TIKVAH-ETHIOPIA
1.36M subscribers
54.2K photos
1.33K videos
185 files
3.57K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስገነባውን አዲስ ህንፃ የሚያስመርቅ መሆኑ ይታወቃል በዚህም መሰረት የምረቃ መርሀ ግብሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ፡-

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ ፍል ውሀ

• ከሳንጆሴፍ መብራት ወደ አራምቤ ሆቴል ወይም አምባሳደር

• ከለገሀር መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር

• ከሰንጋ ተራ ወደ ብሔራዊ ቴአትር

• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር

• ከሜትሪዮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት

• ከሀገር አስተዳደር ወይም ከኢሚግሬሽን ወደ ብሔራዊ ቴአትር

• ከሸራተን ሆቴል ወደ አምባሳደር

• ከንግድ ማተሚያ ወደ ፍልውሀ የሚወስዱ መንገዶች ከጠዋቱ 2፡00 ሠዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይደረጋሉ።

በፍል ውሀ ወይም በምረቃው ስነ ስርዓት በሚካሄድበት 360 ዲግሪ ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#Amhara , #Woldia 📍

" የጥሩ ባህላዊ ሕግ፥ ሥርዓት ባለቤት ነን ብለን የምንናገርበት የሞራል አቅም እያጣነ ነው " - የውይይት ተሳታፊዎች

PDN (Partners In sustainable Development) የተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከUSAID Prmoting the Experience in peacful Coexistence of Diverse Communities in Wollo, Amhara Region ፕሮጀክትና ከባህል ቱሪዝም ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው በባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት ላይ ያተኮረ ውይይት በወልዲያ ተካሄደ።

የሃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእድር መሪዎች እና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ነበር።

የወልዲያ ኮሚኒኬሽን ባወጣው ዘገባ ተሳታፊዎቹ " እንደ ወሎየነት ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊነት ከመቻቻል ፣ ከአብሮነት ፣ ከእውነታነት ፣ ከአድሏዊነት የጸዳ በአበጋሮች፣ በሼሆች፣ በቀሳውስቶች፣ በሀገር ሽማግሌዎች፣ በእድሮች፣ በለገገዲ፣ በመሳል፣ በሼህ ለጋ፣ በዘወልድ፣ የሚከናወኑ ትክክለኛ ባህላዊ የዳኝነት (ፍርድ) እና የግጭት አፈታት ባህላዊ ስርዓት ብሎም እስከ አባ ገዳ ፣ አውራምባ እና ሌሎች ባህላዊ የመልካም የአስተዳደር ስርዓት ሲዳሰስ የድንቅ ባህል ፣ ትውፊት ፣ ወግ፣ እሴት፣ ስርዓት ባለቤት መሆናችንን ባንክድም አሁን ላይ እያፈርን ነው " ብለዋል።

አክለውም በእውነት እና ሚዛናዊነት ቦታ ሀሰትና አድሏዊነት እየነገሠ፤ በመቻቻልና አብሮነት ፈንታ መለያዬት እየገነነ፤ በጥሩ ባህላዊ እሴት አካባቢና ሀገር መፈናቀልና መገዳደል እየሰፈነ፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን የገነቡት ቅርስ በቱሪዝም ሀብት የሚሰጠው ጥቅም ተዘንግቶ ቤተ-እምነትን እየፈረሰ ፣ የእምነት አባቶች እየተገደሉ፣ ህጻናትንና ሴት ለሞትና ስቃይ እየተዳረጉ ነው ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሀገር በቀል ሽማግሌ ተንቆ በባህላችን፣ በወጋችን፣ በእምነታችን፣ ቋንቋችን፣ የማይመስለን "ገልጋይ መስሎ ገፍታሪ" ካላስታረቀን ብሎ የሚባዝን የራሳችን ወገን እየተገዳደረን ፤ ይን እና ይህንን የመሰለው ተዳምሮ የጥሩ ባህላዊ ሕግ፣ እሴት ባለቤት ነን ብለን የምንናገርበት የሞራል አቅም እያሳጠን ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Amhara-Woldia-02-13

@tikvahethiopia
#አሁን

በአሁን ሰዓት በቤንች ሸኮ ዞን የሠላምና ፀጥታ ኮማንድ ፖስት ወይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ በዞኑ የተገኘውን አንፃራዊ ሠላም በማጠናከር ዘላቂ ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመከርበታል ተብሏል።

ከቤንች ሸኮ ዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮው ባገኘነው መረጃ በውይይቱ የሸኮ ፣ የጉራፈርዳ ፣ የደቡብ ቤንችና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አመራሮችና የሚመለከታቸው የፀጥታ ዘርፍ አካላት ተገኝተዋል።

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ ከሰሞኑ የሚታየው የነዳጅ ሰልፍ ምክንያቱ ምንድነው ?

በአዲስ አበባ የመኪና አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሳቢያ (ቤንዚን በተለይ) ረጅም ጊዜያቸውን በሰልፍ እያሳለፉ፣ የስራ ሰዓታቸውም እየተስተጓጎለ ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን እየገለፁ ይገኛሉ።

በበርካታ የነዳጅ ማደያ ቦታዎች ሰልፍ በመኖሩ ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት መቸገራቸው እና ረጅም ሰዓት ነዳጅ ለመቅዳት ተሰልፈው ለማሳለፍ እየተገደዱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከሰሞኑን በከተማው ውስጥ እየታየ ያለውን የነዳጅ እጥረት በተመለከተ ቃላቸውን ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት አቶ ታደሰ ኃይለማርያም (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ) ተከታዩን ብለዋል ፦

" የነዳጅ ሰልፉ ለእኛም ግልፅ አይደለም።

ብዙ ጊዜ ችግር የሚፈጥረው ቤንዚን ነው። የቤንዚን ጭነትን ብንመለከት ይሄ ነገር አዲስ አበባ ውስጥ በጣም ጎላ ብሎ የታየው ከጥር 23 ጀምሮ ነው።

ስለዚህ ከጥር 1 እስከ 23 ድረስ ባለው የተነሳው የነዳጅ መጠን ከጅቡቲ ኖርማል ነው። ታህሳስ ውስጥ የነበረው አማካይ እና ህዳር ውስጥ የነበረው አናካይ አሁን በዛን ወቅት ከተነሳው ምንም ልዩነት የለውም።

ለዚህ ነው በአቅርቦት ላይ ችግር የለም የምንለው፤ በመረጃ ተንተርሰን ከዛ በሚጫነው የጭነት መጠን መሰረት ነው።

... በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ ማለትም መርከብ ሊዘገይ ይችላል አንዳንድ እዛ በጭነት አካባቢ የሆነ ወጣ ገባ የሚል ነገር ካለ ያ አንድ ሶስት አራት ቀን ያን ፊክስ ለማድረግ የሚቆይ ስራ እና በስርጭቱ ላይ ችግር የሚፈጥር ከሆነ መንግስትን አስፈቅደን ከመጠባበቂያ እናወጣለን። ከዛ ያንን አውቶማቲካሊ ችግሩ ሲፈታ ተክተትን በዛ መልክ ነው የምንሰራው።

አሁን ይሄ እጥረት የተፈጠረው ለምን እንደሆነ ለማወቅም አልተቻለም።

... ሰልፎች አሉ ግን ያጠረ ነው። ከአራት እና ከአምስት ቀን በኃላ ወደ ኖርማል ሊመለስ ይችላል። ግን ትልቁ ችግር ለምን ይሄ ተፈጠረ ለሚለው መታየት አለበት። የዚህ ችግር ዋናው ምክንያት ምንድነው የሚለው ካልታየ ልክ በደረሰ ቁጥር ይሄ ነገር ጩኸት እየሆነ መቀጠል የለበትም። ማ ጋር ነው ? እኛ ጋር የቀርቦት ችግር ነበር የሚለውን ካለ መወቀስ እና እርምጃ መወሰድ አለበት፤ ሌላው አካል ጋርም ከሆነ በተመሳሳይ። ይሄ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ብቻ ችግሩን እያነሳን የምንሄድበት አካሄድ እኔ ጥሩ አይስመለኝም። "

@tikvahethiopia
በግንባት እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ምንድነው ?

በግንባታ ግብዓቶች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ነጋዴዎች እየገለጹ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በተለይ በቤት ክዳን ቆርቆሮ እና በሚስማር ምርቶች ላይ በ2 ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።

ለጋዜጣው ቃል የሰጡ ነጋዴዎች ፥ በቆርቆሮ ምርት ላይ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ መታየቱን ገልፀዋል በአንድ ሳምንት ውስጥ ከነበረበት 250 ብር ወደ 400 ብር ከፍ ማለቱን አስረድተዋል።

ከዚህ በፊት 500 ብር የነበረው ጋልቫናይዝድ የቤት ክዳን ቆርቆሮ በአሁኑ ወቅት ከ1,000 ብር በላይ እየተሸጠ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

በሚስማር ዋጋ ላይ በካርቶን እስከ ከ200 ብር በላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። 4 መቶ ብር የነበረው የአንድ ካርቶን ሚስማር ዋጋ በ2 ሳምንታት ውስጥ 6 መቶ ብር መድረሱን ይገልጻል፡፡ በየቀኑም የዋጋ ጭማሪ እያሳየ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

እንደ ቱቦላሬ እና አርማታ ብረት ያሉ የግንባታ ምርቶች ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየታቸውን ተገልጿል።

ከፍተኛ እጥረት እንዳለበት የሚታይበት የሲሚንቶ ምርትም በየጊዜው ጭማሪ እያሳየ ነው፡፡

ቃላቸውን ለጋዜጣው የሰጡ ነጋዴዎች የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ እስከ 720 ብር መድረሱንና በአንድ ወር ውስጥም ከ40 በመቶ በላይ ጭማሪ ማሳየቱን ገልፀዋል።

በምርቶቹ ላይ ያለው ዋጋ እንደ ሌሎች መጠነኛ ጭማሪ እየታየ የመጣ ቢሆንም፣ ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ ያለው የዋጋ ጭማሪ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የጭማሪው ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ እንዳልቻሉ ነጋዴዎቹ ለጋዜጣው ተናግረዋል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#Amhara , #Woldia📍

በወልዲያ ከተማ ዳርቻ የተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰማው የተኩስ ድምፅ " #በወታደራዊ_ስልጠና_የዒላማ_ልምምድ " ምክንያት መሆኑን የከተማው የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ያስገነባው ግዙፍ ህንፃ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ነው የሚመረቀው።

ትላንት የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳሳወቀው ከሆነ የምረቃ መርሀ ግብሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፡-

▪️ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ ፍል ውሀ
▪️ከሳንጆሴፍ መብራት ወደ አራምቤ ሆቴል ወይም አምባሳደር
ከለገሀር መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር
▪️ከሰንጋ ተራ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
▪️ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
▪️ከሜትሪዮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት
▪️ ከሀገር አስተዳደር ወይም ከኢሚግሬሽን ወደ ብሔራዊ ቴአትር
▪️ከሸራተን ሆቴል ወደ አምባሳደር
▪️ከንግድ ማተሚያ ወደ ፍልውሀ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ሌላው በፍል ውሀ ወይም በምረቃው ስነ ስርዓት በሚካሄድበት 360 ዲግሪ ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድም ተከልኳል።

ይህ መልዕክት የደረሳችሁ የቤተሰባችን አባላት የጉዞ መሥመራችሁን እንድታስተካክሉ እናስታውሳችኃለን።

Photo Credit : Isaac Abrham

@tikvahethiopia
#ጭሮ

የ ' አጥንት ካንሰር ታማሚ ' በመምሰል በተሽከርካሪ ላይ እየተዘዋወረች ስትለምን የነበረችውን ወጣት ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጭሮ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ወጣቷ ከሰባት (7) ግብረ አበሮቿ ጋር የአጥንት ካንሰር ታማሚ መስላ በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረች  ስትለምን መቆየቷን በምርመራ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።

የጭሮ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ምርመራ ወጣቷ ግብረ አበሮቿ ጋር በሀሰት የህክምና ማስረጃ የእርዳታ ጥሪ እያሉ ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩ እንደነበረ ያሳያል።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ  በተከራዩት መኝታ ቤት ውስጥ 24 ሺህ 260 ብር በመቁጠር ላይ እንዳሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

የአጥንት ካንሰር ታማሚ መስላ በመተወን ህብረተሰቡን በማጭበርበር ገንዘብ ትለምን የነበረችው ወጣት ከነግብረ አበሮቿ በህግ ቁጥጥር ስር ውላለች።

ወጧቷ ለፖሊስ በሰጠችው ቃል ፦ በጭሮ ከተማ ላለፉት 15 ቀናት በፎቶግራፏና የካንሰር ታማሚ መሆኗን በሚገልፅ ጽሁፍ በያዘ ባነር በተሸፈነ ሚኒባስ መኪና እየተዘዋወረች ስትለምን መቆየቷን ገልፃለች።

ወጣቷ 1 ሺህ 500 ብር በቀን እየከፈለቻት ታማሚ መስላ እንድትለምን በቀጠረቻት ሴት ምክር ተታላ የማጭበርበር ድርጊቱን  እንደጀመረች ለፖሊስ አስረድታለች።

የማጭበርበር ድርጊቱን መናገርና መንቀሳቀስ እንደማትችል ሆና በሰዎች ተደግፋ ህዝብን በሀዘኔታ ሰዎችን እያራራች ትፈጽም እንደነበር እንዲሁም የሰበሰበችውን በርካታ ገንዘብ ለቀጠረቻት ግለሰብ ትሰጥ እንደረነበር ገልጻለች።

የቀጠረቻት ግለሰብ የተመደበላት ገንዘብ 1 ሺህ 500 ብር ብቻ እየተሰጠቻት ትነግድባት እንደነበር አስረድታለች።

የድርጊቱ አቀነባባሪና የሀሰት የህክምና ማስረጃውን አስይዛ መለመኛ ያደረገቻት ወጣት ደግሞ በአዲስ አበባ አውቶቡስ ተራ አካባቢ ሻይ ቡና በመስራት ትተዳደር የነበረች መሆኗንም አመላክታለች።

ወጣቷ ለፖሊስ በሰጠችው የእምነት ቃል በመስተንግዶ ስራ ላይ ተሰማርታ ከነበረችና አሁን ግብረ አበሯ ከሆነች ጓደኛዋ ጋር በመመካከር በአቋራጭ ለመክበር አስባ ድርጊቱን እንደጀመረችው ትናገራለች።

የህክምና ማስረጃው በቅርቡ በአጥንት ካንሰር በሽታ የሞቱት እናቷ መሆኑን ተናግራ መነሻቸው ከአዲስ አበባ መሆኑንና ከአራት ወራት በፊት በስምምነት ስራውን እንደጀመሩት አስረድታለች።

የማጭበርበር ድርጊቱን ጭሮን ጨምሮ
- በጅማ፣
- በቢሾፍቱ፣
- በአዳማ፣
- በሀረር፣
- በድሬደዋ፣
- በበዴሳ፣
- በመተሃራ፣
- በወልቂጤና ሌሎች ከተሞች እየተዘዋወረች ስትፈጽም መቆየቷን ተናግራለች።

ወጣቷ የማጭበርበር ድርጊቱን ከፈጸመችባቸው የከተሞች አስተዳደሮች ፈቃድ ያገኘች የሚያስመስል ሀሰተኛ ደብዳቤ በመያዝ እንደሆነ አስረድታለች ፡፡

ወጣቷ ለሰባቱ ግብረ አበሮቿ በቀን ለእያንዳንዳቸው 1 ሺህ 500 ብር ትከፍል እንደነበርና ለተከራየችው ሚኒባስ መኪና ደግሞ በተመሳሳይ 5 ሺህ ብር ወደ አዲስ አበባ እንደምትልክ በሰጠችው የእምነት ቃል ማረጋገጧን ፖሊስ ለኢዜአ ገልጿል።

@tikvahethiopia
መረጃ ስለ ግዝፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ፦

- የህንፃው መሰረት ድንጋይ የተቀመጠው በሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ/ም በወቅቱ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን በነበሩት በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር አማካሪ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በረከት ስምኦን ነው።

- ግንባታውን ለማካሄድ ረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገ ሲሆን ቦታውን ለማግኘት እራሱን የቻለ ጊዜ ወስዷል ፤ 18,308 ሜትር ስኩዌር መሬት ለህንፃው ከተሰጠ በኃላ በርካቶች የተሳተፉበት የዲዛይን ውድድር ተካሂዶ አሁን ያለው ተመራጭ ሊሆን ችሏል።

- የህንፃውን ዲዛይ እና ግንባታ ተቋም ለመለየት 7 ዓመታት ወስዷል።

- ህንፃው እጅግ ዘመናዊ የሆነ እና በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ያልተለመደ አሰራርን አካቶ ነው የተሰራው።

- የህንፃው ግንባታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (AAiT) ተቆጣጣሪነት በቻይና መንግስት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካኝነት ነው የተካሄደው።

- 4 የምድር ውስጥ እና 49 ከምድር በላይ በድምሩ ባለ 53 ወለል ከፍታ ያለው ርዝመቱ 209.15 ሜትር የሆነ ታወር ሲሆን ሁለት ባለ 11 እና ባለ 13 ወለሎች ግዙፍ ህንፃዎችን አካቷል። በድምሩ ከ165 ሺህ ካሬሜትር በላይ ስፋት ላይ የተገነባ ነው።

- ባለ 11 ወለሉ ህንፃ ለኮንፈረንስ ነው፤ በአንድ ጊዜ 2500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሽ ፣ 300 ሰዎችን የሚይዙ እና 200 ሰዎች የሚይዙ 5 መለስተኛ የስብሰባ አዳራሾች አሉት (ሁሉም እርስ በእርሳቸው መገናኘት ይችላሉ) ፤ የሰራተኞች መመገቢያ እንዲሁም የባንክ ቅርንጫፍ አሉት።

- ባለ13 ወለሉ ህንፃ ለንግድ ስራ ማዕከልነት የሚያገለግል ነው። 5 ክፍሎች ያሉት እጅግ ዘመናዊ የሲኒማ አዳራሽ ፣ የንግድ ማዕከላት፣ ጂምናዚየም ፣ የውበት መጠበቂያ ስፓ፣ የልጆች መዝናኛ ማዕከል ጌም ዞን ፣ ሬስቶራንቶች ፣ ፉድ ኮርት አካቷል።

- የዋናው ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቋሚ የአውደርእይ ማሳያ ነው፣ ከ2ኛ እስከ 46ኛ ፎቅ የባንኩ የዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ቢሮ ይይዛል። 47ኛ እና 48ኛ ፎቆች የካፍቴሪያ እና የመዝናኛ ቦታዎች ናቸው።

- 24 አሳንሰሮች፣ 26 ስኬሌተሮች አሉት። 4ቱ የምድር ውስጥ ወለሎች 1500 መኪና መያዝ የሚችል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ መካኒካል ፓርኪንግ ጨምሮ የያዘ ፣ ሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎት የያዙ ክፍሎች የያዘ ነው።

- ሙሉ ህንፃው ዘመናዊ የእሳት መከላከያ እና የ CCTV ካሜራዎች ፣የሚዲያ ፋሲሊቲ፣ በረጅሙ ህንፃ 3 የአደጋ ጊዜ መቆያ ሪፊውጂ ወለሎች አሉት። ዘመናዊ የደህንነት መጠበቂያ ሲስተም የተገነቡለት ነው።

- ውሃ እና መብራት በቁጠባ ለመጠቀም IBM የተሰኘ ልዩ ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።

- ህንፃው በአዲስ አበባ ረጅሙ ህንፃ በምስራቅ አፍሪካ እና በመላው አፍሪካ ሰማይ ጠቀስ ህፃዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።

- ግንባታው 303.5 ሚሊዮን ዶላር ፈጅቷል።

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ/ም በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቋል።

@tikvahethiopia
#ሀሰት_ነው !

" ከሱዳን ጋር #በቅርቡ በድንበር ጉዳይ የተደረሰ ስምምነት የለም " - በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ሰሞኑን አንዳንድ ሚዲያዎች በሱዳን የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በመጥቀስ የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር በተመለከተ ስምምነት እንደተደረሰ ሲዘግቡ ተስተውሏል።

በተለይ Alsharq AL-awsat English ጋዜጣ በድህረ ገፁ “Addis Ababa, Khartoum Reach Deal on Border Dispute” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ፌብርዋሪ 13 ቀን 2022 ያስነበበው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ጋዜጣው የመረጃውን ምንጭ ሳይጠቅስ ያቀረበው ሲሆን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከዚህ ጋዜጣ ጋር ግንኙነት እንዳላደረጉ እና መረጃ እንዳልሰጡ ኤምባሲው ገልጿል።

@tikvahethiopia
#GamoZone , #Arbaminch📍

" ጋሞ ወጋ ክፍል አንድ የጋሞ ሕዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የሠላም ግንባታ ሥርዓት " በሚል ርዕስ በአቶ ዘነበ በየነ የተዘጋጀ መጽሐፍ ተመረቀ።

የመጽሐፉ አዘጋጅ አቶ ዘነበ በየነ መጽሐፉ ከተዘጋጀ ከ7 ዓመታት በኋላ ለሕትመት መብቃቱን ተናግረዋል።

8 ምዕራፎች ያሉት ባለ 105 ገጽ መጽሐፍ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ፦ የጋሞ ሕዝብ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ፣ የጋሞ ሕዝብ ታሪካዊ አመጣጥ እና አሰፋፈር ፣ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓት ፣ ዘመናዊና ባህላዊ የግጭት አፈታት ፣ ግጭትን በመፍታት ወደ በጎ መለወጥ ፣ ሀገረሰባዊ የእርቅና የሽምግልና ዕውቀቶች ፣ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የሠላም ግንባታ ተግዳሮቶች የያዘ መሆኑን አቶ ዘነበ አብራርተዋል።

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን ፣ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የመጽሐፉ ደራሲ አቶ ዘነበ በየነ ከዚህ በፊት " የጋሞኛ ምሳሌያዊ ንግግሮች እና ሌሎች ስነ ቃሎች በሚል መጽሐፍ አሳትመው ነበር ከጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #USA

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ዛሬ እና ነገ በኢትዮጵየ፣ አዲስ አበባ ቆይታ እንደሚኖራቸው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት መረጃ ያሳያል።

ልዩ መልዕክተኛ ሳተርፊልድ ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት እንዲሁም ከሰብአዊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ።

አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት #ሰላማዊ መቋጫ እንዲያገኝ ጥረት እያደረገች መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#Gambella , #Akobo📍

" የኔትወርክና የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት አዳጋች ሆኗል " - አቶ ኮንግ ጋትዮቴ

በጋምቤላ ክልል በአኮቦ ወረዳ ከደቡብ ሱዳን በሚነሱ የሙርሌ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው ህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የወረዳዉ አስተዳደር አስታውቋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኮንግ ጋትዮቴ እንዳሉት ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙሩሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተለያዩ ጊዜያት ድንበር አቋርጠዉ በመግባት ጥቃት ሲፈፅሙ ቆይተዋል ብለዋል።

ታጣቂ ቡድኑ በሰዉ ህይወት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ ህፃናትንና የቁም እንስሳትን ሲዘርፉ እንደነበር ጠቅሰዉ በአሁኑ ወቅት ከክልሉ የጠጥታ አካላት ጋር በመቀኛጀትና የስጋት ቀጠናዎችን በመለየት መሰል ጥቃት እንዳይፈፀም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳዉ የኔትወርክና የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት አዳጋች እንደሆነባቸዉ ገልፀዉ መንግስት እነዚህ መሠረተ ልማቶች ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት በጥቃቱ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ከ2,500 በላይ ወገኖች በ2 ሚሊዮን ብር 600 ኩንታል በቆሎ በመግዛት ድጋፍ ማድረግ መቻሉን የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ መግለፁን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፦

" በሱማሌ ክልል በድርቅ ለተፈቀሉት በርካታ ወገኖቻችን ውሃ በአስቸኳይ ይደርስ ዘንድ ለአንድ ወር በቀን 5 ቦቴ ድጋፍ ጀምረናል።

በቀብሪ በያ ያየኽቸው ሁሉ በተለይም ሴቶች ጥያቄ አንድ ብቻ ነበር 'ውሃ' ፤ ለዘላቂ ጉድጏድ ቁፋሮም ከክልሉ ጋር እንተባበራለን። "

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TurkiyeScholarships

የቱርክ መንግስት ለቅድመ እና ድኅረ ምሩቃን የ2022 ነፃ የትምህርት ዕድል ክፍት አድርጎ አመልካቾችን እየተቀበለ ነው።

ነፃ የትምህርት ዕድሉ ለመጀመሪያ፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና የምርምር ዲግሪ ፕሮግራሞች ለሚያመለክቱ የሚሰጥ ነው።

የዕድሉ ተጠቃሚ ተማሪዎች ወጪያቸው በቱርክ መንግስት የሚደገፍ ነው።

ከጥር 12 ቀን 2014 ዓ/ም የጀመረው የማመልከቻ ጊዜው የፊታችን የካቲት 13/2014 ዓ.ም ያበቃል።

ለማመልከት ይህን https://turkiyeburslari.gov.tr/ ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

More : @tikvahuniversity