TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ዛሬ በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ፤ ሞቃዲሾ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገደሉ። በዞቤ መንገድ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተነጣጠረ ነበር ተብሏል። በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የፖሊስ አባል፣…
#Update

በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ትላንት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች ሲሞቱ 300 ሰዎች ተጎድተዋል።

በሁለት መኪና በተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገድለዋል።

የሶማሊያ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ፤ የትላንቱን የሽብር ጥቃት " ጭካኔ የተሞላበት እና የፈሪዎች ጥቃት " ሲሉ ገልፀው ድርጊቱን የፈፀመው ሽብርተኛው አልሸባብ መሆኑን አመልክተዋል።

በጥቃቱ ሲቪሎች መሞታቸውን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይችልም ፤ ይልቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ለማሸነፍ (አልሸባብን) ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲሉ ገልፀዋል።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ የሽብር ጥቃቱ የተፈፀመበትን ቦታ በአካል የተመለከቱ ሲሆን በጥቃቱ በትንሹ 100 ሰዎች መገደላቸውን እና 300 የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነዋል።

ህዝቡም ወደ ሆስፒታል እየሄደ ደም እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በትላንቱ እንዲሁም በሌሎች የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ህፃናት ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚመቻች ፕሬዜዳንቱ ቃል ገብተዋል።

የትላንቱ የመኪና የቦምብ ጥቃት በመዲናዋ ሰው ከሚበዛባቸው መገናኛዎች ውስጥ በሚገኘው #የትምህርት_ሚኒስቴር ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ፤ " የቢጫ ወባ ክትባት " መጀመሩን እና አገልግሎቱን የሚፈልጉ በአገልግሎቱ መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቆናል።

@tikvahethiopia
" ከ3 ሳምንት ያላነሰ ጊዜ የሚፈልገውን ሥራ  በአንድ ሳምንት ነው ያጠናቀቁት " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የወልዲያ አላማጣ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ያለዕረፍት በተሰራ ሥራ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና እና የተሰበሩ ኢንሱሌተሮች ቅየራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ መስመሩን መፈተሽ እንደተገጀመረ ነው የተገለፀው።

በአንድ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የደረሰ ጉዳት በቀጣይ የሚጠገን ሲሆን የምሰሶው ጉዳት ግን መስመሩን ኃይል ከመስጠት የሚያግደው አይደለም ተብሏል።

በጥገና ሥራው ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች ከሦስት ሳምንት ያላነሰ ጊዜ የሚፈልገውን ሥራ  በአንድ ሳምንት እንዳጠናቀቁት ነው የተነገረው።

ከወልዲያ እስከ አላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ ያለው መስመር ጥገና መጠናቀቅ ከአላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ በ66 ኪሎ ቮልት ኃይል ሲያገኙ የነበሩት ፦
- ላሊበላ፣
- ሰቆጣ
- ቆቦ እንዲሁም ማይጨው እና አካባቢያቸው ኃይል እንዲያገኙ ያስችላል።

መረጅው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PeaceTalks የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህበረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል። እስካሁን የንግግሮቹን ይዘት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ አልወጣም። በዛው ያሉ ሚዲያዎችም ስለ ሰላም ንግግሩ እና ስለሂደቱ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ እንዳይኖር ተደርጓል።…
#PeaceTalks

ትላንት እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ሰኞም እንደሚቀጥል ተሰምቷል።

ኤፒ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የሰላም ንግግሩ ዛሬም ይቀጥላል።

ከኤፒ በተጨማሪም " SA FM RADIO " የሰላም ንግግሩ ዛሬ እንደሚቀጥል ዘግቧል።

የሰላም ንግግሩን ይዘትና አጠቃላይ አሁን ላይ የደረሰበትን ሂደት በተመለከተ ምንም ይፋዊ መረጃ የለም። የሰላም ንግግሩ ሚዲያዎች መረጃ ሊያገኙበት በማይችል ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

ለሰላም ንግግሩ ቅርብ የሆኑ አንድ ባለስልጣን ንግግሩ ምን እድገት እንዳሳየ ሲጠየቁ፤ " እሱን ጊዜ ብቻ ነው የሚነግረን " ሲሉ መልሰዋል።

ሌሎች ምንጮች ደግሞ የሰላም ንግግሩ ዝግ እያለ እየሄደ ቢሆንም በአካል ተገናኝቶ ፊት ለፊት መነጋገሩ ተቀባይነትን እንዳገኘ አመላክተዋል።

በግጭት ማቆም፣ በሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት እና በወሳኝ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንደገና መጀመር ላይ በተደረገ ንግግር "ትልቅ እድገት" ታይቷል ሲሉ እነዚህ ምንጮች ገልፀዋል።

የሰላም ንግግሩ " ወደ ተኩስ አቁም ይመራል " የሚል ተስፋ እንዳላቸው ሙሳ ፋኪ መሀመት ከቀናት በፊት ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

እስካሁን ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች/ አዘጋጆች በኩል በቀጥታ የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም፤ የሰላም ንግግሩ አዘጋጆች የንግግሮችን ይዘትና ሂደት በተመለከተ ከሚዲያዎች ርቀው ዝግ በሆነ መንገድ ነው እያስኬዱ የሚገኙት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ከላይ ያነበባችሁት መረጃ የተሰባሰበው፦ ከ "The Star kenya" ጋዜጠኛው ኢሊዩድ ኪቢ፣ SA FM RADIO/SABC፣ ከDaily Maveric/South Africa/ እንዲሁም ከኤፒ ነው።

@tikvahethiopia
3 የአልሸባብ አባላት በሞት ተቀጡ።

የጎረቤታችን ሶማሊያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. በ2018-2020 መካከል ባለው ጊዜ የ15 ሰዎችን ህይወት በቀጠፉ ጥቃቶች ጥፋተኛ ናቸው የተባሉ 3 የአልሸባብ አባላትን በሞት ቀጣ።

ሰዎቹ የሞት ቅጣቱ የተፈፀመባቸው ሰኞ ማለዳ በሞቃዲሾ ውስጥ ነው ተብሏል።

ሶስቱ የአልሸባብ አባላት በ2019 የመንግስት ባለስልጣናት እና በርካታ ሲቪሎችን ህይወት የቀጠፉ የሽብር ጥቃቶችን መፈፀማቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ የሶማሊያ የሃይማኖት ሊቃውንት በይፋዊ መግለጫ ለ " አልሸባብ ገንዘብ መስጠት / መክፈል ሀራም ነው " ሲሉ አውጀዋል።

ቡድኑን ለመዋጋትም አንድነት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።

በሃይማኖት ሊቃውንቱ እና በፌዴራል እና በክልል የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስቴር መካከል በተካሄደ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ መግለጫው የወጣው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PeaceTalks ትላንት እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ሰኞም እንደሚቀጥል ተሰምቷል። ኤፒ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የሰላም ንግግሩ ዛሬም ይቀጥላል። ከኤፒ በተጨማሪም " SA FM RADIO " የሰላም ንግግሩ ዛሬ እንደሚቀጥል ዘግቧል። የሰላም ንግግሩን…
#PeaceTalks

2 ዓመት ሊደፍን የተቃረበውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው የሰላም ንግግር ነገ ማክሰኞም ይቀጥላል ተብሏል።

ትላንት ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ይኸው የሰላም ንግግር ተራዝሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉና ነገም እንደሚካሄድ ተሰምቷል።

ከዚሁ የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ ፤ የአፍሪካ ህብረት ንግግሩ የሚጠናቀቅበት ቀነ ገደብ እንዳልተቀመጠ ለኤኤፍፒ በሰጠው ቃል ገልጿል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ቃል አቀባይ ኤባ ካሎንዶ ፤ " በንግግሩ (በሰላም ንግግሩ) ላይ ቀነ ገደብ አልተቀመጠም " ብለዋል።

አሁን ድረስ የንግግሩን ይዘት ፣ ስላለበት ደረጃ እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከተ ምንም አይነት ይፋዊ መረጃ ያልወጣና ሚዲያዎችንም የሰላም ንግግሩን በተመለከተ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ ዝግ የተደረገ ሲሆን አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማት የሰላም ንግግሩ አስተባባሪዎች ንግግሩን በጥብቅ ሚስጥር እንደያዙት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚሊዮን ዶላር ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ የጭነት አገልግሎት ማዕከል እያስገነባ ሲሆን ይኸው ማዕከል በቅርቡ ስራ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ ፤ አየር መንገዱ በካርጎ አገልግሎት ከአፍሪካ ትልቁና በዓለም ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ ዘመናዊ አሰራርን ይከተላል ብለዋል።

በዓለም ላይ የዲጂታል ግብይት እያደገ በመምጣቱ የመደበኛው ካርጎ አገልግሎት እየቀነሰ በአንጻሩ የኢ-ኮሜርስ የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣቱን አንስተዋል።

አዲሱን የካርጎ አገልግሎት ማዕከል እውን ለማድረግ እውቀትና የአሰራር ስርዓት በአግባቡ ተዘርግቶለት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

አሰራሩ ከዚህ ቀደም ከነበረው የካርጎ አገልግሎት በእጅጉ የሚለይ ነው ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ዕቃ ከውጭ ተጭኖ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ይወስድ የነበረውን እስከ 7 ቀን በአዲሱ አሰራር እንደሚቀረፍ ተናግረዌ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስገነባ ያለው የኢ-ኮሜርስ ማዕከል በ15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይሆንበታል።

ማዕከሉ በመጪው የፈረንጆቹ 2023 አጋማሽ ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኢዜአ አየር መንገዱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከ3 ሳምንት ያላነሰ ጊዜ የሚፈልገውን ሥራ  በአንድ ሳምንት ነው ያጠናቀቁት " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የወልዲያ አላማጣ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል። ያለዕረፍት በተሰራ ሥራ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና እና የተሰበሩ ኢንሱሌተሮች…
#Update

ከአላማጣ እስከ ቆቦ የሚገኙ አካባቢዎች ዳግም #የኤሌክትሪክ_ኃይል ማግኘታቸው ተገልጿል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኙት ፦

- አላማጣ፣
- ኮረም፣
- ዋጃ፣
- ጥሙጋ እና ቆቦ ከተሞች ናቸው።

ከአላማጣ እስከ ላሊበላ የተዘረጋውን የ66 ኬ.ቪ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ በአካባቢው ያሉ ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በዝርፊያ ምክንያት ኃይል ተቋርጧል።

ከጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ወደ ጃዊ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች #በሌቦች በመፈታታቸው ኃይል መቋረጡ ተገልጿል።

ይህንን ያሳወቀው የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ነው።

ዝርፊያው የተፈፀመው አይማ ገብርኤል ቀበሌ ጌሾ ወንዝ አካባቢ ነው።

ሦስት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች በሌባ በመፈታታታቸው የወደቁ ሲሆን አንድ ተጨማሪ ምሰሶ በመሳሳብ ጉዳት ደርሶበት ወድቋል።

በዚህ የተነሳ ፦ ለበለስ ስኳር ፕሮጅክት፤ ለጃዊና አካባቢው የሚሰጠው የጃዊ ኤሌትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ ከጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጧል።

የወደቁትን ምሰሶዎች ለመጠገን የቴክኒክ ቡድን በሥፍራው ደርሶ ጥገና የጀመረ ሲሆን ጥገናውን ለማጠናቀቅ እስከ #አንድ_ሳምንት ሊፈጅ ይችላል ተብሏል።

ህብረተሰቡ የደረሰ ጉዳት እስኪጠገን በትዕግስት እንዲጠብቅ ዘራፊዎችን ለፀጥታ አካላት እንዲጠቁም ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethiopia
" ህብረተሰቡ የቤት ሠራተኞች ሲቀጥር በቂ ዋስትናም ማቅረብ እንዳለባቸው ጭምር #ሊያስገድድ ይገባል " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የገዛ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

ወንጀሉ የተፈጸመው ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 10:45 ሰዓት ሲሆን ቦታው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው " አስኮ ሊዝ ሰፈር " ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ መሆኑን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።

ተከሳሽ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሠራበት ከወ/ሮ ፋሲካ ተሾመ ቤት ሲሆን በመሃላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ሟችን በቡና ዘነዘና እና በስለት የተለያዩ የሰውነት አካላቸው ላይ ጉዳት በማድረስ የመግደል ወንጀል ፈጽማለች።

ፖሊስ መረጃው ከህብረተሰቡ ከደረሰው በኋላ ባደረገው ክትትልና ምርመራ ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ከፈጸመች ከ3 ቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር አውሏታል።

ህብረተሰቡ የቤት ሠራተኞችን ሲቀጥር በቂ ዋስትናም ማቅረብ እንዳለባቸው ጭምር ሊያስገድድ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#GebreGuracha

በ " ገብረ ጉራቻ " ከተማ በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን በታጣቂዎች ሲገደል ፤ 11 አገልጋዮች ደግሞ በታጣቂዎች መታገታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ አሳወቀ።

የቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን ፤ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ገርበ ጉራቻ ከተማ በምትገኘው በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም ሌሊት የማኅሌተ ጽጌ አገልግሎት ላይ በነበሩበት ወቅት #ታጣቂዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባት አንድ ዲያቆን በመግደል ሌሎች 11 አገልጋዮችን ማገታቸውን ገልጿል።

በአካባቢው ላይ ተደጋጋሚ ችግሮች በመከሰቱ ምእመናን ስጋት ላይ በመሆናቸው ለመንግስት አካላት የማሳወቅ ሥራ ቢሠራም መፍትሔ ማግኘት አልተቻለም ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በይፋዊ #የተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሽፈራው ለተ.ሚ.ማ. በሰጡት ቃል የተፈጠረውን ጉዳይ እንደሰሙና ለዞኑ አስተዳደርና ለጸጥታ ዘርፉ ማሳወቃቸውን አስረድተዋል። በተለይ በቦታው ቅርብ ርቀት ላይ የመከላከያ ካምፕ መኖሩን ገልፀው ጉዳዩ ሲፈጠር የወሰዱት እርምጃ እንደሌለና ጉዳዩም አዲስ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ይህ ጉዳይ ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ ስለሆነ ጉዳዩን ለቤተ ክህነት ማቅረባቸውን በአካባቢያው ለሚገኙ ቀሪ ምእመናን መፍትሔ እንዲሰጥ እንደጠየቁ እና ምላሽም እየተጠባበቁ ስለመሆኑ ለሚዲያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia