TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Bahirdar : በባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እንዲሁም የብሬን፣ የክላሸና የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋለ። በባህር ዳር ከተማ ልዩ ቦታው ዳግማዊ ምንሊክ ክፍለ ከተማ ማርዘነብ ቀበሌ በተባለው ስፍራ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ፦ - 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣ - 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣ - 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ…
#Bahridar : በባህር ዳር ከተማ ከግለሰብ ቤት ውስጥ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ።

በዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ማር ዘነብ ቀበሌ ሲቱ ዋርካ አካባቢ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ፦
• 3676 የክላሽ ጥይት፣
• 1288 የመትረየስ ጥይት፣
• 3 ክላሽንኮፍ ጠመንጃ እና 20 የተለያዩ ሽጉጦች ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መያዙን የ9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል አሳውቋል።

ፖሊስ ህገወጥ የጦር መሳሪያውን በድንገተኛ ፍተሻ ሊይዝ የቻለው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሆኑን ገልጿል።

Credit : አማራ ፖሊስ

@tikvahethiopia
#KonsoZone : አቶ ዳዊት ገበየሁ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የኮንሶ ዞን የሽግግር ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ዳዊት ገበየሁ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

ሹመቱን ተከትሎ አቶ ዳዊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia
#HalabaZone : ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሹመዋል፡፡

የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ሲሆን ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በትግራይ ክልል እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡ በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች…
የመምህራን ጉዳይ !

" በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጊዚያዊ ምደባ ይሰጣቸዋል " - ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ

በትግራይ ክልል የሚገኙ 4 ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉዳይን በተመለከተ ለትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ-ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ጠይቀናል።

የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ተቋማቱ አዲስ አበባ ባላቸው የጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ አማካኝነት ደሞዝ እየተከፈላቸው መሆኑን ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ተናግረዋል።

እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም በሚሰሩበት ዩኒቨርሲቲ ደሞዝ የተከፈላቸው መምህራን አሁንም ክፍያ እየተፈጸመላቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በሥራ ላይ እንደነበሩ ማስረጃ ማሳየት ያልቻሉና ሚያዝያ/ግንቦት ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህራን፤ ሥራ ማቆማቸው ወይም ውላቸው መቋረጡ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ደሞዝ እየተከፈላቸው ያሉ የአራቱ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለይ የመምህራን እጥረት ባለባቸው የአገሪቱ ዩዩኒቨርሲቲዎች ጊዚያዊ ምደባ እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።

More : https://t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#EZEMA : ዛሬ በኮንሶ ዞን የሽግግር ምክር ቤት እንዲሁም በጋሞ ዞን ምክር ቤት በነበረው ጉባኤ ላይ 2 የኢዜማ አባላት በዞን ስራ አስፈፃሚነት ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

በኮንሶ ዞን የኢዜማ ፓለቲካ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አቤል ለሚታ የኮንሶ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በጋሞ ዞን አስተዳደር ደግሞ አቶ መለሰ ጮራ የዞኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
ችሎት !

በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቢ ህግ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ስም ዝርዝር በመገናኛ ብዙሃን እንዲገለፅ ተወሰነ፡፡

ምስክሮቹ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ተወስኗል፡፡

ይህ የተወሰነው የእነ እስክንድር ነጋን የዛሬ የጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም የክስ ቀጠሮ በተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መሆኑን አል ዓይን ዘግቧል።

ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት እንዲያቀርባቸው የታቀዱ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን እንዳይገለጽ ያቀረበውን የጽሁፍ አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡

በዐቃቤ ህግ ምስክርነት በግልጽ ችሎት የሚቀርቡ ዘጠኝ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን እንዲገለጽም ወስኗል፡፡ ውሳኔውን ተከትሎ የምስክሮቹ ስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት ! በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቢ ህግ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ስም ዝርዝር በመገናኛ ብዙሃን እንዲገለፅ ተወሰነ፡፡ ምስክሮቹ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ተወስኗል፡፡ ይህ የተወሰነው የእነ እስክንድር ነጋን የዛሬ የጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም የክስ ቀጠሮ በተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች…
#ተጨማሪ

በነ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ዐቃቤ ሕግ የዘረዘራቸው ሰዎች 9 ሲሆኑ ዐቃቤ ህግ ቀሪ የ12 ምስክሮች ስም ዝርዝር ነገ ደግሞ ጧት እንዲቀርብ ታዝዟል።

ዘጠኙ መስካሪዎች ፈንታሁን አሰፋ፣ መንበረ በቀለ፣ ወርቁ ታደሰ፣ ፍፁም ተሰማ ፣ ደረጀ ግዛው፣ ቴዎድሮስ ለማ፣ ያየህ ብርሃኑ ፣ ጌትነት ተስፋዬ እና ትንሳኤ ማሞ ናቸው።

ከላይ ከተጠቀሱት 9 ምስክሮች መካከል ሁለቱ ነገ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ባልደራስ ፓርቲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 20 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 20 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5810 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 386 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 555 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የኮቪድ-19 ክትባትን አቅርቦት እና ተደራሽነት ለማሻሻል የኮቪድ-19 ክትባት ለአገልግሎት ፈላጊዎች በግሉ የጤና ዘርፍ በሽያጭ ሊቀርብ መሆኑ ተሰምቷል።

ክትባቱን በሽያጭ የሚያቀርቡት ሜዲቴክ ኢትዮጵያ እና ዋሽንግተን የህክምና ማዕከል በትብብር ነው።

ሁለቱ ተቋማት ከቻይናው የክትባት አምራች ሲኖፋርም ብቻ ለኢትዮጵያ ከሚያቀርቡት 2 ሚሌዬን ዶዝ የአለም ጤና ድርጅትን መስፈርት ያሟላ ክትባት ውስጥ የመጀመሪያውን ዙር 2 መቶ ሺ ክትባት ትላንት ተቀብለዋል።

ክትባቱ ትላንት ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተው እንደነበር ታውቋል።

ሜዲቴክ ኢትዮጵያ እና ዋሽንግተን የህክምና ማዕከል የሚያቀርቡት የኮቪድ 19 ክትባት ዋጋ ተመጣጣኝ እና የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ውስንነት ከግንዛቤ ያስገባ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

Credit : ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ

@tikvahethiopia
#SouthWollo : የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ከሰሞኑን በደቡብ ወሎ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች በአዲስ በተቀሰቀሰው ጦርነት ብቻ ከ250 ሺህ በላይ ወገኖች መፈናቀላቸውን አመልክቷል።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሳይ ማሩ ዛሬ ለጀርመን ድምፅ በሰጡት ቃል ፥ ካለፈው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ እንደአዲስ በተቀሰቀሰ ጦርነት በደቡብ ወሎ ዞን በርካቶች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው ብለዋል።

የተፈናቃይ ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ ነው ያሉት አቶ መሳይ ፤ እየተፈናቀሉ ያሉት አረጋውያን፣ ሴቶች እና ህፃናት ፤ ከዛሬ ነገ ችግሩ ይፈታል ብለው ጫካ ለጫካ የቆዩ ወገኖች ናቸው ብለዋል።

ከዚህ በፊት በደሴ ከተማ 450 ሺህ ተፈናቃዮች የነበሩ ሲሆን አሁን ግን የተፈናቃዮች ቁጥር 700 ሺ መድረሱን አመልክተዋል።

ኃላፊው ፥ ተፈናቃዎችን ለማስተናገድ መጠለያ ከፍተኛ ችግር መሆኑን አንስተዋል፤ ከዚህ ቀደም 24 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮችን ይዘው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ 45 ት/ቤት ደርሷል።

ከት/ቤት በተጨማሪ የመንግስት ሼድ ፣ የግል ሼድ ፣ የተጀመሩ የመንግስት የቢሮ ግንባታዎች ጭምር ለተፈናቃይ መጠለያ እንዲሆን እየተደረጉ መሆኑንም አክለዋል።

በተለይ መርሳ፣ ድሬ ሩቃ ከሚባሉ አካባቢዎች አጠቃላይ ሊባል በሚችል ደረጃ ህዝቡ አካባቢውን ጥሎ መምጣቱን ገልፀው ፤ ከባቲ እስከ ሀርቡ የመንግስት ት/ቤቶች በተፈናቃዮች ተይዘዋል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Photo : File (Dessie Commu.)

@tikvahethiopia
#Waghimra : በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት በጦርነት ቀጠና ያሉ ከ635 ሺህ በላይ ወገኖች በከፋ የረሃብ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ አመልክቷል።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታ ለጀርመን ድምፅ ዛሬ በሰጡት ቃል ፤ በዋግኽምራ በጦርነት ቀጠና ያሉ ከ635 ሺ በላይ ሰዎች ለከፋ የረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ተናግረው ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች እስካሁን ተግባራዊ ምላሽ አልሰጡም ሲሉ ወቅሰዋል።

በአካባቢው መብራት፣ ውሃ ፣ኔትዎርክ የለም መንገድም ተዘጋግቷል ያሉት አቶ መልካሙ ከፍተኛ የሆነ የምግብ አቅርቦት ችግር መኖሩን አመልክተዋል።

በተለይም የጤና አገልግሎት መስተጓጎሉን ስር የሰደደ ህመም ያለባቸው ወገኖች መታከም እንደማይችሉ አክለዋል።

አቶ መልካሙ ፥ ብሄረሰብ አስተዳደሩ ያለበትን ሁኔታ ዝርዝር ጉዳዮችን በሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ ለልዩ ልዩ ረጂ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ቢጠየቅም እስካሁን መልስ እንዳልተገኘ ፤ በአስከፊ ሁኔታ ችግር ላይ የወደቀውን ማህበረሰብ መታደግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በላይ በበኩላቸው ፤ ከነሃሴ 1 ጀምሮ መሰረታዊ ፍጆታዎችን በገበያ ማግኘት እንደማይቻል ገልፀዋል።

አቶ ጳውሎስ ፥ " ጨው፣ ዘይት፣ በርበሬ፣ ሽሮ የለም፤ ቢኖርም ዋጋው ውድ ነው ፣ ባንኮችም ብሎክ ስለሆኑ ብርም የለም ፤ ከአካባቢው እየወጣ የሚመጣው ሰው የሚናገረው ሰቆቃ ነው" ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ በበርካታ ወረዳዎችም የአንበጣ መንጋ በማሳ ላይ የቀረችውን ቀሪ የአርሶ አደር ሰብል እያወደመ ነው ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_መልዕክት !

ለአሶሳ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ፦

ነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም የከባድ መሳሪያ ቶክስ ሙከራ ስለሚኖር በአሶሳ እና አካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች መረጃውን በማወቅ ከድንጋጤ ነፃ በመሆን የተለመደ የስራ ተግባራቸውን እንዲከውኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ወላጆች ልጆቻችሁን መጠበቅ ፣ የሚውሉበትንም መከታተል እንዳትዘነጉ።

በሀዲያ ዞን ግቤ ወረዳ ሀደዬ ቀበሌ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ በአንድ ህፃን ላይ ቀላል የማይባል የአካል ጉዳት መድረሱን ከግቤ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሰምተናል።

ክስተቱ የተፈጠረው በቀን 08/02/2014 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት አከባቢ ሲሆን ጫካ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ነው በተባለ ቦንብ የ7 ዓመት ህጻን ላይ ከባድ የአካል ጉደት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው ህጻኑ ቦንቡን ይዞ በመምጣት መኖሪያ ቤቱ አከባቢ ሲደርስ በደረሰ ፈንዳታ ሲሆን የህጻኑ ሦስት ጣቶች ወዲያው ተቆርጠዋል፤ ሌሎች የሰውነት ክፊሎቹ ላይም ቀላል የማይባል ጉዳት መድረሱን የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ህጻኑ በንግስት ኢሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ሆስታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ሲሆን በተከሰተው ክስት ዙሪያ ቡድን በማዋቀር ፖሊስ ተጨማሪ መረጃዎችን የማሰባሰብ እንዲሁም ምርመራ የማካሄድ ሥራ እየሰራሁ ነው ብሏል።

ፖሊስ ፥ ተመሳሳይ አደጋዎች ልኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ህጻናትን ዝምብሎ መልቀቅ እንደሌለበት መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
" ቀጣናውን ለመረበሽ የሚያልሙ ኃይሎች በንፁህ ዜጋ ላይ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እየፈፀሙ ነው " - አቶ ሰለሞን አልታዬ

መነሻውን ደብረብርሃን መድረሻውን አጣዬ አድርጎ ሲያሽከረክር የነበረ የታርጋ ቁጥሩ ET3 71650 የሆነ የሲኖ ትራክ #አሽከርካሪ በጥይት መመታቱን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ሪፖርት አደረገ።

ወረዳ በአሽከርካሪውን በጥይት ተኩሰው ጉዳት ያደረሱበት "ፀረ ሰላም ሃይሎች" ናቸው ብሏል።

አሽከርካሪው ጉዳት የደረሰበት ወደ አጣዬ በመጓዝ ላይ እያለ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ልዩ ስሙ ቆሮ ድልድይ አካባቢ ሲሆን ድርጊቱም የተፈፀመው ትናንት ከምሽቱ በግምት 3 ሰዓት ላይ ነው።

ግለሰቡ ከተመታ በኋላ እያሽከረከረ ወደ አጣዬ ከተማ መግባቱን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አልታዬ ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት በአጣዬ ድስትሪክት ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑንም ገልፀዋል።

አቶ ሰለሞን ፥ " ቀጣናውን ለመረበሽ የሚያልሙ ኃይሎች በንፁህ ዜጋ ላይ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እየፈፀሙ ነው " ብለዋል።

በአሽከርካሪው ላይ የተፈፀመው እኩይ ተግባር የሚወገዝ ነው ያሉት አቶ ሰለሞን " የቀጣናውን ሰላም የማይፈልጉ አሸባሪ ኃይሎችን የአጣዬ ከተማ እና የወረዳው ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን በንቃት መከታተል አለበት " ብለዋል።

መረጃው የኤፍራታና ግድም ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Semera : በአፋር ክልል መዲና ሰመራ በአሁን ሰዓት በርካቶች የተገኙበት የውይይት መድረክ እየተካሄደ መሆኑን አፋር ማስ ሚዲያ ዘግቧል።

ውይይቱ #በወቅታዊ_ጉዳይ ዙሪያ መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የአፋር ክልል ወጣቶች ፣ ሴቶች እና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች ተካፋይ መሆናቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia