TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአሜሪካን ዋሽንግቶን ዲሲ የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። - ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ተገናኝተው ተውያይተዋል። የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል። - ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ IMF…
#USA #AFRICA
ለ3 ቀናት የተካሄደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ሐሙስ ተጠናቋል።
የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በጉባኤው ምን አሉ ?
- ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች በቅርቡ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች የሚያደርግት ጉብኝት እንደ ፕሬዝደንት የመጀመሪያው ነው። ቀኑን እና የትኞቹ ሀገራትን እንደሚጎበኙ ግን አላሳውቁም።
- አፍሪካ እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልፀው አሜሪካ ትኩረቷን እንደምትጨምርም ጠቁመዋል።
- ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ወደ አፍሪካ እንደሚልኩ ገልፀዋል። ወደ አፍሪካ ከሚላኩት ውስጥ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን፣ የገንዘብ ሚኒስትሯ ጃነት የሊን እና የንግድ ሚኒስትሯ ጂና ሬይሞንዶ ይገኙበታል።
- በሚቀጥለው ዓመት ለሚደረጉ ምርጫዎች 165 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመደብ ቃል ገብተዋል።
ፕሬዚደንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን የአፍሪካ አገራት መሪዎችንና ቀዳማዊ እመቤቶቻቸውን በዋይት ሃውስ የእራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።
በሌላ በኩል ፤ በአሜሪካ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ሊሳተፍ ወደ አሜሪካ አቅንቶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ሀገር መመለሱን የጠ/ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ አመሻሹን አሳውቀዋል።
#ቪኦኤ #አምባሳደር_ሬድዋን_ሁሴን
@tikvahethiopia

😢
ሀገራችን እኛም እንደ ህዝብ በብዙ መከራና ችግር ውስጥ አልፈናል፤ አጠገባችን የነበሩ ብዙዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ግፍ ታፈፅሞባቸዋል፤ እንደወጡም ቀርተዋል።
በርስ በርስ ግጭት፣ ጦርነት ታገዳድለናል፣ ተጨካክነናል፤ አሁን አሁን ግን የሚታየው ድርጊት ሁሉ አንዳንዶች ምን ያህል ትንሽ እንኳን ርህራሬ የሚባል ነገር ውስጣቸው እንዳሌለ የሚያሳይ ነው።
ከዚህ ቀደም በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ እጅግ ለማየት የሚዘገንን ግፍ ሲፈፀም፣ ሰው በቁሙ ሲቃጠል፣ ተወግሮ ሲገደል፣ ሰዎች ከጀርባቸው በጥይት ሲደበደቡና ወደ ገደል ሲከተቱ፤ ከምን በላይ ደግሞ ልክ በጎና ለትውልዱ ፍቅርና ጅግንነት ያስተላለፉ ይመስል በቪድዮ እየቀረፁ ፍፁም ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ሲፈፅሙ የነበሩ ሰዎች አይተናል።
በየወቅቱ ካየነው ተነስተን "ምናልባት በሀገራችን ያላየነው የተደበቀ፤ ከዚህ የከፋ ይኖር ይሆን?" ብለን ስንጠይቅ ነበር፤ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወረው ይኸው ይሁን ?
የሰሞኑን ቪድዮዎች ምንም ይሁን ምን ይኼን ያህል የሰው ልጅ ይጨክናል ወይ? ትንሽ ርህራኔ የሚባል ነገር አልፈጠረበትም ወይ? የሚያስብል ነው።
ከምንም የከፋው መጥፎ ድርጊት ተፈፅሞ ሲገኝ አድርጊዎቹን ለመከላከልና ለነሱ ጥብቅና ለመቆም የሚደረገው ጥረት እንዲሁም ጉዳዩን ለማብራራት የሚኬድበት ርቀት ነው።
ድርጊቱን ከማውገዝና ፍትህ ከመጠየቅ ይልቅ ካለፈው ጋር እያነፃፀሩ አንዱን ግፍ በሌላ ለማካካስ/ቀለል ብሎ እንዲታይ ለማድረግ የሚሞከረው ሙከራ ምን ያህል ሰብዐዊ መሰረታችን ከቀን ወደ ቀን እየጠፋ መሄዱን አመላካች ነው።
አንድ ድርጊት ሲፈፀም ድጋመኛ እንዳይፈፀም አድራጊዎቹ ምን ተደረጉ? የሚለው መሰረታዊ ጉዳይ ሲሆን ሁሉም ዜጋ ግፍን እኩል ማውገዝ ካልቻለና ፍትህ ካልጠየቀ ከዚህ የከፋ አዙሪት መውጣት አዳጋች ነው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሳዑዲ አረቢያ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ምን አለ ?
አምነስቲ ኢንትርናሽናል ከሰሞኑን በሳዑዲ አረቢያ ፤ ኢትዮጵያውያን ስላሉበት ሁኔታ አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
በዚህ ሪፖርቱ የገለፃቸው ፦
- " ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ናቸው " የተባሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ (ከ30 ሺህ ይበልጣሉ) ኢትዮጵያውን ስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች #በሰቆቃ ውስጥ ይገኛሉ።
- ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች የሚገኙባቸው ስደተኞች በዘፈቀደ ተይዘው በእጅጉ በተጨናነቁት አል-ኻራጅ እና አል-ሹማይሲ በተባሉ እስር ቤቶች ይገኛሉ።
- የሳዑዲ ባለሥልጣናት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን #ኢሰብአዊ እና #ጭካኔ በተሞላበት አያያዝ ላልተገደበ ጊዜ በእስር ካቆዩ በኋላ በግድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ይደርጋሉ።
- ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ ውስጥ ለስቃይ የሚዳረጉት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የላቸውም በሚል ሲሆን ይህም ሁኔታ በ"ካፋላ" የሠራተኞች ቅጥር ሥርዓት ምክንያት የተባባሰ ነው።
- ባለፉት 5 ዓመታት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ በማለፋቸው በርካቶች ለከባድ እና ለዘላቂ አካላዊ እና አእምሯዊ ችግሮች ተዳርገዋል። በአሁኑ ወቅት ከ30,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ሁኔታ ተይዘው ተመሳሳይ ዕጣ እየተጋፈጡ ነው።
- የሳዑዲ ባለሥልጣናት ባለፉት 2 ዓመታት በእስር ቤቶች በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ማሰቃየቶችን እንዲሁም ቢያንስ 10 ሞቶች ላይ ምርመራ ሊያካሂዱ ይገባል።
https://www.amnesty.org/en/latest/news/2022/12/saudi-arabia-ethiopian-migrants-forcibly-returned-after-detention-in-abhorrent-conditions/
#BBC

#ዓለም_ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ደማቅ አዲስ ታሪክ ፅፋለች ! በአሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ የሚመራው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በየሱፍ ኤል ነስሪ ብቸኛ ግብ ፖርቹጋልን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል። ⚽️ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫው ታሪክ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል የቻለች ቀዳሚዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች። ⚽️ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ #በተጋጣሚ_ቡድን #ተጫዋች…
#FIFA_World_Cup : አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ በፊፋ ዓለም ዋንጫ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
ፖርቹጋል ላይ ታሪካዊ ድል አስመዝግባ ፤ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ የቻለችው ሞሮኮ በፈረንሳይ ተሸንፋ ለፍፃሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታ ነበር።
ዛሬ ለሶስተኛ ደረጃ ክሮሽያ ጋር በተደረገው ጨዋት 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፋ 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።
ቲክቫህ ስፖርት : https://t.me/tikvahethsport
@tikvahethsport

#Tigray
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአቢ ዓዲ – ዐድዋ የተዘረጋው የባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና 90 % መጠናቀቁን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።
የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ጥገና በአብዛኛው በመጠናቀቁ የዐድዋ እና አክሱም ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ በነገው ዕለት የሙከራ ሥራ እንደሚሠራ ገልጿል።
በተጨማሪም ከዐድዋ – ሽረ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ የተዘረጋው የ66 ኪሎ ቮልት የሥርጭት መስመር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠግኖ የተጠናቀቀ ቢሆንም ከሽረ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ለመስጠት የሙከራ ሥራ ሲከናወን በብሬከሩ ላይ ችግር ማጋጠሙ ተገልጿል።
የብሬከሩን ብልሽት በመጠገን ከመስመሩ ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።
#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል

#GlobalBankEthiopia
" ደቡብ ግሎባል ባንክ " ስያሜውን ወደ " ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ " መቀየሩን ሪፖርተር አስነብቧል።
ባንኩ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤውን ስያሜውን ወደ " ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ " መቀየሩ ተገልጿል።
የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኩ ከዚህ በኋላ በአዲስ ስያሜና አርማ እንደሚቀጥል ያቀረበውን ሀሳብ የባንኩ ጠቅላላ ጉባኤ አጽድቆታል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስያሜ የሚቀጥለው የቀድሞ ደቡብ ግሎባል ባንክ በ2014 ሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 370 ሚሊዮን ብር ማትረፉም ተገልጿል።
ይኸም ካለፈው ተመሳሳይ የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነፃጸር 41 በመቶ ወይም የ108.4 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።
ባንኩ ተቀማጭ ሒሳቡን ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱንና ፣ በ2014 ሒሳብ ዓመትም 2.3 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።
#ሪፖርተር

#ይገምቱ
የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማን ይሆናል ?
#ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና ከ12:00 ጀምሮ የዓለም ዋንጫው ባለድል ለመሆን ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ።
የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል ? የዋንጫው ባለቤት የሚሆነውን #ሀገር በትክክል ለመገመቱ 20 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ250 የሞባይል ብር ካርድ በሥጦታ የምናበረክት ይሆናል።
20 ትክክለኛ ገማቾች የሚለየቱ መልዕክቱን በላኩበት ቅደም ተከተል ነው።
ግምቱን መላክ ሚቻለው ጨዋታው እስከሚጀምርበት ደቂቃ ድረስ ብቻ ሲሆን #Edit የተደረገ ምላሽ ተቀባይነት አይኖረም።
(ግምትዎን #ከታች_ባለው የአስተያየት ማስቀመጫ ላይ ያኑሩ ፤ ፈረንሳይ ወይስ አርጀንቲና ? ከሁለቱ ሀገራት አንዱን ብቻ ይምረጡ ፤ ውጤት / በቁጥር መገመት #አያስፈልግም )

#ይገምቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማን ይሆናል ? #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና ከ12:00 ጀምሮ የዓለም ዋንጫው ባለድል ለመሆን ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ። የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል ? የዋንጫው ባለቤት የሚሆነውን #ሀገር በትክክል ለመገመቱ 20 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ250 የሞባይል ብር ካርድ በሥጦታ የምናበረክት ይሆናል። 20 ትክክለኛ ገማቾች የሚለየቱ መልዕክቱን በላኩበት ቅደም ተከተል…
#Update #WorldCup
በFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እያደረጉ የሚገኙት #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና መደበኛ 90 ደቂቃውን በ2 ለ 2 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።
ምንም እንኳን አርጀንቲና በሜሲ እና ዲማሪያ ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ በበላይነት ብታጠናቅቅም ፈረንሳይ በሁለተኛው አጋማሽ ቡድኗን አጠናክራው በወጣቱ ምባፔ ሁለት ጎሎች አቻ መሆን ችላለች።
ጨዋታው አቻ መሆኑን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።
ይህን የዓለም ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ፍልሚያ ሚሊዮኖች እየተከታተሉት ይገኛሉ። ማን አሸናፊ ይሆን ?
More : https://t.me/tikvahethsport