TIKVAH-ETHIOPIA
1.49M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.86K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ በአፋርና በአማራ ክልሎች የተከሰተውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ ያካሄደውን የምርመራ ሪፖርት ይፋ እያደረገ ይገኛል።

ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-11

@tikvahethiopia
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን አካውንት ለግዜው ያግዳል የተባለው ወሬ ሐሰት ነው አለ።

ንግድ ባንክ " መረጃ አሟሉ አልኩ እንጂ የባንክ ሂሳብ አግዳለሁ አላልኩም " ብሏል።

ዛሬ የደንበኞችን መረጃ የመሰብሰቢያ ቀን የመጨረሻ ነው የተባለውም #ሐሰት ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።

የባንኩ የኮምዩንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ያብስራ ከበደ ባንኩ የደንበኞችን መረጃ ለመሰብሰብ አገልግሎቱን ለጊዜው ገደበ እንጂ አለማገዱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲ.ኤምና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መገደብ ያስፈለገው የብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የግል ባንኮች የላከውን መመሪያ ለመተግበር በመገደዱ መሆኑን ተገልጿል።

ደንበኞች ለጊዜው በኤቲኤም እና በሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ማስተላለፍና ማውጣት አገልግሎት ባያገኙም ወደ ቅርንጫፍ መጥተው ሀብታቸውን እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት ብሏል ባንኩ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞችን መረጃ ለመፈለግ የመጨረሻው ቀን ዛሬ አርብ ነው የተባለው ትክክል እንዳልሆነ ባንኩ ገልጿል።

አክሎም " ደንበኞች በየቅርንጫፉ መጉላላት፣ መሰለፍ እና ጊዜያችሁን ማባከን የለባችሁም ባመቻችሁ ጊዜ ባንኩ የሚጠይቀውን መረጃ መስጠት ትችላላችሁ " ሲል ማሳወቁን #ሸገር_ኤፍ_ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባወጣው ማሳሰቢያ ላይ ደንበኞቹ እስከ መጋቢት 2 /2014 ድረስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጡ ከመጋቢት 2 /2014 በኃላ ግን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት (የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ ፣ እንዲሁም የATM እና የፖስ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም ብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#SPHMMC

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሕክምና ትምህርት ለመማር መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች ተቀብሎ ማሰልጠን እንደሚፈልግ ገልጿል።

ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ፦

1. በ2014ዓ.ም በመደበኛ ትምህርት ፕሮግራም 12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች

2. በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና 1) ሲቪክስ ውጤት ለተያዘላቸዉ ከ700 ያገኙትን ወደ 600 ከቀየሩ በኋላ 2) ሲቪክስ ውጤት ያልተያዘላቸው የሲቪክስ ውጤቱን ቀንሠው በሚያገኙትን ዉጤት መሠረት
• ከስር ከተዘረዘሩት ክልልና ዞኖች ውጪ ያሉ ሁሉም ክልሎች -
👉 ለወንድ 475 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
👉 ለሴት 460 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
• ለአፋር ክልል ፣ ለቦረና ዞን (ኦሮሚያ ክልል) ፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ለጋምቤላ ክልል ፣ ለሱማሌ ክልል፣ለደቡብ ኦሞ ዞን(ደቡብ ክልል)፣ ለዋግ እምራ ዞን(አማራ ክልል)ና ለምእራብ ኦሞ ዞን(ደቡብ ክልል)
👉 ለወንድ 450 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
👉 ለሴት 440 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት

3. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል አማካይ የትራንስክሪፕት ውጤት 80% እና ከዚያ በላይ የሆነ

ማሳሰቢያ፦

1. ማመልከት የሚቻለው Online ብቻ ነው፡፡
2. የማመልከቻ ጊዜው ከመጋቢት 5 - መጋቢት 11 / 2014ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው

www.sphmmc.edu.et

ምንጭ፦ SPHMMC

@tikvahethiopia
Amharic-Executive-Summary-AAIR.pdf
399.8 KB
#Update

በኢትዮጵያ የአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ የተደረገ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።

የምርመራ ሪፖርቱ #አንኳር_ጉዳዮችን በPDF (399.8 KB) ከላይ ያንብቡ።

@tikvahethiopia
Full AAIR With Annexes.pdf
5.2 MB
ሙሉ ሪፖርት ፦

በኢትዮጵያ የአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ ያደረገው ምርመራ ሙሉ ሪፖርት ከላይ በPDF (5.2 MB) ተያይዟል።

ኢሰመኮ በዚህ ሰፋ ባለ የምርመራ ሪፖርቱ ፦

- በሲቪል ሰዎች ፣ በሲቪል ተቋማት፣ በሌሎች ጥበቃ በሚደረግላቸው ሰዎች ላይ ስለተፈፀሙ ጥቃቶች ፤

- ከህግ አግባብ እና ከፍርድ ውጪ ስለተፈፀሙ የሲቪል ሰዎች ግድያዎች እና የአካል ጉዳቶች ፤

- የጭካኔ ፣ ኢ-ሰብዓዊና አዋራጅ አያያዝ እና ቅጣት፤

- የዘፈቀደ እስር ፣ ጠለፋ እና አስገድዶ መሰወር ፤

- ወሲባዊ እና ፆታዊ ጥቃቶች ፤

- የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ፤

- በንብረት ላይ የተፈፀሙ ዘረፋዎች፣ ገፈፋ እና ውድመቶች ፤

- የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ክልከላ ፤

- ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና የባህል መብቶች ፤

- በህፃናት ላይ የተፈፀሙ ጥሰቶች ፤

- የአከል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ጉዳዮችን በስፋት ዳሷል።

🔹በዚህ የኢሰመኮ ሪፖርት በአፋር እና በአማራ ክልሎች ላይ በተደረገው ምርመራ ሆነ ተብለው የተፈሙ ሕገወጥ ግድያዎችን ሳይጭም በጦርነት ውስጥ 403 ሲቪል ሰዎች ለሞት እንዲሁም 309 ሲቪል ሰዎች ለቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መዳረጋቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
የሚዘጉ መንገዶች።

ከዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ አንደኛውን የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ታስተናግዳለች።

ጉባኤውን ተከትሎ መጋቢት 2 ቀን እና መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ፕሮግሞች ይካሄዳሉ ተብሏል።

በዚህ መሰረት መጋቢት 2 / 2014 ዓ/ም ምሽት አራት ኪሎ አካባቢ የሚካሄደው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ 4 ኪሎ የሚወስዱ መንገዶች ፦

👉 ከፍል ውሃ ወደ ሸራተን ሆቴል
👉 ከኦርማ ጋራዥ በሸራተን ሆቴል ወደ ንግድ ማተሚያ
👉 ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኮንሰን
👉 አምባሳደር መናፈሻ ወደ ሸራተን ሆቴል

በተመሳሳይም መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው ተመሳሳይ ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ወደ አራት ኪሎ የሚውስዱ መንገዶች፡-

👉 ከቀበና በቤልኤር ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቤልኤር መብራት
👉 ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቅድስተ ማርያም ትራፊክ መብራት
👉 ከፒያሳ በሰባ ደረጃ ቅድስተ ማርያም የሚወስደው መንገድ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ቢሮ
👉 ከቴዎድሮስ አደባባይ በእሪ በከንቱ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ እሪ በከንቱ መብራት
👉 ከአዋሬ ገበያ በጥይት ቤት አራት ኪሎ የሚወስደው አዋሬ አደባባይ
👉 ከኮንሰን ወደ ፓርላማ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሱት ቀናት ዝግጅቶቹ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቁ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትእዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#Russia

የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ።

ፑቲን ፤ " ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ " ካሉ በኋላ፤ " እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን " ብለዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ ጦር ጎን መሰለፍ የሚፈልጉ 16 ሺህ ሰዎች አሉ ሲሉ ለፑቲን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለፀጥታ ምክር ቤታቸው ምዕራባውያን " በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመተላለፍ ተዋጊዎችን ለዩክሬን እየቀጠሩ ነው " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም ዩክሬን በ "አፍሪካ" በተለያዩ ሀገራት በሚገኙት ኤምባሲዎቿ በኩል በ #ቅጥር ለዩክሬን የሚዋጉ ሰዎችን እንደምትፈልግ ማስታወቋ በኃላ ይህ ጥሪው ቁጣን ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ትላንትና ህ/ተ/ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አሳስቧል። ማሳሰቢያው ከተሰጣቸው ፓርቲዎች መካከል ፦ ብልፅግና፣ ኦፌኮ፣ አብን ፣ ኦነግ ፣ ነእፓ፣ ኦብነግ፣ መኢአድ ይገኙበታል።…
ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ዛሬ 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

ፓርቲው ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂድ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት ይቆያል።

በአሁኑ ሰዓት ላይ የጉባኤው የመክፈቻ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ሲሆን የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ታድመዋል።

ዛሬ ጉባኤውን የጀመረው ብልፅግና ፓርቲ ፤ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እና አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ከሰጣቸው 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

" ነዳጅ እና ጋዝ አምራች ሀገራት አቅርቦታችሁን ጨምሩ " - G7

በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሀገራት ስብሰብ G7 ፤ ሩስያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው "ወረራ" በዋጋ ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ለመቋቋም ትላልቅ የነዳጅ እና ጋዝ አምራች ሀገራት አቅርቦቶችን እንዲያሳድጉ አሳስቧል።

የG7 የኢነርጂ ሚኒስትሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ ነዳጅ እና ጋዝ አምራች ሀገራት ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲሰሩ እና ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች የሚደርሰውን ምርት የማሳደግ አቅማቸውን እንዲፈትሹ ጠይቀዋል።

በዚህ ላይ ኦፔክ (የነዳጅ አምራች አገራት ኅብረት) ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሚኒስትሮቹ በመግለጫቸው የጋዝ ዋጋ መጨመርን ለማስቆም ውጤታማ እርምጃዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የG7 የኢነርጂ ሚኒስትሮች የኃይል ምርቶች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ጭማሪ በቤትውስጥ እና በንግድ ስራዎች “በተለይም በአውሮፓ ሀገራት” ላይ ያለው ጫና “አሳሳቢ” ነው ብለዋል።

ታዳጊ አገራት ውስጥ ያለውም ጫና እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል።

የሩስያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በዚህ ሳምንት የነዳጅ ዋጋ በ14 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በመታይወቅ መልኩ ጨምሮ 140 ዶላር ድረስ ደርሶ እንደነበር ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈ የG7 አባል ሀገር አንዷ የሆነችው አሜሪካ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከሩስያ የኃይል አቅርቦቶችን (ነዳጅ፣ ጋዝ) ገዝታ እንደማታስገባ እንዲሁም ሌላኛዋ የG7 አባል ብሪታኒያም ከአመቱ መጨረሻ በኃላ ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ ማስታወቋ ሩስያም ለምዕራባውያኑ ድርጊት አፀፋ ለአውሮጳ የምታቀርበውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን እንደምታቋርጥ መግለጿ በነዳጅና ጋዝ ምርቶች ላይ አሁን እየጨመረ ካለውም በላይ ጭማሪ እንዳያሳይ ተሰግቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2014 ተጠናቋል። መረጃዎችን ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ሆነዋል (በሚሊዮን ሊቆጠሩ ናቸው ተብሎ ይታመናል) ፤ አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉትም በመመሪያው መሰረት መረጃ ሲሰጡ ብቻ ነው። የ " መታወቂያ እድሳት…
በሁለት ወር ተራዝሟል !

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ላለፉት 6 ወራት ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ ሲሰሩ ነበር።

በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ላልቻሉ ደንበኞች ተጨማሪ የ2 ወር ጊዜ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የባንክ ደንበኞች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ከወዲሁ ወደ ባንክ በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

#CBE

@tikvahethiopia
የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ በመስቀል አደባባይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን ሽኝት ይካሄዳል ፤ የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም ደግሞ መጋቢት 4 /2014 ዓ/ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል።

ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፦

👉 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ

👉 ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ

👉 ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት

👉 ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መብራት

👉 ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር

👉 ጦር ኃይሎች ፣ በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት

" #ይለፍ_ለሌላቸው_ተሽከርካሪዎች " ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በእለቱ የብፁእነታቸው አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ (ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን) በሚንቀሳቀስበት ወቅት ፦

👉 ከመስቀል አደባባይ ፣ በብሔራዊ ቤተ መንግስት፣ ውጭ ጉዳይ ፣ አራት ኪሎ ፣ ቅድስት ማርያም የሚወስደው መንገድ፣

#መጋቢት_4 የብፁዕነታቸው የቀብር ስነ-ስርዓት የሚፈፀም በመሆኑ የቀብር ስነ-ስርዓቱ እስከሚፈፀም ወደ ቅድስት ማርያም ፣ አራት ኪሎ እና ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆነ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል።

ለታዳሚዎች ፦ ለጋራ ደህንነት ፍተሻ መኖሩን እንዲገነዘቡም ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል።

ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ መረጃ ተለዋውጥናል።

በየጊዜው የነበሩ እጅግ ዘግናኝ ከህግ ሆነ ከሞራልም ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ወደ ኃላ ተመልሰን ለመዘርዘር ጊዜውም አይበቃን ፤ በተለይም ከቲክቫህ ጋር ዓመታትን ያሳለፋችሁ የምታውቁት ነው።

ሌላው ይቅር በቅርብ ጊዜ እንኳን ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተነሳ በኃላ እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ቪድዮዎች ተሰራጭተው ስለጉዳዩ መረጃ መለዋወጣችን የቅርቡ ትውስታችን ነው።

ዛሬ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የተሰራጨው አሰቃቂ ቪድዮ በርካቶችን ያስደነገጠ ያሳዘነ ሆኗል። ቪድዮውን እዚህ አምጥቶ ማጋራት ትክክል እንዳልሆነ ታውቁታለቹ ፤ በጥቅሉ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የሰው ልጅ #በህይወት_እያለ በእሳት እንዲቃጠል ሲደረግ የሚያሳይ ነው።

ከቪድዮው ጋር በተያያዘ እነማን ? መቼ ? የት ? እና እንዴት ? ስለሚለው ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚል አካል በአስቸኳይ ወጥቶ ማብራሪያ መስጠት ይጠበቅበታል።

በተለይም ደግሞ በቪድዮው ላይ የፀጥታ ኃይሎችን የደንብ ልብስ ያደረጉ ሰዎች በግልፅ ስለሚታዩ ተቋማቱ ማብራሪያ መስጠት አለባቸው።

የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ጉዳዩን ሊከታተሉትና ለህዝብ ሊያሳውቁ ይገባል።

እንዲህ ያለው ነገር በቪድዮ አደባባይ ላይ ሲወጣ መነጋገሪያ ይሆናል እንጂ ያልተቀረፀው ፣ ህዝብ ያላወቀው ስንት ጉድ ይኖር ይሆን ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ በመስቀል አደባባይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን ሽኝት ይካሄዳል ፤ የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም ደግሞ መጋቢት 4 /2014 ዓ/ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል። ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፦ 👉 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ 👉
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሐግብር በአሁን ሰዓት መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶች ፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የውጪ አገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ፎቶ ፦ ENA / የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል። ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ…
#Update

በትላንቱ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ እንደ ሰው ልጅም አንገት አስደፊ ቪድዮ ላይ የተከሰተው ክስተት በተመለከተ የተገኘው መረጃ ፦

👉 ቀኑ ፦ በግልፅ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም።

👉 ክልል ፦ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

👉 ዞን ፦ መተከል ዞን

👉 ወረዳ ፦ ጉባ ወረዳ

👉 ቀበሌ ፦ አይሲድ ቀበሌ

👉 በእንደዛ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ፦ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም

👉 የድርጊቱ ተሳታፊዎች በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው ፦ አይታወቅም

👉 የተወሰደ እርምጃ በተመለከተ ፦ መንግስት አጣርቼ እርምጃ ወስዳለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በትላንቱ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ እንደ ሰው ልጅም አንገት አስደፊ ቪድዮ ላይ የተከሰተው ክስተት በተመለከተ የተገኘው መረጃ ፦ 👉 ቀኑ ፦ በግልፅ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም። 👉 ክልል ፦ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 👉 ዞን ፦ መተከል ዞን 👉 ወረዳ ፦ ጉባ ወረዳ 👉 ቀበሌ ፦ አይሲድ ቀበሌ 👉 በእንደዛ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ፦ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም…
" አጣርቼ እምርጃ ወስዳለሁ " - መንግስት

ትላንትና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨውን አሰቃቂ ቪድዮ (የሰው ልጅ በህይወት እያለ ሲቃጠል የሚያሳይ) በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ አውጥቷል።

መንግስት ድርጊቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ሰሞኑን መፈፀሙን ገልጿል።

ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂ ፣ ጭካኔ የተሞላበት እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት ነው ያለው መንግስት መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን አጣርቼ ህጋዊ እርምጃ ወስዳለሁ ብሏል።
 
" ድርጊቱ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ፣ እሴት እና ከማንኛውም የሰብዓዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው " ያለው መንግስት " ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትህን እውን ሊያደርግ አይችልም " ብሏል።

መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነት ለመቆጣጠር እና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከክልሉ እና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር እየተሰራ ይገኛል ብሏል።
 
" የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን ከዚህ በኋላ አልታገስም " ያለው መንግስት " በወንጀል ስራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስባለሁኝ " ብሏል።

@tikvahethiopia