TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SUDAN : የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አዲስ ሉዓላዊ ምክር ቤት አቋቋሙ፡፡

ቡርሃን ምክር ቤቱን ያቋቋሙት በመፈንቅለ መንግስቱ የፈረሰውን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ለመተካት ነው፡፡

አዲስ የተመሰረተው ምክር ቤት 15 አባላት ያሉት ሲሆን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን ሲመሩት የነበሩት ቡርሃን ራሳቸውን የአዲሱ ም/ቤት መሪ አድርገው ሾመዋል፡፡

ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን በምክትልነት ሲመሩ የነበሩት ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳገሎ (ሄሚቴ)ም በአዲሱ ምክር ቤት ምክትል መሪነት እንደሚቀጥሉ ቡርሃን አስታውቀዋል፡፡

ከ15ቱ የምክር ቤቱ አባላት መካከልም 5ቱ የሃገሪቱ ጦር መሪ ጄነራሎች ናቸው፡፡

የሱዳን ጦር ከ20 ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሚመራው የሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡

መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎም የሲቪል አስተዳድሩ ወደ ቀድሞ ስልጣኑ እንዲመለስ የሱዳን ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ከታላቁ የኅዳሴ ግድብ በዓመት 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የኢትዮጵያ የኢኖቬስን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ደኤታ ሁሪያ አሊ ማህዲ አስታወቁ።

ኢትዮጵያ በዚሁ ከመጀመሪያ ዙር እንደምታመነጭ ከሚጠበቀው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጠቃላይ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በ14 ከመቶ እንደሚያሳድገው ገልፀዋል።

ሚኒስትር ደኤታዋ ሁሪያ አሊ ይህን ያሳወቁት ዛሬ በይነ መረብ በተካሄደ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ኢትዮጵያን በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለማሳደግ በርካታ ፕሮጄክቶችን እያከናወነች ነው ያሉት ምኒስትር ዴኤታዋ ፥ ከዋነኞቹ ፕሮጀክቶች ግንባር ቀደሙ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከጥቂት ወራት በኃላ 700 ሜጋ ዋት ማመንጨት ይጀምራል ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጫ ሰጥቷል። ኤጀንሲው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል ብሏል። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ ነው…
#ተጨማሪ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና #በማህበራዊ_ሚዲያ ላይ ወጥቷል የሚል ጥቆማ እንደደረሰውና በቀጣይ ታይቶ በማስረጃ የሚረጋገጥ ከሆነ እርምጃ ወይም ማስተካከያ እንደሚወሰድ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳውቋል።

የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ የ4 ቀኑ ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ፤ በማህበራዊ ሚዲያ ፈተናው ወጥቷል የሚል ጥቆማ እንደደረሳቸው ገልፀዋል።

ይህ ጥቆማም በቀጣይ ታይቶ በማስረጃ የሚረጋገጥ ከሆነ እርምጃ ወይም ማስተካከያ የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል።

በማስረጃ ተረጋግጦ ትክክል ከሆነ በትምህርት ቤት ደረጃ፣ በተማሪ እና በትምህርት ዓይነት ላይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን መጠቆማቸውን ኤዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#CentralStatisticsAgencyኢትዮጵያ

ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ምጣኔ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ34.2 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል።

የምግብ የዋጋ ግሽበት በ40.7 በመቶ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ደግሞ በ25.2 በመቶ ከአምናው ጭማሪ ማሳየቱን ኤጀንሲው አመልክቷል።

በእህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በመጠኑ የተረጋጋ ሲሆን፤ ሩዝ፣ ጤፍ እና ስንዴ አነስተኛ የዋጋ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የበቆሎ ዋጋ በመጠኑ መጨመሩን የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል፡፡

ሥጋ፣ ወተት፣ አይብ እና እንቁላል፣ ቅመማ ቅመም (በዋናነት ጨው እና በርበሬ) መጠነኛ ቅናሽ ማሳየታቸውም ተጠቅሷል፡፡

ይህም ከመስከረም ወር ጋር ሲነጻጸር የምግብ የዋጋ ግሽበት በ1.3 በመቶ ቅናሽ እንዲያሳይ አድርጎታል ተብሏል፡፡

ከውጭ የሚገባው የምግብ ዘይት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ዋጋው የጨመረ ሲኾን፤ በአገር ውስጥ የሚመረተው ዘይትና ቅቤ ዋጋ ትንሽ እንደቀነሰ የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል፡፡

በሌላ በኩል የቡና ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

የጥቅምት ወር 2014 ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ25.2 በመቶ ጭማሪ እንደሚያሳይ ኤጀንሲው ይፋ አድርጓል፡፡

የዋጋ ግሽበቱ ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ ልብስና ጫማ፣ ጫት፣ ማገዶ እና ከሰል፣ የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶ፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ የግንባታ እቃዎች እና ወርቅን ጨምሮ በጌጣጌጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል፡፡

Credit : Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
በደቡብ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለ1 ሳምንት ተራዘመ።

በደቡብ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ በቀጣይ አንድ ሳምንት ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚካሄድ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት ለ5 ተከታታይ ቀናት የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦችና ተቋማት እንዲያስመዘግቡ ዉሳኔ መተላለፉን ገልፀው በነዚህ ቀናት መዝግቦ ማጠናቀቅ ባለመቻሉ ከነገ 03/03/2014 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት ለመጨረሻ ጊዜ ይካሄዳል ብለዋል።

በመሆኑም እስከአሁን የጦር መሳሪያ ያላስመዘገቡ ግለሰቦችና ተቋማት በቀጣይ አንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ በቅርበት ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርበዋል ።

ባለ ሁለት እግር ሞተርና አሽከርካሪዎች፣ የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡና የአከራይ ተከራይ ምዝገባ ለቀጣይ 7 ቀናት መራዘሙን ሃላፊዉ ገልጸዋል ።

በተራዘሙት የምዝገባ ቀናት የማያስመዘግቡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ኃላፊው ማሳወቃቸውን ከክልሉ ኮሚኒካሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ባለፉት ቀናት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት #ቴሌግራም እና #ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች ትላንት ፈተናው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ተደርጎ የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopia
#SUDAN : በሱዳን የኢንተርኔት አገልግሎት ለ19ኛ ቀን እንደተቋረጠ መቀጠሉን ኔትብሎክስ አሳውቋል።

ባለፈው ወር በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ምክንያት ለአብዛኛዎቹ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን እስካሁን ድረስ መስተጓጎሉ በመቆየቱ በሰብአዊ መብት፣ በዲሞክራሲ እና በሰዎች ህይወት ላይ እንቅፋት መፍጠሩ ተገልጿል።

ኢንተርኔትን መሰረት አድርገው ህይወታቸውን የሚገፉ በርካታ ሱዳናውያን መኖራቸውን ተጠቁሟል።

@tikvahethiopia
#GERD

ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረገው የሶስቱ ሀገራት ድርድር ውጤት ያመጣል ብለን እናምናለን ይህንንም እንደግፋለን አሉ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት የኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤል አፕተን።

አምባሳደሩ ይህ ያሉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተገኝተው ከሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በመከሩበት ወቅት ነው።

በዚሁ ግዜ ነው አምባሳደሩ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነትን እንደሚደግፉ አሳውቀዋል።

በቀጣይ ግዜም የዜሮ ካርበን ልቀት መጠን ግብን ለማሳካት በአፍሪካ ህብረት በኩል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ሃገራቸው ማቀዷን ገልጸው ከዚህ ውስጥ #ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ መሪነት ባለፉት ሁለት አመታት ከ4 ቢሊየን በላይ የተለያዩ አይነት ችግኞት መተከላቸውን ገልጸው ይህ ተግባር የአባይ ወንዝ ጨምሮ በሃገሪቱ ያሉ የውሃ አካላትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የህዳሴ ግድብም ለሱዳንና ልግብፅ ያለውን ጥቅም አስረድተዋቸዋል።

ሚኒስትሩና አምባሳደሩ በቀጣይ በጋራ በሚሰሯቸው ታዳሽ ሀይል ልማት፤ የውሃና ሳኒቴሽን፤ ድርቅን፣ የአከባቢ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#Amhara

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም በክልሉ ያሉ ተፈናቃዮች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን ማለፉን ሪፖርት አደረገ።

ህወሓት በክልሉ ላይ በከፈተው ጦርነት ምክንያት 1 ነጥብ 14 ሚሊዮን ዜጎች ተፈናቅለዋል።

918 ሺህ ዜጎች ደግሞ በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተፈጠሩ ግጭቶች መፈናቀላቸውን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ በአማራ ክልል የተፈናቀሉ እና ለእለት እርዳታ የተዳረጉ ዜጎች ቁጥር 2 ሚሊዮን 55 ሺህ ደርሷል።

በተቋሙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ጀምበሩ ደሴ በህወሃት ጥቃት ምክንያት የሚፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዋግ እና ሰሜን ወሎ ወረዳዎች ተፈናቅለው በደሴ እና ኮምቦልቻ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች በድጋሚ መፈናቀላቸው የሀብት እጥረቱን እንዳባበሰው አቶ ጀምበሩ አክለዋል፡፡

በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ከ500 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው ለ300 ሺህ ያህሉ ለአንድ ወር የሚበቃ ምግብ እና ሌሎች አልባሳት አድርሰን ነበር የሚሉት አቶ ጀምበሩ የህወሃት ታጣቂዎች ወደከተሞቹ መግባታቸውን ተከትሎ “የሰጠናቸውን ድጋፍ ትተው ወደ ደብረብርሃን እና ሌሎች ቦታዎች ተሰደዋል” ብለዋል፡፡

ይህ መሆኑ “በፊትም የነበረብንን የሀብት እጥረት የባሰ አክብዶብናል” ሲሉ አቶ ጀምበሩ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ደብረብርሃን፣ መካነሰላም፣ እብናት፣ መቄት፣ መርጦለማርያም፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ደሃና እና ሰሃላ ቦታዎች ላይ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፎችን እያደረሱ መሆኑንም ገልጸዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ምንጭ ፦ አል ዓይን
ፎቶ ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቶ አመልካቾችን በመመዝገብ የአመልካቾችን የትምህርትና ተዛማጅ ማስረጃዎች የማጣራት ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ሆኖም " ከከፈላችሁ ፈተና እንልክላችኋለን " የሚሉ አካላት እንዳሉ ደርሼበታለሁ፥ ለዚህ የአጭበርባሪዎች ሥራ ምንም አይነት ምላሽ እንዳትሰጡ ሲል አሳስቧል።

ባንኩ በቀጣይ ለፈተና የሚቀርቡ እጩዎችን በባንኩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ጨምሮ በተለያየ ሚዲያ አሳውቃለሁ ብሏል።

መሰል የማጭበርበር ድርጊት ጥያቄዎች ሲያጋጥማችሁ ስልካቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን 0115520159 ላይ በመደወል እንዲጋለጡ እንድታደርጉ ጠይቋል።

@tikvahethmagazine
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ የቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ መቼ ይወጣል ?

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ የቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚወጣ ሲጠበቅ ነበር ፤ ነገር ግን የዕጣው ማውጫ ቀን ተራዝሞ ነበር።

በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች ሲሸጥ የቆየው የሎተሪ ትኬት በወቅቱ ምክንያት ሁኔታ በአንዳንድ አካባቢዎች የተሸጡና ያልተሸጡ ትኬቶችን ሪፖርት ማግኘት ባለመቻሉና የሁሉም አካባቢዎች የሽያጭ ሪፖርት ተሰብስቦ እስኪጠናቀቅ ድረስ ጊዜ በመውሰዱ ምክንያት ዕጣው ሳይወጣ ሊቆይ እንደቻለ ተገልጿል።

ቤተክርስቲያንቱ ለገቢ ማሰባሰቢያ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፈቃድ በመውሰድ ያዘጋጀችው የቶምቦላ ሎተሪ ሽያጭ መስከረም 10/ 2014 ዓ.ም የተጠናቀቀ ሲሆን የዕጣ ማውጫ ቀኑ የሽያጭ ሪፖርቱ ተሰብስቦ እስኪጠናቀቅ ድረስ የተራዘመ መሆኑን የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" በሚቀጥሉት 3 ወራት ዕጣ የወጣባቸውን 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስረከብ እየሰራን ነው " - የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚቀጥሉት 3 ወራት ዕጣ የወጣባቸውን 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስረከብ እየሰራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ ዕጣ ወጥቶባቸው ወደ ባለዕድለኞች ያልተላለፉ 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በቀጣይ 3 ወራት ለባለቤቶቹ ለማስተላልፍ እየሰራን ነው ብሏል።

በሌላ በኩል ከተማ አስተዳደሩ በተያዘው በጀት ዓመት 139 ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ እንደሆነና ቤቶቹ በተለያየ የግንባታ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ከቤቶቹ ግንባታ በተጨማሪ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች እንዲሟላላቸው ከሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር በበኩሉ ከተማ አስተዳደሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን በሽርክና፣ በመንግሥትና በግል አጋርነት እያስገነባ መሆኑን አሳውቋል።

በመንግስት ከሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ ከ12 ሺ በላይ ዜጎች በማሕበር እንዲደራጁ በማድረግ የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አማራጭ ለመፍጠርም እየተሰራ መሆኑን የቤቶች ልማት አስተዳደር ገልጿል።

ቤቶቹ ሲገነቡ የገንዘብ ችግር እንዳያጋጥም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ተቋሙ ጠቁሟል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከ650 ሺህ በላይ ቤት ፈላጊዎች ተመዝግበው የቤት ባለቤት ለመሆን ገንዘብ እየቆጠቡ መሆኑን የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ እንደሚያመለክት ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ህዳር 3 ድረስ እንዲካሄድ ተወስኗል። ፈቃድ ያለው ይሁን የሌለው የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በአዲስ አበባ ደረጃ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በስሩ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እየቀረበ መሳሪያውን እንዲያስመዘግብ ከዚህ ቀደም ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም። ምዝገባው ለሁለት ጊዜ መረዛሙ ይታወሳል። ምዝገባውን በሃገር አቀፍ ደረጃ ወጥ ለማድረግ…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ትላንትና ድረስ ከ23 ሺህ በላይ መሳሪያዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 42 በመቶ የሚሆኑት ፍቃድ የሌላቸው መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገኘው ሪፖርት ያስረዳል።

በአዲስ አበባ ፍቃድ ያለውም ይሁን የሌለው የጦር መሳሪያ በእጁ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ግለሠብ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በስሩ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመቅረብ እንዲያስመዘግብ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።

የምዝገባ ጊዜው በተለያዩ ምክንያቶች ሲራዘም እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ከቀናት በፊት የተራዘመው የምዝገባ ቀን ዛሬ አርብ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ/ም ተጠናቋል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ በኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት በድረገጹ እንዳስታወቀው በሁለት የኤርትራ ባለስለጣናት እና በ4 ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጥሏል።

አሜሪካ ኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ የጣለችው በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ መሆኑን አሳውቃለች።

እንደ አሜሪካ ግምጃ ቤት መረጃ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች አብርሃ ካሳ ነማርያም የኤርትራ ብሄራዊ ደህንነነት ቢሮ ሀላፊ እና የኤርትራ ህዝብ ዲሞክራሲ እና ፍትህ ንቅናቄ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ሀጎስ ገብረህይወት ናቸው።

በተጨማሪም የኤርትራ መካላከያ ሰራዊት እና የኤርትራው ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትሕ (ህግደፍ) ማዕቀብ እንተጣለባቸው የአሜሪካ ግምጃ ቤት አስታውቋል።

የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ነብረት የሆነው ህድሪ ትረስት እና የቀይ ባሕር ንግድ ኮርፖሬሽንም ማዕቀቡ የተጣለባቸው ተቋማት መሆናቸው ታውቋል።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ማዕቀቡ የተጣለባቸው ተቀዋማት እና ግለሰቦች በአሜሪካ ያላቸው ንብረት እንዳይንቀሳቀስ እና የጉዞ እገዳን ያካትታል።

ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች እና ተቋማት በትግራይ ክልል በንጹሃን ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽማዋል በሚል መሆኑንም ግምጃ ቤቱ አስታውቋል።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከትግራይ ክልለ ጋር በተያያዘ በኤርትራ ጦር ዋና አዛዥ በጀነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

ምንጭ፦ አል አይን

@tikvahethiopia