TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ፦ - ኢትዮጵያዊያን በግለሰብ ደረጃ ከ100 ሺህ ብር በላይ ለድርጅቶች ደግሞ ከ200 ሺህ ብር በላይ ቤት ውስጥ ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸወል። - ገንዘብ በባንክ መቀመጥ አለበት ፤ የግብይት ስርዓትም በባንክ ማካሄድ ይቻላል። - መመሪያው ከሚፈቅደው የገንዘብ መጠን በላይ አስቀምጦ የተገኘን አካል #የጠቆመ ግለሰብ 15 በመቶ የወረታ ክፍያ…
በምን ልጠቁም ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕገ ወጥ የሆነ የገንዘብ ዝውውርን ለሚጠቁሙ ወሮታ የሚከፈልበትን መመሪያ በተመለከተ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በቅርቡ ብሄራዊ ባንክ 4 ህገወጥ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲያደርግ እና ጥቆማውን ለሚያደርጉ ዜጎች #ወሮታ እንደሚከፍል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. ከተፈቀደ በላይ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ገንዘብ ማከማቸት፤

2. ሀሰተኛ የገንዘብ ህትመት መፈፀም፤

3. የወርቅ ክምችት፤

4. ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መንገድ ያለፈቃድ ማስተላለፍ በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ ዜጎች ጥቆማ እንዲሰጡ እና ዜጎች ለሚሰጡት ጥቆማ ወሮታ እንደሚከፈላቸው ገልጾ ነበር።

- በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን ለጠቆሙ ከተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣
- የውጭ ሀገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣
- ሕገወጥ ሐዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ወሮታ ይከፈላቸዋል።

ለግለሰቦች በቀን ከ100 ሺህ ብር በላይ መያዝ፣ ለተቋማትም በቀን ከ200 ሺህ ብር በላይ መያዝ የተከለከለ ነው።

ይህን መመሪያ የተላለፈን ግለሰብ ወይም ተቋም ለጠቆመ #ምስጢራዊነቱን በተጠበቀ መልኩ ወሮታው ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገልጿል።

ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ በከባድ የኢኮኖሚ ወንጀል እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ነው የተመላከተው።

ጠቋሚዎች በስልክ ቁጥር 0118133960፣ በኢ.ሜል አድራሻ tikoma@nbe.et፣ በፋክስ ቁጥር 0115514366 እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፖ.ሣ.ቁጥር 5550 ላይ ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የሰላም ንግግር በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙን ሮይተርስ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ቀጠሮ የተያዘለት የሰላም ንግግር መራዘሙ ከሎጂስቲክስ ዝግጅት ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸው እስካሁን አዲስ ቀን እንዳልተቆረጠ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በአፍሪካ…
#PeaceTalks

ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከ4 ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ቀን እንደተቆረጠለት ተሰምቷል።

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የነበረውና በሎጅስቲክስ ዝግጅት ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከዛሬ 4 ቀናት በኃላ (ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ/ም) በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ መሆኑ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን  ለማድረግ ለጥቅምት 14/2015 ዓ/ም ቀን መቁረጡን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ፤ " በዚሁ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናችንን በድጋሚ አረጋግጠናል " ብለዋል። " ነገር ግን መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን የመከላከል ርምጃ ለማጠልሸት የሃሰት ከስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አካካት ላይ ያለውን ቅሬታ ይገልፃል።" ሲሉ አክለዋል።

አፍሪካ ህብረት በህብረቱ የሚመራና በደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ የሰላም ንግግር ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለህወሓት ግብዣ አቅርቦ እንደነበርና በሁለቱም በኩል ግብዣው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።

የሰላም ንግግሩ ፤ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ እንደሚመራም መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Peace

የኢፌዴሪ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንደሚቋጭ እና ሰላምም እንደሚሰፍን ተናገሩ።

ይህንን የተናገሩት በቡራዩ ከተማ የተገነባ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፅጊያ ኢንስቲትዩት በመረቁበት ወቅት ባሰሙት ንግግር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው " በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ነገር ይቋጫል፤ ኢትዮጵያም ሰላም ትሆናለች " ብለዋል።

" እንዲሁ እንደተዋጋን አንቀጥልም ያሉት " ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በሰላም፣ በልማት የትግራይ ወንድሞቻችንን ለማልማት በጋራ የምንቆምበት ጊዜ ቅርብ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ በንግግራቸው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቋጫ ስለሚያገኝበት እና ሰላም ስለሚሰፍንበት መንገድ በዝርዝር አልተናገሩም።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተጀመረ የፊታችን ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ/ም ሁለት ዓመት የሚደፍን ሲሆን ጦርነቱ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ክስተት እያስተናገደ ዛሬ ላይ ደርሷል።

ይኸው ጦርነት የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ሚሊዮኖችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፣ ለችግርም ጥሏል።

ጦርነቱ ባመጣው መዘዝ ባለፉት በርካታ ወራት የትግራይ ክልል ነዋሪዎች እና ከትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆኑ የአማራ እና አፋር ክልል አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎት ለማግኘት አዳጋች ሆኖባቸዋል።

ጦርነቱ እንዲቋጭ የተለያዩ የሰላም ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን የፊታችን ሰኞም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግር ይጀመራል ተብሎ ቀን ተቆርጧል። በዚሁ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ መንግስት ቁርጠኛ ነኝ ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ እንደሚገኝ አሳውቋል። ፈተናው እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ መሰጠት ይቀጥላል። በሌላ በኩል ከትላንት ሰኞ ከእኩለ ቀን አንስቶ የተገደበው የቴሌግራም አገልግሎት ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ ነው። ቴሌግራም ኢትዮጵያ ባሉት በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች…
#Update

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም በሚሰጠው የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ፈተና ይጠናቀቃል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች / የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ከመስጠትም ባሻገር የተለያዩ ተቋማት ፈተናውን #በደህንነት_ካሜራ ጭምር ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ ለመመለከት ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ላለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ስርዓትን እንደመከታተሉ ይሄ ፈተና ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በተለይም በፈተና ስርቆት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ #ቀድሞ ማሰራጨትን #በመከላከል በኩል እጅግ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ሆኖ አግኝቶታል።

ነገር ግን በዚህኛውም " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅትም ሆነ በባለፈው " የማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት በጥብቅ የተከለከለውን ስልክ / ሌላ የመገናኛ ዘዴ / ይዘው ወደ ክፍል በመግባት ፈተና በሚሰጥበት ሰዓት የፈተናውን ወረቀት ፎቶ በማንሳት በ " ቴሌግራም " ሲያሰራጩ የነበሩ ተፈታኞችን ተመልከተናል።

ይህንን ድርጊት ለመቆጣጠር ይመስላል ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት " ቴሌግራም " እንዲገደብ እየተደረገ የሚገኘው። አብዛኛው ተማሪም ወደ ፈተና ማዕከል ስልክ ይዞ እንዳይገባ በመደረጉ ተደራሽነቱ አነስተኛ ነው።

በፈተና ተቋማት ውስጥ ስለነበረው ጠንካራ ጎን፣ ክፍተት / ችግር ደግሞ የፈተናውን መጠናቀቅ ተከትሎ ከተፈታኞች ፣ ወላጆች ፣ ፈታኝ መምህራን አስተያየቶችን አሰባስበን እንክላችኃለን።

NB. ከብሔራዊ ፈተናው ጋር በተያያዘ እየተገደበ ያለው " ቴሌግራም " ከዛሬ ፈተና መጠናቀቅ በኃላ ሙሉ አገልግሎቱ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

* የቅጣት ውሳኔ ማሻሻያ !

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ተማሪ ፅጌረዳ ግርማይን በስለት ወግቶ የገደለው ተማሪ በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውሳኔ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ፤ " ያቀረብኩትን የፍቅር ጥያቄ አልተቀበለችም ፣ ሌላ ፍቅረኛ ይዛ ውጪ ልትወጣ ነው። " በሚል ስሜት ተነሳስቶ ተማሪ ጽጌረዳ ግርማይን አካል 9 ጊዜ በስለት ወጋግቶ የመግደል ወንጀል ፈፅሟል።

በቀድሞው አጠራር የጋሞ ዞን ዐቃቤ ህግ የመሠረተውን የወንጀል ክስ ተመልክቶ ግራና ቀኙን ሲያከራክር የቆየው የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በቀን 19/10/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የ17 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ውስኖ እንደነበር ይታወሳል።

የዞኑ ዐቃቤ ህግ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘቱ ይግባኙን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ሲከታተል ቆይቷል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የበየነው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል አኳያ ተገቢነት ያለው ሆኖ ባለመገኘቱ የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አሻሽሎ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የ22 ዓመት ፅኑ እሥራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

ምንጭ ፦ የጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update * የቅጣት ውሳኔ ማሻሻያ ! የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ተማሪ ፅጌረዳ ግርማይን በስለት ወግቶ የገደለው ተማሪ በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውሳኔ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ። የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ፤ " ያቀረብኩትን የፍቅር ጥያቄ አልተቀበለችም ፣ ሌላ ፍቅረኛ ይዛ ውጪ ልትወጣ ነው። " በሚል ስሜት ተነሳስቶ…
#Update

ላለፉት አራት ቀናት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተጠናቋል።

ዛሬ ጠዋት የተሰጠውን የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው መመለስ ጀምረዋል (በተለይ በቅርብ ርቀት የሚገኙ።)

ተማሪዎቹ በተዘጋጀላቸው ትራንስፖርት ወደየመጡበት እየተሸኙ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ነው።

ምስል፦ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የፊታችን ሰኞ በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግር ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ዛሬ የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ ሚ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ  ላደረጉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በዚሁ ማብራሪያ የኢትዮጵያ መንግስት የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

የመንግስት ልዑክ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ በታሰበው የሰላም ውይይት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠውላቸዋል።

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅና የግዛት አንድነቷን ለማረጋገጥ በምትወስደው እርምጃ ላይ ግን የሚደረግን ማንኛውንም አይነት ጫና እንደማትቀበል አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ፤ ህወሓት ሰኞ ጥምቅት 14 በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር ላይ እንደሚሳተፍ አሳውቋል።

ህወሓት በደቡብ አፍሪካው የሰላም ንግግር ላይ " የኛም ልዑካን ይሳተፋሉ " ሲል ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ም/ቤት የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት በሰላም ለመፍታት አፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ንግግር ዙሪያ ዛሬ ውይይት አድርጎ ነበር።

በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴዬ፣ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ፣ የኢጋድ እና የኢትዮጵያ ተወካዮች ገለጻ አድርገዋል።

ሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የሰላም ንግግር ከዚህ ቀደም በሎጅስቲክስ ዝግጅት ክፍተት ምክንያት የተራዘመው የሰላም ንግግር ሲሆን የሚመራው ደግሞ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በመስቀል አደባባይ፤ " ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምፄን አሰማለሁ " በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ ይካሄዳል።

የድጋፍ ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ  ኡራኤል አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 4ኛ ክፍለጦር

- ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር  ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ

- ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደለገሃር የሚሄዱ ለገሀር

- ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር  የሚወስደው ሜክሲኮ አደባባይ

- ከተክለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ  ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚንየም አካባቢ

- ከጌጃ ሰፈር፣ በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ አካባቢ

- ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ

- ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ መንገድ ላይ

- ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ

- በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት አካባቢ

- ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ

- ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ ፍል ውሃ አካባቢ #ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁመው መሄድ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia