TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቅዱስ ፓትርያርኩ ምን አሉ ?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ በቅርቡ በቤተክርስቲያኗ ላይ የደረሰው ችግር በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት በመፈታቱ እጅግ በጣም ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸውና ውጭ ሀገር የነበሩት እነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የመጡበት ወቅት አይነት ስሜት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

" በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር ችግር የሌለበት ጊዜ የለም " ያሉት ቅዱስነታቸው " ችግሩን በእውቀት ፣ በማስተዋል መፍታት ያለ ነገር ነው የኛም ድርሻ ነው ፤ አሁንም ቢሆን የተደረገው ይሄው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ቅዱስነታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትላንቱ ቀን እንደሚመጣ ብዙ መልፋታቸውንና መድከማቸውን አንስተዋል " ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ ለፍተዋል ፣ብዙ ደክመዋል በተለይ ሰሞኑን እንደው አላረፉም ፤ ሁላችንም እንደዚሁ፤ ወንድሞቻችንም ፣ አባቶችም ሲመላለሱ እንደሰናበቱ አውቃለሁና ይሄንን ታላቁን የቤተክርስቲያን ሚስጥር ወደ ቤቱ መመለሱ በጣም በጣም እጅግ የሚያስደስት ነው " ብለዋል።

" እናተም ደስ ሊላችሁ ይገባል አባቶች (የተመለሱ አባቶችን ማለታቸው ነው) ፤ ወደ ሰላም ስንመለስ አብረን ስንሆን ደስ ሊላችሁ ይገባል ፤ እኛ በእውነቱ የቀኖና ቤተክርስቲያን ስለሆነ ዝም ብለን ስንል ሰነበትን እንጂ ሃዘናችን አልቀረም ፤ እናተን ወንድሞቻችንን በማጣታችን እጅግ ልባችን ሳይቆስል አልቀረም፤ ነገር ግን ቀኖና ቤተክርስቲያን ለመጠበቅ ስለሆነ እኛም ኃላፊነት ስላለብን ነው ይሄን ሁሉ ስናደርግ የሰነበትነው እንጂ ደስ ብሎን አይደለም። ይህንን በማየታችን ደስ ብሎናል ፤ እኔም በጣም ተደስቻለሁ፤ ክብሩ ጠ/ሚኒስትር እናመሰግናለን። " ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Oromia

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ ታጥቆ ለሚብቀሳቀሰው የ " ኦነግ ሸኔ " ቡድን የሰላም እና የእርቅ ጥሪ አቀረቡ።

ጥሪውን ያቀረቡት ዛሬ በጀመረው በጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን ሁለተኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የክልሉ መንግስት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ወቅት "ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው፣ ሰላም በሌለበት ስለ ልማት ማሰብ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ሽመልስ ፤ የክልላቸው መንግስት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው ፤ " በዚህ በተከበረው ጨፌው ፊት በክልላችን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ማለትም ኦነግ ሸኔ በእርቅ ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመልሶ እንዲገባ በክብር ጥሪ አቀርባለሁ " ሲሉ ተደምጠዋል።

" መንግስት ለሰላም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ኦነግ ሸኔ እና መሰል የጥፋት ሃይሎች ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ እየሰራ ነው " ብለዋል።

በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እስከ ሕይወት መሰዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ የጸጥታ አካላትም ምስጋና ያቀረቡት ያቀረቡት አቶ ሽመልስ " ለክልሉ ሰላም የሰሩት ሥራ ሁሌም በታሪክ ስዘከር ይኖራል " ብለዋል።

የጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው ዕለት ማካሄድ በጀመረው ጉባኤው የሥራ አስፈፃሚ አካላትን የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በማድመጥ፣ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ለጨፌው የሚቀርቡ ሌሎች አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Credit : አል አይን ኒውስ

@tikvahethiopia
#አቢይ_ጾም

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ፓትርያርክ የአቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ዛሬ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት የተወሰደ ፦

" በሀገራችን እየታየ ያለው የሰላም ጭላንጭልና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ዝንባሌ በእጅጉ ጠቃሚና ለሁለንተና ልማታችንና ለዕድገታችን እንደዚሁም ለተሟላ አንድነታችን ጠቃሚነቱ የጎላ ስለሆነ እግዚአብሔር ለዘለቄታው እንዲያሳካልን ከልብ እንድናዝንና ወደ አምላካችን በተመሥጦ እንድንጸልይ በአጽንዖት በማሳሰብ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ 

መልካም የጾም ወራት ያድርግልን!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን ! "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዛሬ ባስተላለፉት የአቢይ ጾም መልዕክታቸው ስለ ሰሞነኛ የቤተክርስቲያን ጉዳይ አንስተዋል።

ቅዱስነታቸው፤ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በቤተ ክርስቲያኗ ተከሥስቶ የነበረውን ሕጋዊ ያልሆነ ድርጊት የቤተ ክርስቲያኗን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና ባሕላዊ መርሕን የናደ፣ እንደዚሁም በኢትዮጵያ ይቅርና በዓለም ታሪክ ተደርጎ የማያውቅ ድርጊት እንደሆነ ቤተ ክርስቲያኗ በአጽንዖት ስትገልጽ መቆየቷን ተናግረዋል።

"ይህንን የቤተ ክርስቲያን ድምፅ በመስማትና በመቀበል ሕዝበ ክርስቲያንና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለእግዚአብሔር ባቀረቡት ኃዘንና ጸሎት እንደዚሁም ባደረጉት መጠነ ሰፊና ዙርያ መለስ የሆነ የድጋፍ ርብርብ ስሕተቱ ሊታረም ችሏል" ብለዋል።

ለተገኘው መንፈሳዊ ውጤት ጠ/ሚንስትሩና መንግሥታቸውን፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲከበር ከፍተኛ መሥዋዕትነት ለከፈለው መላው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲሁም ይህ ስሕተት እንዲታረም ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን ተሰልፈው ድምፃቸውን ላሰሙ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በቤተ ክርስቲያኗ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው፤ ከቤተ ክርስቲያኗ ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዓት መከበር እንደዚሁም ከሉዓላዊ አንድነቷ መጠበቅ በመለስ ያለው ጥያቄ ለማስናገድ ቤተ ክርስቲያ ዝግጁ መሆኗን ለመላው ኢትዮጵያውያን አረጋግጠዋል።

ቤተ ክርስቲያ ሕዝቦች በቋንቋቸው የመማር፣ የማስተማርና የማምለክ እንዲሁም የመተዳደር መብትን ካሁን በፊትም፣ አሁንም፣ካሁን በኋላም የምትነፍግበት መሠረት እንደሌለና ይህን ሁሉም ሊያውቀው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቋንቋ የመጠቀም መብት በሕገ ቤተክርስቲያኗ በግልጽ መቀመጡን የገለፁት ቅዱስነታቸው፤ በቋንቋ የመጠቀም ጥያቄ በሕግ ደረጃ ተመልሶ በተግባር እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#AU #ETHIOPIA #AddisAbaba

እስካሁን  ወደ አዲስ አበባ የገቡ መሪዎች እነማን ናቸው ?

ለ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።

እስካሁን የገቡ ፦

- የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ
- የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ
- የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ ኦልድ ጋውዛኒ
- የኬፕቬርዴ ፕሬዚደንት ጆሴ ማሪያ ፔሬ
- የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ፋሊፔ ኒዪሲ
- የቻድ ፕሬዝዳንት መሃማት ዴቢ
-  የማዕከላዊ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጄ ቶውድራ
- የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሶው ንጌሶ
- የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ
- የሌሴቶ ፕሬዚዳንት ሳም ማትኬኔ

በተጨማሪም ፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣  የዑጋንዳ እና የደቡብ ሱዳንና የሊቢያ ምክትል ፕሬዚዳቶች እና የሌሎች የአፍሪካ አገራት መሪዎች እዚህ አዲስ አበባ ይገኛሉ።

Photo Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቀናት በፊት ስምምነት ላይ የደረሱት አባቶች ስምምነቱን እንዲሁም ቀኖናውን ደግመው መጣሳቸውን አሳወቀች።

ይህንን በተመለከተ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ፅህፈት ቤት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተከታዩን ብለዋል ፦

" ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል።

በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ነው።

ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ' #አዲሱ_ሲኖዶስ ' በሚል አዲስ ስም እስካሁን ድረስ ከሚጠቀሙበት ለየት ባለ ስም የተሰጠ መግለጫ በሚል በሰጡት ባስተላለፉት ሁሉም በአንድነት ጵጵስናው የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸውም የ #ኤጲስ_ቆጶስነቱ ደረጃም በስምምነቱም በጋራ የጠፋ ወይም የተሻረ የተደመሰሰ መሆኑን እያወቁም የቅድስናውን ልብስ በመልበስ እና ሌሎችም የስምምነቱ አካል ሆነው ስምምነቱን ያነበቡት ሳይቀሩ በአንድ ላይ ስምምነቱን ጥሰውታል ቀኖናውን እንደገና ደግመው ጥሰውታል። 

ሀይማኖቱን ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል።

ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል።

ይህ ከዕለት ወደ ዕለት የሚታይ የሚሰማ ከንቱ ክስ ሆኗል።

ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ተጎናጽፏል።

በሃይማኖታዊ መንገድ በሰላምና በፍቅር በክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ በክርስቶስ ደም የተዋጁትን ምእመናን ከማስተማር ይልቅ በኃይልና በጉልበት ሁሉንም በነገረ ሰሪነት ግጭት በመፍጠር ሁሉንም ለመቆጣጠር ከዕለት ወደ ዕለት ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ።

አስተሳሰባቸው አነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል።

25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል።

ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይህንን አድርገው ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ ቤታቸው ውስጥ [ቤተ ክህነት] ገብተዋል።

... ቤተ ክርስቲያንም እስቲ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት እንየው በማለት ዝም ብለን እየተመለከትን ነው።

ስለዚህ ሕግን የጣሰ ሰው ስምምነትን ያፈረሰ ሰው ዛሬም ደግመው ደጋግመው እውነት ለማስመሰል ሐሰትን በሚለፍፉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ድፍረት የሚመለከተው አካል ሊመለከተውና አሁንም በቃ ሊለው ይገባል ብለን መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"

#TMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን ገልጿል። ቦርዱ የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ለህዝብ ይፋ ተደርጓል ብሏል። @tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች ፦
- በኮንሶ፣
- በደቡብ ኦሞ፣
- በወላይታ፣
- በጋሞ፣
- በጌዴኦ፣
- በጎፋ እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም ፦
• በቡርጂ፣
• በባስኬቶ፣
• በአሌ፣
• በአማሮ፣
• በዲራሼ ላይ ያካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ ጊዜያዊ ውጤት የማዳመር ሥራ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ላይ አጠናቆ በዞንና በልዩ ወረዳ ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ መደረጉን አስታውሷል።

ቦርዱ የመጨረሻውን ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የሕዝበ ውሣኔው ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ቀደም ሲል ቦርዱ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ የመጨረሻውን በቦርድ የተረጋገጠ ውጤት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ እንደሚያደርግ የገለፀ ቢሆንም በርከት ያሉ ግድፈቶችና የምርጫ ህግ ጥሰቶች በቦርዱ የምርጫ ክትትል ቡድን እንዲሁም በምርጫ ታዛቢዎች ሪፖርት በመቅረቡ የማጣራት እና ውጤት የማረጋገጥ ስራን በታቀደበት ግዜ ለማጠናቀቅ አልተቻለም ብሏል።

በዚህም የውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ ስራ ፦

የዲራሼ፣
አሌ፣
ደቡብ ኦሞ፣
ባስኬቶ፣
ኮንሶ
ቡርጂ ውጤቶችን የማጣራትና የማረጋገጥ ስራ ተጠናቆ ውጤታቸው በቦርዱ #ፀድቋል

በቀጣይም በቀሪዎቹ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ማለትም ፦
በአማሮ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ እና የጎፋ ግዜያዊ ውጤቶች የማጣራትና የማረጋገጥ ሂደት እንደተጠናቀቀ ቦርዱ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ሲል አሳውቋል።

በቦርዱ የፀደቀውን ውጤት ከላይ ተያይዟል በተጨማሪ በዚህ ማግኘት ይቻላል : https://nebe.org.et/am/Referendum_Result

#NEBE

@tikvahethiopia