TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደመወዝ

• " ደመወዝ በሰዓቱ እየተከፈለን ባለመሆኑ ቤተሰብ ለማስተዳደር አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሰናል " - ሰራተኞች

• " በዚህ ወር ለሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ቢሆንም አሁን ላይ 8 ሚሊየን ብር ብቻ ነው የተገኘው " - ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ት ቤት

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው የካፋ ዞን ፤ ጌሻ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በአግባቡ እየተከፈላቸው እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ሰራተኞቹ ፤ የወርሃዊ ደመወዝ በአግባቡ አለመከፈሉ ለችግር እየዳረጋቸው መሆኑን አመልክተዋል ፤ በዚህ ሳቢያ ህይወታቸውን ለመግፋት ፈተና እንደሆነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

የወረዳው ኮሚኒኬሽን በበኩሉ ፤ በየወሩ በተደጋጋሚ ደምወዝ በአግባቡ ባለመከፈሉ ምክንያት የመንግስት ሰራተኞች #ለአላስፈላጊ_ወጪዎች እና #ችግሮች መዳረጋቸውን እንደገለፁ አሳውቋል። ገልጿል።

" በተያዘው የበጀት አመት አንድም ቀን ደመወዝ በጊዜው ተከፉሎ አያውቅም " ያሉት ሰራተኞቹ " ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሩ እየተባባሰ መጥቷል " ብለዋል።

የመንግስት ሰራተኞቹ ያለፈው የህዳር ወር ደመወዝ እስከ ትላንት ታህሳስ 12 ቀን ድረስ እንዳልተከፈላቸዉ ገልፀው " ቤተሰብ ለማስተዳደር አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሰናል " ብለዋል።

" ቀጣይም የሚከበረውን #የገናን_በዓል ለማክበር ደመወዝ በወቅቱ የማይገባ ከሆነ ለከፋ ችግር ልንዳረግ እንችላለን " ሲሉ ስጋታቸውን ጠቁመዋል። ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ዘላቂ መፍትሔ እንዲያበጅለትም ቅሬታ አቅራቢዎች ጠይቀዋል።

የጌሻ ወረዳ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ፅህፈት ቤት ፤ " የሰራተኞችን ቁጥር ታሳቢ ያላደረገ በጀት ከዞኑ መለቀቁ ለችግሩ መባባስ ምክንያት ነው " ሲል አሳውቋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታደሰ ቆጭቶ ፤ " ችግሩ ከዞን የሚለቀቀው ደመወዝ ሰራተኛውን ያመጣጠነ አለመሆኑ ነዉ " ያሉ ሲሆን በተለይም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ደመወዝ እየተለቀቀ እንዳልሆነና በዚህ ወር ለሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ቢሆንም አሁን ላይ 8 ሚሊየን ብር ብቻ ማግኘት እንደተቻለ ተናግረዋል።

ኃላፊው "አሁን ላይ ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታትና ከመማር ማስተማር ጋር ተያይዞ መስተጓጐል እንዳይፈጠር ለመምህራን ብቻ ደመወዝ መክፈል ተችሏል " ያሉ ሲሆን " የሌሎችን ሰራተኞች ችግር ለመፍታት ከሚመለከተው አካላት ጋር እየተወያየን ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ በዞኑ በ " ገዋታ ወረዳ " ያሉ የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ባለፉት በርካታ ወራት ደመወዝ በአግባቡ እየገባላቸው እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

የባለፈው ህዳር ወር ደመወዝም እስካሁን እንዳልገባ ገልፀው ፤ " ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሩ ከመፈታት ይልቅ እየተባባሰ ነው የሄደው፤ ለምን ይህ ይሆናል ? ብለን ስንጠይቅ የተለያየ ምክንያት ነው የሚሰጠን " ብለዋል።

ዛሬ በስልክ ያነጋገርነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆነ አንድ መምህር ባለፉት በርካታ ወራት ለአንድም ቀን ደመወዝ በአግባቡ እየገባ እንዳልሆነና በዚህ ምክንያት የትምህርት ስርዓቱ ላይ መስተጓጎል እንደተፈጠረ አመልክቷል።

መምህሩ ፤ " ለበርካታ ወራት በሰዓቱ ደመወዝ ገብቶ አያውቅም ፤ ግፋ ቢል 15 ቀን 13 ቀን ወስዶ ነው እየገባ ያለው። የዚህ ጉዳይ ምክንያት ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ ከፋይናንስ በጀት ተቀንሶ እየገባ መሆኑና ለሴክተር ሰራተኞች / ለመምህራን ማዳረስ እንደማይቻል ተብሎ ነው እየተነገረ ያለው። ለዚህ መፍትሄ አጥተን ነበር እንደአጋጣሚ ዛሬ ለመምህራን ደመወዝ እየገባ እንደሆነ እየተነገረ ነው ገና የህዳር ወር ፤ በዚህ ደመወዝ በአግባቡ አለመከፈሉ ምክንያት ትምህርትም ተስተጓግሎ ነበር ፤ እስከዚህ ድረስ ነው የችግሩ ስፋት " ብለዋል።

እኚሁ መምህር ፤ ዛሬ ሀሙስ ታህሳስ 13 የህዳር ወር ደመወዝ እየገባ እንደሆነ የሰሙት የመምህራንን ብቻ እንደሆነ ለሴክተር ሰራተኞች ገና መፍትሄ እየተፈላለገ ስለመሆኑ እንደሰሙ ገልፀዋል።

በወረዳው ደመወዝ በአግባቡ አለመግባት ሰራተኛውን ለችግር እና ለተለያዩ ወጪዎች እየዳረገው መሆኑ ተገልጿል ፤ ችግሩ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚፈልግም መልዕክታቸውን የላኩ ሰራተኞች አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
40/60

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ ወጥቶላቸው የቤት ቁልፍ የተረከቡ የ40/60 2ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች፣ የአዲስ አበባ አስተዳድር ቤቶቹን አጠናቆ ሊያስረክባቸው አለመቻሉን ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ቤቶቹን አጠናቆ ማስረከብ ባለመቻሉ ቅሬታ የቀረበባቸው ቤቶች አያት 2 ሳይት የሚገኙ 13 ብሎኮች ሲሆኑ የቅሬታ አቅራቢዎቹ ዕድለኞች ቁጥር 1,390 ነው፡፡

በሳይቱ ከአጠቃላይ ቤቶቹ ውስጥ የ11 ብሎክ ባለቤቶች ቁልፍ የተረከቡ መሆናቸውን፣ 2 ብሎኮች ደግሞ ከጅምሩ ቁልፍ አለመረከባቸውን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል፡፡

ባለዕድለኞች ምን አሉ ?

-  "ቤቶቹ ተጠናቀዋል፡፡ ቀሪው ሥራ  በአጭር ጊዜ ይጠናቃቀል" ተብለን ቁልፍ ብንረከብም ዕጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቤታችን ገብተን ለመኖር የሚያስችል የመንገድ፣ የመብራት፣ የውኃና የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የወለል ሴራሚክና የመታጠቢያ ቤት፣ የአሳንሰር እንዲሁም የፓርኪንግና የግንባታ ተረፈ ምርቶች ማንሳት እስካሁን አልተጀመረም።

- የቤቶቹ የአልሙኒየምና የመስታወት ሥራ፣ የውኃና የኤሌክትሪክ መስመርና የበረንዳ ሥራዎች ተጀምረው አልተጠናቀቁም፡፡

- ቤቶቹ ግንባታቸው ከተጀመረ 8 ዓመታት ሆኗቸዋል፤ ከጅምሩ ውል ስንገባ #በ18_ወራት ተጠናቀው እንደምንረከብ ቢገለጽም፣ አሁን የቤቶቹን ቁልፍ ብንቀበልም ቤቶቹ ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ላይ ስላልሆኑ ለከፍተኛ ወጪ ዳርጎናል።

የአ/አ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የተባለው ቅሬታ መኖሩን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ቤቶቹን ለማጠናቀቅ ባለፉት ዓመታት አገሪቱ የነበረችበት ሁኔታ ጋር ተዳምሮ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ሠርቶ ማጠናቀቅ እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ 👉 ያንብቡ : telegra.ph/RE-12-22-3

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ያፌት ዉብሸት ተክሉ ነዋሪነቱ በአሜሪካ ኒዉዮርክ ከተማ ሲሆን አለምን በመዞር ፎቶግራፎችን በማንሳት አፍሪካዊ እይታዉን ያንፀባርቃል::

ይንንም ተከትሎ አለምዐቀፉ አዶቤ አስር ተስፋ ከሚጣልባቸዉ ፎቶግራፈሮች ዉስጥ መድቦታል:: አርቲስቱ የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 15,2015 ቀን ዘ ኤድተር ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ስራዎቹን ያቀርባል

የፎቶ ኤግዚብሽኑ ከ ታህሳስ 15 - ጥር 6 2015 ይሆናል
H ኤዲተር  አትላስ ከ ሳፋየር አዲስ ጀርባ

@tikvahethiopia
#NewsAlert

" ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል " - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲሸጥ ተወሰነ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገለፀ።

መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር ገልጾ በዚህም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ሲሚንቶን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸው እንደነበር አሳውቋል።

በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው ተብሏል።

የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ተገልጿል።

#መንግስት ከግብይቱ የወጣ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም መንግስት ሽያጩ ያለ ደረሰኝ እንዳይካሄድ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ሚኒስቴሩ አሳውቋቃ።

በግብይቱ ውስጥም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ግዴታ መሆናቸውን የተጠቆመ ሲሆን እያንዳንዱ ፋብሪካ የተደራሽነት አድማሱን በማስፋትም አከፋፋዩን የመምረጥ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል ብሏል ሚኒስቴሩ።

ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚወጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ የመዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደሚኖርበት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert " ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል " - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲሸጥ ተወሰነ። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገለፀ። መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር ገልጾ…
#ሲሚንቶ

ፋብሪካዎች ያቀረቡት የመሸጫ ዋጋና የተወሰነው መሸጫ ዋጋ !

👉 ዳንጎቴ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 549.49
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 811.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤795.93

👉 ደርባ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.59
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 779.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 761.55

👉 ሙገር

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 643.95
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 802.73
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 755.70

👉 ናሽናል

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል➤ 561.00
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 779.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 756.50

👉 ሀበሻ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 683.44
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 947.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 754.48

👉 PIONEER

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 510.04
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1783.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 753.95

👉 ኢትዮ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 595.66
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 973.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 753.60

👉 INCHINI

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 0
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1298.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤750.21

👉 KUYU

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 628.10
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤1019.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 752.50

👉 ኢስት

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 506.99
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1064.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤753.82

👉 ካፒታል

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 633.38
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 905.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤751.34

#አማካይ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.3
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1014.6
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 758.1

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የፌደራል መንግስት እና የህወሓት ኃላፊዎች በአንድ ሳምንት ግዜ ውስጥ (ታህሳስ ወር ከማለቁ በፊት) የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ላይ ተገናኝተው ቀሪ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው ዛሬ በናይሮቢ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዜዳንት አሁሩ ኬንያታ ፤ " በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙርያ በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው። " ያሉ ሲሆን " መጪው የኢትዮጵያ የገና በአል የሰላም በአል እንደሚሆን አንጠራጠርም። የውጪ ሀይሎች ከትግራይ መውጣትም በስምምነቱ ላይ ያለ ጉዳይ ነው፣ አካሄዱም በእሱ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል።" ብለዋል።

ዛሬ ናይሮቢ ላይ በተጠናቀቀው ውይይት ላይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ፣ ጄነራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ እና ሌሎችም ተካፍለው እንደነበር ተገልጿል።

የአፍሪካ ህብረት ያወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ሃሳብ ከላይ ተያይዟል።

Credit : Elias Meseret
Photo : Social Media

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የፍ/ቤት መጥሪያ ፈርመው ወስደው ሳይቀርቡ ቀርተዋል የተባሉት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት #ታስረው እንዲቀርቡ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አዘዘ።

አቶ ሽመልስ "የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ተጭበርብሯል" ተብሎ የከባድ ሙስና ወንጀል በቀረበባቸው ተከሳሾች ላይ የዓቃቢህግ 2ኛ ምስክር ሆነው የተቆጠሩ ሲሆን መጥሪያ ፈርመው ተቀብለው ባለመቅረባቸው ምክንያት ነው ታስረው እንዲቀርቡ ፍ/ቤት ያዘዘው።

ሃምሌ 1/2014 ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር ተያይዞ  ዕጣው ተጭበርብሯል ተብሎ የአ/አ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱንና ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሀም ሰርሞሌን ጨምሮ አጠቃላይ በ11 ተከሳሾች ላይ በየደረጃው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ተከሳሾቹ ወንጀሉን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ገልጸው የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዓቃቢህግ ምስክር እንዲሰሙለት ጠይቆ ነበር።

በዚህ መሰረት ዓቃቢህግ ከቤቶቹ ዕጣ አወጣጥ ስርዓት ጋር ተያይዞ እንዲሁም ለምቷል የተባለው ሶፍትዌርን የሚመለከትና የተደረገ የኦዲት ስርዓትን ላይ ያተኮረ ምስክርነት እንዲሰማለት የምስክር ጭብጥ ካስመዘገበ በኋላ በህዳር 22/ 2015 ጀምሮ ፍ/ቤቱ የዓቃቢህግ ምስክር ቃል መሰማት ጀምሮ ነበር።

ፍ/ቤቱ እስካሁን የ8 የዓቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ያዳመጠ ሲሆን በ2ኛ የዓቃቢህግ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ግን መጥሪያ ደርሷቸው ፈርመው የወሰዱ ቢሆንም በችሎት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

ፍ/ቤቱም ግለሰቡ በፖሊስ ታስረው በይደር እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ያቀረቡት የመሸጫ ዋጋና የተወሰነው መሸጫ ዋጋ ! 👉 ዳንጎቴ - በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 549.49 - አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 811.00 - የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤795.93 👉 ደርባ - በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.59 - አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 779.00 - የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 761.55 👉 ሙገር - በስራ ላይ…
#ሲሚንቶ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በልሁ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ስለሆነው የሲሚንቶ ስርጭትና ግብይት መመሪያ ምንድነው ያሉት ?

አቶ ተሻለ በልሁ ፦

" ... አዲሱ መመሪያ አንደኛ የቀየረው ሲሚንቶ በገበያ ስርዓት ይመራ ነው። በገበያ የሚመራ ሲባል ምን ማለት ነው አከፋፋዮቻቸውን ፤ ቸርቻሪዎቻቸውን የመምረጥ ነፃነት #የፋብሪካዎች ነው። እስከዛሬ ማን ነበር የሚመርጥላቸው ? ሁለቱ ከተሞች እና ክልሎች ነበሩ። ስለዚህ ይሄ መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ #የመንግስት_አካል አከፋፋይ እና ቸርቻሪ አይመርጥም።

ለተወሰነ ጊዜ ምርታማነት እስከሚጨምር በገበያ የሚፈለገውን ያህል መጠን ፋብሪካዎቻችን አምርተው ማሰራጨት እስከሚችሉ ድረስ የፋብሪካ የብር ዋጋ ብቻ በሚኒስቴሩ ይተመናል ይሄም በ6 ወር አንዴ ብቻ ነው እንደ አስፈላጊነቱ ፤ አላስፈላጊ ከሆነ ገበያው እራሱ የሚመራው ከሆነ የዋጋ ተመን አይኖርም።

ሌሎቹን ማን ይተምናቸዋል ? መመሪያው ያስቀመጠው የትራንስፖርት ዋጋን ፣የወራጅ እና አውጪ ዋጋን፣ ውስን ትርፍ ህዳግን መነሻ በማድረግ የፋብሪካ ብር መሸጫ ዋጋን እንደ ቤንች ማርክ ወስደው ፋብሪካዎቹ እያንዳንዳቸው ያሳውቃሉ። ስለዚህ መንግስት ከፋብሪካ ውጭ ያለውን ዋጋ አይተምንላቸውም የሚተምነው ማነው ? ፋብሪካዎች ናቸው ። "

@tikvahethiopia
#መልዕክት

እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ፦

- የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት፣
- የቫይታሚን ኤ ጠብታ፣
- የአንጀት ጥገኛ ትላትል መድሀኒት፣
- የህፃናት የዞረ እግር ልየታ
- የምግብ እጥረት ልየታ እንዲሁም
- ለእናቶች ከወሊድ ጋር የተያያዘ ፊስቱላ ልየታ ከትላንት ታህሳስ 13 ጀምሮ በጤና ተቋማት እና በጊዜያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ይኸው ዘመቻ የሚዘልቀው እስከ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

በተለይ የቫይታሚን ኤ ጠብታ ህፃናት #በሽታን_የመከላከል አቅማቸው እንዲጎለብት እና በዳፍንት በሽታ በቀላሉ እንዳይጠቁ ያደርጋል።

በተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ወቅት እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የቫይታሚን ኤ ጠብታ ስለሚሰጥ ወላጆች በአቅራቢ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ወይም ጊዜያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያ በመሄድ ልጃችሁን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አድርጉ።

ውድ ቤተሰቦቻችን ይህን መልዕክት ላልሰሙት ይደርስ ዘንድ ሼር / ፎርዋርድ ያድርጉላቸው።

@tikvahethiopia
" ለኢትዮጵያ የሚያደርገው የልማት እና የምጣኔ ሀብት ድጋፍ ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ይደርጋል " - የአውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ህብረት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው ስምምነት ተፈጻሚ መሆን ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት መልሶ ለመጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጿል።

ህብረቱ ምን አለ ?

- ህብረቱ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ ያታዩ ለውጦችን አድንቋል። ለዚህም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

- የስምምነቱ በዘላቂነት ተግባራዊ መሆን ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነትን መልሶ ለመጀመር እንደሚያስችለው አሳውቋል።

ማስታወሻ ፦ የአውሮፓ ኅብረት በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ ወደ 110 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የበጀት ድጋፍ እንዲዘገይ ማድረጉ ይታወሳል።

- የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ መሆን፣ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና ለመብት ጥሰቶች ተጠያቂነት መኖር ለኢትዮጵያ የሚያደርገው የልማት እና የምጣኔ ሀብት ድጋፍ ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ያደርጋል ብሏል።

- በሰሜን ኢትዮጵያ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ የእርዳታ አቅርቦት ፍላጎት በመኖሩ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና መሠረታዊ አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲል ገልጿል።

- ኤርትራን በተመለከተ የድንበር ጦርነቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥታት መካከል የተደረሰውን #የአልጀርስ_ስምምነት እንዲሁም ከአራት ዓመት በፊት የተደረሰውን የሰላም ስምምነትን ጠቃሚነት ገልጾ ፤ የኤርትራ ሠራዊት በአስቸኳይና ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ጠይቋል።

#BBC

@tikvahethiopia
#ክብሩ_ዶክተር_አጋ_ጠንጠኖ

የክብር ዶክተር አጋ ጠንጠኖ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የክብር ዶ/ር አጋ ጠንጠኖ ማን ነበሩ ?

- በ1937ዓ.ም ነበር ከአባታቸው ጠንጠኖ ጉዬ እና ከእናታቸው ጋልጋሉ ሃላኬ የተወለዱት።

- ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የጉጅ ኦሮሞ አባ ገዳ በመሆን ህዝባቸውን አገልግለዋል።

- የስልጣን ጊዜያቸውን አጠናቀው በገዳ ስርዓት የአስተዳደር ጊዜያቸውን ለ73ኛው የጉጂ አባ ገዳ ዋቆ ዱቤ በ2000ዓ.ም ነበር ያስረከቡት  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከኋላቸው ላሉት ለገዳ ስርዓት መሪዎች እንዴት ሀገርን መምራት እና አብሮ መኖር እንደሚችሉ በመምከር እና ሰላምን በማጎልበት ትልቅ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል።

- የገዳን ሥርዓት ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከገዳ ምክር ቤት ጋር ሠርተዋል።

- በህይወት ዘመናቸው መቻቻል፣ መከባበር እና በሰላም አብሮ የመኖር ባህልን በመገንባት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። 

- የገዳ ትምህርት በዩንቨርሲቲዎች እንዲሰጥ እና የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) እንዲመዘገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

- በ2008 ዓ.ም ካቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷቸዋል።

መረጃው ምንጭ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #AddisAbaba

የ2ኛውን ዙር የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በ16 / 4 /2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ ዛሬ አሳስቧል።

የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia