TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጠቃላይ_20_80_አዲስ_የቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_1.pdf
988.2 KB
አጠቃላይ የ20/80 አዲስ የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር !

Credit : Mayor Office of AA

@tikvahethiopia
አጠቃላይ_20_80_ነባር_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
4.8 MB
አጠቃላይ የ20/80 ነባር የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር !

Credit : Mayor Office of AA

@tikvahethiopia
አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
1.3 MB
አጠቃላይ የ40/60 የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር !

Credit : Mayor Office of AA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የባለ ዕድለኛ የዕጣ ዝርዝር ላይ ስማችሁን ማግኘት ያልቻላሁ / ባለዕድለኛ #መሆን #አለመሆናችሁን ማረጋገጥ የምትፈልጉ ፦

- በቅድሚያ የPDF ፋይሉን https://t.me/tikvahethiopia/74809 አውርዱ (Download)

- በመቀጠልም ከላይ በምስሉ የሚታየውን የመፈለጊያውን ምልክት ተጫኑ፤

- በመጨረሻም ስማችሁን በማስገባት የመፈለጊያውን ምልክት ከስልካችሁ ላይ ተጫኑ፤

- የPDF ፋይሉ በአማርኛ የተዘጋጀው ከሆነ በአማርኛ ስማችሁን አስገብታችሁ ፈልጉ በእንግሊዝኛ ከሆነም በእንግሊዝኛ ስማችሁን አስገቡ፤

- የስም መመሳሰል ካለ በአግባቡ የባንክ ቁጥር መረጃችሁን ተመልከቱ።

@tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ጠቅላይ  ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን ይፋ አድርገዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፤ የልዩ ሎተሪ ዕጣ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ/ም መውጣቱን አሳውቋል።

(አጠቃላይ የዕጣ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)

* ከቀኑ 6:00 ላይ Update የተደረገ።

@tikvahethiopia
#iSonXperiences

ከትላንት ጀምሮ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያሳያል።

ሰራተኞቹ የሥራ አድማውን ያደረጉት መስሪያ ቤታችን ቅሬታችንን ሊመልስልን አልቻለም በሚል መሆኑን ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ ካቀረቡት ጥያቄዎች ዋነኛው " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞቹን በራሱ ሥር ያካተን ፤ በኤጀንት ለምን ያሰራናል ? " የሚል ነው።

በተጨማሪ ፦

➢ ለሙያው ከሚገባውና ካለው የሥራ ጫና አንጻር ተገቢ ያልሆነ የደመወዝ አከፋፈል ፤ ደመወዝ አላግባብ ተቆራርጦ መድረስ እና በጊዜው አለመግባት

➢ ለሰራተኛ የሚገባውን የሕይወትና የአካል ጉዳት ኢንሹራንስ አለመግባት፤

➢ ሰራተኛው ለማጁን የሰለጠነበት የምስክር ወረቀት አለመስጠት፤

➢ ድርጅቱ በተለያዩ የቀን እና የለሊት ፈረቃ ለሚሰሩ ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የመጓጓዣ አገልግሎት ጉድለት የሚሉና #ሌሎችም ቅሬታዎች አሏቸው።

ቲክቫህ ከቤተሰቦቹ እንደተረዳው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች በቀጥታ የተቀጠሩት በሳፋሪኮም ሳይሆን ISON Xprience በተባለ ድርጅት አማካኝነት ነው።

ከሰራተቹ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የ " ISON Xprience " የሥራ አመራሮች ህዳር 1 ቀን ከሰራተኛ ተወካዮች ጋር ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

በዚህ ስብሰባ ላይ ክፍያን በተመለከተ ፤ " በኢትዮጵያ ህግ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ስለሌለ ደመወዝ በድርድር / በድርጅቱ የደመወዝ ስኬል የሚወሰን ነው።" ሲል ገልጿል።

ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የደረሱን ቅሬታዎች ይዘን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ለማነጋገር እና ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርገናል።

ሳፋሪኮም ፤ " የጥሪ ማዕከላችንን በሚያስተዳድርልን ድርጅት (ISON Xprience) እና በሰራተኛው መካከል አለመግባባቶች እንዳሉ ተረድተናል። " ያለን ሲሆን " በደርጅቱ ሥራ አስፈጻሚዎችና ሰራተኞች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተፈትቶ መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴዎች እንደሚቀጥሉ ተስፋ እናደርጋለን " ብሏል።

በዚህ ወቅት፤ ለደንበኞቹ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንደከዚህ ቀደሙ ፤ በተለመደው መልኩ እንደ ቀጠለ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/ISON-Xprience-11-16
TIKVAH-ETHIOPIA
የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የባለ ዕድለኛ የዕጣ ዝርዝር ላይ ስማችሁን ማግኘት ያልቻላሁ / ባለዕድለኛ #መሆን #አለመሆናችሁን ማረጋገጥ የምትፈልጉ ፦ - በቅድሚያ የPDF ፋይሉን https://t.me/tikvahethiopia/74809 አውርዱ (Download) - በመቀጠልም ከላይ በምስሉ የሚታየውን የመፈለጊያውን ምልክት ተጫኑ፤ - በመጨረሻም ስማችሁን በማስገባት የመፈለጊያውን ምልክት…
Addis Lissan Hidar 8-2015 .pdf
52.3 MB
የ20/80 እና የ40/60 የቤት ባለዕድለኞች የስም ዝርዝር በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ (በልዩ ዕትም) ታትሞ ወጥቷል።

ከላይ የተያያዘው " የአዲስ ልሳን " ጋዜጣ ቅጂ (ሶፍት ኮፒ) ነው።

ከላይ የተያያዘውን " 52.3 MB " PDF ፋይል በማውረድና በመክፈት የመፈለጊያ ምልክቷን በመጫን ስምዎትን በአማርኛ / በእንግሊዝኛ በማስገባት ስምዎት በጋዜጣው ላይ ታትሞ ስለመውጣቱ #ማረጋገጥ ይችላሉ።

Credit : Addis Lissan

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተድርጓል።

ከዚህ ቀደም ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ በነበረው የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዕቃዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክና ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ማሻሻያ የተደረገባቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

1. በታሪፍ ቁጥር 9401. 9000 እና 9403. 9000 የሚመደቡ እቃዎች ክፍሎች ማምረቻ ግብአቶች፣

2. ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በውጭ ምንዛሬ የመሸጥ ፍቃድ ያላቸው ሬስቶራንቶችና ሱፐር ማርኬቶች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣

3. ባለ ኮከብ ሆቴሎች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስመጧቸው ዕቃዎችና

4. የቀረጥ ነጻ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች

የውጭ ምንዛሬ ክልከላው የማይመለከታቸው መሆኑ ተገልጽዋል፡፡

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ የ38 እቃዎች ዝርዝር በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወሳል (ለማስታወሻ ያህል ከላይ ተያይዘዋል) ።

ምንጭ፦ ገንዘብ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
" ... አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " - አቶ ዳመነ ተሾመ

ከጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ. ም ጀምሮ እስካሁን ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአዳማ እስከ መተሃራ ባለው አውራ ጎዳና የሚንቀሳቀሱ 5 የአገር አቋራጭ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ታግተው ተወስደው 3ቱ #በሕይወት_እንዳልተገኙ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማሕበር አመራር አባል አቶ ዳመነ ተሾመ ለዶቼ ቬለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " ታግተው ጫካ ከተወሰዱት 5 ሹፌሮች መካከል ገንዘብ ከፍለው የወጡ አሉ " ብለዋል።

አቶ ዳመነ ፤ ይህንን እገታ የፈፀሙትን አካላት ማንነት እንዳላወቁትና መንግሥትም የደረሰበት እንደማይመስላቸው ተናግረዋል።

" በኮሪደሩ ላይ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረ ነው። አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " ብለዋል።

ማሕበራቸው ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጋር ትናንት በችግሩ እና መፍትሔዎች ዙሪያ መወያየቱን ገልፀው ፤ " የሾፌሮች መታገት እና መንገላታት ይቁም። እኛ የአበል፣ የደሞዝ ጥያቄ ሳይሆን መንግሥት #ከለላ እና #ጥበቃ ያድርግልን የሚለውን ሀሳብ አንሸራሽረናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዋናነት ከአዳማ እስከ መተሃራ በምእራብ ወለጋ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ችግር ውስጥ እንደሆኑ የጠቆሙት አቶ ዳመነ አሽከርካሪዎቻችን ወደ ቤታቸው ለመግባት በየመንገዱ ችግር እየተፈጠረባቸው ወደ 21 ቀናቶችን ፈጅቶባቸዋል " በማለት የሚገጥማቸው ችግር ምን ያህል አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ አስገንዝበዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ ሬድዮ

@tikvahethiopia
" የአሜሪካ መንግስት ዋሽቶናል፣ በምሥጢራዊ ሂደት መብታችንን ቀምቶናል " - የሟች ቤተሰቦች

በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዥያ በተከሰከሱት ሁለት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ሳቢያ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች በአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት እና በቦይንግ መካከል በተደረሰው ስምምነት ላይ ቅሬታቸውን እንዳሰሙ ሮይተርስ ዘግቧል።

ተጎጂ ቤተሰቦቹ እአአ በ2021 የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር የደረሰውን ስምምነት በመቃወም ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ነው የጠየቁት።

ቤተሰቦቻቸውን በሁለቱ አደጋዎች ያጡት ሰዎች በመሥሪያ ቤቱ እና በቦይንግ መካከል የተደረሰው ስምምነት፣ አውሮፕላን አምራች ኩባንያው "የወንጀል ክስ ሳይመሠረትበት እንዲያመልጥ"  በማድረጉ ማብራሪያ መጠየቃቸውን የሮይተስ ዘገባ ይጠቁማል።

ባለፈው ወር አሜሪካዊው ዳኛ ሪድ ኦኮነር ቴክሳስ ውስጥ ባሳለፉት ውሳኔ በሁለቱ የ737 ማክስ አውሮፕላን ደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን "#የወንጀል_ሰለባ" ናቸው ብለዋል። ምን ዓይነት ማካካሻ መሰጠት እንዳለበት እንደሚወስኑም ዳኛው ተናግረዋል።

እንደሮይተርስ ዘገባ ባለፈው ዓርብ ዕለት የሟቾች ቤተሰቦች እና ጠበቆቻቸው  ከመንግሥት ጠበቆች ጋር መገናኘታቸውንና በቦታው ያልነበሩ ሰዎች ደግሞ በበይነ መረብ ስብሰባውን ተካፍለዋል።

የሟቾቹ ቤተሰቦች የአሜሪካ መንግሥት "ዋሽቶናል፣ በምሥጢራዊ ሂደት መብታችንን ቀምቶናል" ሲሉ ለዳኛ ሪድ ኦኮነር ተናግረዋል።

እአአ በ2021 ቦይንግ አውሮፕላኑ ላይ ስላሉ ግድፈቶች ይፋ ካለማድረጉ እንዲሁም ከማጭበርበር ጋር በተያያዘ ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ከተደረገ በኋላ የተሰጠው ያለመከሰስ መብት እንዲነሳና ተጠያቂ እንዲደረግ አሳስበዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reuters-11-19 /ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የነገ እሁድ ፕሮግራማችሁን ታስተካክሉ ዘንድ ፦

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ22ኛ ጊዜ ነገ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ይካሄዳል፡፡

ውድድሩ፦
- በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣
- በቡናና ሻይ ፣
- በባልቻ መታጠፊያ፣
- በጌጃ ሰፈር ፣
- በ5ኛ መስቀለኛ፣
- በአረቄ ፋብሪካ ፣
- በሜክሲኮ፣
- በሰንጋ ተራ፣
- በብሄራዊ ቴአትር፣
- በሃራምቤ ሆቴል፣
- በፍል ውሃ ፣
- በካዛንቺስ ፣
- በኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ባምቢስ ታጥፎ መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደርጋል፡፡

ሩጫው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲዝተቀሙ #ለተሸከርካሪ_ዝግ የሆኑ መንገዶች ይኖራሉ።

በዚህም መሰረት ፦  

• ኮመገናኛ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 እና ዘሪሁን ህንፃ ፤

• ከቦሌ መድሃኔአለም ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤ/ክርስቲያን የሚወሰወደው መንገድ አትላስ መብራት ፤

• ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ ላይ፤

• ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አጠገብ፤

• ከጎፋ በቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ ፤

• ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪ ቡልጋሪያ ማዞሪያ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ገነት ሆቴል አጠገብ ፤

• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አካባቢ ትራፊክ መብራት ላይ፤

• ከልደታ ፀበል  ወደ ቅድስት ልደታ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  ልደታ ፀበል አካባቢ፤

• ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ኑር ህንፃ አካባቢ፤

• ከፈረሰኛ ወደ ጌጃ ሰፈር ፈረሰኛ መብራት ላይ፤

• ከሞላ ማሩ ወደ ጌጃ ሰፈር ሞላ ማሩ ፤

• ከበርበሬ በረንዳ ወደ 5ኛ በርበሬ በረንዳ አካባቢ፤

• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል፤

• ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት ሜትሮሎጂ አካባቢ፤

• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሄራዊ ቴአትር ጎማ ቁጠባ አጠገብ፤

• ከጎማ ቁጠባ ወደ አረቄ ፋብሪካ እና ሰንጋተራ የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ፤

• ከቸርችል ጎዳና  ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ላይ (ኢሚግሬሽን አካባቢ)፤

• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ፍልውሃ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት አካባቢ፤

• ከአራት ኪሎ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት እና አሮጌው ቄራ መታጠፊያ ላይ፤

• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ እና ወደ ቶታል የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ አካባቢ ፤

ከለሊቱ 11፡00 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ከዋዜማው ምሽት ጀምሮ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድና ማሳደር የተከለከለ ነው።

ተጨማሪም አሽከርካሪዎች የውድሩሩ ተሳታፊዎች ወደ ሚያልፉባቸው መንገዶች ተሽከርካሪ ይዞ መውጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት ፦ 011-1-11-01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም ይቻላል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia