TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.1K photos
1.4K videos
202 files
3.8K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia ሳፋሪኮም - ኢትዮጵያ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሥራ እንደሚጀመር አሳውቋል። የድርጅቱ የቁጥጥር እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ከመንግስት ጋር ያላቸው ስምምነት እንደሚያሳየው ፍቃድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በዘጠኝ ወር ወደ ስራ መግባት እንደሚኖርባቸው ገልፀው ከመጪው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በይፋ የንግድ ሥራ ለመጀመር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። ኃላፊው ይህን…
#Update

' ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ' ትላንት በራሱ ቡድን የተተከለውን የመጀመሪያ የኔትዎርክ ጣቢያ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ለሥራ ዝግጁ ማድረጉን አሳውቆናል።

የመጀመሪያው ጣቢያ የተተከለው በአዲስ አበባ ነው።

ድርጅቱ ፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ለመግባት ፍቃድ ሲያገኝ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኔትወርክ ለመገንባት ቃል ገብቶ እንደነበር አስታውሷል።

በራሱ ቡድን የተተከለው የመጀመሪያ ጣቢያ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ለሥራ ዝግጁ መሆኑ የዚህ ማሳያ ነው ብሎታል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ይህን የመሰሉ ጣቢያዎች ደንበኞቹ ጋር ለመድረስ የሚያስችሉት የመጨረሻዎቹ ክፍሎች መሆናቸውን አስረድቷል።

የመጀመሪያው ጣቢያ በአዲስ አበባ የተተከለ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ይተከላሉ ብሏል።

ሳፋሪኮም አገልግሎቱን ለመጀመር በተዘጋጀበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ እውን የሚያደርግ ጥራት ያለው ኔትዎርክ የመገንባት ጥረቱን አፋጥኖ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ይህ ወር የሚያኮሩ ወሳኝ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ያለው ሳፋሪኮም ዋና መስሪያ ቤቱን የገባንበት፤ የተሳካ የመጀመሪያ ጥሪ ያደረገበት ፣ አሁን ደግሞ የራሱን የኔትዎርክ ጣቢያ የተከለበት መሆኑን አሳውቆናል።

በሂደቱ ለተመዘገበው ስኬት ያለእረፍት ሲሰሩ ለነበሩት ባልደረቦቹ እና አጋሮቹ እንዲሁም አስፈላጊውን ድጋፍ ለሚያሰርግለት የኢትዮጵያ መንግስት ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
Qnash.com

ከ150 ብር ጅምር የተለያዩ በቤቶ ሊኖሩ የሚገቡ ዕቃዎች! ጥራት፣ ቅናሽ፣ ዋስትና ያላቸው::

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ - t.me/qnashcom

🏬አድራሻ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3 ተኛ ፎቅ ቁጥር 329 ከሊፍት እንደወረዱ በግራ በኩል የፎቁ መጨረሻ ዞር እንዳሉ

ስልክ ፦ 0946966440/ 0905464599 / +251118639952
ከአቢሲንያ ባንክ ሁለት ቅርንጫፎች በሌላ ሰው የሂሳብ ቁጥር 30 ሺ ብር አጭበርብሮ እንደወሰደ የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጭሮ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የጭሮ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ግለሰቡ ገንዘቡን  አጨብርብሮ ከወሰደባቸው  መካከል 15 ሺህ ብር ከባንኩ ጭሮ ቅርንጫፍ ነው።

ግለሰቡ በዚህ ቅርንጫፍ የካቲት 10/2014 ዓ.ም የገንዘብ  ማውጫ ማዘዣ ላይ የራሱ አስመስሎ ገዛኸኝ ከተማ የሚለውን ስም በመጻፍ ለገንዘብ ከፋዩ በመስጠት ነው ያጨበረበረው ፡፡

በዚህም ገንዘቡን ከከፋዩ ከወሰደ  በኋላ   በፍጥነት ከእይታ ለመሰወር ቢሞክርም  መረጃው የደረሳቸው የባንኩ ጥበቃ ሰራተኛ ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ፓትሮልና ሚሊሻዎች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ ሳሳን ባንተ ነኝ ብሎ ራሱን ቢገልጽም  ትክክለኛ ማንነቱና አድራሻው  እየተጣራ ነው።

በተመሳሳይ ሰሞኑን በሂርና ከተማ ከሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ጡሎ ቅርንጫፍ 15 ሺህ ብር ያወጣ መሆኑ ተረጋግጧል።

በተደረገው ፍተሻ 7 የተለያዩ ሰዎች መታወቂያዎች ይዞ ተገኝቷል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ? ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ "የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት ጀመረ" የሚሉ በርካታ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። መንግስት በዚህ ጉዳይ በይፋ ያሳወቀው ነገር ባይኖርም ከዚህ ቀደም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት መቃረቡ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጩ ለነበሩት የግድቡ መረጃዎች ምንጫቸውን ለማወቅ ብናስስም ልንደርስበት…
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነገ እሁድ የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሁለት ስማቸው ያልተገለፀ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ በዛሬው ዕለት ዘግቧል።

ዛሬ አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን [ስማቸው ያልተገለፀ] " ነገ የግድቡ የመጀመሪያው የሃይል ማመንጫ ይሆናል" ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሌላ ሁለተኛ ከፍተኛ ባለስልጣን መረጃውን ማረጋገጣቸውን ገልጿል።

ሁለቱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ጉዳዩ በይፋ ስላልተገለፀ ነው ተብሏል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የገለፀ ሲሆን መቼ ? ለሚለው ግን መረጃ አልሰጠም ነበር።

ይኸው ጉዳይ ባለፉት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ነበር፤ ነገር ግን በመንግስት በኩል ይፋዊ መረጃ አልተሰጠም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አንደኛው ሁኒት [ ዩኒት 10 ] ኃይል ማመንጨት መጀመሩን የግድቡ ሰራተኞች ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። @tikvahethiopia
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ፦

"... ማመንጨት ተጀመረ እንጂ ፕሮጀክቱ ተጠናቀቀ ማለት አይደለም።

ፕሮጀክቱን ለመጠናቀቅ አሁን ብለው ሁኔታ ከሁለት ዓመት ተኩል እስከ ሶስት ዓመት ሊፈጅብን ይችላል።

ስለዚህ ህዝቡ ከመጀመሪያውም ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት ነው። ፋይናንስ ሚደረገው በመንግስትና በኢትዮጵያ ነው ስለዚህ ይሄን ተገንዝበን ፕሮጀክቱን እስከመጨረሻው ፋይናንስ ማድረግ አለብን።

የኢትዮጵያን እውነታ አሁን ተርባይኑን መቶ ነው ውሃ እየፈሰሰ ያለው ስለዚህ ኢትዮጵያ ከዚህ ውሃ ምንም የምትቀንሰው ነገር ስለሌለ ዓለምም ይህን እንዲረዳ እያንዳንዳችን ተረባርበን ለፕሮጀክቱ ዲፕሎማት ሆነን መንቀሳቀስ አለብን። "

@tikvahethiopia
#ITena

• በስትሮክ፣ በአደጋ፣ እና በሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለተፈጠረ አለመንቀሳቀስ (Paralysis)
• እድሜ በመግፋት ለሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደ አልዛይመርስ፤ ዲሜንሻ
• ከተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ለማገገም
• በሙሉ (Coma) ወይም በከፊል የንቃተ ህሊና መቀነስ ላላቸው ታካሚዎች እንክብካቤ
• ለካንሰር እና ተከታታይ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች

👉በ 0901222233 ይደውሉልን

Telegram FB IG LinkedIn Twitter 🌍

🏥 አድራሻችን ጀሞ ከ ጀሞ ሞል 200m ገባ ብሎ፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ፦ "... ማመንጨት ተጀመረ እንጂ ፕሮጀክቱ ተጠናቀቀ ማለት አይደለም። ፕሮጀክቱን ለመጠናቀቅ አሁን ብለው ሁኔታ ከሁለት ዓመት ተኩል እስከ ሶስት ዓመት ሊፈጅብን ይችላል። ስለዚህ ህዝቡ ከመጀመሪያውም ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት ነው። ፋይናንስ ሚደረገው በመንግስትና በኢትዮጵያ ነው ስለዚህ ይሄን ተገንዝበን ፕሮጀክቱን…
#የምስራች🎉

አባይ ኃይል መስጠት ጀመረ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል መስጠት ጀምሯል።

ግድቡ ዛሬ ኃይል ማመንጨት የጀመረው ካሉት 13 ተርባይኖች ውስጥ በአንዱ ተርባይን አማካኝነት ነው።

አንዱን ተርንባይን በመጠቀም ወደ ስራ የገባው ግድቡ 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደት ሲያደርግ የነበረ ሲሆን የሙከራ ሂደቱ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል መስጠት ጀምሯል።

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የግድቡን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ሂደቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ፎቶ ፦ አሚኮ & TK.SS

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች ጋር በመሆን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ተርባይን ኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ ስርዓት ላይ።

ፎቶ ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia