" ለኢትዮጵያ የሚያደርገው የልማት እና የምጣኔ ሀብት ድጋፍ ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ይደርጋል " - የአውሮፓ ህብረት
የአውሮፓ ህብረት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው ስምምነት ተፈጻሚ መሆን ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት መልሶ ለመጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጿል።
ህብረቱ ምን አለ ?
- ህብረቱ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ ያታዩ ለውጦችን አድንቋል። ለዚህም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
- የስምምነቱ በዘላቂነት ተግባራዊ መሆን ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነትን መልሶ ለመጀመር እንደሚያስችለው አሳውቋል።
ማስታወሻ ፦ የአውሮፓ ኅብረት በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ ወደ 110 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የበጀት ድጋፍ እንዲዘገይ ማድረጉ ይታወሳል።
- የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ መሆን፣ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና ለመብት ጥሰቶች ተጠያቂነት መኖር ለኢትዮጵያ የሚያደርገው የልማት እና የምጣኔ ሀብት ድጋፍ ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ያደርጋል ብሏል።
- በሰሜን ኢትዮጵያ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ የእርዳታ አቅርቦት ፍላጎት በመኖሩ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና መሠረታዊ አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲል ገልጿል።
- ኤርትራን በተመለከተ የድንበር ጦርነቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥታት መካከል የተደረሰውን #የአልጀርስ_ስምምነት እንዲሁም ከአራት ዓመት በፊት የተደረሰውን የሰላም ስምምነትን ጠቃሚነት ገልጾ ፤ የኤርትራ ሠራዊት በአስቸኳይና ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ጠይቋል።
#BBC
@tikvahethiopia

#ክብሩ_ዶክተር_አጋ_ጠንጠኖ
የክብር ዶክተር አጋ ጠንጠኖ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የክብር ዶ/ር አጋ ጠንጠኖ ማን ነበሩ ?
- በ1937ዓ.ም ነበር ከአባታቸው ጠንጠኖ ጉዬ እና ከእናታቸው ጋልጋሉ ሃላኬ የተወለዱት።
- ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የጉጅ ኦሮሞ አባ ገዳ በመሆን ህዝባቸውን አገልግለዋል።
- የስልጣን ጊዜያቸውን አጠናቀው በገዳ ስርዓት የአስተዳደር ጊዜያቸውን ለ73ኛው የጉጂ አባ ገዳ ዋቆ ዱቤ በ2000ዓ.ም ነበር ያስረከቡት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከኋላቸው ላሉት ለገዳ ስርዓት መሪዎች እንዴት ሀገርን መምራት እና አብሮ መኖር እንደሚችሉ በመምከር እና ሰላምን በማጎልበት ትልቅ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል።
- የገዳን ሥርዓት ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከገዳ ምክር ቤት ጋር ሠርተዋል።
- በህይወት ዘመናቸው መቻቻል፣ መከባበር እና በሰላም አብሮ የመኖር ባህልን በመገንባት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
- የገዳ ትምህርት በዩንቨርሲቲዎች እንዲሰጥ እና የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) እንዲመዘገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።
- በ2008 ዓ.ም ካቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷቸዋል።
መረጃው ምንጭ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #AddisAbaba
የ2ኛውን ዙር የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በ16 / 4 /2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ ዛሬ አሳስቧል።
የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።

#AddisAbaba የፍ/ቤት መጥሪያ ፈርመው ወስደው ሳይቀርቡ ቀርተዋል የተባሉት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት #ታስረው እንዲቀርቡ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አዘዘ። አቶ ሽመልስ "የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ተጭበርብሯል" ተብሎ የከባድ ሙስና ወንጀል በቀረበባቸው ተከሳሾች ላይ የዓቃቢህግ 2ኛ ምስክር ሆነው የተቆጠሩ ሲሆን መጥሪያ…
#Update
የፍ/ቤት መጥሪያ ፈርመው ወስደው በቀጠሮ ቀን ሳይቀርቡ የቀሩት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ታስረው እንዲቀርቡ ትናንት በነበረ ቀጠሮ ትዕዛዝ የወጣባቸው ቢሆንም ዛሬም ሳይቀርቡ መቅረታቸው ተሰምቷል።
አቶ ሽመልስ ታምራት " የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ተጭበርብሯል" ተብሎ የከባድ ሙስና ወንጀል በቀረበባቸው ተከሳሾች ላይ የዓቃቢህግ 2ኛ ምስክር ሆነው የተቆጠሩ ሲሆን መጥሪያ ፈርመው ተቀብለው ባለመቅረባቸው ምክንያት ነው ታስረው እንዲቀርቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ያዘዘው።
ምንም እንኳን ፍ/ቤቱ ታስረው እንዲቀርቡ ቢያዝም ኃላፊው ዛሬም እንዳልቀረቡ ተገልጿል።
በሌለ በኩል ዛሬ በነበረ ችሎት በአ/አ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለምቷል የተባለውን ሶፍትዌር በሚመለከት በስራ ኃላፊነት ቁጥጥርና ክትትል አላደረጉም ተብለው የተከሰሱት የአ/አ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ የባለቤታቸውና የራሳቸው የባንክ ሒሳባቸው መታገዱን ተከትሎ የህጻናት የልጆቻቸው ት/ቤት ሊቋረጥባቸው እንደሆነ ገልፀወል።
ዶ/ር ሙሉቀን ለህጻናቱ ምሳ መቋጠር የማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱንና ችግር ላይ መሆናቸውን የዕንባ እየተናነቃቸው ለችሎቱ ገልጸዋል።
በተጨማሪ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ በነበሩበት ወቅት ወላጅ አባታቸው መታሰራቸውንና ወላጅ እናታቸው በአሁን ወቅት ህመምተኛ መሆናቸውንና ችግር ላይ መሆናቸውን ገልጸው የተፋጠነ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የችሎቱ ዳኞች በተቻለ መጠን ተከሳሾች የተፋጠነ ፍትህ እንዲያገኙ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ያንብቡ: telegra.ph/Tarik-Adugna-12-23
(Credit: ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ)

#መቐለ #ራያ #አክሱም #ዓዲግራት
ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡
በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።
በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡
በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC
@tikvahuniversity

#የጠፋ_መታወቂያ
የአዲስ አበባ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ #ለጠፋ_መታወቂያ_አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ኤጀንሲው ይህንን ያሳወቀው ዛሬ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሰጠው ቃል ነው።
የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፤ " ለጠፋ መታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት አጠናቀናል " ያሉ ሲሆን " ይህንንም በቀጣይ ሳምንት ውስጥ ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል " ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ፤ በአዲስ አበባ ተቋርጦ የቆየው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ባለፈው ህዳር 1 ቀን በድጋሚ ከጀመረ ወዲህ ከ250 ሺ በላይ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት መቻላቸውን ኤጀንሲው አሳውቋል።
ኤጀንሲው " አዲስ የአገልግሎት ምዕራፍ " በሚል ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ/ም በተጀመረ የመታወቂያ አገልግሎት የተገልጋዮችን መጉላላት ለመቀነስ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከስራ ሰዓታት ውጪ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጿል።
በእድሜና በጤና እክል ምክንያት በአካል ተገኝተው መገልገል ላልቻሉ ዜጎችም የቤት ለቤት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ኤጀንሲው ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግሯል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከመታወቂያ አገልግሎት ጋር በተያያዘ አገልግሎቱ ተቋርጦ መቆየቱ በርካቶች ብዙ ጉዳያቸው እንዲስተጓጎል አድርጎ ቆይቷል ፤ የእድሳት አገልግሎት ከተጀመረ በኃላም የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ሌሎችም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ፤ ሰዓታቸውም በዚሁ ጉዳይ እየጠፋና አንዳንዳችም እየተጉላሉ ስለመሆኑ ይገልፃሉ።
በ " መታወቂያ እድሳት " አገልግሎት ጉዳይ ምን ገጠማችሁ ? ምን በጎ ጎንና ክፍተት ያለባቸውን ተግባራት ታዘባችሁ ? @tikvahethiopiaBOT

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ ኑሮአቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህፃናትን በተመለከተ የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 17 መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቆናል።
ሚኒስቴሩ ፤ " መዋያና ማደሪያቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህፃናትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ከጎዳና ለማንሳትና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማስቻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በርካታ ተግባራትን እያከናወንኩ እገኛለሁ " ብሏል።
ሆኖም ግን አንዳንድ የሚዲያ አካላት በቂ መረጃና ማስረጃ በሌለበት እንዲሁም የተቋሙን ገጽታ በሚያበላሽ መልኩ የተሳሳተ ትርጓሜ በመስጠት በተዛባ መንገድ ዘገባዎችን እያሰራጩ መሆኑን በክትትል ሥራ ማረጋገጥ ችለናል ሲል ገልጿል።
በጉዳዩ ዙሪያም ሚኒስቴሩ የፊታችን ሰኞ ታህሣስ 17/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ላይ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የሥራ አስፈጻሚዎች በኩል መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።
ውድ ቤተሰቦቻችን መግለጫውን ተከታትለን እናሳውቃችኃለን።

" 3 የኤጀንሲው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል "
የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ 3 የኤጀንሲው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን አስታወቀ።
ኤጀንሲው ፤ የህትመት ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ መደበኛ የኦዲት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጾ በዚህም በተገኘው ግኝት የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ጽ/ቤት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና ማስረጃ ቡድን #መሪ እና 2 ባለሙያዎች በሰሩት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ሲል ገልጿል።
ኤጀንሲው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት በደረሰው ጥቆማ ላይ ተመስርቶ ባሰባሰበው ማስረጃ ፦
- ለወረዳው ፈቃድ ሳይሰጥ የውጭ ዜጎችን #ገንዘብ_በመቀበል ጋብቻ በመፈፀም፣
- ባልተሟላ ማስረጃ የልደት ምዝገባ በማከናወን እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያዎችዎቹ ተጠርጥረው ከስራ እንዲታገዱ በማድረግ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ አድርጓል ብሏል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ኤጀንሲው ፤ #በለሚ_ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ጽህፈት ቤት 1 ቡድን መሪ እና ባለሙያዎች በወንጀል ጉዳዮቸው እየታየ መሆኑ አስታውሷል።
ነዋሪዎች የትኛውንም ዓይነት ቅሬታ ፣ ጥቆማ ወይም መረጃ ለመስጠት የኤጀንሲውን ነፃ የስልክ መስመር 7533 መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ " የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች፣ #በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦ 👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣ 👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣…
" ... የተመዘገበ የሀብት መጠንን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ህጉ አይፈቅድም " - የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን
የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ፤ በባለስጣናት እና በመንግሥት ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ በርካታ ዜጎች እና ተቋማት እየጠየቁ እንደነበር እና አሁንም እየጠየቁ እንደሆነ ይታወቃል።
ከጥቂት ቀናት በፊትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች፣ #በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ መጠየቁም ይታወሳል።
ይህን በተመለከተ ለምን ኮሚሽኑ የተመዘገበን ሀበት ለህዝብ ይፋ እንደማያደረግ ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።
ኮሚሽኑ ለጥያቄው ምላሽ የሰጠው ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
የኮሚሽኑ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ ለሬድዮ ጣቢያው ፤ " የሀብት ምዝገባ እና ማሳወቅ አዋጅ 668 ህዝባር 2002 ላይ በተደነገገዉ መሰረት የተመዘገበን ሀብት ማየት ለሚፈልግ የትኛዉም ሰዉ መጥቶ የሚጠይቅ ከሆነ ህጉ በሚፈቅደዉ አሰራር መሰረት ይስተናገዳል " ብለዋል።
" ሆኖም ግን የተመዘገበን ሀብት ለሁሉም ህዝብ ይፋ ማደረግን ህጉ ይከለክላል " ሲሉ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ የተመዘገበን ሀብት በህጋዊ መንገድ ለሚጠይቁ አካላት የማሳየት ስራን እየሰራ መሆኑን ገልፀው " የተመዘገበን ሀብት ትክክል ነዉ አይደለም የሚለዉን ለመለየት የሚፈለጉ ዜጎች በህጋዊ መልኩ የሚጠይቁ ከሆነ እና ተመዘገበዉ ሀብት እዉነተኛ አለመሆኑን የሚጠቁሙበት አጋጣሚ ካለ የሀብቱን አንድ አራተኛ እንዲያገኙ ይደረጋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።
#Credit_Ahadu

T-MAX FLASH
በጣም ፍጥነት ያለውን T-MAX USB Flash Disc ለገበያ አቅርበናል።
💎 ጫፉ የማይሸራረፍ ባለ ብረት
💎 ፍጥነቱ በጣም ጥሩ የሆነ
💎 ከተጠቀሙ በኋላ ወደ ውስጥ የሚሰበሰብ ዲዛይን
💎 ከጀርባው ህትመት/Logo ለማስቀመጥ ምቹ
🔔በፈለጉት መጠን በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን
➭ 8 GB /16 GB/32 GB /64 GB/128 GB
☎️ 0933111111 / 0911676767
🌟የ T-Max Electronics ምርቶችን ለማየት ተከታዩን ሊንኩን ይጠቀሙ፦
https://linktr.ee/tmaxelectronics
📍 አድራሻ፦ መርካቶ ይርጋ ኃይሌ ህንጻ ሱቅ ቁጥር G-96 Ground Floor
www.tmaxelectronics.com

' የገናን በዓል በላሊበላ አክብሩ '
ባለፉት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት በሚፈለገው መልኩ የገና በዓል ባልተከበረባት ላሊበላ የፊታችን ታህሳስ 29 ቀን 2015 ዓ/ም የሚከበረውን የገና በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅቷን አድርጋለች።
የከተማው ወጣቶችም በተለመደው የእንግዳ አቀባበል ባህላቸው እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል።
ወጣቶቹ በላስታ ላሊበላ ወግ ባህል መሠረት እንግዶችን በመቀበል እግር አጥቦና ስንቅ ያለቀበትን ስንቅ በማዘጋጀት የቆዩ የማህበረሰቡ መልካም የእንግዳ አቀባበል እሴቶችን በማጠናከር ለማስተናገድ ስለመዘጋጀታቸው ተናግረዋል።
የከተማው ወጣቶች " ባለፉት አመታት በነበረው ጦርነት ምክንያት በዓሉን በሚፈለገው መልኩ አለማክበራችን ቆጭቶናል " ብለዋል።
የላስታ ላሊበላ ማህበረሰብ እንግዳ ተቀባይ ነው ያሉት ወጣቶቹ በዓሉን ለማክበር በርካታ ኪሎሜትሮችን በእግር ፣ በተሽከርካሪ ተጉዘው ወደ ከተማዋ የሚገቡ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር እንግዶችን አቅጣጫ በማሳየት በዓሉ በሰላም አክብረው እንዲመለሱ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአልና የፃዲቁ የቅዱስ ላሊበላ ልደት የፊታችን ታህሳስ 29 በድምቀት ይከበራል።
መረጃ ምንጭ የላሊበላ ኮሚኒኬሽን።
Photo Credit : Hilena Tafesse