TIKVAH-ETHIOPIA
#DigitalLottery አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ህዳር 23 /2015 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል። 1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 005187503482 ሆኖ ወጥቷል። 👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 005187503482 👉 800 ሺህ ብር - 005304384029 👉 350 ሺህ ብር - 005255580874 👉 200 ሺህ ብር - 005230182809…
#DigitalLottery
አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ታህሳስ 25 /2015 በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።
1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 006304740687 ሆኖ ወጥቷል።
👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 006304740687
👉 800 ሺህ ብር - 006299531220
👉 350 ሺህ ብር - 006144680758
👉 200 ሺህ ብር - 006297990128
👉 160 ሺህ ብር - 006266851201
👉 120 ሺህ ብር - 006282798312
(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)
@tikvahethiopia

H. c. marketing directive draft 2nd edition (1) (1).pdf
142.6 KB
#Coffee : የውጭ ንግድ ደረጃ ያለውን ቡና በሃገር ውስጥ በውጭ ምንዛሬ ለመሸጥ የሚያስችል ረቂቅ የአፈጻጸም መመሪያ ይፋ ተደርጓል።
ይኸው መመሪያ ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ሲሆን መመሪያው ለተጨማሪ ግብዓት ነው ይፋ የተደረገው።
ረቂቅ መመሪያው ከዛሬ ጀምሮ እስከ 15 ቀናት ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተመልክተውት እና አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ሀሳቦቹ እንዲካተቱ ይደረጋል ተብሏል።
በረቂቅ መመሪያው ዙሪያ ማንኛውም አይነት አስተያየት ያለው ectacomm@gmail.com በሚለው ኢሜይል አድራሻ እስከ ጥር 9/2015 ዓ.ም ድረስ እንዲልክ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጥሪ አቅርቧል።
(ረቂቅ መመሪያው ከላይ ተያይዟል)

Photo
" በእሳት አደጋዎቹ 14 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል "
ዛሬ ከሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ የእሳት አደጋዎች 14 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተሰምቷል።
የአዲስ አበባ እሳትና የድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን በሰጠው መረጃ አደጋዎቹ የደረሱት በቂርቆስና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ነው፡፡
ከደረሱት የእሳት አደጋዎች ውስጥ አንዱ በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ " ገነት ሼዶች " ተብሎ በሚጠራው ቦታ በማምረቻ ሼዶች ላይ የተከሰተው ድንገተኛ የእሣት አደጋ ነው።
አደጋው ከቀኑ 9:40 ሰዓት አካባቢ ላይ የደረሰ ሲሆን በአደጋው 12 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ወድሟል፡፡ ኮሚሽኑ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ርብርብ 90 ሚሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።
የእሣት አደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል።
በሌላ በኩል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ ጋራጅ ላይ የእሳት አደጋ የተከሰተ ሲሆን በአደጋው 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ንብረት ወድሟል።
አሁን ላይ የእሳት አደጋውን መማጥፋት የተቻለ ሲሆን የአደጋው መንስኤም እየተጣራ ነው።
በሁለቱም አደጋዎች ግን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ያለመኖሩን የአዲስ አበባ እሳትና የድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን ስለማሳወቁን #ኤፍ_ኤም 96.3 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
ከትላንት በስቲያ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ የሚዘነጋ አይደለም።
ፎቶ/ቪድዮ ፦ Chere Rona , Yosef Kinfe (Tikvah Family) & Akaki Kality Communication

#ዋጋ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ያለአገልግሎት የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን መሸጫ የዋጋ ዝርዝር ይፋ ሆኗል። 1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 64.00 2. ካስት አይረን - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.75 3. አልሙኒየም - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 120.00 4. ስክራፕ ያደረገ…
#MinistryofFinance
የገንዘብ ሚኒስቴር እና የማዕድን ሚኒስቴር ፤ ዛሬ የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ መደረጉን አሳውቀዋል።
ምን ያህል ነው ቅናሽ የተደረገው ?
ከዚህ ቀደም የነበረው ፦
1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 64.00
2. ካስት አይረን - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.75
3. አልሙኒየም - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 120.00
4. ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ / ማሽነሪ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.25
5. ያገለገለ የተሽከርካሪ / ማሽነሪ መለዋወጫ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.25
ዛሬ የተሻሻለው ዋጋ ፦
1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 48.00
2. ካስት አይረን - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 35.00
3. አልሙኒየም ስክራፕ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 90.00
4. ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ / ማሽነሪ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 39.00
5. ያገለገለ የተሽከርካሪ / ማሽነሪ መለዋወጫ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 39.00

#መልዕክት
የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፦
" የገና በዓል ሲከበር ህብረተሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።
በበዓሉ ወቅት ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በፍጥነት ለመቆጣጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር ተዘርግቷል።
እሳትና ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በነጻ የስልክ መስመር 939 ፤ በቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም በ 011 156 86 01 ደውሎ ማሳወቅ ይቻላል። "
#ENA

#ቫት
መንግስት በመሰረታዊ ፍጆታ በሆኑ #ምግቦች ላይ #ቫት እንዲያስቀር ተጠየቀ።
መንግሥት ከድጎማ ይልቅ መሠረታዊ የዜጎች ፍጆታ በሆኑ ምግቦች ላይ የሚጣለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲያስቀር ፐርፐዝ ብላክን ጨምሮ ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት መንግሥትን ስለመጠየቃቸው ሪፖርተር አስነብቧል።
የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍስኃ እሸቱ በሰጡት ቃል ፤ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥያቄው በአካል መቅረቡን የገለፁ ሲሆን የጉዳዩ ዋነኛ ባለቤት የሆነው የገንዘብ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ምልክታ እንዲያደርግ ጥያቄ ለማቅረብ በሚቀጥለው ሳምንት ቀጠሮ መያዙን ገልፀዋል።
ዶ/ር ፍስኃ እሸቱ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦
" ለዋጋ ግሽበት አንዱና ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለው ጉዳይ በተለይ በምግብ ውጤቶች ላይ የሚጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጉዳይ ነው።
ዝቅተኛ ገቢ ያለው ኅብረተሰብ ክፍል በሚመገበው ምግብ ላይ 15 በመቶ ታክስ መጨመር ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሯል።
ከወር በፊት ይኸው ጥያቄ ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቧል። የገንዘብ ሚኒስትሩን ለማግኘት ጥረቶች እንደተደረጉ ነው፤ ምናልባት በሚቀጥለው ሳምንት ዕድሉ የሚሳካ ከሆነ ጥያቄውን በግምባር ለማቅረብ እየተሰራ ነው።
ጥያቄውን በአዋጅ ሳይሆን በመመርያ ደረጃ መመለስ የሚቻል ነው። የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ይሁንታ ካገኘ መስተካከል የሚችል ነው።
አነስተኛ የሆነ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሟቸው በተለይም የአትክልት እና የፍራፍሬ ውጤቶች (ሽንኩርት ፣ ቲማቲም እና ሌሎችም) ከታክስ ነፃ ናቸው ከሚባሉት እንቁላልና ሥጋ በበለጠ ተዘውታሪ በመሆናቸው፣ መንግሥት ከእነዚህ ምርቶች የሚሰበሰበው ቫት እንዲቀር ተጠይቋል።
ፐርፐዝ ብላክ የምርት ውጤቶቹን ቫት በማከል ነው ለሸማች የሚያቀርበድ ይህም ምርቶችን በጣም በረከሰ ዋጋ እንዳያቀርቡ አንዱ እንቅፋት ሆኗል።
ኢትዮጵያ ውስጥ #የዋጋ_ንረት_መባባስ የጀመረው #የተጨማሪ_እሴት_ታክስ አሠራር ከመጣ ወዲህ መሆኑን ጥናት ያስረዳል።
መንግሥት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች #ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ሳይረሳ ነገር ግን በሁሉም ምግብ ፍጆታዎች ላይ ሳይሆን ኅብረተሰቡ በመሠረታዊነት የሚጠቀምባቸውን ምርቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ማድረግ ይገባዋል። "
🍏🥬🫑🥕🍋🍌🍇🍎🍓🍍🧄🥔🍅🌶
#ቫት ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ (20) ዓመታት በፊት ያወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ማዘጋጀቱ ይታወሳል።
ረቂቅ አዋጁ መንግሥት ከቫት ታክስ የሚሰበስብበትን መሠረት የሚያሰፋ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በ1994 ዓ.ም. ከወጣ በኋላ በ2001 ዓ.ም. እና በ2011 ዓ.ም. ለሁለት ጊዜያት መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት የቀጠለ ሲሆን ፣ አዲስ እየወጣ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ሲፀድቅ የበፊቱን ይሽራል ተብሏል፡፡
በረቂቅ አዋጁ በሰንጠረዥ ሁለት አንቀጽ ስምንት ከታክስ ነፃ የሆኑ አቅርቦቶች መዘርዝር ሥር የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያ ላይ ዝርዝራቸው የሚወሰን የምግብ አቅርቦቶች እንደሚኖሩ የተደነገገ ሲሆን የትኞቹ ናቸው በሚለው ላይ ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ አለመስፈሩ ታውቋል፡፡
Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ (www.Ethiopianrepoter.com)

#Mekelle
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ የተመራ የማኅበሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ዛሬ መቐለ ከተማ ገባ።
ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢቀመማ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ ረ/ፕሮፌሰር የማነ ዘርዓይን ጨምሮ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።
ልዑኩ በቆይታው ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ #የተሽከርካሪዎች_ርክክብን ጨምሮ ማኅበሩ በክልሉ እያከናወነ ባለው ሰብዓዊ አገልግሎትና ቀጣይ ሰብዓዊ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት የሚያደርግ ይሆናል።
ምንጭ ፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር

ፎቶ ፦ " የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና/ቻን " እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅት ዛሬ ሞሮኮ ካዛብላንካ በሰላም መድረሱን የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።
ቡድኑ ወደ ሞሮኮ ከመሄዱ በፊት በሀገር ውስጥ ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል።
በሞሮከ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚያደርግ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ እና ሰኞ ከሞሮኮ #የቻን ቡድን ጋር #ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ውድድሩን የተመለከቱ መረጃዎችን በስፍራው ከሚገኙት የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት በ @tikvahethsport ማግኘት ይቻላል።
ፎቶ ፦ Tikvah Sport

#የጥንቃቄ_መልዕክት
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣ የምግብ ደኅንነት ኢንስፔክተር መሀመድ ሁሴን ፦
" ሕብረተሰቡ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦችን የመጠቀሚያ ጊዜያቸውን እያስተዋለ መግዛት አለበት።
በተለይ መጪዎቹን የበዓል ወቅቶችን አስታኮ በርካታ ጊዜያቸው ያለፋባቸው ምግቦችና መጠጦች በቅናሽ ዋጋ ወደ ገበያ ሊወጡ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።
ከምግብ ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል አላስፈላጊ ትርፍ ለማጋበስ ከሚጥሩ ሕገ-ወጦችም ራስን መጠበቅ ይገባል።
ሕብረተሰቡ የሚገዛቸውን የምግብና የመጠጥ ምርቶች በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ምርቶቹን ከመግዛቱ በፊት ማን እንዳመረታቸው ? መቼ እንደተመረቱና ? የመጠቀሚያ ጊዜያቸው መቼ እንደሚያልቅ? በአግባቡ ማየት አለበት።
ከእነዚህ ምግቦችና መጠጦች መካከል #ጁሶች ፣ የተለያዩ የታሸጉ #ብስኩቶችና ሌሎች #መጠጦች ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል።
በተለይ ሕገ-ወጥ የሆኑና ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ወይም በክልል ጤና ቢሮዎች ሥር ባሉ ተቆጣጣሪ የፈቃድ ማረጋገጫ ሳይወስዱ የምግብ ንግድ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሕገ-ወጦች አሉ።
ባለሥልጣን መ/ቤቱ የራሱን መቆጣጠሪያ ስልቶችን ነድፎ ቁጥጥር ያደርጋል ፤ ሕብረተሰቡ ለዚህ ሥራ የሚሰጠው መረጃ ቀላል ባለመሆኑ የተለመደ ትብብሩን ሊያደርግ ይገባል። "
#ENA
@TIKVAHETHIOPIA