ መውሰድ አለበት፣ በስርዓት የግንባታ ፍቃድ ማግኘት አለበት፣ የክልሉ ህግና ስርዓት ጠብቆ መሄድ አለበት እነዚህ ሳይሟሉ በራሳችን መዋቅር ድክመት / አሰራር መብራት ስላልስገባ / ውሃ ስላስገባ የማይፈርስ የለም። ያ እንደጥፋት የምናየው ከአሁን በኃላ መደገም የለበትም።

➣ ሰብዓዊነት እኛም ይሰማናል መታየት ያለበት ግን ህግ መከበር አለበት፤ እኛ ይሄንን ከጨረስን በኃላ በክልል ደረጃም ይሁን በከተማ ደረጃ አንድ ሰው ቤት ማግኘት ሰብዓዊ መብቱ ስለሆነ እኛ በምናወጣቸው ፕሮግራሞች አካተን ያለውን ችግር መፍታት እንችላለን።

➣ የምናፈርሰው ግልፅ የሆነ አንድ ዘመናዊ ከተማ ላይ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው። ከእንቅፋቶቹ አንዱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የመሬት ወረራ እና ህገወጥ ግንባታዎች ነው ይሄን መሰረት አድርገን ነው የምንሄደው (የግንባታ ፍቃድ የሌላቸው፣ በስርዓት መሬት ያልወሰዱ፣ ካርታ የሌላቸው) ይሄን ነው የምንከተለው ፈረሳው ብሄርን / ዘርን መሰረት ያደረገ አይደለም። ማንንም ዒላማ አድርገን አይደለም የምንሰራው።

➣ ቅደመ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡን አወያይተን ፣ ህገወጥ እንዳሆኑ ነገረን ፣ ህገወጥ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ አስረድተን፣ ምልክት አድርገን ነው የምናፈርሰው ፤ በእኛ ሀገር ' ቤት ሰባቴ ካልፈረሰ ቤት አይሆንም ' የሚል የማይሆን አመለካከት ስላለ በአንድ በኩል አያፈርሱም ብለው ያስባሉ ቢፈርስም ትንሽ ዞር ሲሉ መልሰን እንገባበታለን የሚል ነገር አለ ስለዚህ እየነገርን እየታወቀ ነው ፈረሳው የሚደረገው።

@tikvahethiopia
" ክስ መቋረጥን ተከትሎ ከእስር የመፍታት ስራ ተጀምሯል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ውስጥ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየመከረ ይገኛል።

ቡድኑ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተወያየ የሚገኘው በትግራይ መልሶ ማቋቋም እና ሌሎች ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስለመሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ ልዑኩ በአዲስ አበባ ካሉ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ ጋር የተወያየ ሲሆን የትግራይ ተወላጆች ትግራይን መልሶ ለመገንባት እና ሁለንተናዊ ችግሯን በመቅረፍ የበኩላቸውን ለማበርከት " ዝግጁ ነን " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በዚሁ መድረክ ላይ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጥን ተከትሎ ከእስር የመፍታት ስራ መጀመሩን አሳውቀዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚያደርገው ምክክር መቀጠሉን የክልሉ ቴሌቪዥን / ትግራይ ቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ለመምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የመጋቢት ጨምሮ የ4 ወራት ደምወዝ ተከፍሏል " - ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ስራ ለመጀመር የሚያስችለው የዩኒቨርሲቲ ካዉንስል ስብሰባ ትላንት በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ አከናውኖ ነበር።

በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው አመራር አባላት ባካሄዱት ውይይት ስራ ለመጀመር የሚያስችል የሶስት ወራት እቅድ ስለማዘጋጀት አስፈላጊነት ስምምነት ተደርሶበታል።

በውይይቱ ወቅት በየደረጃው የተቀናጀ ጥረት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል ወደሚችልበት ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል ግንዛቤ ተወስዷል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ሁሉም ኮሌጆች፣ ትምህርት ክፍሎች፣ ዳይሬክተሮችና ሌሎች ፅ/ቤቶች መደበኛ ስራቸው እንዲጀምሩ መመርያ ተሰጥታል።

ዩኒቨርሲቲው ለመምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የመጋቢት ጨምሮ የአራት ወራት ደምወዝ የከፈለ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

#AdigratUniversity

@tikvahethiopia
#አሳዛኝ_የትራፊክ_አደጋ

ዛሬ በባንጃ ወረዳ " ዚቅ ጎመርታ " ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሠው ህይወት አለፈ።

ዛሬ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም በባንጃ ወረዳ ዚቅ ጎመርታ ቀበሌ 2:00 ሰአት አካባቢ የ " ዳሳሽ አካዳሚ ት/ት ቤት " ተማሪዎችን ወደቻግኒ ታሪካዊ ቦታዎችን ለማስጎብኘት ይዞ እየሔደ እያለ በደረሠ የትራፊክ አደጋ 3 የህፃናት ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

አንድ ህፃን እና አንዲት መምህር ደግሞ ወደ ህከምና እንደደረሱ ህይወታቸው አልፏል።

ሌሎች ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት ወደ እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። ወደ ህክምና ከገቡት መካከል 4ቱ አገግመው ወደ ቤተሠቦቻቸው ተቀላቅለዋል።

ወረዳው ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እንደሚሰጥ ገልጿል።

@tikvahethiopia
ለተሽከርካሪዎ ነዳጅ ሞልተው ጥሬ ገንዘብ 1.. 2... 3... ብለው ቆጥረው የሚከፍሉበት ዘመን እያበቃ ነው፡፡

ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት በሆነው ቴሌብር የነዳጅ ክፍያዎን በቀላሉ ይፈፅሙ፤ በአዲሱ ሱፐርአፕ ተጠቅመው በትራንዛክሽን ሪፖርት ወጪዎን በቀላሉ ይቆጣጠሩ!

አዲሱን የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ!

(ኢትዮ ቴሌኮም)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲያን_ባንክ

በካሽ ጎ በፍጥነት ሀገር ቤት ይድረሱ !

ቪዛ ወይም ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው በካሽጎ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ በነፃ ይላኩ፡፡

የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store ወይም  App Store በማውረድ ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች 👇
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

#CashGo #visa #mastercard  #የሁሉም_ምርጫ
" የቡድን እና የነፍስወከፍ መሳሪዎችን የማስፈታቱ ሂደት ዘግይቷል " - የብሔራዊ መልሶ ማቋቋም ኮሚሽን

የፕቶሪያውን የህወሓትና የፌደራል መንግስትን ስምምነት ተከትሎ ህወሓት ታጥቋቸው የነበሩ ከባድ መሳሪያዎችን የማስፈታት ሥራው በተሳካ ሁኔታ ቢፈፀምም፣ የቡድንና የነፍስወከፍ መሳሪዎችን የማስፈታቱ ሁኔታ በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን የብሔራዊ መልሶ ማቋቋም ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ይህን ያስታወቀው ዛሬ በባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው።

የተሀድሶ ኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ፤ አገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ ማለፏን ጠቅሰው ጦርነቱ ያስከተለውን ጥፋት በማየትና ካለፍንባቸው ችግሮች መማርና ወደ ሰላም መምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ በበኩላቸው፤ የፕሪቶያውን ስምምነት ተከትሎ የትግራይ ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ትጥቅ መፍታታቸውን ጠቁመዋል።

የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ግን በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ማስፈታት ሳይቻል መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

ለመዘግየቱ ዋነኞቹ ምክንቶች ፦ ኮሚሽኑ የቅድመ ዝግጅት ስራ ስለነበረበት፣  በትግራይ ክልል የሽግግር መንግስት ሳይቋቋም በመቆየቱና ሌሎች አንዳንድ መሰናክሎች እንደነበሩ ነው ያስረዱት፡፡

አሁን ግን ሁኔታዎች እየተስተካከሉ በመሆኑ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ተግባራት ይፈፀማሉ ብለዋል።

በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርን ዶ/ር ጌታቸው ጀንበርን ጨምሮ ሌሎች የሲቪልና ወታደራዊ ባለስልጣናት ተገኝተው እንደነበር ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#ቦረና

በ ' ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ' የተሰራ የውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ።

ፋውንዴሽኑ በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ፣ በቦኩ ሉቦማ መንደር እና ዱቡሉቅ ወረዳ የንፁህ ውሃ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ አስመርቋል።

ፕሮጀክቱ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት ተመላክቷል።

በዝግጅቱ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የመንግስት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የውሃ ፕሮጀክቱ የሁለቱን ወረዳዎች 52,325 ነዋሪዎችን የመጠጥ ውሃ ችግር ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን

@tikvahethiopia