TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* Update

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።

ሐመር በዚሁ ወቅት ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ፤ በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ መወያየታቸውን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

ሐመር ከህወሓት ሊቀመምበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር እንዴት/በምን ተገናኝተው እንደተነጋገሩ ባይገለፅም ለእሳቸውም ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ እንዳስገነዘቧቸው ተገልጿል።

እንደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም እና ወደ ድርድር ለመግባት በመጪዎቹ ቀናት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ ሞሊ ፊ ፣ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና ሌሎችም የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከአፍሪካ ህብረት እንዲሁም ከቀጠናው ቀልፍ ናቸው ከሚባሉት ተዋናዮች ተመድ ፣ አውሮፓ ህብረት ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም ልዑካን ጋር ይመክራሉ።

መስሪያ ቤቱ ፤ የአሜሪካ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ፤ ኤርትራም ወደ ድንበሯ እንድትመለስ ዴፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ ነው ብሏል።

ለግጭቱ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም ያለው የአሜሪካ መንግስት መፍትሄድ በሁሉም ወገን ዘንድ የሰላም ድርድር ማድረግ ብቻ ነው ብሏል።

አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት#የግዛት_አንድነት ቁርጠኛ አቋም አለኝ ስትልም በድጋሚ ማረጋገጧን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* Update

" መግለጫው ኃላፊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው ነው " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተመድ የተቋቋመው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡትን መግለጫ እንደማይቀበለው ገልጿል።

የኮሚሽኑ ባለሙያዎች መግለጫ " ሃላፊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው " ነው ሲል አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ህወሓት የሰብአዊ ተኩስ አቁሙን በመጣስ ስለፈጸመው ጠብ አጫሪነት ምንም አለማለቱን የገለፀው ሚኒስቴሩ ፤ ኮሚሽኑ ለሰላምና ለደህንነት ስጋት በሆኑ ጉዳዮች ላይ የመናገርም ሆነ የመወሰን ስልጣን እንደሌለው ገልጿል።

ነገር ግን ኮሚሽኑ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ማቅረቡ የኮሚሽኑን ሃላፊነት የጎደለው ባህሪ እንደሚያሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገንዝቧል።

ይህ ድርጊትም መንግስት የኮሚሽኑ እንቅስቃሴና ስራ ፖለቲካዊ ይዘት አለው በሚል የሚያነሳውን ሃሳብ ያረጋገጠ ሆኗል ብሏል።

ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን የፖለቲካ ጫና ለማሳረፍ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ የገለፀው ሚኒስቴሩ ይህ አካሄዱ የኮሚሽኑን እውነተኛ ማንነት ያጋለጠ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

የኮሚሽኑን መግለጫ ውድቅ ያደረገው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መንግስት የሰብአዊ መብቶችን በማክበር እና በማስከበር አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።

(የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia
* መልዕክት

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ2015 ዓ/ም የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፋለች።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ካስተላለፉት መልዕክት ፦

" በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን ሁሉ በአጽንዖት የምንመክረው ዓቢይ ምክር በግጭት ችግሮቻችንን መፍታት በፍጹም አንችልም፤ በመራራቅም ማደግ አንችልም ፤ በተለያየን ቊጥር ድህነታችንን ከማስቀጠልና ደካሞች ከመሆን በቀር የምናገኘው አንዳች ፋይዳ የለም፤ እውነቱ ይህ ከሆነ ከገባንበት ያላስፈላጊ ግጭት በፍጥነት ወጥተን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ወደሚያስችል ወደ ምክክርና ውይይት እንግባ፤ አዲሱ ዓመት እውነተኛ አዲስ ዓመት ሊሆን የሚችለው ይህንን ያደረግን እንደሆነ ነው፡፡

አሮጌውን አስተሳሰብ እንዳለ ተሸክመን ለመቀጠል እየዳዳን ከሆነ አዲስ ዓመት ማለቱ የአፍና የጆሮ ቀለብ ከመሆን በቀር የሚሰጠን አንዳች ትርጉም የለም፡፡

ስለሆነም አዲሱን ዓመት አዲስ የሆነ የሰላምና የዕርቅ የስምምነትና የአንድነት የይቅርታና የምሕረት የፍትሕና የእኩልነት መርሕ አንግበን ፍጹም ሰላምን ለማንገሥ በቊርጥ ማሰብና መነሣሣት አለብን፣ ይህንንም ለማሳካት በአንድ አዳራሽ፣ በአንድ ጠረጴዛ ተገናኝተን ችግሮቻችንን በውይይትና በምክክር እንድንፈታ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የበረከት የዕድገት የሃይማኖትና የልማት ዓመት እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር በመጸለይና በብሩህ ተስፋ እንድንቀበለው መልእክታችንን በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል - ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* መልዕክት

የኢትየጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የ2015 ዓ/ም የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፋለች።

ብፅዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የኢትየጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳት ለመላው ምዕመናን ካስተላለፉት መልዕክት ፦

" የተወደዳችሁ የአገራችን ህዝቦች አገራችን በውስጣዊ ጦርነት ላይ የምትገኝ ቢሆንም ጦርነት ለማንም የማይበጅ አጥፊ ስለሆነ በአዲሱ ዓመት ሁሉም ወገኖች ለሰላምና ለእርቅ ቦታ ሰጥተው ወደ ውይይት እንዲቀርቡና እንዲነጋገሩ አገራቸውንና ሕዝባቸውን ከጥፋት እንዲያድኑ ቤተክርስቲያናችን ትማፀናቸዋለች፡፡ምዕመናንም እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲሰጠን በጸሎት እንዲተጉ አደራ እንላለን፡፡

በዘመን መለወጫ በዓላችን ሁላችንም በምንችለውን ዓይነት በችግርና በመከራ በጭንቀት ላይ የሚገኙትን ወገኖች በማሰብ አቅማችን በሚፈቅደዉ መጠን በመተጋገዝና በመረዳዳት በዓሉን እንድናሳልፍ አደራ ማለት እወዳለሁ።

በመጨረሻም ለመላዉ የአገራችን ሕዝቦች በሙሉ በየሆስፒታሉና በቤታችሁ በህመም ላይ ያላችሁ የእርሱን ምህረትን፣ በየማረሚያ ቤቶች ለምትገኙ የሕግ ታራሚዎች መፈታትን፣ በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ ያላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም የመንፈስ ልጆቻችን እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲያወርድላችሁ፣ በተለያየ ምክንያት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በስደት ላይ የምትገኙ ወገኖቻችን ለአገራችሁና ለአካባቢያችሁ  እንዲያበቃችሁ እየተመኘሁ ለሁላችንም አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የበረከት፣ የመደማመጥ፣ የመወያየት፣ የመተዛዘንና የመተሳሰብ፣ የማስተዋልና የጥበብ ዘመን ይሁንልን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል - ያንብቡ )

@tikvahethiopia
#WorldBank #Ethiopia

የዓለም ባንክ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በእጅጉ እንደሚያስበው አመልክቷል።

በርካታ ግጭቶች እንዲሁም በታሪክ የታየው አስከፊ ድርቅና ሌሎች ሁኔታዎች ጋር ተዳምረው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ በመጎዳታቸው ሀገሪቱ ባለፉት አመታት ያስመዘገበችውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አደጋ ላይ ጥሏል ሲል ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ የኢትዮጵያ ህዝብ የበለጠ የመቋቋም አቅምን ለመደገፍ እና በግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ድጋፉን ለመቀጠል ካለው ስትራቴጂ ጋር በሚስማማ መልኩ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ሲል ከኢትዮጵያ ጋር ያለው አጋርነት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት የዓለም ባንክ ቡድን ኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ የዜጎቿን መሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም የትምህርት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የሴቶች አቅም በማጎልበት፣  የማህበራዊ እና የአካባቢ ጥበቃን ለማሟላት በምታደርገው ጥረት ድጋፉን እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ልማት ላይ ያተኮረ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በአባል ሀገራቱ የውስጥ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ ሥልጣን ባይኖረውም የልማት ተራድኦ ቡድን አባል እንደመሆኑ መጠን ደግሞ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየቱን እንደሚቀጥል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ነፍጥ ያነገቡ ሁሉ #ነፍጣቸውን_አስቀምጠው ወደ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጥሪ አቀረቡ።

ፕሮፌሰር መስፍን ፤ ጠብመንጃ ጥቅም እንደሌለው ቢያንስ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት አይተናል ያሉ ሲሆን ለሰላም የትኛውንም ዋጋ መክፈል እንደሚገባ ገልፀዋል።

ለሰላም ከሚከፈለው ዋጋ ደግሞ ፤ " መጀመሪያ ላይ ሰላምን መንከባከብ ቢሆን ውጤታማ ነው ፤ ሰላም ከደፈረሰ በኃላ ግን ሰላምን ለማስከበር የሚነሳው ነፍጥ የበለጠ ሰላምን እያደፈረሰው ነው የሚሄደው "  ሲሉ አስረድተዋል።

" የነፍጥን የሰላም ማስከበር ሂደት አይተነዋል ፤ አይጠቅምም ስለዚህም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያለ ያለው ነፍጥ / ጠብመንጃ ይቀመጥ ! እስኪ ለጊዜው ጠብመንጃውን እናስቀምጠውና ወደ ምክክር ጠረጴዛው ተገናኝተን እንወያይ ከተወያየን የማይፈታ ነገር የለም ነው " ሲሉ አክለዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ፤ ነፍጥ ባነገቡ አካላት የህዝቡ ስቃይ እየተባባሰ መሆኑን ገልፀው በሁሉም አቅጣጫ ነፍጥ ያነገቡ ነፍጣቸውን አስቀምጠው ወደ ውይይት እና ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

" የትኛውም የሀገራችን ክፍል ያለው ህዝብ በቅቶታል፣ ተሰላችቷል ብዬ ነው የማስበው " ያሉት የኮሚሽኑ ሰብሳቢ በ2015 ዓ/ም ሁሉም በሰላም ዙሪያ የሚሰባሰብበት ጊዜ እና ኢትዮጵያውያን የእራሳችንን አጀንዳ እራሳችን በመቅረፅ ተወያይተን ምንግባባበት እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ፥ " በምዕራብ ይሁን ሰሜን ይሁን ያሉ ወገኖች በአስቸኳይ ነፍጥ ያስቀምጡና ወደ ውይይቱ መድረክ ይምጡ ፣ በየቦታው ያሉ ፣ ግጭት ውስጥ ያሉ ፣ ጦርነት ውስጥ ያሉ መሪዎች ልቦና ሰጥቷቸው ፤ ለህዝባቸው ተቆርቁረው ህዝባችን ይብቃው ሰቆቃ በዝቶበታል ስለዚህ ያለን አማራጭ በዚህ ባቋቋምነው ኮሚሽን በተቻለ መጠን ወደ ቀላሉና ውዱ ነገር የሰላም ፍለጋ መድረክ እንድንገናኝ ነው ጥሪ የማቀርበው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የ96 ዓመቷ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት  በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የንግስቷን ህልፈት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Kenya

ኬንያ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች !

ኬንያ በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች።

ተሰናባቹ የጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ዕልፈት ለ3 ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን ማወጃቸውን ሲትዝን ቴሌቪዥን (Citizen TV Kenya) ዘግቧል።

ፕሬዜዳንቱ በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈት ለ3 ቀናት ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አዘዋል።

በኬንያ በቅኝ ግዛት አገዛዝ ወቅት ከተፈፀመ አሰቃቂ ታሪኮች ጋር በተያያዘ አብዛኛው ኬንያውያን ሀዘናቸውን ለመግለፅ ባይፈልጉም ኬንያታ የሶስት ቀን ሀዘን አውጀዋል ሲል የኔሽን ሚዲያው ጋዜጠኛ ኦዴኪ ጎፌሪ ፅፏል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኬንያውያን (በንግስት ኤንዛቤት ዳግማዊት ንግስና) በቅኝ ግዛት ወቅት ከፈተፀሙ በደሎች ጋር በተያያዘ የሀዘን ቀን መታወጁን እንደማይደግፉት ፅፈው ተመልክተናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#በወንጀል_ይፈለጋሉ #Wanted የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በፎቶ የሚታዩትን ተጠርጣሪዎች በወንጀል እየፈለጋቸው ይገኛል። የተጠርጣሪዎቹን አድራሻቸውን የሚያውቅ አልያም በአጋጣሚ የተመለከተ ማንኛውም ገለሰብ በስልክ ቁጥር ፦ 👉 0115309139 ዘውትር (በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30) 👉 በ0111119475 / 0111711012 በማንኛውም ሰዓት ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል። ነፃ የስልክ…
#ምስጋና🙏

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለህብረተሰቡ ምስጋና አቅርቧል !

ተደራጅተው ከወርቅ መሸጫ ጌጣጌጦች የዘረፉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም በማህበራዊ ሚዲያዎች በተሰራጨ ቪድዮን ተከትሎ ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

እንደ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ በቡድን ተደራጅተው ዝርፊያውን የፈፀሙት ግለሰቦች በሞጆ ከተማ ሲሆን በቲክቶክ ላይ የአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ የተባለው ስህተት እንደነበር ገልጿል።

ግለሰቦቹ ከወርቅ መሸጫው ሱቅ 49 ግራም የሚመዝኑ የወርቅ ጌጣጌጦችን ዘርፈው ከአካባቢው ተሰውረው የነበር ቢሆንም በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደቻሉ ተገልጿል።

የዘረፋ በድኑ አባላት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ህብረተሰቡ ላሳየው ትብብር እና ፈጣን ምላሽ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ  ፥ " በቡድን ተደራጅተው በተለያየ ጊዜ የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ዘረፋ የሚያካሄዱ ግለሰቦች እየተበራከቱ መጥተዋል " ያሉ " ይህ ተግባር የፀጥታ ኃይሉን ስም ለማጠልሸትና የጠላትን ዓላማ ለማሳካት ሆን ተብሎ የተፈፀመ ነው " ብለዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ ፤ ፖሊስ ከህዝብ አብራክ የወጣና የህዝብ አገልጋይ በመሆኑ ለደንብ ልብሱና ለዓላማው ልዩ ክብርና ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው የማዕረግ የደንብ ልብሱን ለብሶ ማንም ሰው ስሙን ማጠልሸትና ማጉደፍ እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ነገ የሚከበረውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Update የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል። ሐመር በዚሁ ወቅት ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ፤ በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት…
#AU #ETHIOPIA

የኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ኃላፊነት ተራዝሟል።

ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያፈላልጉ እና ችግሩ በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ስልጣን / ኃላፊነት መራዘሙን ለመስማት ተችሏል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ ኦባሳንጆ የተሰጣቸው ኃላፊነት መራዘሙንም አመልክተዋል። በእሳቸው (በኦባሳንጆ) ላይ ያላቸው እምነት ሙሉ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪ ፤ በኢትዮጵያ እና በቀጠናው ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ ከሁለቱም ወገኖች እና ከዓለም አቀፍ ተዋናዮች ጋር የቀጠሉትን ግንኙነት አበረታታለሁ ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ትላንት እዚሁ አዲስ አበባ ላይ መመካከራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ትኩረቱን ያደረገው በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር በተመለከተ ሲሆን ይህንን ንግግር አሜሪካ እንዴት በተሻለ ሁኔታ መደገፍ እንደምትችል ምክክር መደረጉን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia