TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በተጠናቀቀው የህዳሴ-ደዴሳ የባለ 500 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተለያየ ምክንያት የተሰበሩትን ኢንሱሌተሮች በአዲስ የመተካት ስራ ተጀመረ።

የምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ቶማስ መለሰ እንደገለፁት ኢንሱሌተሮቹን የመተካት ሥራው የተጀመረው በቅርቡ የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መስመሩን ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡

ኢንሱሌተር የመቀየር ሥራው ከህዳሴ- ደዴሳ - ሆለታ ድረስ ከተዘረጋው መስመር መካከል እስከ ደደሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ ባለው በሁለቱም የማስተላለፊያ መስመሮች (ሎት1ና ሎት2 ) በተተከሉ ምሶሶዎች ላይ የሚከናወን መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በመስመሩ ላይ በተካሄደለት የፍተሻ ስራ መሠረት በሁለቱ መስመሮች ላይ ከተተከሉት 1 ሺ 535 ምሶሶዎች መካከል በ3 መቶ 12 ምሶሶዎች ላይ የሚገኙ ኢንሱሌተሮችን በሌላ የመቀየር ስራ እንደሚከናወን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በቀጣይ ከደደሳ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ሆለታ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው ባለ 500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በተመሳሳይ የመቀየር ሥራ እንደሚከናወን ተጠቁማል።

የደደሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ስምንት ባለ 33 እና ሁለት ባለ 132 እንዲሁም አንድ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ በአሁኑ ሠዓት ሁለት ባለ 33 እና አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ለነቀምቴ ከተማና አካባቢው ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የህዳሴ ደደሳ ሆለታ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ቻይና ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጅ በተሰኘ ኩባንያ መገንባቱ ይታወሳል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክኃይል

@tikvahethiopia
በኦሮሚያ ሆሮ ጉድሩ ዞን 27 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

የሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዮት በቀለ ፥ 27 የጸጥታ ኃይሎች ትናንት ሐሙስ በታጣቂዎች መገደላቸውን ገለፁ።

አስተዳዳሪው/፥ ከተገደሉት የጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ጸጥታ ኃይሎቹ ላይ ጥቃቱ የተነሰዘረው ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ገደማ ሲሆን ድርጊቱ የተፈጸመው በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ የ "ሸኔ" ታጣቂዎችን በማሰስ ላይ ባሉበት ወቅት እንደነበር አቶ አብዮት አስረድተዋል።

የጸጥታ ኃይሎቹ በሁለት ዙር ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸውን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው አቶ አብዮት ፥ ጥቃቱ የተሰዘረው በመጀመሪያው ዙር በተጓዙ 47 የፌደራል ፖሊስ እና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ላይ ነው ብለዋል።

ከስምንት አመታት በላይ ያገለገሉ እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሁለት ሚሊሺያዎች ትናንት ሐሙስ ሰኔ 3፤ አካዩ ቀበሌ በተባለ ቦታ በተፈጸመው ጥቃት 24 የጸረ ሽብር ፖሊስ እና ሁለት የሚሊሺያ አባላት፤ በድምሩ 26 የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ጥቃቱ የተሰነዘረው ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑ የሚገልጹት የሚሊሺያ አባላት ፤ በጥቃቱ ስምንት የጸጥታ ኃይሎች ቆስለው ወደ ሻምቡ አጠቃላይ ሆስፒታል “ሪፈር” መባላቸውን ለ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ደረገፅ ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ ethiopiainsider.com/2021/3536/

@tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፤ ጅዳ #ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

ለፅ/ቤቱ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦
- በጄዳ ፣
- መዲና ፣
- ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ።

በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

በሳዑዲ አረቢያ በተጠቀሱት ከተሞች የምትገኙ የቲክቫህ አባላት በሙሉ የቆንስላ ጽህፈት ቤቱን የጥንቃቄ መልዕክት #በአፅንኦት እንድትወስዱ ፣ እራሳችሁን እንድትጠብቁ ፤ ጥንቃቄም እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,568 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 214 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 273,892 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 4 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,235 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,932,522 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#Somali

የሶማሌ ክልል ልማት ማህበር ማጠቃለያ መርሃግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድን ጨምሮ የአዲስ አበባ እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሶማሊ ባህል ማዕከል ግንባታ 5 ሺህ ካሬ ሜትር ስኩዌር ካርታን አስረክቧል።

Photo Credit : SRMMA

@tikvahethiopia
የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ፦

- የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች
- አልባኒያ፣
- ብራዚል፣
- ጋቦን እና ጋና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታ ምክር ቤት በተለዋጭ አባልነት ዛሬ ተመርጠዋል፡፡

ሀገራቱ ኤስቶኒያ፣ ኒጀር፣ ቱኒዚያ ፣ ቬትናም እንዲሁም ሴንት ቪንሴንት ኤንድ ዘ ግሬናዲንስን የተኩ ናቸው።

በፀጥታው ምክር ቤት አሜሪካ ፣ ሩሲያ ፣ ቻይና ፣ ብሪታንያ እና ፈረንሣይ ቋሚ አባላት ሲሆን 10 ቋሚ ያልሆኑ አባላትን አሉት። በአጠቀላይ ምክር ቤቱ 15 አባላት ነው ያሉት።

#Reuters

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፤ ጅዳ #ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል። ለፅ/ቤቱ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦ - በጄዳ ፣ - መዲና ፣ - ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ኢትዮጵያውያን…
#Update #SaudiArabia #Attention

"...የአካል ወይም ንብረት ጉዳት የደረሰባችሁ ዜጎች ያላችሁን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽ\ቤቱ ማቅረብ ትችላላችሁ" - በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ

የሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ኃይሎች በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተከትሎ ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ማስተላለፉ ይታወቃል።

በዚህ ሂደት በተለይ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ኖሯቸው በህግ አስከባሪ አካላት ከመጠን ያለፈ ኃይል አጠቃቀም ምክንያት የአካል ወይም የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ያላቸውን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

አሁንም #ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲቀጥሉ የቆንስላ ጽ\ቤቱ በድጋሚ የጥንቃቄ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ዛሬ ማምሻውን የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያን የወደፊት አካሔድ ለመወሰን እና የአገሪቱን ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት እና መላ ኢትዮጵያውያን ከምርጫ በኋላ ለሚካሔድ አካታች የፖለቲካ ብሔራዊ ውይይት ቁርጠኛ እንዲሆኑ ነው የባይደን አስተሳደር ጥሪ ያቀረበው።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሚመሩት የአሜሪካ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሠራተኞቹ ጥረቶች እውቅና ቢሰጥም ፤ 6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚካሔድበት ከባቢ “አሳሳቢ ነው” ብሏል። 

የአሜሪካ መንግስትን አቋም የሚያንጸባርቀው መግለጫ ዛሬ ማምሻውን አንቶኒ ብሊንከን በሚመሩት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኩል ነው የወጣው።

የባይደን አስተዳደር የኢትዮጵያ ምርጫ አሉበት ያላቸው ፈተናዎች ፦
- የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስር፣
- የገለልተኛ ሚዲያ መዋከብ፣
- የአካባቢያዊ እና ክልላዊ መንግሥታት ወገንተኝነት እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ በብሔሮች እና በማህበረሰቦች መካከል የተቀሰቀሱ ግጭቶች ለነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንቅፋት ናቸው ብሏል።

"በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች በክልሎች እና ብሔሮች መካከል ያለው ልዩነት መካረር የአገሪቱን አንድነት እና የግዛት ሉዓላዊነት ያሰጋል” ያለው የአሜሪካ መንግስት #ከምርጫው_በኋላ መፍትሔ ሊፈለግ እንደሚገባ አሳስቧል።

የአሜሪካ መንግስት ፥ “ከምርጫው በኋላ ያለው ጊዜ #ኢትዮጵያውያን ተባብረው እነዚህን ልዩነቶች ለመጋፈጥ ኹነኛ ወቅት ነው” ብሏል።

የአሜሪካ መግለጫ : www.state.gov/elections-in-ethiopia/

#EthiopiaInsider #SpokespersonNedPrice #Ethiopia

@tikvahethiopia
#UNICEF

የተመድ ህፃናት መርጃ ድርጅት ( ዩኒሴፍ ) በትግራይ 33 ሺህ የሚሆኑ ህፃናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት በሞት አደጋ ላይ መሆናቸውን አስታወቀ።

ዩኒሴፍ እርዳታ የሌላቸው አካባቢዎች የእርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒሴፍ ቃለ አቀባይ የሆኑት ጄምስ ኤልደር ፤ "በአሁኑ ወቅት የዳሰሳ ጥናት ከተደረገባቸው 20 በመቶው ሕዝብ መካከል 350 ሺህ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ላይ መሆናቸውን ማሳየቱ ይፋዊ በሆነ መልኩ ረሃብ (ፋሚን) አለ ብሎ ለማወጅ ከተቀመጠው በታች ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሰዎች እየሞቱ በቃላት ባንጫወት ጥሩ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

33 ሺህ የሚሆኑ ህፃናትና ጨቅላዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት ምክንያት በህመም አፋፍ ላይ ናቸው። በሞት አደጋም ላይ ናቸው በማለት ዩኒሴፍ አስጠንቅቋል።

ከሰሞኑን ተመድ ባወጣው ሪፖርት ከ350 ሺህ በላይ የሚሆኑት የክልሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ በሚባል ችግር ውስጥ ናቸው ብሎ ነበር።

የክልሉን ሁኔታ የገመገመው የተመድ ሪፖርት በክልሉ ያለው የምግብ ሁኔታን "ካታስሮፊ" በሚል ጉዳትን እንደሚያስከትል ፈርጆታል።

በዚህ ትርጉም መሰረት በአሁኑ ወቅት ቸነፈር (ረሃብ) እና ሞት እየተከሰተ ያለ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ሊዛመት እንደሚችል የሚገልፅ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር በአ/ አ የህሙማን ማዕከል ሊገነባ ነው።

የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር አስራ አምስት (15) ዓመታትን በኪራይ ቤት ውስጥ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የአዕምሮ ህሙማን ከጎዳና ላይ በማንሳት እንክብካቤ አድርጎላቸዋል። ከነዚህም ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩት ሙሉ ለሙሉ ድነው አሁን ሌሎችን በመርዳት ላይ ይገኛሉ።

ማህበሩ አሁን ያለበት ቦታ አመቺ ባለመሆኑ ህሙማኑ በጠባብ ግቢና ለአደጋ በተጋለጡ ባለ ሦስት ተደራራቢ አልጋዎች ላይ ከጎዳና ይሻላል በሚያስብል መልኩ በርካታ ዓመታትን ገፍተዋል።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የማህበሩ መስራች ሊቀ ህሩያን መለስ አየለ ከረጅም ጊዜ ደጅ መጥናት በኋላ በያዝነው ዓመት 3000 ካሬ ሜትር ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ማግኘታቸውን ነግረውናል። በዚህም ቦታ ላይ የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ለመገንባት ማቀዳቸውንም ነው የጠቆሙት።

አዲስ የሚገነባው ማዕከል ግንባታው ሲያልቅ ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ የአዕምሮ ህሙማንን እንዲሁም የሰራተኛ ማደሪያና ትላልቅ አዳራሾችንም ያካትታል ተብሎ መታሰቡን ሊቀ ህሩያን መለስ ገልጸዋል። ለፍጻሜውም የበርካቶችን ድጋፍ ጠይቀዋል።

ከዚህ የቦታ ፈቃድ በተጨማሪም " ኢትዮ ቴሌኮም " ለገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን አጭር የመልዕክት ቁጥር በነጻ ያቀረበ ሲሆን ፈቃደኛ ሰዎች በ '6860 ላይ Ok' በማለት የጌርጌሴኖን አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበርን ለመደገፍ አባል መሆን ይችላሉ ተብሏል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል የኮሌራ ክትባት በይፋ መስጠት ተጀመረ፡፡

ክትባቱ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስትቲዩት ከዓለም ጤና ድርጅትና ከዩኒሴፍ (UNICEF) ጋር በመተባበር ነው መሰጠት የተጀመረው።

የኮሌራ ክትባት ግብአት ለሁለት ሚሊየን ሰዎች በሽታው ሊከሰትባቸው በሚችሉ በ13 ወረዳዎች ክትባቱ ይሰጣል ተብሏል።

ክትባቱ በመጀመሪያው ዙር እስከ ሰኔ ዘጠኝ 2013 ዓ/ም ከአንድ አመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ይሰጣል።

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኝ የክትባቱ ማእከላት እየሄደ እንዲከተብ ጥሪ ማቅረቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውስኔ መራዘም ቅሬታ አስነሳ። የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ዉሳኔ የመራዘሙን ውሳኔ እንደማይቀበሉ የካፋ እና የዳውሮ ዞኖች ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ዉሳኔ እንዲራዘም መወሰኑን ተከትሎ ከካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዉሳኔውን ተቃውሟል። የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳሻው ከበደ በሰጡት መግለጫ ''ለህዝበ ውሳኔው አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ…
"...ቦርዱ የህዝበ ውሳኔውን ቀን ለማራዘም ያሳለፈውን ውሣኔ ዳግም ሊመለከተው ይገባል" - የደቡብ ምዕራብ ክልል አደራጅ ዓብይ ኮሚቴ

የደቡብ ምዕራብ ክልል አደራጅ ዓብይ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔ ቀን ለማራዘም ያሳለፈውን ውሣኔ ዳግም እንዲመለከት ጠይቋል።

ዓብይ ኮሚቴው ይህንን የጠየቀው የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተከትሎ በአዲስ አበባ ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው።

ኮሚቴው የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሣኔው ቀደም ብሎ በተያዘለት ጊዜ ከ6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ጋር እንዲፈፀም ጠይቋል።

የመንግስት ውሣኔና አቅጣጫ ተከትሎ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ህዝበ ውሣኔው በተቀመጠለት የጊዜ ሠለዳ እንዲካሄድ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አስታውሷል።

የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ብሏል።

የአካባቢው ህዝቦች የዘመናት ጥያቄያቸው ላይ ውሳኔ ለማሳረፍ የምርጫውን ቀን እየተጠባበቁ ይገኛልም ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሪፌረንደሙን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለማስፈፀም ላሳየው ተነሳሽነት እና የተግባር እንቅስቃሴ ዓብይ ኮሚቴው ምሥጋና ማቅረቡን www.waltainfo.com ዘግቧል።

ትላንት የካፋ ፣ የዳውሮ እንዲሁም የቤንች ሸኮ ዞኖች የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተቃውመው መግለጫ ማውጣታቸው አይዘነጋም።

የዳውሮ፣ ካፋ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ ዞኖችና ኮንታ ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል እንዲመሰርቱ መወሰኑ ይታወሳል።

@tikvahethiopia