TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Wenchi : ወንጪ ሐይቅ ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ ተመረጠ። በስፔን ማድሪድ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በ24 ኛው የአለም የቱሪዝም ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ወንጪ ሐይቅ የ2021 ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ ተመረጠ። በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ የሚገኘው ወንጪ ሐይቅ ከ170 የቱሪዝም መንደሮች መካከል ቀዳሚ ሆኖ መመረጡ በጉባኤው ላይ ይፋ ተደርጓል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት…
#Ethiopia | #Wenchi

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ፥ ወንጪ ሐይቅ በአለም የቱሪዝም ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ በመመረጡ ' እንኳን ደስ ያለን ! ' ብለዋል።

ድንቅ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት የሆነው የወንጪ ሃይቅ ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ የተመረጠው ባለው ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብት መሆኑን ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ ፥ የአካባቢውን የተፈጥሮ ጸጋ ተንከባክበው ለዚህ እንዲበቃ ላስቻሉት የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
" አቋማችን ግልፅ ነው፤ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት ነው " - ዶ/ር ኢሴ ኬይድ

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ኢሴ ኬይድ ለቢቢሲ ሶማሌኛ አገልግሎት ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል።

በዚህ ቃለ መጠይቅ ሶማሌላንድ በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት በሱማሊላንድ በኩል ያለው አቋም ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን አብራርተዋል።

ዶክተር ኢሴ ኬይድ ኢትዮጵያን " የሶማሌላንድ ታሪካዊ ወዳጅና ወንድም ሀገር " ሲሉ ገልፀዋል።

ሁልጊዜም ለኢትዮጵያ ብልጽግናን እንመኛለን ያሉ ሲሆን ሁሉንም ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶች እንደግፋለን ብለዋል።

" ነገር ግን በቅርብ ጊዜ ሁኔታዎች ላይ ያለን አቋም ግልጽ ነው " ያሉት ዶ/ር ኤሴ ኬይድ ይህም " በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

Source : Horn Diplomat

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በቁጥጥር ስር መዋሏን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " የጋሸናን ግንባር ምሽጎችን በመሰባበር የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ…
#Update

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በ3ኛው ግንባር ዶጎሎ ሆነው በቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ዛሬ እና ነገ በሚሰሩ ኦፕሬሽኖች ከሚሴን ፣ ባቲን፣ ኮምቦልቻን እና ሌሎችም ከተሞች እንቆጣጠራለን ብለዋል።

በተጨማሪም ፥ ኦፕሬሽኑ ወደ ደሴ የሚቃረብበትን አቅጣጫ እንደሚይዝም ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

" አብዛኛው ከተሞች በዛሬ እና ነገ ኦፕሬሽኖች ይፀዳሉ " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፥ " ጠላት ፈርሷል፣ ተሸንፏል፣ አሁን የተበተነውን ኃይል መሰብሰብ ፣ የሰረቀውን ማስቀረት፣ ትጥቅ ማስቀረት፣ ተደራጅቶ እንዳይወጣ የማድረግ ስራዎች ናቸው የሚቀሩን ለዚህ ስራ የህዝቡ ሚና ክፍተኛ ነው " ብለዋል።

" ህዝቡ በተበተነ መንገድ የሚንቀሳቀሰውን ጠላት እየለቀመ ትጥቅ ማስፈታት አለበት ፤ ሚሊሻው ፣ ልዩ ኃይሉ በየሸጡ የሚጓዘውን የጠላት ኃይል እየለየ ትጥቅ እያስፈታ ማስቀረት አለበት " ሲሉ ነው የገለፁት።

" ህዝቡ የጠላት ኃይል ትጥቅና የሰረቀው የሚስረክብ ከሆነ አብዛኛው ጨቅላ ህፃናት ስለሆኑ እንዳይጎዱ በትክክል ይዞ፣ መግቦ ተንከባክቦ እንዲያቆይ፤ ምርኮኛ ማቆየት የጀግና ባህል ነው ፣የኢትዮጵያዊነት ባህል ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በተሰራ ኦፕሬሽን በምስራቅ እና ምዕራብ ግንባር ጋሸናን ጨምሮ አስፈላጊ ቦታዎች መያዛቸውን አስታውሰው ወደ ሰቆጣና ወልዲያ የማስፋት ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#Update

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሸዋሮቢት ከተማ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት መመለሱን ዛሬ አሳውቋል።

በተጨማሪ በደብረሲና አካባቢ ያሉ አርማንያ፣ አስፋቸውና ጭራ ሜዳ የተባሉ የገጠር ከተሞች ዛሬ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ የተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

ደብረሲናና ሌሎች ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማደረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ ከህወሓት እጅ ነፃ የሆኑ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል ቡድን አቋቁሞ እየሰራ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት ! አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል የግድያ ቦታ አመቻችታለች ተብላ የተከሰሰችው ላምሮት ከማል በተሻሻለው አንቀጽ በ5 ሺህ ብር ዋስትና እንድትወጣ ታዘዘ። የዋስትና ትዛዙን የሰጠው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ 113 ንዑስ ቁጥር 2 መሰረት የጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተከሰሰችበት…
ችሎት !

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል ቦታ አመቻችታለች ተብላ በሽብር ወንጀል የተከሰሰችውን እና የክሱ አንቀጽ ተቀይሮ በዋስ የተፈታችው ላምሮት ከማል የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በአቃቢህግ ማስረጃ ይፈረድብኝ ስትል ፍርድ ቤቱን መጠየቋ ተሰምቷል።

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተከሰሰችበት የሽብር ወንጀል ተቀይሮ አደጋ ላይ ያለ ሰውን በቸልተኝነት ያለመርዳት የወንጀል ህግ አንቀጽ 575 እንድትከታተል መወሰኑ ይታወሳል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከ2 ሳምንት በፊት በነበረ ቀጠሮ እንድትከላከል በተቀየረው አንቀጽ ዋስትና አያስከለክልም ሲል በ5 ሺህ ብር ዋስ አስይዛ ከስር እንድትፈታ ወስኖ ነበር።

በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ/ም የመከላከያ ማስረጃ እንድታቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በዛሬው ቀጠሮ ተከሳሿ ከእስር ተፈታ በጽ/ቤት ቀርባ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌላት እና ዐቃቤ ህግ ባሰማው ማስረጃ ይፈረድብኝ ስትል ፍርድ ቤቱን ጠይቃለች።

ፍርድ ቤቱም ፍርድ ለመስጠት ለህዳር 29 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የትምህርት ሚኒስቴር ለተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል የትምህርት ጽ/ቤቶች ጋር በመወያየት ውሳኔ በተሰጠባቸው ሀሳቦች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሀገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ የሁሉንም ዜጋ ኀላፊነት እና ትብበር የምትፈልግበት በመሆኑ ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ተግባር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች በጦርነቱ የዘማች አርሶ አደሮችን የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ቤተሰቦችን በመርዳት ትብብር እንዲያደርጉ ወስኗል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ " ለዘመቱ አካላት የሚሆን የስንቅና የደም ልገሳ በማድረግ የዜግነት ግዴታን የምንወጣበት ጊዜ ነው " ያሉ ሲሆን " ተማሪዎች ትምህርት በሚቋረጥበት ጊዜ ከትምህርታቸው ሳይዘናጉ የወገን ጦርን የሚረዱበትና የሀገር ፍቅራቸውን የሚያሳዩበት ይሆናል " ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የትምህርት ሚኒስቴር ለተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል የትምህርት ጽ/ቤቶች ጋር በመወያየት ውሳኔ በተሰጠባቸው ሀሳቦች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ሀገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ የሁሉንም ዜጋ ኀላፊነት እና ትብበር የምትፈልግበት በመሆኑ ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ተግባር ለተወሰነ…
ትምህርት ሚኒስቴር ፦

በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ።

ዝግ የሚሆኑት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ነው።

#ምክንያት ፦ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው። ት/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት ይካሄዳል።

NB : ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናቶች በሙሉ ትምህርት ቤቶች በሚያወጡት የማካካሻ መርሀ ግብር መሰረት እንዲካካስ ይደረጋል።

መረጃውን ከትምህርት ሚኒስቴር ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#LieutenantGeneralBachaDebele 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ለቢቢሲ ቃለምልልስ ሰጥተዋል።

ቃለምልልሱ በወቅታዊ የጦርነቱ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ህወሓት ባደራጀው ሰራዊት አዲስ አበባ ገብቶ ኢትዮጵያን እበትናለሁ በሚል ሂሳብ እስከ ሰሜን ሸዋ የተወሰኑ አካባቢዎች ድረስ ገብቶ እንደነበር ገልፀዋል።

" በመከላከል ማዳከም ከዚያም በማጥቃት ለመደምሰስ በሚለው መርህ መሰረት። ይህንን ኃይል ለተከታታይ አንድ ወር መከላከል አድርገናል። ለማጥቃት የሚያስችለንን ተገቢ ዝግጅት በመከላከል ውስጥ ሆነን አድርገናል። ሰሞኑን የማጥቃት እርምጃ ወስደናል " ብለዋል።

በተወሰደው የማጥቃት እርምጃ ሰሜን ሸዋ የነበረውን የጠላት ኃይል አባረናል ፤ በጋሸና፣ በደቡብ ወሎ፣ በወረ ኢሉ እንዲሁም በምሥራቅ ከጭፍራ አልፈን በዋናው መስመር በባቲ በኩል የነበረውም እንደዚሁ አባረናል ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ አርብ ባቲም፣ ደሴም ኮምቦልቻም አንድ ላይ ይያዛሉ የሚል ግምት እንዳለ የተናገሩት ሌ/ጄነራሉ አሳውቀዋል።

እየታየ ያለው ውጤት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ግንባር ከመሄዳቸውም ጋር እንደሚያያዝ እና የጠ/ሚኒስትሩ ወደዚያ መሄድ የሠራዊቱን የመስራት አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደጨመረው ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከትላንት በስቲያ #ህወሓት በአማራ ክልል ተይዘው ከነበሩ ቦታዎች በታክቲካዊ ውሳኔ ሠራዊቱ ለቆ መውጣቱን ስለገለፀበት መግለጫ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ፥ "ምን እንዲሉ ነው የሚጠበቀው ? በአቅማቸው በጉልበታቸው አይደለም እዚህ የደረሱት። በላኳቸው ሰዎች ጉልበትና አቅም ነው እዚህ የደረሱት። ስለዚህ ጌቶቻቸው ለማስደሰት ምን ይበሉ ? " ብለዋል።

አክለውም ፥ " እነሱ እኮ አዲስ አበባ ለመግባት በቀናት ሳይሆን ሰዓታት ነበር ሲቆጥሩ የነበሩት። አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን እኮ አዲስ አበባ ተከባለች፣ ሊገቡ ነው የሚል ዘገባ ሲያስተላልፉ ነው የነበሩት። እነዚህ ሰዎች ተሸነፍን ሊሉ አይችሉም " ሲሉ መልሰዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ ስለድርድር ሲነሳ "መንግስት የለም ጦርነቱ አልቋል፣ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው" ብለዋል ሲሉ ያስታወሱ ሲሆን አሁን እነሱ ባልጠበቁት መንገድ የማጥቃት ጎርፍ ሲወስዳቸው ሊሉ የሚችሉት ይህንን ብቻ ነው ብለዋል።

" ለምን እንደድሮው ጻድቃን የሚባለው ወይም የእነሱ ሰዎች ወጥተው መግለጫ አይሰጡም? " ሱሉ የጠየቁት ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ " ስለመኖራቸውም እጠራጠራለሁ፤ ሁለተኛ ደግሞ ያንን ለማድረግ ሐፍረት ይዟቸዋል። ሐፍረት የያዛቸው ስለጌቶቻቸው ነው። በዚህ ጉዳይ ትልልቆቹ ምዕራባዊያን ናቸው የሚያፍሩበት። ሊሉ የሚችሉት አልተሸነፍንም ለቀቅን ነው። መልሰን እናጠቃለን የሚል ቃል ለመግባት የተደረገ ነው " ብለዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ " በሳተላይት ይከታተሉናል ሲሉ ነበር። ስለዚህ ከየት ቦታ እንደወጡ በደንብ ያያሉ። ስለዚህ ተመትተው እንደወጡ እነሱ ቢክዱም ጌቶታቸው ያውቃሉ " ያሉ ሲሆን " ከአማራ ክልል ለቀን ወጣን ካሉ ከአፋር ክልልስ ይህንን ሁሉ መሬት እንዴት አድርገው ለቀቁ ? ጭፍራ፣ ቡርቃ፣ ጪፍቱ አፋር ናቸው። ይሄንን ሁሉ መሬት እንዴት አድርገው ነው የለቀቁት። አመኑም አላመኑም የሆነው ይሄ ነው " ብለዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ፤ በቀጣይ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ትግራይ ክልል መዲና #መቐለ የማምራት እቅድ ይኖረው እንደሆነ ተጠይቀው ፥ " ይህ ወታደራዊ ጉዳይ ነው። እኛ እዚህ ጋር እንቆማለን አንልም። ወታደራዊ ሁኔታው ነው የሚወስነው። ጦርነት በእርግጠኝነት የሚነገር ነገር አይደለም። የማይገመቱ ነገሮች (አንሰርቴይኒቲ) የሞላበት ነው። ስለዚህ በቀጣይ የሚፈጠረው ነገር ነው የሚወስነው። ነገር ግን እኛ አንቆምም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጦሩ ህወሓት የያዛቸውን ቦታዎች ደረጃ በደረጃ እያስለቀቀ እና እየደመሰስ እንደሚቀጥል የተናገሩት ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ፤ " መቐለ ነው የምንቆመው የት ነው የምንቆመው ለሚለው፤ የምንቆም አይደለንም። አሁን ግን እቅዳችን እዚህ ድረስ ነው የሚል ነገር የለንም " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጦር ህወሓት የገባበት ገብቶ እስከሚያጠፋው ድረስ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#LieutenantGeneralBachaDebele  በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ለቢቢሲ ቃለምልልስ ሰጥተዋል። ቃለምልልሱ በወቅታዊ የጦርነቱ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር። ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ህወሓት ባደራጀው ሰራዊት አዲስ አበባ ገብቶ ኢትዮጵያን እበትናለሁ በሚል ሂሳብ እስከ ሰሜን ሸዋ የተወሰኑ አካባቢዎች ድረስ ገብቶ እንደነበር ገልፀዋል።…
" እኔ ስለሰላም ድርድር ጉዳዬ አይደለም። መዋጋት ነው ሥራዬ " - ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ ጄነራል ባጫ ደበሌ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሰላም እንዲፈታ እና ስለሰላም ድርድር ጥረት ከቢቢሲ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ፥ " እኔ ስለሰላም ድርድር ጉዳዬ አይደለም። መዋጋት ነው ሥራዬ። ከፈለጉ በሰላም ይጨርሱ ከፈለጉ ይደራደሩ። ይህንን ፖለቲከኛ ነው የሚያውቀው። በእኔ በኩል ግን ፊት ለፊቴ ያለ ጠላት አለ፣ እሱን ደምስስ ተብያለሁ፣ የገባበት ገብቼ አጠፋዋለሁ " ብለዋል።

አክለው ፥ " በቃ አቁም በሰላማዊ መንገድ እንጨርሳለን፣ ድርድር ጀምረናል እና አቁም ሲባል አቆማለሁ። ይኼው ነው። ቢደራደሩ ጥሩ ነው አይደለም የሚል አስተያየት መስጠት የእኔ ኃላፊነት አይደለም። ሥራዬም አይደለም መርሁም አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ለቢቢሲ ከሰጡት ቃለምልልስ (telegra.ph/BBC-12-03-2)

@tikvahethiopia
" ለሰላሙ ብቸኛው መፍትሄ ተኩስ አቁም እና ፖለቲካዊ ንግግር ነው " - ሙሳ ፋኪ መሀመት

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ በተረጋገጠ ይፋዊ በትዊተር ገፃቸው ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት ብቸኛው መፍትሄ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ማድረግ እና ፖለቲካዊ ንግግር መጀመር ነው ብለዋል።

ሙሳ ፋኪ ፥ " ግጭቱ በሚያሳዝን ሁኔታ ቀጥሏል " ያሉ ሲሆን በአፍሪቃ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ሁለቱን ወገኖች ለማሸማገል የጀመሩትን እንቅስቃሴ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አንድ_ሚሊዮን_ዳያስፖራ ወደ ሀገር እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ሰሜን አሜሪካና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በራሱ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚፈለገውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትኬት ቅናሽ እንዲሁም ተጨማሪ የሻንጣ የኪሎ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና አየር መንገዱ የማይበርበትም ሥፍራ ቢኖር፣ ገበያውን ለማምጣት እንደሚሰራ ከአየር መንገዱ መስማቱል ሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚ ቀደምም ሆነ ወደፊትም ለልዩ ልዩ በዓልና ተመሳሳይ ወቅቶች የተለየ ቅናሽ እንዲሁም አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በሌላ አጭር መረጃ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ''ቢዝነስ ትራቭለርስ '' መጽሄት የሚያዘጋጀውን “የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች የአፍሪካ ምርጥ” አሸናፊ ሆኗል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ሊያገኝ የቻለው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያያዘ እየወሰዳቸው ያሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች ፣ ከጉዞ ትኬት ጋር በተገናኘ የሚሰጠው ፈጣን ምላሽ እንዲሁም በወረርሽኙ ወቅት ለተከሰቱ የጉዞ መስተጓጐሎች ለሰጠው የተቀላጠፈ የጉዞ ማስተካከያ አገልግሎት እና ተያያዥ መስፈርቶች በቢዝነስ መንገደኞች በመመረጡ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ነው።

አካል ጉዳተኞችን እንደተረጂ ማየት ትክክል አይደለም!

አካል ጉዳተኞችን በህክምና እንዴት ማስተካከል ወይም ማከም እንደሚቻል ብቻ ማሰብ ትክከለኛ አመለካከት አይደለም!

#ዓለም_አቀፍ_የአካል_ጉዳተኞች_ቀን ዘንድሮ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ29ኛ ጊዜ እና በዓለም ለ30ኛ ጊዜ “የአካል ጉዳተኞችን መሪነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ አካታች፣ ተደራሽ እና ዘላቂ ድህረ ኮቪድ-19 ዓለምን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ እየተከበረ ይገኛል።

#ጤናማቃላት #ኢሰመኮ #ሁሉንምያካተተ

@tikvahethiopia
#Sudan | የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የተባበሩት መንግሥታት (UN) የሽግግር መንግሥቱን እንዲደግፍ ጥሪ አቀረቡ።

ሌ/ጀነራል አል-ቡርሃን ጥያቄውን ያቀረቡት የተመድ የሱዳን ተወካይ የሆኑትን ቮልከር ፔርዝስ አግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ቮልከር ፔርዝስ ከአል-ቡርሃን ጋር መገናኘታቸውን በተረጋገጠ የትዊተር ገጻቸው የገለጹ ሲሆን፤ ምንም አንኳ ሱዳን ሕገ መንግሥታዊው ሥርዓት እንዲመለስ ብትስማም፤ ሌሎች ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮች መከናወን አለባቸው ብለዋል።

ጀነራል አል-ቡርሃን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት የሲቪል መንግሥት መሪ ጠ/ሚ አብደላ ሐምዶክ ጋር አብሮ ለመሥራት እና ምርጫ እስኪከናወን ድረስ አብደላ ሐምዶክ ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት በ18 ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲያካሂድ ጫና እየተደረገበት መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia