TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሳዑዲ_አረቢያ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሪያድ የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን እቃዎች ከሱቆች እና ከመደብሮች እየሰብሰበ ይገኛል። የሳዑዲ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃል በሚል የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን አሸንጉሊቶች፣ ቲሸርቶች፣ የጸጉር ማስያዣዎች፣ ኮፊያ፣ እና የእርሳስ መያዣወችን ከየመደብሩ እንዲሰበሰቡ እያደረገ ነው። የሀገሪቱ መንግስት ህፃናትን ለመጠበቅ ሲል " መርዛማ መልዕክት…
" እኛ የሙስሊም ሀገር ነን። ባህሎች እና ወጎች አሉን እናም እስልምና እነዚህን ድርጊቶች (የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን) ይከለክላል " - አል ሃማሚ

ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል እንዲሆንና ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንዲጣል እየሰራች መሆኗን አሳውቃለች።

የኢራቅ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚከለክል ህግ ለማፅደቅ ማቀዱን አስታውቋል።

ኢራቅ በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሶስት ብዙ አረቦች ከሚኖሩበት ሀገር መካከል አንዷና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #በግልፅ ወንጀል እንደሆነ ካላወጁ ሀገራት የምትጠቀስ ናት፤ ሌሎቹ ጆርዳን እና ባህሬን ናቸው።

ምንም እንኳን በግልፅ ወንጀል ነው ተብሎ ባይገለፅም ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ በጣም የተወገዘ ነው።

አሁን ያለው ሁኔታ ያላማራት ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል እንደሆነ በህግ ለመደንገግ እየሰራች ሲሆን ህጉ ከወጣ ኢራቅ ሌሎች ድርጊቱን በህግ ወንጀል እንደሆነ ካፀደቁ ሀገራት ተርታ ትሆናለች።

አብዛኛዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በቀጥታ በግልፅ የሚከለክሉ እና ወንጀል ነው ያሉ ሲሆን ከገንዘብ ቅጣት እስከ እስራት ፤ ሳውዲ አረቢያ ደግሞ #የሞት_ቅጣት ትቀጣለች።

በኢራቅ ፓርላማ የህግ ኮሚቴ ውስጥ ያሉት የፓርላማ አባል አሬፍ አል ሃማሚ ለDW በሰጡት ቃላቸው ፥ " አዲሱ ህግ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያላቸውን በወንጀል ተጠያቂ ያደርጋል ፤ በእነሱ ላይም ከባድ ቅጣት ይጥላል " ብለዋል።

ህጉ እስካሁን ድምጽ ያልተሰጠበት ሲሆን ድምፅ እንዲሰጥበት እየተሰራ ነው።

አል ሃማሚ ፤ ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ #የሰብአዊ_መብት_ተሟጋች_ድርጅቶች ትችት ቢሰነዘርም ህጉ ይፀድቃል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ያንብቡ telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-19

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ህግ ይከበር ፤ ፍትህ ይሰጠን " ለማስፋፊያ ስራ ተብሎ #ህግን_ባልተከተለ መልኩ ቤታችን ፈረሰብን ያሉ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል። ያሉበት ቦታ ለማስፋፊያ ስራ ይፈለጋል የተባሉ ዜጎች ለማስፋፊያ አንደሚፈለግ ያወቁት ሰኔ 29/2013 ዓ/ም አንደሆነ ከዛ በፊት ስለጉዳዩ ምንም እንደማያቁ / እንዳልተነገራቸው ፤ ጉዳዩን የሚያውቁት ከወረዳው…
" ፍትህ ሳናገኝ አንድ ወር ሞላን " - ነዋሪዎች

ከዛሬ አንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ፍትህ ሳያገኙ አንድ ወር እንደሞላቸው ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሁኔታ በዝርዝር ማስረዳታቸው አይዘነጋም።

ቤታቸው የፈረሰው ፍርድ ቤት ለእነሱ ወስኖላቸው (በቦታው እንዲፀኑ) መሆኑንና አፍራሽ ግብረኃይል በኃይል ህግ እና ስርዓትን በመጣስ እንዳፈረሰው መግለፃቸው ይታወሳል።

እኚህ ወገኖች እስካሁን ድረስ አንዳች መፍትሄ ሆነ ፍትህ ሳያገኙ ከ30 ቀን እንዳለፋቸው ተናግረው አሁንም ይመለከተኛል የሚል የመንግስት አካል ፍትህ እንዲሰጣቸው ፤ ህግን በጣሱ እና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባላከበሩት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ፥ ቤታቸው በግፍ የፈረሰባቸውን 30ኛ ቀን ምክንያት በማድረግ የቦሌ ኆህተ ብርሃን ቤተ ክርስትያን በፀሎት እና በትምህርት አስባው ማምሸቷን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል

ፍ/ቤት በቦታው ላይ እንዲፀኑ ፈርዶላቸው ፍትህ ያጡበትን ሁኔታ በማየት የሚመለከተው አካል ፍትህ እንዲያሰፍንና ሜዳ ላይ የተበተኑበትን ሁኔታ ተመልክቶ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው የጠየቀች ሲሆን ለተጎዱትም ወገኖች የተለያዩ እርዳታዎችን አድርጋለች፡፡

ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀደም የተፈፀመውን ድርጊት የሰሙ የተለያየ እምነት ተከታዮችም እንዳፅናኗቸው ፣ መጥተው እንደጠየቋቸውም ገልፀዋል።

አሁንም ለፍትህ የቆመ አካል ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው።

@tikvahethiopia
" ... ካልተጨበጠ መረጃ በቀር የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያው ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል የሚል መረጃ  ተመልክታችኋል? " - አብዲካሪም አሊ ካር

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐመድ አስተዳደር በኤርትራ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩት የሃገሪቱ ወታደሮች በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት አልተሳተፉም አለ።

የተመድ እና ህወሓት የሶማሊያ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከፌደራል መንግሥቱ ጎን ተሰልፈው ተዋግተዋል ማለታቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የቀድሞ የሶማሊያ መንግሥት ፕሬዝዳንት አስተዳደርም ሆነ አዲሱ መንግሥት፤ የሶማሊያ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት አልተሳተፉም ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማሊያ ወታደሮች በትግራዩ ጦርነት ተሳትፈዋል የሚለውን ክስ ማስተባበሉን አይዘነጋም።

ትናንት ሐምሌ 12/2014 ዓ.ም. የፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያው ጦርነት ተሳትፈዋል መባሉ ያልተረጋገጠ መረጃ ነው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አብዲካሪም አሊ ካር ፥ " ካልተጨበጠ መረጃ በቀር የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያው ጦርነት ተሳትፈዋል የሚል መረጃ  ተመልክታችኋል? " ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ጠይቀዋል።

በርካታ ሶማሊያውያን ወታደሮች ፤ መቼ እና በምን ሁኔታ ወደ ሶማሊያ እንደሄዱ ሳይገለጽ ቆይቶ ሰሞኑን የፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጉብኝትን ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት ሐምሌ 3/2014 ዓ.ም ለሶስት ዓመታት ያህል ወታደራዊ ሥልጠና ሲወስዱ የነበሩት የሶማሊያ ወታደሮች ተመርቀዋል ተብሏል።

ተቀናቃኞች በበኩላቸው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ወታደሮቹን ወዳልታወቀ ስፍራ ልከው በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ ማግደዋቸዋል በሚል ሲወቅሷቸው ቆይተዋል።

የወታደሮቹ ቤተሰብ አባላትም ስለልጆቻቸው ሁኔታ በመጠየቅ መንግሥትን አስጨንቀው ነበር።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ አብዲካሪም አሊ ካር ፤ በኢትዮጵያ ተሰልፈው ተጋዋግተዋል የሚለው ብቻ ሳይሆን የሶማሊያ ወታደሮች በኤርትራ የቆዩት ሶማሊያ የሚጠበቅባትን ገንዘብ መክፈል ባለመቻሏ ወታደሮቹ እንደመያዣነት ተይዘው ነው የሚባለውም ሐሰት ነው ብለዋል።

አብዲካሪም አሊ ካር ፦

" ... ሐሰት ነው ወታደሮቹ እንደመያዣነት አልተያዙም። ለማንም መክፈል ያለብን ገንዘብ የለም።

እንደ ተርኪዬ ፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት የሶማሊያንወታደሮች ያሰለጥናሉ።

ስልጠና የሚሰጣቸው ለገንዘብ አይደለም " ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ የሚገኙት የሶማሊያ ወታደሮች ብዛት 5 ሺህ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሞቃዲሹ መንግሥት ወታደሮቹን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ እየሠራ ይገኛል ማለታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያ የሆነች አንዲት ግለሰብ 10 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ መያዟን አስታወቀ።

የጉለሌ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያ የሆነችው ግለሰብ አንድን ባለ ጉዳይ " ጉዳይህን እኔ እጨርስልሀለሁ " በማለት 10 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል ሀምሌ 6 ቀን 2014 ዓ/ም እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ የግለሰቧን ስም ይፋ አላደረገም።

የግል ተበዳይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከድንበር ጋር የተያያዘ ጉዳዩን ለማስጨረስ በሄደበት አጋጣሚ ግለሰቧ 30 ሺህ ብር ጉቦ የጠየቀችው ሲሆን 10 ሺህ ብር ቅድሚያ እንደሰጣት እና ቀሪውን 20 ሺህ ብር ደግሞ ጉዳዩ ሲያልቅ ለመወሰድ መጠየቋን የግል ተበዳይ ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አሳውቆ ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ምም ጉቦውን ስትቀበል በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት ፖሊስ ገልጿል።

አዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ማህበረሰቡ መሰል ወንጀል ፈፃሚዎችን ለህግ አካል አጋልጦ የመስጠት ልምዱ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው ብሏል።

ወደፊትም ህዝብን እና መንግስት የሰጣቸውን እምነት በማጉደል በማህበረሰቡ ላይ በደል የሚፈጽሙ አካላትን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብሏል፡፡

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

የብርሃን ሞባይል ባንኪንግን ተጠቅመው :-

የዋይፋይ እና የሌሎችም የኢትዮ ቴሌኮም ክፍያዎችን በቀላሉ ያከናውኑ ፤ የአየር ትኬትዎን ይቁረጡ ፤ቀሪ የብድር መጠንዎን ይወቁ ፤ (*881#) በመጠቀም ያለ ኢንተርኔት ገንዘብ ያስተላለፍ በሞባይልዎ የቼክ ደብተር ይዘዙ ፤ የት/ቤት ክፍያዎን በቀላሉ ይክፈሉ ፤ ከራስዎ የባንክ ሂሳብ ወደ ሌሎች ባንኮች ሂሳብ ገንዘብ ያስተላልፉ።
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.me/berhanbanksc
#OLF

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በቡራዩ እስር ላይ ካሉ 7 የኦነግ አመራሮች 4ቱ ከእስር እንዲለቀቁ የቡራዩ ወረዳ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ጠበቃ አቶ ደምሴ ፍቃዱ ጉዳዩን በተመለከተ ለ #ቪኦኤ_ሬድዮ በሰጡት ቃል አራቱ የኦነግ አመራሮች አካልን ነፃ የማውጣት አቤቱታ አቅርበው እንደነበር፤ አቤቱታ የቀረበለት የቡራዩ ከተማ ፍ/ ቤት ግለሰቦቹ በማን እና ለምን እንደታሰሩ ለመረዳት ለሶስት ተከታታይ ችሎት ጥሪ ሲያቀርብ ነበር።

ነገር ግን ፖሊስ ሆነ እስረኞች አልቀረቡም። አርብ ሀምሌ 8 የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማብራሪያ ሠጥቷል።

ጠበቃ ደምሴ ፍቃዱ ፦

" 1ኛ አመልካች የሆነው ሚካኤል በቀለ ከዚህ ቀደም የወንጀል መዝገብ ተጣርቶበት በወንጀል አንቀፅ 42 መሰረት የተጠረጠረበት ጉዳይ ወንጀል ነው ተብሎ የሚያስከስስ ባለመሆኑ መዝገቡ ተዘግቶ ፖሊስ ከእስር ቤት እንዲለቀው ትዕዛዝ ፅፈንለት ፖሊስ ግን አለቅም ማለቱን አቃቤ ህግ ገልጿል።

2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ለሚ ቤኛ እና ዳዊት አብደታን በተመለከተ በተጠረጠሩበት ወንጀል ተከሰው የአቃቤ ህግ ምስክሮች ከተሰሙ በኃላ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ የሚያስቀጣ አይደለም በማለት በነፃ ካሰናበታቸው በኃላ ፖሊስ በራሱ ስልጣን ነው ያሰረው ሲል አቃቤ ህግ ለፍ/ ቤት አመልክቷል።

4ኛ አመልካች ገዳ ገቢሳ የተጠረጠረበት ወንጀል አቃቤ ህግ ከመረመረ በኃላ አያስከስስም ብሎ መዝገቡን ዘግቶ ከእስር እንዲለቀቅ ለፖሊስ ትዕዛዝ መስጠቱን አብራርቷል።

ከአቃቤ ህግም ምንም መዝገብ የላቸውም ሲል ነው የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፍ/ ቤት ያስረዳው። "

ፍ/ቤት ሀምሌ 11 ከእስር እንዲለቀቁ የወሰነ ቢሆንን ታሳሪዎቹ እስካሁን አልተለቀቁም።

@TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ4ኛ ቀን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል። የሀገራችን ልጆች የሚካፈሉበት ውድድር የሚከተሉት ናቸው። 🏟️ በማራቶን የሴቶች ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ጎይቶቶም ገ/ስላሴ 🇪🇹 አባበል የሻነህ 🇪🇹 አሸቴ በክሬ (ሰዓት - ቀን 10:15) 🏟️ 3,000 ሜትር መሰናክል የወንዶች ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ለሜቻ ግርማ 🇪🇹 ሀይለማርያም አማረ 🇪🇹 ጌትነት ዋለ (ሰዓት - ለሊት 11:20)…
#ማስታወሻ🇪🇹

የአለም ሻምፒዮናው 6ኛ ቀኑ ይዟል። በዛሬው ዕለት ሀገራችን አንድ የፍፃሜ ውድድርን ጨምሮ ሁለት ማጣርያዎችን የምታደርግ ይሆናል።

🏟️ የሴቶች 5,000 ሜትር ማጣርያ ፦

🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ዳዊት ስዩም

(ሰዓት - ለሊት 8:25)

🏟️ የወንዶች 800 ሜትር ማጣርያ ፦

🇪🇹 ኤርሚያስ ግርማ
🇪🇹 ቶሎሳ ቦደና

(ሰዓት-ሌሊት 9:20)

🏟️ የሴቶች 3,000 ሜትር መሰናክል #ፍፃሜ

🇪🇹 መቅደስ አበበ
🇪🇹 ወርቅውሃ ጌታቸው

(ሰዓት - ሌሊት 11:45)

ድል ሀገራችን 🇪🇹 !

ተጨማሪ ስፖርታዊ ጉዳዮች https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DrTazebachew

የዶ/ር ታዘባቸው ውዴ ጉዳይ ዛሬም ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ፤ ዩኒቨርሲቲውም አንዳች ነገር ሳይል ቀጥሏል።

ዶ/ር ታዘባቸው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ተመርቆ ይርጋለም ሆስፒታል ለ2 ዓመት አገልግሎ ለማህፀንና ፅንስ ስፔሻላይዜሽን ትምህርት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ተቀላቅሎ ትምህርቱን ሲከታተል ነበር።

ዶ/ር ታዘባቸው ከልጅነቱ ጀምሮ በአንድ አይኑ ላይ የመሸዋረር ችግር ያለበት ሲሆን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲመረቅ ሆነ ወደ አ/አ ጥቁር አንበሳ ሲቀላቀል አንድም ቀን ስለአይኑ ጉዳይ ተነስቶም፤ ተጠይቆ አያውቅም።

ጥቁር አንበሳን ሲቀላቀልም በቃል እና በፁሁፍ ፈተና ተፈትኖ ብቃቱን አስመስክሮ ተቋሙ ገብተህ መማር ትችላለህ ብሎት ነው።

ነገር ግን 4 ዓመት እጅግ ከፍተኛ ድካምና ጥረት የሚጠይቀውን የስፔሻላይዜሽን ትምህርቱን ቀንና ሌት እንቅልፍ አጥቶ ተምሮ ሊመረቅ ጥቂት ቀናት ሲቀረው ድንገት የዓይን ምርመራ አድርግ ይባላልና ብቁ አይደለህም ተብሎ ወደሌላ ዲፓርትመንት ገብቶ (ኒውሮሎጂ) ከአንደኛ አመት እንዲጀምር ተደርጓል።

ዶ/ር ታዘባቸው ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ነገር ሰምቶ እንደማያውቅ ተናግሮ እሱ ብቻውን ከሌሎች በተለየ የአይን ምርመራ እንዲያደርግ ታዞ ምርመራ ካደረገ በኃላ በአጭር ፅሁፍ ትምህርቱን መቀጠል እንደማይችል እና አንደማይመረቅ እንደተነገረው ያስረዳል።

የአይኑ መንሸዋረር አንድም ቀን ለስራው ፣ለትምህርቱ እንቅፋት ሆኖበትና በዚህ ምክንያት በርካታ የቀዶ ጥገና ስራ ሲሰራ ችግር ተፈጥሮ እንደማያውቅም ይገልፃል።

4 ዓመት ከለፋበት ትምህርት ወጥቶ ወደሌላ ዲፓርትመንት እንዲገባ የተደረገው ዶ/ር ታዘባቸው ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው ካልሆነ መብቱን ለማስከበር ወደህግ እንደሚወስደው ከጠበቃው ጋር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመኪና ዝርፊያ ! ከጥቂት ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ወገኖች ላይ የሚፈፀመው ዝርፊያ አሳሳቢ መሆኑን አመልክተን ነበር። በወቅቱ አንድ የቤተሰባችን አባል ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራባትን መኪና ዘራፊዎች በስለት አስፈራርተውት እንደዘረፉት መግለፁ አይዘነጋም። ትናንት አርብ ምሽት 4:00 ላይ ደግሞ ሌላ አንድ ወንድማችን ከፍየል ቤት ወደ ሀያሁለት…
#አዲስ_አበባ

አዲስ አበባ ውስጥ የቀጠለው ዝርፊያና ጥቃት !

ከሰሞኑን የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት የሚሰጡ ወገኖች ላይ እየደረሰ ስላለው ወንጀል መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ማመልከታችንም የሚታወስ ነው።

ለማስታወስ ፦

👉 አንድ የቤተሰባችን አባል ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራበትን መኪና ዘራፊዎች በስለት አስፈራርተውት እንደዘረፉት : t.me/tikvahethiopia/71682?single

👉 ባለፈው አርብ ምሽት አንድ ወንድማችን ከፍየል ቤት ወደ 22 ከመገድ ላይ ሰው ጭኖ አውራሪስ አካባቢ ሲደርስ አንገቱን አንቀው እራሱን እንዲስት በማድረግ ከመኪናው አሰወጥተው በመወርወር መኪናውን ይዘው መሰወራቸውን አሳውቀን ነበር : t.me/tikvahethiopia/72020?single

የአሁኑ ግን ከዝርፈያም ባለፈ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ነው።

ከላይ በፎቶ የምትመለከቱ ሳላዲን ሐሰን ይባላል።

የምትመለከቷት መኪናም የእሱ ነበረች።

ትናንት ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ እጅግ በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ተገድሎ መኪናው ተዘርፏል።

ሳላዲን የራሱን እና የቤተሰቦቹን ኑሮ ለማሻሻል ሲል ይተዳደርበት በነበረው የመኪና እጥበት ስራ ከሚያገኘው ገቢ በመቆጠብ ነው መኪናዋን ገዝቷት የነበረው።

ሳላዲን በጩቤ ተወግቶ ተገድሎ መኪናው ከመዘረፉ በፊት የመጨረሻ አገልግሎት ለመስጠት የተደወለበት አካባቢ ገርጂ 24 ልዩ ቦታ ኤርትራ ቆንጽላ ጽ/ቤት አካባቢ መሆኑን የሚሰራበት ድርጅት እንደነገራቸው ጓደኞቹ ገልፀዋል።

ቤተሰቦቹ ከባድ በሆነ መሪር ሀዘን ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ጓደኞቹም በተፈጠረው ሁኔታ እጅግ መደናገጣቸውንና ከባድ ሀዘን ውስጥ እንዳሉ ነግረውናል።

ለበለጠ መረጃ፦ 0944322244 (አብዲ ሰይድ) ፤ 0967803785 (ካሊድ አብዱልቃድር)

@tikvahethiopia