TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬን ጨምሮ የዕረፍት ቀናቶችን የት ለማሳለፍ አስበዋል ?

የአዲስ አበባ ከተማን ገፅታ ከቀየሩ ፕሮጀቶች አንዱ " የወዳጅነት ፓርክ " ነው።

የዚህ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተከፍቶ በርካቶች እየጎበኙት እንደሆነ ይታወቃል ፤ ከቀናት በፊት ደግሞ የሁለተኛው ምዕራፍ በይፋ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተከፍቶ በነፃ እየተጎበኘ ነው።

የምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ምን ይዟል / ስለፓርኩስ የሚታወቀው ምንድነው ?

ይህ የምዕራፍ 2 የወዳጅነት ፓርክ በ11 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ነው ያረፈ ሲሆን 3 ክፍሎችም አለቱ።

1ኛ. የህፃናት መጫወቻ ስፍራ ፦

ሰፊውን የፓርኩን ክፍል የሚሸፍን ሲሆን ልጆች አካላዊ እና አእምሯዊ እድገታቸውን ለመጨመር እንዲያግዝ ተድረጎ ያተገነባ ነው። በተጨማሪ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን መለማመድ ያስችላቸዋል።

2ኛ. የወጣቶች የስፖርት ስፍራ፦

የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያው ስፍራ ወጣቶች የአካል ብቃት የሚሰሩበት እና አእምሯቸውን ዘና የሚያደርጉበት ሲሆን በውስጡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የቴኒስ መጫወቻ ፣ የመሮጫ መም ፣ የባስኬት መጫወቻ የያዘ ነው።

3ኛ. የሰርግ አፀድ፦

ይህ የፓርኩ ክፍል ጥንዶች የሰርግ ስነስርዓታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያዘጋጁ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ነው። ጥንዶች ጋብቻቸውን ሲፈፅሙ እንደአንድ አማራጭ አድርገው ሊወስዱት የሚችል ደረጃውን የጠበቀ ስፍራ ነው።

የወዳጅነት ፓርክ ምዕራፍ 2 እንደ ፕሮጀክት 1 ሁሉ ለፎቶ፣ ቁጭ ብሎ እራስን ለማዝናናት፣ ከራስ ጋር ለመሆን ምቹ ስፍራ ነው።

መግቢያ አለው ?

ፓርኩ ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ ከነገወዲያ እሁድ ድረስ #በነፃ ለጎብኝዎች ክፍት ሲሆን በቀጣይ ተመጣጣኝ የሆነ የመግቢያ ዋጋ ይፋ ይደረግለታል ተብሏል።

ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር እስከ እሁድ መጎብኘት ትችላላሁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* Confirmed

በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች በኩል ዝርዝሩን በተመለከተ በግልፅ ለህዝቡ ምንም ሳይባል ሰዓታት አልፈው ነበር።

ይህም አንዳንድ ሲሰራጩ የነበሩት የስምምነቱ " Draft " ወረቀቶች ትክክል ናቸው / ሀሰት ናቸው የሚሉ አካላትን ፈጥሯል።

ዛሬ ጥዋት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በሰላም ንግግሩ ተሳታፊ የሆኑት እና እዚህ የስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ብዙ የቡድን እልህ አስጨራሽ ክርክሮች ተደርጎ የተፈረመበት ያሉትን ትክክለኛውና ዝርዝር ስምምነቱን የያዘውን ወረቀት አሰራጭተዋል።

(አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በተረጋገጠ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያሰራጩት የስምምነቱን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
#Update

ዛሬ " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " አባላት ፤ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አጠቃላይ ሂደት እና ቀጣይ ስራዎችን በሚመለከት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ለሁለቱ ም/ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች ፣ ለክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች ፣ ለከፍተኛ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሀሴን የተናገሩት ፦

- ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቋል።

- በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችልና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- ከህገ-መንግስት ውጪ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቆመው በትግራይ ክልል በህገ-መንግስቱ መሰረት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ #ጊዜያዊ_አስተዳደር ይቋቋማል።

- ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ቀደመው ማህበራዊ ትስስር እንዲመለሱ በጋራ ይሰራል።

- የወደሙ ተቋማትን ጨምሮ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በጋራ ርብርብ ሊከናወኑ ይገባል። የትስስርና የተግባቦት ስራዎች የህዝቦችን መጻኢ የጋራ ጉዞ ታሳቢ ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል።

- በግጭቱ ምክንያት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እንዲሁም በሌሎች መስኮች የደረሰውን ጫና በማስተካካል ረገድ በትብብር መስራት ይጠበቃል።

- የመገናኛ ብዙሃን #ቁርሾዎችን ማባባስ ሳይሆን ዜጎች ከችግሩ ተምረው በቀጣይ አብሮነታቸውን አጠናክረው የሚሄዱበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ሊሰሩ ይገባል።

- #በማወቅም ሆነ #ባለማወቅ የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሰሩ ኣካላትን በጋራ ማስቆም ይገባል።

- ሁሉም ዜጋ ለሰላም ስምምነቱ #ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ  ይገባል።

#ENA

@tikvahethiopia
#Update

• ከቀያቸው የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋሙ ሂደት ላይ ህዝበ ሙስሊሙ በንቃት እንዲሳተፍ ይፋዊ ጥሪ ቀርቧል።

ዛሬ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የፕሪቶሪያውን የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ስምምነት እስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፤ " በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ተከስቶ የነበረውን የእርስበርስ ጦርነት ለማቆም ሲደረግ የነበው የሰላም ውይይት ስምምነት ላይ በመድረሱ ለመላው ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የእንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

ለሐገራችን ዘላቂ ሰላም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ብሔር፣ ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት ሳይለይ በጋራ ጠንክሮ መሥራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በጦነቱ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖች የአላህን እዝነት ፣ ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ መጽናናትን ተመኝተው ከቀያቸው የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋሙ ሂደት ላይ በተለይ ህዝበ ሙስሊሙ ከጠቅላይ ም/ቤቱ በሚወጡ መርሐ ግብሮች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

" አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካ ችግሮች " በሚለው መርሕ መሠረት በደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ የነበረውን ድርድር ላመቻቹት የአፍሪካ መሪዎች፣ ለተወከሉት ተደራዳሪዎች እንዲሁም ለአፍሪካ ሕብረት የላቀ ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የደረሰን መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
አባታዊ የደስታ መልዕክት !

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የደስታ መግለጫ አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ሰላም በመሸናነፍ መርህ የሚገኝ አይደለም፣ ጠብ የሚባል ነገርንም አያውቅ ይልቁንም #የትህትና እና #የይቅር ባይነትን መንፈስ ያጎናጽፋል እንጂ። 

አሁን የተደረሰበት ስምምነት የበርካታ እናቶችን እምባ የሚያብስ፣ የህጻናትን ሰቆቃ የሚያቆም እንዲሁም በወንድማማች ሕዝቦች መካከል የተከሰተውን ደም መፈሰስ ለማቆም መሰረት የሚጥል፣ ሕዝቦችንም ወደ አንድነት እና ሰላም የሚመራ በጎ እርምጃ ነው ብለን እናምናለን። 

በመሆኑም የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመስንግስት የስራ ሃላፊዎች፤ የሚመለከታቸው ሁሉ እና በጎ ፈቃድ ያላችሁ በሙሉ የሀገራችን ሰላሟ በዘላቂነት እንዲረጋገጥ፤ በህዝባችን መካከል የይቅርባይነት እና የእርቅ መንፈስ እንዲሰፍን እና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደየቀዬአቸው መመለስ እንዲችሉ እንድንረባረብ አደራ እላችኋለሁ።

በጸሎታችሁም በርቱ።

እግዚአብሔር እትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ "

(የብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
የ ' ሰላም ስምምነቱ ' #ስኬታማ እንዲሆን ምን ይደረግ ?

የፕሪቶሪያው የ "ሰላም ስምምነት" ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦች በአግባቡ መሬት ይዘው፤ ሲፈጸሙና የጦርነቱ ሰለባ የሆነው ሕዝብ እፎይታን ሲያገኝ እና ሲታከም ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በላከል መግለጫ አሳውቋል።

ም/ ቤቱ የሰላም ስምምነቱ ፍሬያማ ይሆን ዘንድ ፦

- የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሓት በስምምነቱ ማእቀፍ ሊተገብሩ በተስማሙት ሠነድ መሠረት ፦ የአፈጻጸም ሂደቱ አካታች ፣ ተዓማኒ እና ግልጽ ሆኖ በታመለት ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንዲቻል በፍጹም ቁርጠኛነት እንዲሁም በተጠያቂነት መንፈስ እንዲያከናውኑ በአጽንዖት ጠይቋል።

- የፓለቲካ ኃይሎች ስምምነቱ ፍሬ እንዲያፈራና በሀገራችን ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲኖር የሰላም ደጋፊ ሊሆኑ ይገባል ብሏል። የእልህ እና የብሽሽቅ ፕሮፖጋንዳዎች ቆመው የአሸናፊነትና ተሸናፊነት ኋላቀር አስተሳሰብ ሊወገዝ እንደሚገባው ገልጾ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን #በይቅርታ ሕመማችንን በጋራ እንድናክም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

- የተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት እጅግ በጣም ውጤታማ ይሆን ዘንድ በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብሏል ፤ ለዚህም ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርቧል።

- በተደረገው የሰላም ስምምነት ስኬታማነት ላይ ስጋት ያላቸው ዜጎች ፣ ፖለቲከኞች ፣ አክቲቪስቶች ፣ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎችም ኢትዮጵያ ከሰላም ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በማወቅ ስለሰላም መልካሙን እንዲያስቡና እንዲያደርጉ አሳስቧል።

(ሙሉ የም/ቤቱ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ተስፋ

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከምንም በላይ ለበርካታ ወራት የእናት አባቶቻቸውን ፤ የእህት ወንድሞቻቸውን ፣ የወዳጆቻቸውን ድምፅ ያልሰሙ እጅግ በርካቶች ስምምነቱ በፍጥነት #ወደተግባር ገብቶ ያናፈቋቸውን ሁሉ ድምፃቸውን ሊሰሙ ጓግተዋል።

ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት በመኖሩ እያገዟቸው የነበሩ መላ ቤተሰቦቻቸውን ዳግም አግኝተዋቸው የየትኛውም የእርዳታ ድርጅት እና ተቋም /አካል ደጅ እንዳይጠኑ ለማድረግና ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ እየተጠባበቁ ነው።

ቤተሰቦቻቸው " በህይወት ይኑሩ አይኑሩ " እርግጠኛ ያልሆኑ ሚሊዮኖች የሰላም ስምምነቱ እጅግ በፍጥነት ተተግብሮ ፣ መሰረታዊ አገልግሎት ጀምሮ ለማየት ተስፋን ሰንቀዋል።

ከማንም ከምንም በላይ የጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂዎች ህመማቸው ፣ ናፍቆታቸው ፣ ሀዘናቸው የከፋ ነውና ይህ የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እና እፎይ እንዲሉ በተለይ #በማህበራዊ_ሚዲያ አፍራሽ ስራ የሚሰሩ ፣ የበለጠ ጥላቻን የሚዘሩ ፤ ሰላም በመሆኑ ጥቅማቸው የሚጎድልባቸው አካላት ከድርጊታቸው ቢታቀቡ መልካም ነው።

የሰላም ስምምነት መፈረሙ " የመጀመሪያው እርምጃ " እንጂ የመጨረሻ አይደለምና በተለይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ለስኬቱ የራሳቸውን በጎ ድርሻ መጫወት ይጠበቅባቸዋል። በሰላም ሁሉም አሸናፊ ነውና ከብሽሽቅ ፣ ከጥላቻ ከአጉል የአሸናፊነት ስሜት መራቅ ይገባል።

#ሰላም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
#Update

የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የወታደራዊ አመራሮች #ሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም በጎረቤት ሀገር ኬንያ ፤ ናይሮቢ ሊገናኙ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

በዚህ መድረክ ላይ የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ ተገናኝተዉ በትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት ላይ እንደሚወያዩ የተገለፀ ሲሆን በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ #ስራዎች_መጀመራቸው ተገልጿል።

በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

የፊታችን ሰኞ ደግሞ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው እንደሚወያዩ መገለፃቸውን የብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia