TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DawroZone 📍

በዳውሮ ዞን ባጋጠመ የዝናብ እጥረት እና የአየር መዛባት ምክንያት ወገኖቻችን ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል።

በ5 ወረዳዎች በተከሰተ የምግብ እጥረት እናቶች እና ህፃናት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

በተለይ በዛባ ገዞ ወረዳ፤ ሰዎች እየተራቡ የቤት እንስሳትም እየሞቱባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ከቤት እንስሳት በተጨማሪ በጫካ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት ጭምር በምግብ እጥረት እንደሞቱ ገልጸዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ " የተለያየ ነገር እንተክላለን ነገር ግን ዝናብ የለም፤ ዝናብ ቢዘንብ እንኳን በቀበሌ ደረጃ ብንቆጠር 4 የሚሆን ጥማድ በሬ ማግኘት አንችልም። በመኖር እና በመሞት መካከል ነው የምንገኘው " ብለዋል።

የምግብ ጥረቱ በመማር ማስተማር ላይም ተፅእኖ ያሳደረ ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠዋል።

የዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያ የአደጋ ፅህፈት ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው የምስክ ምልከታ 112 ሺ በላይ ወገኖቻችን ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አረጋግጧል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በበኩሉ አሁን በከፋ ሁኔታ ላይ የሚገኙና አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን 44 ሺ ሲሆኑ የቀሩት በሴፍቲኔትና በምግባ ይካተታሉ ብሏል፤ በችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን መግለፁን የጀርመን ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ መረጃ ፤ በዳውሮ ዞን በቆላማ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን የተለያዩ አካላት ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን፤ የቤንች ሸኮ ዞን ፣ ካፋ ዞን፣ ኮንታ ዞን ፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ የቦንጋ መምህራን ኮሌጅ፣ ቀይ መስቀል፣ የክልል ቢሮዎች ሌሎችም ድጋፍ አድርገዋል።

@tikvahethiopia
#IFTAR

ዛሬ በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ይካሄዳል።

ለዚህም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።

ከደሴ ከተማ ኮሚኬሽን ቢሮ ባገኘነው መረጃ ዛሬ አርብ የሚካሄደው ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት እንደ አምናው " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ሲሆን ለደሴ ከተማ የክርስትና እምነት የተከታዮችም " ኑ በጋራ እናፍጥር " ውብ የሆነውን የወሎን እሴት እናስቀጥል የሚል ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ መረጃ ነገ ቅዳሜ ረመዳን 15 (ሚያዚያ 8) በድሬዳዋ ከተማ " የአብሮነት ኢፍጣር በድሬዳዋ " በሚል በምድር ባቡር ለገሃር አደባባይ ይካሄዳል፤ በዕለቱ በአብሮነት ከማፍጠር ባለፈ የቁርዓን እጥረት ላለባቸው ከተሞች ቁርዓን የሚሰበሰብ ሲሆን እስከ 1000 ቁርዓን ለማሰባሰብ ታቅዷል።

በተጨማሪ የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 9 በኮምቦልቻ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት መዘጋጀቱ ተሰምቷል።

እንዲሁም በሀረር ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሚያዚያ 9 ከራስ ሆቴል እስከ ጁምዓ መስጂድ ድረስ ይካሄዳል ተብሏል።

በሌሎችም የሀገራችን ከተሞች ላይ ተመሳሳይ ስነ ሥዓቶችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

ፎቶ ፦ ደሴ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ነዋሪዎችን ያማረሩት ጫኝ እና አውራጆች ፦

ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፦

" ... በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በሁሉም ሰፈር ማለት ይቻላል በህገወጥ ጫኝና አውራጆች በሚጠየቅ የተጋነነ ክፍያ ምክንያት ዕቃ መኪና ላይ መጫንም ሆነ ማውረድ አዳጋች ሆኗል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህ ህገ ወጦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ሊታደግ ይገባል።

ሰው ተሰቃይቷል ፤ ህዝቡ ተበሳጭቷል ፤ ጉረቤትህ እና ልጆችህ እንኳ ተባብረው ሊያራግፉልህ እድል አይሰጡም።

እነዚህ ወጣቶች ሌላው በመቶ ብር ሚያራግፈውን እነሱ ቢያንስ እስከ 3 ሺ ብር ይጠይቃሉ። "

ከሰሞኑን ከዚህ ነዋሪዎችን እያማረረ ካለው ህገወጥ ድርጊት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ለሸገር FM 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል አሳውቋል።

በአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፥

" ብዙ ችግር ነው ያለው። ለምሳሌ ፦

👉 ቁሳቁሱን እኛ ብቻ ነን የምናወርደው ፤ የምንጭነው ብለው እራሳቸው ይወስናሉ በሰው ንብረት።

👉 ተመጣጣኝ ክፍያ አይጠይቁም።

👉 እርስ በእርስም የሚጣሉበት ሁኔታ አለ፤ በዚህም ንብረት ይወድማል አካል ጉዳት ይደርሳል። ምንም በማያገባው እዛ ባለው ግለሰብ ንብረት ላይ ጭምር ጉዳት ይደርሳል።

👉 ግለሰቦችን ማጨነቅ አለ እኛ ካላወረድነው እናወድመዋልን የሚሉም አሉ።

ይሄ እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነው። ስለዚህ ይሄን ስራ የሚሰሩ ሰዎች ተለይተው ህብረተሰቡ ለፖሊስ መረጃ በመስጠት አደብ እንዲገዙ መደረግ መቻል አለበት ካለበለዚያ ከባድ ስጋት ነው የሚሆኑት። " ብለዋል።

ፖሊስም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት በህገወጥ ጫኝ እና አውራጆች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ምክትል ኮማንደር ማርቆስ አሳውቀዋል።

ም/ኮማንደር ማርቆስ ፦

" በለሚኩራ ክ/ከተማ በ6 ወር በ21 መዝገቦች 80 ተከሳሾች ይዘን ምርመራ እያጣራን ነው። በተመሳሳይ በ12 መዝገቦች 45 ተጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤት ወርደው ጉዳያቸውን በህግ እንዲከታተሉ እየተደረገ ነው።

በቦሌ ክ/ከተማ በ10 መዝገቦች 63 ተከሳሾች ላይ ክስ ተመስርቷል። 62ቱ ተይዘዋል። እነዚህም ምርመራ እየተጣራባቸው ነው።

ንፋስስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሰፈራ የሚባል አካባቢ ባለፈው ወር የተሰራ ስራ በቀን 21/7/2014 ዓ/ም በአንድ መዝገብ 10 ተከሳሾች ይዘን ምርመራ እያጣራን ነው።

በለቡ ፖሊስ ጣቢያ ፤ ሆፕ ዩኒቨርሲቲ የሚባል አለ እዛ አፓርታማ ቤቶች አሉ እዛ የሚገቡ ሰዎች ላይ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ በአንድ መዝገብ 13 ተጠርጣሪዎች ተይዘው በ4ቱ ላክ ሁለት ሁለት ወር እንዲወሰንባቸው ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " አንዳንድ ስራቸውን በአግባቡ የሚሰሩ ጫኝና አውራጆች አሉ፤ በቅርቡም ጥይቶች ተጭነው እስከማጋለጥ የደረሱ መኖራቸውን ተመልክተናል " ያሉ ሲሆን ያልተገባ ስራ የሚሰሩትን ፤ ወደ ህግ ከማቅረብ ይልቅ #ተስማሙ የሚሉ የፖሊስ አባላትን ህብረተሰቡ ሲመለከት በ 991 ነፃ የስልክ መስመር እና በ 0111110111 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ከሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tigray

በትግራይ ክልል ያሉ ህሙማን በህይወት አድን መድሃኒቶችና ኦክሲጅን እጥረት ሳቢያ እየሞቱ መሆኑን የጤና ባለሞያዎች መግለፃቸውን ኤፒ ዘግቧል።

ለአብነት በመቐለ በሚገኘው የአይደር ሆስፒታል የሚሰራ አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ ዶክተር እኤአ ከሀምሌ ወር ጀምሮ ቢያንስ 60 የኩላሊት ህሙማን በየጊዜው ለሚደረግ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች ባለማግኘታቸው ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

ሌሎች 81 ታማሚዎች ደግሞ እኤአ በህዳር 2020 በፌደራል መንግስት እና ትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሓት) መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኃላ "በቀጥታ በኦክሲጅን እጥረት" ህይወታቸው ማለፉን ዶክተሩ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል፤ በሆስፒታሉ የሚሰሩ ሰራተኞች ለወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው እና ብዙዎቹም ምግብ ለመግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንደሌላቸው የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎች ገልፀዋል።

ይህም ሁኔታ በክልሉ ያለውን ሰፊ ​​የሆነ የሰብአዊ ቀውስ ተግዳሮቶችን አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ከአጠቃላዩ የትግራይ ክልል ነዋሪ 90% የሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልገው ሲሆን ከነዚህም መካከል 115 ሺ ህጻናት በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ውስጥ መሆናቸውን የUN መረጃ ያሳያል።

እኤአ ከጥር ወር መገባደጃ ጀምሮ ወደ ክልሉ በዓለም ጤና ድርጅት እና የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በረራ ወደ ክልሉ የደረሰው 438 ሜትሪክ ቶን የህክምና እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት አንዳንድ እጥረቶችን ቀርፏል።

ነገር ግን እኚህ አቅርቦቶች ከሚያስፈልገው ውስጥ 4% ብቻ የሚሸፍኑ መሆናቸውን ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት።

apnews.com/article/health-ethiopia-africa-united-nations-dialysis-f9c2c16ba1ee9704fa3799d1846d7ee5

@tikvahethiopia
" ... ከ1.1 ሚሊየን የተመረቁ ተማሪዎች መካከል ከ100 ሺ በላይ የሚሆኑት ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የያዙ ናቸው " - የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን

የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የትምህርት ጥራትን ከመቆጣጠር ባሻገር የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነትን የማረጋገጥ ሥራ ይሰራል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃና የትምህርት ማስረጃ ከምዝገባ እስከ ምረቃ ድረስ ለባለሥልጣኑ የመላክ ግዴታ አለባቸው።

ይህን ተከትሎ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ከ1995 ጀምሮ እስከ 2014 ዓ.ም መረጃቸውን ለተቋሙ ካስገቡ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ክትትል አድርጓል።

በእነዚህ ተቋማት እስካሁን ከተመረቁ 1.1 ሚሊየን ተማሪዎች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የያዙ ናቸው ተብሏል።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃውን የያዙት ግለሰቦች የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው፤ በ10+1 እና በ10+2 የዲግሪ የምስክር ወረቀት ከማግኘት እስከ እውቅና በሌለው የትምህርት መስክ እስከተመረቁ ይገኙበታል።

እርምጃ መውሰድ ቢጀመር አንዳንድ ክልሎች ቢሮዎቻቸው ሊዘጉ ይችላሉ የተባለ ሲሆን በአስመራቂ ተቋማትና የሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃው ባለቤቶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝርዝር ማጣራት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ የወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከት ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር መስራት መጀመሩን ገልጿል።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሰጡ ተቋማትን በሕገወጥ መንገድ ዲግሪ ያገኙ ተመራቂዎችን ለማጋለጥ ወደ ኋላ እንደማይል ማሳወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

t.me/TikvahUniversity/3508

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UNGA በአሜሪካ አነሳሽነት 193 አባል ሀገራት ላሉት የተመድ ጠቅላለ ጉባኤ የቀረበው ሩስያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት የማገድ የውሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ዛሬ ፀድቋል። የውሳኔ ሃሳቡን ከ193 አባልት 93 ሀገራት የደገፉት ሲሆን 58 ሀገራት ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል፤ 24 ሀገራት ደግሞ ተቃውመዋል። በዚህም በአብላጫ ድምጽ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ታግዳለች። የውሳኔ ሃሳቡ ለጉባኤው…
#RUSSIA #ETHIOPIA

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በቅርቡ በተደረገው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩስያ ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ ቤት እንድትታገድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ለምን የተቃውሞ ድምፅ ሰጠች ?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሲመልሱ ፦

" ...እኛ ሀገሮችን በማግለል፤ እንደ UN ካሉት ዓለም አቀፍ ተቋም በማስወጣት ጥቅም አይመጣም ሰላምም በእንዲህ አይነት አይመጣም ከሚል የመነጨ ነው በዋናነት።

አሁንም ቢሆን ይሄ ነገር በሰላም እንዲዘጋ እንደምንፈልግ ገልፀናል። በሰላማዊ መንገድ ፤ በሰላማዊ ሂደት ይሄ ነገር እንዲቆም ነው እንጂ #አንድን_ወገን_ለይቶ_በማግለል ሊመጣ የሚችል ሰላም የለም ከሚል የመነጨ አቋም ነው።

ከተባለው ሀገር (ሩስያ) ጋርም ያለን ግንኙነት በጣም ጠንካራ ስለሆነ ነው። እንደሚታወቀው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መድረክ የሰጡን ድጋፍ የሚታወስ ነው። " ብለዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት 193 አባል ሀገራት ላሉት የተመድ ጠቅላለ ጉባኤ የቀረበው ሩስያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት የማገድ የውሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ መፅደቁ ፤ ሩስያም ከም/ቤቱ መታገዷ ይታወሳል።

በወቅቱ የውሳኔ ሃሳቡን ከ193 አባልት 93 ሀገራት የደገፉት ሲሆን 58 ሀገራት ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል፤ 24 ሀገራት ደግሞ ተቃውመዋል፤ ከተቃወሙት 24 ሀገራት አንዷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጭሮ የ ' አጥንት ካንሰር ታማሚ ' በመምሰል በተሽከርካሪ ላይ እየተዘዋወረች ስትለምን የነበረችውን ወጣት ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጭሮ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ወጣቷ ከሰባት (7) ግብረ አበሮቿ ጋር የአጥንት ካንሰር ታማሚ መስላ በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረች  ስትለምን መቆየቷን በምርመራ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል። የጭሮ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ምርመራ ወጣቷ ግብረ…
#AddisAbaba

በመዲናችን አዲስ አበባ የ10 ዓመት ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል።

የሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በህፃኑ ስም ገንዘብ ሲያሰባስቡ ተገኝተው በቁጥጥር ስር የዋሉት 11 ግለሰቦች (9 ሴቶች እና 2 ወንዶች) ሲሆኑ አሁን ላይ ምርመራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በ3 ክፍለ/ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሃኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች (ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169 ኮድ 3 ኦሮሚያ) ጋር በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማና በፀጥታ ኃይሎች ክትትል ነው ተብሏል።

አሁን ላይ በከተማዋ የተለያዩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ያልታመመ ሰውን ታሟል በማለት የሚመለከተው የህክምና ተቋም ማረጋገጫ ሳይሠጥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚካሄዱ ልመናዎች በዝተወልና ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪ ወንጀለኞች ራሱንና ንብረቱን ይጠብቅ ተብሏል።

ከዙህ ቀደም (የካቲት ወር ላይ) በጭሮ ከተማ የ ' አጥንት ካንሰር ታማሚ ' በመምሰል በተሽከርካሪ ላይ እየተዘዋወረች ስትለምን የነበረችውን ወጣት በፖሊስ መያዟ ይታወሳል (ለማስታወስ ይኸው ሊንኩ t.me/tikvahethiopia/67710 )

እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በእርግጥም ታመው እና አቅም አንሷቸው በህምመም ለሚሰቃዩ ወገኖቻን በሚደረገው ድጋፍ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፤ ሰዎች ድጋፋቸውን ለማድረግ እንዲጠራጠሩም ይሆናል፤ በዚህም ምክንያት በእኛ የ10 ብር እና 20 ብር ድጋፍ ተሰባብሶ ሊተርፉ የሚችሉ ወገኖቻችን እናጣቸዋለን።

ምን ቢደረግ የተሻለ ነው ? ሃሳባችሁን አካፍሉ ፤ ተነጋገሩት👇

@tikvahethiopiaBOT
#SIDAMA

ዘንድሮ " ፊቼ ጫምባላላ " በአደባባይ በድምቀት ይከበራል።

ላለፉት ለሁለት ዓመታት የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በጉዱማሌ አለመከበሩ (ህዝቡ በየቤቱ እንዳከበረ) ይታወቃል።

ዘንድሮ ግን በአደባባይ በ " ጉዱማሌ " ለማክበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ በተጨማሪ በሀገር ደረጃ (በሌሎችም የሀገራችን ከተሞች) ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰስ ቅርስ አንዱ እንደመሆኑ በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ እንድግዶችን ፣ ቱሪስቶች እና ለባለድርሻ አካላት ለማስተናገድ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

መረጃውን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል ፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WFP #UN #Ethiopia #TigrayRegion ዛሬ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ አልሚ ምግብን ጨምሮ ህይወት አድን ፍጆታዎችን የጫኑ 47 ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን አሳውቋል። ከ47ቱ ተሽከርካሪዎቹ በተጨማሪ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች የሚውል ነዳጅ የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ። ከሁሉም ባለስልጣናት በተደረገው ድጋፍ እስካሁን ጉዞው የተሳካ እና መልካም የሚባል…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

#Tigray, #Mekelle 📍

ትላንትና በጉዞ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን የጫኑት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪዎች የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ደርሰዋል።

ሁሉም (50ውም) ተሸከርካሪዎች በሰላም ነው መቐለ የደረሱት።

ምን ይዘዋል ?

➡️ 1,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና ጥራጥሬ ፤
➡️ 700 ሜትሪክ ቶን የጤና ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና WASH (ውሃ፣ የአካባቢ እና የግል ንፅህና መጠበቂያ እቃዎች) + 115,000 ሊትር ነዳጅ ይዘው ነው መቐለ የደረሱት።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም መቐለ የደረሱትን እነዚህን ምግብ / አልሚ ምግቦች በዚህ ሳምንት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ማከፋፈል እንደሚጀምር አሳውቋል።

በዚህም ድርጅቱ 43,000 አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንዲሁም ተጋላጭ ለሆኑ 24,000 እናቶች እና ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ ለመድረስ ማቀዱን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IFTAR ዛሬ በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ይካሄዳል። ለዚህም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ። ከደሴ ከተማ ኮሚኬሽን ቢሮ ባገኘነው መረጃ ዛሬ አርብ የሚካሄደው ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት እንደ አምናው " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ሲሆን ለደሴ ከተማ የክርስትና እምነት የተከታዮችም " ኑ በጋራ እናፍጥር " ውብ የሆነውን የወሎን እሴት እናስቀጥል የሚል ጥሪ ቀርቧል። በሌላ መረጃ ነገ ቅዳሜ ረመዳን…
#IFTAR

በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሄደ።

በደሴ ከተማ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ተካሂዷል።

የኢፍጣር ስነስርዓቱ ከ " ፒያሳ እስከ መናኸሪያ " ባለው ጎዳና ላይ የተካሄደ ሲሆን እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የደሴ ከተማ ነዋሪ ታድሟል።

በሌላ በኩል ደሴ የረመዳንን በዓል አስመልክቶ " ከኢድ እስከ ኢድ " በተሰኘው መርሃ ግብር ደሴ የሚገቡ እንግዶችን ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ትገኛለች።

ፎቶ፦ ሶሻል ሚዲያ የተሰባሰበ

@tikvahethiopia