TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Senegal የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሴኔጋል፤ ዳካር ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴኔጋል ቆይታቸው ከሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋር የሁለትዮሽ ጉዳዮችና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። #PMofficeEthiopia @tikvahethiopia
#Senegal #Ethiopia #Ghana

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በሴኔጋል ፣ ዳካር ከተማ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳልን አመሰገኑ።

ጠቅለይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለሊት በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ፥ "በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል መካከል ያለው ግንኙነት መሠረት የአፍሪካ ህብረት እንዲቋቋም ያስቻለው #የፓን_አፍሪካኒዝም መንፈስ ነው ፤ በዚህ መሠረቶች ላይ የበለጠ ለመገንባትና በአፍሪካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተናል" ሲሉ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ በሴኔጋል የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደጋና አቅንተዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ጉባኤው አዲሱ ዓመት 2014 ዓ.ም በሀገራችን በሁለንተናዊ መልኩ ፍጹም ሰላም እና አንድነት የሚታይበት ስኬትን የሚመዘገብበት እንዲሆን ተመኝቷል።

አዲሱ 2014 ዓ.ም ሲጀመር የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች የጳጉሜን ወር በጸሎት አና ጾም እንዲያልፍ አዋጅ በማወጅ እና መልካም ምኞት በመግለጽ በሀገራችን የሚታዩ ፦
- ግጭቶች፣
- ያለመግባባቶች፣
- በደሎችና ጉዳቶች በዘላቂነት ተፈትተው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሰላምና በመከባበር መንፈስ አዲሱን ዓመት ለመቀበል ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል ተብሏል።

ለዚህም በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ፃገር ያሉ ኢትዮጵያውያን አማኖች ሁሉ የዕድሜ ፣ የጾታ ፣ የማህበራዊ እና መሰል ሁኔታዎችን ሳይለዩ ስለሃገራቸው ሰላም እና አንድነት ስለወገኖቻቸው ሁለንተናዊ ደህንነት እንደሀገር ያጋጠሙንን ፈተና ለማለፍና መጪውን ዘመን ለሁላችንም የተሻለ እንዲሆን እያንዳንዳችን የሃይማኖታችን አስተምህሮና ሥርዓት በሚያዘው መሠረት ከአባቶቻቸን ጋር በመሆን ወደፈጣሪ አጥብቀን እንድንጸልይ ጉባኤው ጥሪውን አቅርቧል።

ከዚህም ባለፈ ሃይማኖቶች የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የዕርቅ፣ የመተዛዘን እና የመረዳዳት ምሳሌዎችና መሰረቶች በመሆናቸው የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲናር በጎውን እና መልካሙን እንዲሰሩ በማስተማር ማህበራዊ አንድነትን እና የሰውን በጎ ትስስር የሚያጠፉ የክፋት እና የጥላቻ አስተሳሰቦችን እና ተግባራትን እንዲያወግዙ ጉባኤው በአጽንኦት አሳስቧል።

በተጨማሪ ጉባኤው ሁሉም አማኞች አዲሱን ዓመት 2014 ሲቀበሉ በተለያየ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን፣ በጦርነት የተጎዱትን በማሰብና የሰብኣዊ ድጋፍ በማድረግ ሊሆን ይገባል ብሏል።

@tikvahethiopia
"የቦይንግ የቦርድ ዳይሬክተሮች ክስ ሊመሰረትባቸው ይገባል" - ዳኛ ሞርጋን ዘርን

የአሜሪካው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ የቦርድ ዳይሬክተሮች ከ737 ማክስ አውሮፕላን ጋር በተያያዘ ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሚገባ ሞርጋን ዘርን የተባሉ ዳኛ መወሰናቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ዳኛ ሞርጋን ዘርን እንዳሉት አውሮፕላኖቹ ከደኅንነት ሥርዓት ጋር በተያያዘ ስጋት እንዳለባቸው ቢገለጽም የቦርድ አባላቱ ግን ይህንን እውነታ ችላ ብለውታል።

በዚህ ስህተት ዋነኞቹ ተጎጂዎች አውሮፕላኖቹ ባጋጠማቸው አደጋ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ናቸው ያሉት ዳኛው፤ በተጨማሪ ደግሞ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ለኪሳራ እንዲጋለጥ አድርጓል ሲሉ አክለዋል።

ብይኑን ያስተላለፉት ዳኛው "በቦይንግ ድርሻ ያላቸው ባለሀብቶች ወደዚህ ፍርድ ቤት ቀርበው የቦይንግ የቦርድ ዳይሬክተሮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዳልተወጡ እና የአውሮፕላኑን የደኅንነት ስጋት በቸልታ ማለፋቸው ደግሞ የእነሱ ድርሻ ላይ ጫና ስለማሳደሩ ቅሬታቸውን ገልጸዋል" ብለዋል።

የአሜሪካው ዳኛ ውሳኔውን ካስተላለፉ በኋላ የቦይንግ ቃል አቀባይ በፍጥነት ማስተባበያ ሰጥተዋል።

"ፍርድ ቤቱ በወሰነው ውሳኔ በእጅጉ አዝነናል" ብለዋል። "የቀረበውን ሐሳብ በጥልቀት ከመረመርን በኋላ በሚቀጥሉት ቀናት ምን አይነት እርምጃ እንደምንወስድ አማራጮችን እንመለከታለን።"

በእአአ 2018ና 2019 ላይ የኢንዶኔዢያ እና የኢትዮጵያ ንብረት የሆኑ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ባጋጠማቸው ችግር ተከስክሰው በውስጥ የነበሩ ሁሉም 346 ተሳፋሪዎች ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው። (BBC)

@tikvahethiopia
"...ሱዳን ውስጥ ያሉት የስደተኛ መጠለያዎች ለኢትዮጵያ አማጺያን መሸሸጊያ እንዲሆኑ አልፈቅድም" - UNHCR

[BBC]

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ለስደተኞች የሚሰጥ መታወቂያን የያዙ ግለሰቦች ከህወሓት ጋር ሆነው እየተዋጉ ነው ማለቱ ይታወቃል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቀናት በፊት #UNHCR የሚሰጠውን የስደተኞች መለያ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ከሱዳን ድንበር ተሻግረው ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን ገልጾ ነበር።

አማራ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አገኘሁ ተሻገርም ከሳምንት በፊት በሰጡት መግለጫ በሱዳን አቅጣጫ ጥቃት ሊያደርሱ ሲሉ እርምጃ የተወሰደባቸው የህወሓት ታጣቂዎች የተመድ (UN) የስደተኛ መታወቂያ የያዙ መሆናቸውን አሳውቀው ነበር።

ዛሬ ደግሞ UNHCR ባወጣው መግለጫ በሱዳን በሚገኙ ካምፖች ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም እነዚህ ስደተኞች የት እንዳሉ አላውቅም ብሏል።

UNHCR ከስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚወጡት ስደተኞች የት እንደሚሄዱ የሚያረጋግጥበት መንገድ የለኝም ሲል ገልጿል።

UNHCR የመዘገባቸውና መታወቂያ የሰጣቸው ግለሰቦች በስደተኞች ማቆያ ካምፕ ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ መውሰዳቸውን አረጋግጦ ለዚህም ምዝገባ የሚሆን የራሱ አሠራር እንዳለው አመልክቷል።

"ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች ስደተኛ ተደርገው አይወሰዱም" ሲል አሠራሩን አብራርቷል።

ስደተኛ የሚለው መለያ፤ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ለሆነ ሰው እንደማይሰጥም ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/UNHCR-09-08

@tikvahethiopia
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የ2014 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለመላው ምዕምናን ያስተላለፉት መልዕክት !

@tikvahethiopia
ስኩል ኦፍ ኔሽን ትምህርት ቤት ታገደ።

ትምህርት ሚኒስቴር የአለም አቀፍና የማህበረስብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት መመሪያን መሰረት አድርጎ ስኩል ኦፍ ኔሽን ትምህርት ቤት ላይ እገዳ መጣሉን ዛሬ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት በትምህርት ክፍያ ጭማሪ ዙሪያ በተደጋጋሚ ከወላጆች ቅሬታ በመቅረቡ የትምህርት ሚኒስቴር የዘርፍ አመራሮችና የባለሙያዎች ቡድን ትምህርት ቤቱንና የወላጅ ኮሚቴውን በማወያየት ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ በተደጋጋሚ ጊዜ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷል።

በዚህም በተደረጉት ውይይቶች ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ መንግስት (ትምህርት ሚኒስቴር) ባወጣው መመሪያ መሰረት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ፈጥኖ በመነጋገር ሪፖርት እስኪያደርግ ድረስ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰራ መታገዱ ተገልጿል፡፡

#MoE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Senegal #Ethiopia #Ghana የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በሴኔጋል ፣ ዳካር ከተማ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳልን አመሰገኑ። ጠቅለይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለሊት በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ፥ "በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል መካከል ያለው ግንኙነት መሠረት የአፍሪካ ህብረት እንዲቋቋም ያስቻለው #የፓን_አፍሪካኒዝም መንፈስ…
#Update

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ከጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አዶ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ።

ዶ/ር ዐቢይ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ "ከልዑካን ቡድኔ ጋር በአክራ በሚገኘው ቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስላደረግነው ውይይት ለፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አዶ አድናቆቴ ይድረሳቸው" ብለዋል።

አክለው ኢትዮጵያና ጋና በሁለትዮሽ እና የጋራ ትኩረት በሆኑ የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ በቅርበት ይሠራሉ ሲሉ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
"...ከአንድ ቤተሰብ 5 እና 6 ሰዎች የሞቱ አሉ" የጭና ነዋሪዶች

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ "ጭና" ተብሎ በሚጠራ ቦታ የህወሓት ታጣቂዎች ከአንድ መቶ በላይ ንፁሃንን መግደላቸውን ነዋሪዎች አሳውቀዋል።

ግድያው የተፈጸመው አካባቢው በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ ሲሆን ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ህጻናት በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

አንድ የጭና አጎራባች ቀበሌ አብጥራ፣ ነዋሪ የሆኑ አስማረ ታፈረ የተባሉ ግለሰብ ለቢቢሲ በሱጡህ ቃል ፥ ነሐሴ 12 ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በአካባቢው የህወሓት ታጣቂዎች በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና ውጊያ መካሄዱን ጠቁመዋል።

ጦርነቱ እስከ ነሐሴ 29 ድረስ መካሄዱን የገለፁ ሲሆን፥ እስካሁን ድረስ ተገድለው የተገኙ 119 ሰዎች በጦርነቱ ያልተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው ብለዋል።

"ይህ ቁጥር መሞታቸው ታውቆ ለቅሶ እየተለቀሰ ያለ ነው" በማለት ይህ ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።

እንደነዋሪው ገለፃ፥ ከአንድ ቤተሰብ 5 እና 6 ሰዎች ሞተዋል።

ዛሬ ደግሞ ሌሎች የአይን እማኝ ነን ያሉ ነዋሪዎች በጭና ተክለሃይማኖት ቀበሌ የተገደሉ ንፁሃ ከ200 በላይ መሆናቸውን አመልክተዋል። 193 የሚሆኑት በጭና ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን መቀበራቸውን አመልክተዋል።

ከ20 በላይ የሚሆኑት በዲያ ጊዮርጊስ መቀበራቸውን አሳውቀዋል።

አሁንም ተጨማሪ አስከሬን እየተገኘ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን የደረሱበት ያልታወቀ እንዳሉም ነው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

More : https://telegra.ph/CHEENA-09-08

Source : #Reuters #BBC #FBC

@tikvahethiopia
* AFAR

የአፋር ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን የህወሓት ቡድን ከአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ሙሉ በሙሉ ማስወጣት መቻሉን አሳውቋል።

ቡድኑ ፈንቲ ረሱ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ፥ የአፋር ህዝብ፣ የአፋር ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ እንዲሁም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት ትግል መሆኑን አመልክቷል።

የአፋር ወስንን ጥሶ ሰርጎ የገባው ህወሓት የተለያዩ የፈንቲ ረሱ (ዞን) ከተሞችን በመውረር ንፁሀንን በመግደል፣ በርካቶችን ከቀያቸው በማፈናቀል በአፋር ህዝብ ላይ ትልቅ በደልን፣ መቼም የማይሽር የማይረሳ ግፍን ፈፅሟል ብሏል የአፋር ክልል።

ይህ እኩይ ተግባርን ለመመከትም የአፋር ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ በመታገል ህወሓትን ከአፋር ምድር በጥንቃቄ የማውጣትና የማጥራት ስራ ስኬታማ ነበር ሲል አሳውቋል።

በዚህ ጥረት ህወሓት ከወረረባቸው የአፋር አካባቢዎች እንዲወጣ መደረጉን የአፋር ክልል በይፋ አሳውቋል።

የህወሀት የረጅም ጊዜ ህልሙን የ "ትግራይ ሪፐብሊክ / ታላቋ ትግራይ" ለመመስረት የአፋርን መሬት በማጠቃለል ለመውሰድ እና በሌላም በኩል ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሙከራ ቢያደርግም በኢትዮጵያ ድረድር የማያውቀው የአፋር ህዝብ የህወሓትን ቅዠት እንዲመክን ትልቅ ሚና ተጫውቷል ሲል ክልል ገልጿል።

የአፋር ክልል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህወሓትን ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እስከመጨረሻው ቀብሩ ድረስ እንደሚፋለመው ገልጾ፤ ህወሓት በህይወት እንዳይኖእ አስፈላጊውን መስእዋትነት እንከፍላለን ብሏል።

@tikvhethiopia
* UPDATE

#መስከረም_20 በሚካሄደው ምርጫ የሚወዳደሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች ከዛሬ ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማካሄድ እንደሚጀምሩ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

በምርጫ ግዜ ሰሌዳው መሰረት የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻው መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

@tikvahethiopia
* ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ካምፓሶቹ የ2013 ዓ.ም የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ መራዘሙን ገልጿል።

የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የሁሉም ካምፓሶች የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባን ከመስከረም 06 እስከ 07/2014 ዓ.ም ለማከናወን ታስቦ ነበር።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ምርቃት የሚደረገው መስከረም 08/2014 ዓ.ም በመሆኑ እና የክረምት ተማሪዎች ትምህርት ባለመጠናቀቁ ምክንያት ምዝገባው መራዘሙ ተገልጿል።

በመሆኑም የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ የሚከናወንበት ቀን በይፋ ወደፊት እንደሚገለጽ የዩኒቨርሲቲው የውጭ ግንኙነትና ፓርትነርሺፕ ዳይሬክተር ማንእንዳንተ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ምዝገባውን ከመስከረም 26 እስከ 27/2014 ዓ.ም ለማከናወን ይፋዊ ያልሆነ (በጊዚያዊነት) ዕቅድ መያዙን ገልጸውልናል።

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
"...ዓለም አቀፍ ሚድያዎች የደረሳቸው 123 የሚለው የሟቾች ቁጥር የመጀመርያ ሪፖርት ነው" - አቶ ሰውነት ውባለም (የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ)

የሰሜን ጎንደር ዞን የጤና ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ ከሰሞኑ በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉ የተለያዩ ስፍራዎች የህወሓት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ከ200 በላይ ናቸው ሲሉ አመለከቱ።

አስተዳዳሪዎቹ ይህን ያሳወቁት ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ከደቂቃዎች በፊት ነው።

በአንዳንድ አለም አቀፍ ሚድያዎች በዚህ ጥቃት 123 ዜጎች ህይወታቸውን እንዳጡ ቢገለፅም ቁጥሩ ከ200 በላይ እንደሆነ የጤና ቢሮው ሀላፊ አቶ በቀለ ይትባረክ አስረድተዋል።

አቶ በቀለ ፥"ይህ በአይናችን ያየነው ነው፣ በህወሀት ታጣቂዎች በተለይ ነሀሴ 28 እና 29 የተገደሉ ተጨማሪ ሰዎች እንደሚኖሩ ስለተገመተ ፍለጋው ቀጥሏል" ብለዋል።

የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም ፤ "ጎንደር ለመግባት አስበው የነበሩት ታጣቂዎች ሳይሳካላቸው ሲቀር ሲቪሎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፣ ዝርፊያ አድርገዋል" ያሉ ሲሆን በተለይ ደግሞ በ "ጨና ቀበሌ" ላይ ከፍተኛ ግፍ ተፈፅሟል ብለዋል።

አለም አቀፍ ሚድያዎች የደረሳቸው 123 የሚለው የሟቾች ቁጥር የመጀመርያ ሪፖርት እንደነበር ገልፀው ቁጥሩ አሁንም እያሻቀበ እንደሆነ አሳውቀዋል።

Credit : Ethiopia Check

@tikvahethiopia
ህይወት ለማዳን ሲሉ ህይወታቸው ያለፈው የሩሲያ ሚኒስትር ...

የሩሲያው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሚኒስትር የሰውን ህይወት ለማዳን ሲሞክሩ ህይወታቸው አለፈ።

የሩስያ አስቿኳይ ጊዜ ሁኔታ ሚኒስትር ህይወታቸው ያለፈው በኖርልስክ አርክቲክ ከተማ አቅራቢያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚደረግበት ጊዜ “ሕይወት የማዳን ”ኃላፊነታቸው ሲወጡ ነው ተብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ኢቭጂኒ ዚኒቺቭ ህይወትን ለማዳን በቁፋሮ ስራ ላይ ሳሉ ለሞት የሚዳርግ አደጋ እንዳጋለጠቸውንም ነው የተገለጸው።

መስርያ ቤታቸውም ዚኒቺቭ “ የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሲሞክሩ ህይወታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ ሊያልፍ ችለዋል” ብለዋል፡፡

በጉብኝታቸው ኖርልስክ ከተማ አዲስ የእሳት አደጋ ጣቢያ ሲመረምሩም ነበር ሚነሲትሩ።

የአር.ቲ. ዋና አዘጋጇ ማርጋሪታ ሲሞንያን በአደጋው ጊዜ “ሚኒሰትሩ እና የካሜራ ባለሙያ ጠርዝ ላይ ቆመው ነበር ከዛም የካሜራ ባለሙያው ተንሸራቶ ወደ ውሃው ውስጥ ወደቀ። በርካታ ሰዎች በስፍራው የነበሩ ቢሆንም ፣ ዚንክቼቭ ወደ ውሃው እስኪወድቁና ኩፉኛ አስኪመቱ ድረስ ምን እየሆነ እንዳለ ለመገንዘብ አልቻሉም ነበር" ስትል ሁኔታውን አስረድታለች።

ማርጋሪታ ሲሞንያን ፥ “እሱ እንደ አዳኝ ሞተ - በሰላም እረፍ”ም ስትል ኃሳቧን ገልጻለች። ማርጋሪታ የካሜራ ባለሙያው ህይወት ማለፉንም አስታውቃለች፡፡

Credit : አል ዓይን

Video : ሚኒስትሩ ከመሞታቸው ከሰዓታት በፊት የተቀረፀ ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ26 ዜጎች ህይወት አለፈ። በየዕለቱ በሽታው የሚገድላቸው ሰዎች ቁጥር እይሻቀበ ነው።

ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 26 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 8,353 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,529 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 726 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ በመሆኑ መላው የቲክቫህ አባላት ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድታጠነክሩ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* AFAR የአፋር ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን የህወሓት ቡድን ከአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ሙሉ በሙሉ ማስወጣት መቻሉን አሳውቋል። ቡድኑ ፈንቲ ረሱ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ፥ የአፋር ህዝብ፣ የአፋር ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ እንዲሁም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት ትግል መሆኑን አመልክቷል። የአፋር ወስንን ጥሶ…
* Afar

የአፋር ሰብዓዊ መብት ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት ገአስ አህመድ የህወሓት ታጣቂዎች ተቆጣጥረው ከነበረው ያሎ፣ ጎሊና፣ አውራ እና እዋ ወረዳዎች ተጠራርገው መውጣታቸውን አረጋገጡ።

አቶ ገአስ ዛሬ ምሽት ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል የአፋር ልዩ ኃይል ፣ የአፋር ሚሊሻ፣ የአፋር ታጋዮች ከትላንት በስቲያ እዋን ፤ ትላንት ደግሞ አውራ ጎሊና እና ያሎን አስለቅቀው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ገልፀዋል።

ህወሓት ተቆጣጥሯቸው በነበሩት ቦታዎች ውድመት ደርሷል ያሉት አቶ ጋአስ በጎሊና በሚገኘው የጤና ተቋም፦
- ሙሉ በሙሉ ዝርፊያ ተፈፅሟል።
- ቢሮዎች ፣ የሰራተኞች ዶክመንቶች ተዘርፈዋል፣ ተመዝብረዋል፤ ግማሹን አቃጥለዋል ሲሉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል አቶ ገአስ አህመድ ተጎጂዎችን ለማቋቋም ስለሚሰራው ስራም ያስረዱ ሲሆን የክልሉ መንግስት በተወሰነ ደረጃ በነፍስ ወከፍ እርዳታ ሲያደርግ ነበር ፤ ያ ግን አጥጋቢ ስላልነበር ብዙ ሮሮዎች ይሰሙ ነበር ብለዋል።

አቶ ገአስ በእነሱ በኩል በቅርቡ ጎፈንድሚ አካውንት በመክፈት ለተፈናቃዮች እርዳታ ለማሰባሰብ ጥረት እያደረጉ መሆኑን በማንሳት የተፈናቀሉትን ወገኖችን ፣ ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጎች ስራ ነው ፤ ይህንን ኃላፊነትም ሁሉም ይወጣዋል ብዬ አምናለሁ ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በግለሰብ እንዲሁም በክልሎችም ደረጃ ተፈናቃዮችን ለመርዳት በተወሰነ ደረጃ እንቅስቃሴ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጋአስ አሁን ትልቁ ስራ የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቦታቸው መልሶ ማቋቋሙ ነው ፤ ይህንንም የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ ሆኖ ያደርገዋል ብዬ አምናለሁ ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray #Afar

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ተፈናቅለው በሽራሮ እና አስገደ ወረዳዎች ለሚገኙ ከ42 ሺ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚረዱ ፦
- መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎችን፣
- መጠለያ ቁሳቁሶች
- የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አከፋፍለዋል፡፡

በሌላ በኩል ICRC በአፋር ክልል ለሚገኘው ዱፕቲ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ግብአቶችን አድርሷል።

የዱብቲ ሆስፒታል አስተዳደር ዶ/ር መሐመድ የሱፍ ፥ ‹‹የቆሰሉ በርካታ ህሙማንን በማስተናገድ ላይ ስለምንገኝ የህክምና ቁሳቁስ እጥረት እያጋጠመን ነው ፤ ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የድንገተኛ ህክምና ግብአቶችን እና መኝታዎችን አቅርቦልናል፡፡ አሁን ህሙማንን ማከም እና ህይወት አድን ቀዶጥገናዎችን ማከናወን እንችላለን" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

@tikvahethiopia