TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እጅግ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ያመለጡት ፍልስጥኤማውያን …

6 ፍልስጤማውያን እስረኞች ጠንካራ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት ካመለጡ በኋላ እስረኞቹን አድኖ ለመያዝ እስራኤል ኦፕሬሽን ጀመረች።

ከ6ቱ 5ቱ የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ናቸው::

ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ለወራት ያህል የእስር ቤት ክፍላቸውን ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ዋሻ ለመሥራት ሲቆፍሩ ቆይተዋል ተብሏል።

እስረኞቹ ትናንት ለሊት ላይ ማምለጣቸው የተገለጸ ሲሆን፤ እስረኞቹ በእርሻ ስፍራ ሲሯሯጡ የተመለከቱ አርሶ አደሮች ለእስራኤል ባለሥልጣናት ጥቆማ አድርሰዋል።

ፍልስጤማውያኑ እስረኞች ተረዳድተው ከመጸዳጃ ክፍላቸው ጀምረው የቆፈሩት ዋሻ ከእስር ቤቱ ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ነው።

ጄሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ከሆነ እስረኞቹ ዋሻውን ለመቆፈር ያረጀ ማንኪያ ተጠቅመዋል። የእስራኤል ደኅንነት ኤጀንሲ በበኩሉ እስረኞቹ ከእስር ቤቱ ውጪ ካለ አካል ድጋፍ ሳያገኙ አይቀርም ብሏል።

የእስራኤል ማረሚያ ቤት አገልግሎት ኃላፊዎች የእስረኞቹን ማምለጥ፤ "ከፍተኛ የደኅንነት ውድቀት ነው" ሲሉት የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች ደግሞ፤ "ጀግንነት" ሲሉ አወድሰዋል።

ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ዌስት ባንክ አልያም ጆርዳን እንዳይገቡ የእስራኤል ፖሊስ መንገዶችን በመዝጋት ፍተሻ እያካሄደ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ዌስት ባንክ እና ጆርዳን ከእስር ቤቱ 14 ኪሎ ሜትሮች ብቻ እንደሚርቁ ተመልክቷል።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ‘ሱና‘ ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓጉዘው ሱዳን ስለገቡ ጦር መሳሪያዎች የተዛባ ዘገባ ሰርቶ ነበር:: ሱና መሳሪያው "[በሱዳን] መንግሥት ላይ ወንጀል ለመፈጸም" ጥቅም ላይ ሊውል ነበር የሚል ጥርጣሬ አለ ሲል ገልጽዋል:: የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ካርቱም ከገቡ በኋላ ተይዘዋል ስላለው የጦር መሳሪዎች ምርመራ…
#Update

“በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጭነው ወደ ካርቱም የገቡ “ጦር መሳሪያዎች ተያዙ” መባሉ ከእውነት የራቀ ነው" - የሱዳን የሃገር ግዛት ሚኒስቴር

የሱዳን የሃገር ግዛት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጭነው ወደ ካርቱም የገቡ “ጦር መሳሪያዎች ተያዙ” መባሉ “ከእውነት የራቀ” ነው ያለስ ሲሆን የጦር መሳሪያው ተገቢው የጉምሩክ ክሊራንስ ሂደት መጀመሩንም ገልጸዋል::

ሚኒስቴሩ የሱዳን ጉሙሩክ ባለስልጣናት ያዝን ያሉት “ጦር መሳሪያ” ምንም ዐይነት የህግ ግድፈት እንደሌለበት አስታውቋል::

ባለስልጣናቱ ያዝን ያሉት “ጦር መሳሪያ” ራሳቸው በሰጡት ህጋዊ ፈቃድ ተጓጉዞ ወደ ካርቱም የገባ እንደሆነ የጦር መሳሪያዎቹ ባለቤት የሆነውና ‘ዋዒል ሸምሰዲን’ የተባለው የንግድ ተቋም ገልጸዋል::

የተቋሙ ጠበቃ የሆኑት ሲራጁዲን ሃሚድ ተያዙ የተባሉትን ጦር መሳሪያዎች በህጋዊ መንገድ እንደገቡ መግለጻቸውን የአል ዐይን ኒውስ ዘግቧል::

‘ዋዒል ሸምሰዲን’ ለሲቪል ግልጋሎት የሚውሉ ጦር መሳሪያዎችን ከውጭ የማስገባት እና የመነገድ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው፡፡

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/Al-Ain-News-09-06

Credit : AL AIN NEWS (አል ዓይን ኒውስ)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ22 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 6,679 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,190 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 22 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 727 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ትላንት 904 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

ነገ ባህር ዳር ከተማ የኢትዮጵያ እና የዚምባቡዌ የእግር ኳስ ፍልሚያን ታስተናግዳለች።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደጋና አቅንታ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት መሸነፏ ይታወሳል፤ የነገው ጨዋታ ሁለተኛው የማጣሪያ ጨዋታ ነው።

ይህን ጨዋታ የምታስተናድገው ደግሞ ውቢቷ ባህር ዳር ከተማ ናት።

የነገው ጨዋታ ኮሚሽነር ከኤርትራ ፤ የዳኞች ገምጋሚ ከኮትዲቫር ፤ አራቱም የጨዋታ አመራሮች ከሲሼልስ ናቸው።

በነገው ፍልሚያ ብሄራዊ ቡድናችን የተለመደውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሚለብስ ይሆናል።

የኢትዮጵያና የዚምባቡዌ ብሄራዊ ቡድኖች በነገው እለት የሚያደርጉት ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ጥያቄ ቢያቀርብም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፍቃደኛ ባለመሆኑ ጨዋታው ያለተመልካች እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነት ሊኖር ይችላል ሀገር ግን እስከመጨረሻው ድረስ ሀገር ናት ፤ እናት ናት 🇪🇹 !

የኢትዮጵያ ስም በክፉ ሲነሳ ሮጠው ቀድመው ለብዙሃን ለማሰራጨት የሚጥሩ በእግጥም ለኢትዮጵያ ክፉ የሚመኙ አካላት እንዳሉ በተለያየ ጊዜ መመልከት ተችሏል።

እንደማሳያ ትላንት SUNA/ሱና የሰራውን ፍፁም ከእውነት የራቀ፣ ሀሰተኛ፣ የተዛባ እና እጅግ በጣም አደገኛ ዘገባ አንድ እና ሁለቴ ሳያጣሩ የኢትዮጵያ ስም በክፉ መነሳቱን አንድም በጥላቻ፣ በሌላ መልኩ ለራሳቸው የተቃውሞ ሀሳብ ማጠናከሪያ ለመጠቀም ሲሯሯጡ የነበሩ ሰዎች ታይተዋል።

መረጃው ሱና ባወጣበት ቅፅበት የኢትዮጵያ አየር መንገድን አንዳች ምላሽ ሳይጠይቁ/የአየር መንገዱን መግለጫም ሳይጠብቁ የአንዱን ወገን እጅግ አደገኛ ዘገባ በድስታ ሲያሰራጩ የተዩ ብዙ ናቸው።

ይህንን ካደረጉት መካከል የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚፅፉ የውጭ አክቲቪስቶች ፣የሀገር ውስጥ አክቲቪስቶች ፣ ማህበራዊ ሚዲያን መሰረት ያደረጉ ሚዲያዎች ይገኙበታል።

አንዳዴ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተከታይ ለማፍራት እና የራሳቸውን ስሜት ለማጋራት፣ የሚፈልጉትን አጀንዳ ለማራመድ ሲሉ በአግባቡ መጣራት ያለባቸውን የተለያዩ ዘገባዎች አንድ ጊዜም መለስ ብለው ሳያዩ ለህዝብ የሚያጋሩ ሀገር ከሌለ እነሱም እንደሌሉ አውቀው መጠንቀቅ አለባቸው።

መንግስትን ፣ ፓርቲን መደገፍ አለመደገፍ ፣ የመንግስት ተቃዋሚዎችን ፓርቲዎችን መደገፍ አለመደገፍ ምንም ችግር የለውም ሚሊዮኖች ለሚኖሩበት ሀገር ፣ ላሳደች ሀገር፣ ክፋ ማሰብ እጅግ አሳፋሪና አደገኛ ድርጊት ነው።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

"ዴልታ" የተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገኘ።

አደገኛው የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች፣ የሚሞቱና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በጣም አሻቅቧል” ብለዋል።

አዲሱ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ ዝርያ መሆኑን ገልፀዋል።

ክትባት በየጤና ተቋማቱ በመገኘት እንዲወስዱ፣ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከሁሉም ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚጠበቅም አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ሺህ 300 ሰዎች በወረርሽኙ ተይዘዋል።

እስካሁን በአገሪቱ 313 ሺህ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።

በኮቪድ ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔውም ከ1 በመቶ ወደ 20 በመቶ አሻቅቧል ፤ ባለፈው ሳምንት 118 ሰዎች ሞተዋል። #ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ተራዝሟል ? የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ግዜ አለመራዘሙን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፤ ፈተናው በጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል ማለታቸው አይዘነጋም። ሰሞኑን ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደተራዘመ…
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጥቅምት ወር አጋማሽ እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናው ከሚሰጥበት ቀን ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ለ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity ደርሰው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅናቸው የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ "የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ግዜ #አለመራዘሙን" በድጋሜ አረጋግጠዋል።

ሰሞኑን ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደተራዘመ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ #ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል።

"ምንም የተቀየረ ነገር የለም" ያሉት ዳይሬክተሩ ፤ "ፈተናው በጥቅምት ወር አጋማሽ ይሰጣል" ብለዋል።

ተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎችን ከካርድ / CARD ጋር በመቀናጀት በሚሰራው የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገፅ ይከታተሉ : https://t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
"ሀገር አቀፍ የፆምና የፀሎት ምህላ አዋጅ" የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲሱን አመት በሰላም ለመቀበል ያለመ ለ5 ቀናት የፀሎት መርሐግብር አወጀ። የፀሎት መርሐግብሩ ከጷግሜ 1 እሰከ 5 የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል። ጉባኤው አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ የሰላም ጥሪን በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። አገሪቱ ያጋጠማት ወቅታዊ ችግር በይቅርታና በፍቅር እንዲፈታ የተለያዩ እምነት…
የሀይማኖት አባቶች በመላ ሀገሪቱ ያወጁት የፀሎት እና ፆም ቀናት ከትላንት ጳጉሜ አንድ ጀምሯል።

የፀሎት እና ፆም መርሀግብሩ እስከ ጳጉሜ አምስት ድረስ ይቀጥላል።

ስለኢትዮጵያ እና ስለህዝቧ ሰላም ፣ ደህንነት የሚያሳስበው ፣ በችግር ላይ ያሉ ዜጎችም መፍትሄ ያገኙ ዘንድ፣ ሀገር ሰላም እንድትሆን ፣ ደም መፋሰሱ፣ መሳደዱ እንዲገታ፣ የእናቶችና ህፃናት ፣ የአረጋውያን መንገላታት መጎሳቆል እንዲቆም ሁሉም በየሀይማኖቱ ፈጣሪው የሚማፀንባቸው ቀናት ናቸው።

የሀይማኖት አባቶች ያወጁት የፆም እና ፀሎት ቀናት አዲሱን አመት በሰላም እንድንቀበል ያለመ ነው።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ የሀማኖቶት ተቋማት ጉባኤ ባቀረበው የሰላም ጥሪ አገሪቱ ያጋጠማት ወቅታዊ ችግር በይቅርታና በፍቅር እንዲፈታ የተለያዩ እምነት የሚከተሉ ዜጎች በየሐይማኖታቸው የልዩ ፀሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረቡ አይዘነጋም።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር መቼ ይፈፀማል ? የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2013 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የአርቲስቱ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል። የአርቲስቱ የአስክሬን ሽኝት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን መገለፁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ከትናንት በስቲያ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ባደረበት…
#Update

የአንጋፋው ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በአንጋፋው ድምፃዊ የክብር ሽኝት የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ቤተሰቦቹ፣ አድናቂዎቹ፣ የሙያ ባልደረቦቹ ተገኝተዋል።

ከመስቀል አደባባዩ የስንብት መርሃ ግብር በኋላ የቀብ ሥነ ሥርዓቱ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈፀም እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ።

@tikvahethiopia      
ቁጥሮች ...

ከነሃሴ 15 ቀን 2013 እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ኢትዮጵያ 3,379 ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን መልሳልች።

ወደሀገራቸው ከተመለሱት መካከል 1,094 ህፃናት ናቸው።

አሁንም የራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ሲሉ ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱና እጅግ በጣም በከፋ ችግር ላይ የሚገኙ ወንድም እህቶቻችን በሳዑዲ አረቢያ ይገኛሉ፤ ዜጎቻችን ለመመለስ የሚሰራው ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

በሌላ ቁጥራዊ መረጃ ፦ ነሃሴ 28 ቀን 2013 እና ነሃሴ 29 ቀን 2013 ዓ/ም ከሊባኖስ 82 ዜጎቻችን (ሁሉም ሴቶች) እንዲሁም የመን፣ ኤደን ከተማ 120 ዜጎቻችን ለሀገራቸውን በቅተዋል።

ሀገር 🇪🇹 በከፋን ፣ በችግራችን ፣ በጉድለታችን ጊዜ መሸሸጊያችን ፤ መጠለያችን ናት ፤ የሁላችንም ዞሮ መግቢያ ናት፤ ሰላሟን ፣ ደህንነቷን፣ ፍቅር እና አንድነቷን ብቻ እንመኝላት።

በስደት ላይ የምትገኙ ወንድም እና እህቶቻችን መጪው አዲሱ አመት ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት ፤ በችግር ላይ የምትገኙም ለሀገራችሁ 🇪🇹 የምትበቁበት ዓመት እንዲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል።

NB : ቲክቫህ ሁሉንም ቁጥሮች የሰበሰበው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ነው።

@tikvahethiopia