TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ ዛሬ ረቡዕ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ተመርቋል።

ስለ ማዕከሉ ምን ይታወቃል ?

- ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሊዝ ነፃ ባቀረበው በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያለው መሬት ላይ የተገነባ ነው።

- የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

- የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሸፍኗል።

-  የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ 25 ወራትን  ፈጅቷል።

- ማዕከሉ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን፣ የመረጃ፣ የላብራቶሪ፣ የስልጠና ፣ የኮንፈረንስ ማዕከል ፣ ቢሮዎች እና አፓርትመንቶች አሉት።

- የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ (አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች) እየተካሄደ ነው።

- ማዕከሉ በቅርቡ ሙሉ ስራው ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል።

- በግንባታው ላይ #ቻይናውያንና #ኢትዮጵያውያን የህንፃ ባለሞያዎች እየተሳተፉበት ነው።

Info : ENA
Photo Credit : Tesfaye Wube (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ? የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦ " ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት። ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም። ስርዓተ…
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔውም በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ ተወያይቷል።

በዚህም ፤ ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የሕዝብ ( #የተማሪ_ወላጆችን_ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው ዕለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን ማሳለፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ፤

2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ  (ሁለተኛ) ቋንቋ እንዲሰጥ፤

3ኛ:- ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም የከተማው  ትምህርት ቤቶች የአገር ውስጥ ቋንቋ መማራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉንም የትምህርት አይነቶችን በእንግሊዘኛ መማር እንዲችሉ እንዲደረግ፤

4ኛ:-  ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች #አረብኛና #ፈረንሳይኛ በሃይስኩል ደረጃ አማራጭ ትምህርት ሆኖ እንዲቀጥል፤

5ኛ:- የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት መጀመሪያ እድሜ ከ4 ዓመት እንዲሆን፤

6ኛ:-  በአዲሱ የስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የሥራ እና ቴክኒክ ትምህርት  በተለያዩ አመራጮች እንደሚማሩ በሚያስቀምጠዉ መስረትና ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በክላሰተር በቅንጅት እንዲሰጥና  በተጠናው ጥናት  መሰርት ወደ ግንባታ እንዲገባ እንዲደረግ፤

7ኛ:-  የግል ትምህርይ ቤቶችን የመፅሐፍት እጥረት ለመቅረፍ በሽያጭ ለማቅረብ ለመጽሓፍት ህትመት የተዘዋዋሪ ፈንድ  250 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት፤ በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮምያ ክልል ለኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማርያነት በውሰት ተወስዶ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ስርአተ ትምህርት በአዲሱ ስርዐት ትምህርት የሚተካ ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥምቀት ጎንደር ከተማ በጥምቀት በዓል ሰሞን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጓ አሳውቃለች። የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ፤ በጥምቀት በዓል ሰሞን እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አሳውቋል። በጥምቀት በዓል ወቅት ከ750 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ጎብኚ ወደ ጎንደር እንደሚመጣ ይጠበቃል…
#GONDAR

የጥምቀት በዓል እጅግ በድምቀት የሚከበርባት ጎንደር ከተማ ዝግጅቷ በማጠናቀው እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው።

በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና በክብር ለማስተናገድ ዝግጅታችንን ሁሉ አጠናቀናል ብለዋል።

ዘንድሮ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የከተማ አስተዳደሩ " የጥምቀት በዓልን የጥበብ መፍለቂያና የፍቅር ከተማ በሆነችው በጎንደር  ኑ አብረን እናክብር " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ጎንደር የሃይማኖት፣ የፍቅር ፣ የጥበብ መፍለቂያ፣ የቱሪስት ምስእብ ፣ የኩሩ ህዝብ ባለቤት ከተማ ናት " ያለው አስተዳደሩ ፤ የጎንደር ህዝብ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰው አክባሪ ህዝብ ነው ፤ ኑ የጥምቀት በዓል በጋራ እናክብር ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ከነገ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ውል ማዋዋል ስራ ይጀመራል። የውል መዋዋያው " #መገናኛ " በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ነው። በሁለቱም የቤት ልማት መርሀ-ግብር ባለድለኞች #በአካል እየተገኙ ውል እንዲዋዋሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል። …
የ20/80 እና 40/60 ውል እንዴት እየሄደ ነው ?

" በሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራሞች 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን መውሰድ ችለዋል " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/ 60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ " በጥሩ ሁኔታ " እየተካሄደ ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ኮርፓሬሽኑ በ20/80 14ኛ ዙር  እና በ40/60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ  ከጥር  1/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

" ውል ከጀመረበት ቀን ጀምሮ 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን በሁለቱም የቤት ልማት ኘሮግራሞች መውሰድ ችለዋል " ብሏል።

ተቋሙ ፤ " ባለ እድለኞች እንዳይጉላሉ በቂ ቦታ እና የሰው ሃይል መድቤ በማስተናገድ ላይ ነኝ " ያለ ሲሆን ውሉ ከተጀመረ ጀምሮ ለተከታታይ 60 የስራ ቀናት ብቻ ይቆያል ሲል አስታውሷል።

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መንፈቅ ዓመት 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት መጀመሪያ ካስተዋወቀ በኋላ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱን ዛሬ አቅርቧል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈታሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት አጋማሽ 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። ኩባንያንያው ይህም የእቅዱን 96% ማሳካቱን ነው የገለጸው።

የተገኘው የገቢ ድርሻ በአገልግሎት አይነት ሲታይ ፦

- የድምጽ አገልግሎት 47.4% ድርሻ ሲኖረው

- ዳታና ኢንተርኔት 28%፣

- ዓለም አቀፍ ገቢ 8.4%፣

- እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶች የ6.5%፣

- እቃ ሽያጭ( Device) 4.3%

- የመሰረተ ልማት ማጋራት Infra.Sharing (2.2)

- ሌሎች አገልግሎቶች 3.2% ድርሻ አላቸው ተብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 64.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 90% ያሳካ ነው ተብላል።

ኩባንያው የደንበኞቹ ቁጥር 70 ሚሊዮን መድረሱንም ወ/ሮ ፍሬህይወት ገልጸዋል ፦

- የድምጽ አገልግሎት 67.7 ሚሊዮን

- ዳታና ኢንተርኔት 31.3 ሚሊዮን

- መደበኛ የብሮድባንድ 566.2 ሺ ተጠቃሚዎች

- መደበኛ የስልክ 862.2 ሺ ተጠቃሚዎች መድረሱን አስታውቀዋል።

በዚህም በበጀት አመቱ ግማሽ አመት 15.1  እድገት ያሳየ ሲሆን 9.2 ተጨማሪ ደንበኞችን ማግኘቱን አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በውድድር ገቢያ ውስጥ ሆነን ደንበኞችን የማቆየትና አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገብንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthioTelecom ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መንፈቅ ዓመት 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት መጀመሪያ ካስተዋወቀ በኋላ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱን ዛሬ አቅርቧል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈታሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮ ቴሌኮም በ2015…
ተጨማሪ መረጃዎች ፦

(ኢትዮ ቴሌኮም)

#DevicePenetration 📱

በኢትዮጵያ 31 ሚሊየን (46%) ዜጎች የዘመናዊ ስልክ ( SmartPhone) ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ከዚህ ውጭ ያሉ (Basic Feature Phone) ተጠቃሚዎች ደግሞ 47.5 ሚሊዮን መድረሳቸውን ነው የተገለጸው። ዳታ የሚጠቀሙ መሳሪያዎች (Data Devices) ደግሞ 1.2 ሚሊዮን መድረሱን ገልጿል።

#NetProfit 💶

ኢትዮ ቴሌኮም በ2022 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት መሰረት 9 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።

በያዝነው በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ሪፖርቱ መሰረት ደግሞ 8.18 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

ይህም በግማሽ ዓመቱ የተገኘ ትልቅ ውጤት መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ለዚህም ኩባንያው የያዘው የወጪ ቁጠባ ስትራቴጂ ትልቅ ድርሻ ተጫውቷል ተብሏል። በዚህም በግማሽ በጀት ዓመቱ 3.5 ቢሊዮን ብር የወጪ ቁጠባ ማድረጉን አስታውቀዋል።

#TeleBirr

የቴሌ ብር ደንበኞች 27.2 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን 217 ቢሊዮን ብር ዝውውር መፈጸሙ ነው የተጠቀሰው። ይህም ከ193 ሚሊዮን የዝውውር ብዛት (Transaction Volume) የተገኘ ነው።

ከኢንተርናሽናል ሬሚታንስ ደግሞ 1.6 ሚሊዮን ዶላር ዝውውርም የተፈጸመ ሲሆን ይህም ከ44 ሀገራት (Remitance Countries) የተገኘ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ 98.8 ኤጀንቶች፤ 372 ሱቆች፤ 18 ባንኮች፤ 25.5 ሺህ ሻጮች በመተግበሪያው ተመዝግበው እንደሚገኙ በግማሽ ዓመት ሪፖርቱ ተጠቅሷል።

@tikvahethiopia