TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ ኑሮአቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህፃናትን በተመለከተ የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 17 መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቆናል።

ሚኒስቴሩ ፤ " መዋያና ማደሪያቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህፃናትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ከጎዳና ለማንሳትና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማስቻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በርካታ ተግባራትን እያከናወንኩ እገኛለሁ " ብሏል።

ሆኖም ግን አንዳንድ የሚዲያ አካላት በቂ መረጃና ማስረጃ በሌለበት እንዲሁም የተቋሙን ገጽታ በሚያበላሽ መልኩ የተሳሳተ ትርጓሜ በመስጠት በተዛባ መንገድ ዘገባዎችን እያሰራጩ መሆኑን በክትትል ሥራ ማረጋገጥ ችለናል ሲል ገልጿል።

በጉዳዩ ዙሪያም ሚኒስቴሩ የፊታችን ሰኞ ታህሣስ 17/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ላይ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የሥራ አስፈጻሚዎች በኩል መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን መግለጫውን ተከታትለን እናሳውቃችኃለን።

@tikvahethiopia
" 3 የኤጀንሲው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል "

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ 3 የኤጀንሲው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን አስታወቀ።

ኤጀንሲው ፤ የህትመት ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ መደበኛ የኦዲት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጾ በዚህም በተገኘው ግኝት የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ  ጽ/ቤት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና ማስረጃ ቡድን #መሪ እና 2 ባለሙያዎች በሰሩት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ሲል ገልጿል።

ኤጀንሲው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት በደረሰው ጥቆማ ላይ ተመስርቶ ባሰባሰበው ማስረጃ ፦

- ለወረዳው ፈቃድ ሳይሰጥ የውጭ ዜጎችን #ገንዘብ_በመቀበል ጋብቻ በመፈፀም፣

- ባልተሟላ ማስረጃ የልደት ምዝገባ በማከናወን እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያዎችዎቹ ተጠርጥረው ከስራ እንዲታገዱ በማድረግ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ አድርጓል ብሏል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ኤጀንሲው ፤ #በለሚ_ኩራ ክ/ከተማ  ወረዳ 13 ጽህፈት ቤት 1 ቡድን መሪ እና ባለሙያዎች በወንጀል ጉዳዮቸው እየታየ መሆኑ አስታውሷል።

ነዋሪዎች የትኛውንም ዓይነት ቅሬታ ፣ ጥቆማ ወይም መረጃ ለመስጠት የኤጀንሲውን ነፃ የስልክ መስመር 7533 መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ " የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች፣ #በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦ 👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣ 👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣…
" ... የተመዘገበ የሀብት መጠንን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ህጉ አይፈቅድም " - የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ፤ በባለስጣናት እና በመንግሥት ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ በርካታ ዜጎች እና ተቋማት እየጠየቁ እንደነበር እና አሁንም እየጠየቁ እንደሆነ ይታወቃል።

ከጥቂት ቀናት በፊትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች#በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ መጠየቁም ይታወሳል።

ይህን በተመለከተ ለምን ኮሚሽኑ የተመዘገበን ሀበት ለህዝብ ይፋ እንደማያደረግ ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።

ኮሚሽኑ ለጥያቄው ምላሽ የሰጠው ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

የኮሚሽኑ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ ለሬድዮ ጣቢያው ፤ " የሀብት ምዝገባ እና ማሳወቅ አዋጅ 668 ህዝባር 2002 ላይ በተደነገገዉ መሰረት የተመዘገበን ሀብት ማየት ለሚፈልግ የትኛዉም ሰዉ መጥቶ የሚጠይቅ ከሆነ ህጉ በሚፈቅደዉ አሰራር መሰረት ይስተናገዳል " ብለዋል።

" ሆኖም ግን የተመዘገበን ሀብት ለሁሉም ህዝብ ይፋ ማደረግን ህጉ ይከለክላል " ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ የተመዘገበን ሀብት በህጋዊ መንገድ ለሚጠይቁ አካላት የማሳየት ስራን እየሰራ መሆኑን ገልፀው " የተመዘገበን ሀብት ትክክል ነዉ አይደለም የሚለዉን ለመለየት የሚፈለጉ ዜጎች በህጋዊ መልኩ የሚጠይቁ ከሆነ እና ተመዘገበዉ ሀብት እዉነተኛ አለመሆኑን የሚጠቁሙበት አጋጣሚ ካለ የሀብቱን አንድ አራተኛ እንዲያገኙ ይደረጋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

#Credit_Ahadu

@tikvahethiopia
T-MAX FLASH

በጣም ፍጥነት ያለውን T-MAX USB Flash Disc ለገበያ  አቅርበናል።
💎 ጫፉ የማይሸራረፍ ባለ ብረት
💎 ፍጥነቱ በጣም ጥሩ የሆነ
💎 ከተጠቀሙ በኋላ ወደ ውስጥ የሚሰበሰብ ዲዛይን
💎 ከጀርባው ህትመት/Logo ለማስቀመጥ ምቹ

🔔በፈለጉት መጠን በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን
➭ 8 GB /16 GB/32 GB /64 GB/128 GB
☎️ 0933111111 /  0911676767
🌟T-Max Electronics ምርቶችን ለማየት ተከታዩን ሊንኩን ይጠቀሙ፦

https://linktr.ee/tmaxelectronics
📍 አድራሻ፦ መርካቶ ይርጋ ኃይሌ ህንጻ ሱቅ ቁጥር G-96 Ground Floor
www.tmaxelectronics.com
' የገናን በዓል በላሊበላ አክብሩ '

ባለፉት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት በሚፈለገው መልኩ የገና በዓል ባልተከበረባት ላሊበላ የፊታችን ታህሳስ 29 ቀን 2015 ዓ/ም የሚከበረውን የገና በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅቷን አድርጋለች።

የከተማው ወጣቶችም በተለመደው የእንግዳ አቀባበል ባህላቸው እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል።

ወጣቶቹ በላስታ ላሊበላ ወግ ባህል መሠረት እንግዶችን በመቀበል እግር አጥቦና ስንቅ ያለቀበትን ስንቅ በማዘጋጀት የቆዩ የማህበረሰቡ መልካም የእንግዳ አቀባበል እሴቶችን በማጠናከር ለማስተናገድ ስለመዘጋጀታቸው ተናግረዋል።

የከተማው ወጣቶች " ባለፉት አመታት በነበረው ጦርነት ምክንያት በዓሉን በሚፈለገው መልኩ አለማክበራችን ቆጭቶናል " ብለዋል።

የላስታ ላሊበላ ማህበረሰብ እንግዳ ተቀባይ ነው ያሉት ወጣቶቹ በዓሉን ለማክበር በርካታ ኪሎሜትሮችን በእግር ፣ በተሽከርካሪ ተጉዘው ወደ ከተማዋ የሚገቡ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር እንግዶችን አቅጣጫ በማሳየት በዓሉ በሰላም አክብረው እንዲመለሱ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአልና  የፃዲቁ የቅዱስ ላሊበላ ልደት  የፊታችን ታህሳስ 29 በድምቀት ይከበራል።

መረጃ ምንጭ የላሊበላ ኮሚኒኬሽን።

Photo Credit : Hilena Tafesse

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

አንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቀናት በኃላ መሰጠት የሚጀምረውን 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምረዋል።

ተቋማቱ ከወዲሁ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ከገቡ በኃላ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከተፈቀደላቸው የተቋሙ ሰራተኞች እና ፈተና አስፈፃሚዎች በስተቀር ተፈታኞች ባሉባቸው ቦታዎች ማንኛውም አካላት እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

በተለያዩ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከታህሳስ 18 እስከ 21 ድረስ ባሉት ቀናት ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎች ፈተና ውጤት እስካሁን ይፋ ያልተደረገ እና ይፋ የሚደረግበት ትክክለኛ ቀን ያልታወቀ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት #ከሁለተኛ_ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

Photo Credit : ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ እጅግ አስከፊ በነበረበት ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች ፦ " እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን። ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል። የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት…
" ከታህሳስ 30 በኃላ ከስራ ገበታችን ልንሰናበት ነው " ያሉ የጤና ባለሞያዎች ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ፃፉ።

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልፅ ደብዳቤ የፃፉት በCOVID-19 ወረርሽኝ ግዜ በጤና ሚኒስቴር በኮንትራት ተቀጥረው እየሰሩ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ናቸው።

ጉዳዩን ያስረዱት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፤ " ጤና ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ጋር በመነጋገር  ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በኮንትራት ከቀጠረን መካከል 1407 የጤና ባለሞያዎች ቋሚ እንደሆንን በደብዳቤ አሳውቆናል፤ ከ1000 በላይ የጤና ባለሞያዎች ቋሚ ከሆኑ  በኋላ ግን የተቀረነውን ከ350 - 400 የምንሆን የጤና ባለሞያዎች በተስፋ ከነገ ዛሬ ቋሚ ያርጉናል ብለን ሰንጠብቅ ከነአካቴው ከስራ ሊያሰናብቱን ነው " ብለዋል።

የጤና ባለሞያዎቹ ከታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ እንደሚሰናበቱ በማሰብ ከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ በቁጥር ከ300 በላይ እንደሆነ ያመለከቱት የጤና ባለሞያዎች ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፃፉት ደብዳቤ ፤ ጉዳዩን በተመለከተ መፍትሄ ለመፈለግ ከታች የጤና ሚኒስቴር ሰው ሀብት ክፍል እስከ ጤና ሚኒስትሯ ድረስ ብንጠይቅም መፍትሄ ቀርቶ የሚያፅናና ቃል ሊሰጠን አልቻለም ብለዋል።

" 3 አመት ሙሉ ህዝብንና ሃገርን ያገለገልን ጤና ባለሙያዎች በዚ መልኩ #ሞራልን_ጎድቶ መግፋት ለሙያውም ለስርአቱም ገፅታ ጥሩ አደለም ብቻ ሳይሆን ትልቅ ጠባሳን የሚጥል ነው "  ያሉት የጤና ባለሞያዎቹ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጡን ሲሉ ጠይቀዋል።

(ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የፃፉት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia