TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ልማት አመራሮች በትግራይ ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ተሰምቷል። ውይይቱ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ እንደሆነ ይጠበቃል። ስብሰባው በትግራይ ክልል ባለው የሰብዓዊ ቀውስና ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ማዕቀፍ ውስጥ አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ…
#Update
ዛሬ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብዓዊ ቀውስን በተመለከተ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት (EU) ከፍተኛ ባለስልጣናት በኦንላይን ውይይት አድርጋዋል።
የዛሬው ውይይት ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በቀጥታ ተላልፏል።
በውይይቱ እነማን ተሳተፉ ?
- በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ፣
- የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር፣
- የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ
- የአውሮፓ ሕብረት የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌነርቼክ
- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ተሳታፊ ሆነውበታል።
እነንማን ምን አሉ የሚለውን በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-06-10
በሌላ በኩል በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዛሬ በዚህ መድረክ ባሰሙት ንግግር ነገ የቡድን ሰባት (G7) አገራት ሰብሰባ እንደሚኖራው ገልጸው ፤ ከG7 አገራት አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ጉዳይም የተባበሩት መንግሥታት (UN) የጸጥታ ም/ ቤት አጀንዳ መሆን አለበት ብለዋል። ፌልትማን ረሃብ የጦርነት መሳሪያ ተደርጎ መወሰዱ የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት አጀንዳ ያደርገዋል ሲሉ ተደምጠዋል።
ተኩስ እንዲቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረስ እና የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ጫና ማድረጋችንን መቀጠል አለብን ብለዋል።
#BBC
@tikvahethiopia

'የNISS ጥቆማ መቀበያ 910 '
ዜጎች ማንኛውም አይነት ለሀገርና ህዝቦች ሰላምና መረጋጋት እንቅፋት የሚሆኑና ከሀገራዊ ምርጫው ጋር በተያያዘ የደህንነት ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በአቅራቢያቸው ሲመለከቱ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አጭር የጥቆማ መስጪያ ቁጥር " 910 " በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ተገልጿል።
#EPA

#BREAKING የኢትዮጵያ ብሄራቂ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14/2013 የሚካሄደው 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ በሶማሌ ክልል እንደማይካሄድ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ፥ ለምርጫው በተያዘለት ጊዜ አለመካሄድ የህትመት ችግር እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎችን በምክንያትነት አስቀምጠዋል። የክልሉ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት እጩዎች…
#UPDATE #ምርጫ2013
ከሶማሌ ክልል በተጨማሪ በሐረሪ ክልል ሰኔ 14 ቀን 2013 ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ እንደማይካሄድ ተገልጿል።
በሁለቱም ክልሎች ምርጫው ጳጉሜ 1 የሚካሄድ እንደሚሆን ተገልጿል።
በሶማሌ ክልል ምርጫው የተራዘመበት ምክንያት ከዚህ ቀደም በመራጮች ምዝገባ ላይ በታዩ ቅሬታዎች ምክንያት ምርጫው እንደማይደረግ ከተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች በተጨማሪ አሁን ላይ በተፈጠረው የህትመት ችግር መሆኑ ተጠቅሷል።
ቦርዱ በትላንትናው ዕለት 54 የምርጫ ክልሎች ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት እንደሚያስፈልጋቸው ገልጾ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በድጋሜ ህትመታቸው ተጠናቆ ለሰኔ 14ቱ ምርጫ የሚደርሱትን መለየቱን ዛሬ አስታውቋል።
በቀጣይም የህትመት ሁኔታው እየታየ ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፥ ቀጣይ ሂደቶችን በተከታታይ አሳውቃለሁ ብሏል።
#TikvahFamily

#NewsAlert
የኦሮሚያ ፖሊስ ከሌሎች ፀጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር 95 የ "ኦነግ ሸኔ" ታጣቂ ቡድን አባላትን መደምሰሱን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳወቀ።
የምስራቅ ኦሮሚያ እና የደቡብ ኦሮሚያ ዞን ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ በመጣመር ከተለያዩ ጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ለተከታታይ 4 ቀናት በልዩ ሁኔታ ኦፕሬሽን ተካሂዷል ሲል ገልጿል።
በዚህ ኦፕሬሽን ህዝቡን በመዝረፍ፣ በማሰቃየት እና በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል የነበረ ያለውን የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ 95ቱ ተደምስሰዋል ብዙዎቹን ቁስለኛ ሆነዋል ብሏል።
ልዩ የነው የተባለው ኦፕሬሽን ስራ የተሰራው በደቡብ ኦሮሚያ በጉጂ ዞን እና በቦረና ዞን ሲሆን ግንቦት 24 ፣ ግንቦት 25 ፣ ግንቦት 26 ፣ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ነው ተብሏል።
በኦፕሬሽኑ ሙት እና ቁስለኛ ከሆኑት የታጣቂ ቡድኑ አባላት በተጨማሪ ብዛት ያላቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መማረኩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።
ፖሊስ ማረኩኝ ካላቸው የጦር መሳሪያዎች መካከል ፦ ብሬን፣ ክላሽ ፣ SKS (ኤስ ኬ ኤስ) M14 (ኤም14) ይገኙበታል።
በተጨማሪም፦ ሞተር ሳይክሎች፣ የተለያዩ መድኃኒቶች፣ የምግብ ሬሽን ኮሾሮ፣ ፓስታ፣ እና የተለያዩ የምግብ እቃዎችን መማረኩን ገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ ኦፕሬሽኑ እንዲሳካ ላደረገው ህዝብ ምስጋና አቅርቧል።
በተጨማሪ የሶማሌ ክልል ፖሊስ በተለይ የዳዋ እና ሊበን ዞን ፖሊሶች ላደረጉት ትበብር ምስጋና አቅርቧል በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ።

የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ?
ወደ #ኤርትራ ለሥልጠና ተልከው የነበሩ በሺዎች ሚቆጠሩ የሶማልያ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ በተደረገው ውጊያ ተካፋይ ሆነዋል በሚል፣ በዚህ ሳምንት በወጣው ሪፖርት የተነሳ በሶማልያ መንግሥት ላይ የሚደረገው ግፊት እያየለ መምጣቱ ተነግሯል፡፡
የልጆቻቸው አድራሻ የጠፋባቸው የወታደሮቹ ቤተሰቦች የሱማሊያ ፕሬዚዳንት የሆኑትን መሀመድ አብዱላሂ መሀመድን (ፈርማጆን) ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን እሳቸው ግን ሪፖርቱን አስተባብለዋል፡፡
ቪኦኤ እንደዘገበው የተወካዮቹ ምክር ቤት ኮሚቴ የወታደሮችን አድራሻ በሚመለከት ምርመራ እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡
በተባበሩት መንግስታት (UN) የሰአብአዊ መብት ጉባኤ በዚህ ሳምንት የወጣው ዘገባ እንዳመለከተው “ለሥልጠና ወደ ኤርትራ ተልከው የነበሩ ወታደሮች በኢትዮጵያው የትግራይ ውጊያ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡”
የሶማልያ መንግሥት ግን ወታደሮቹ ትግራይ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን አስተባብሏል፡፡
የሱማሊያ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ኦስማን ዱቤ ትላንት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ከሱማሊያ ወታደሮች ጋር የሚወጡት መረጃዎች ሀሰተኛ፣ መሰረተቢስ አሉባልታ፣ እና ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ ነው ብለዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/SOMALIA-06-11

#MarkLowcock
የተባበሩት መንግስታት (UN) የሰብአዊ ጉዳዮች ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ "በሰሜን ኢትዮጵያ ረሃብ አለ" አሉ።
ይህን ያሉት በተባበሩት መንግስታት የተደገፈ ጥናት ከተለቀቀ በኋላ ነው።
ሎውኮክ “አሁን ረሃብ አለ” ያሉ ሲሆን አክለው “ይህ በጣም የከፋ እየሆነ ነው” ብለዋል።
የተመድ ጥናቱ እንዳመለከተው በጦርነት በተጎዳው ትግራይ ክልል እንዲሁም በአጎራባች አማራና አፋር ውስጥ 350,000 ሰዎች “በከባድ ቀውስ” ውስጥ ይገኛሉ።
በትግራይ ክልል ውስጥ በተደረገው ውጊያ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ፤ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።
ያንብቡ : https://t.co/py8S8JgFjX?amp=1

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በUN የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ታዬ አፅቀስላሴ ተመድ (UN) "በትግራይ 350,000 ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል" ብሎ ይፋ ያደረገውን ሪፖርት ውድቅ አድርገዋል።
አምባሳደር ታዬ የተመድን ሪፖርት ውድቅ ያደረጉት ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ ተደራሽነትን እያገደ ነው በሚል የሚወጡትን ሪፖርቶችንም ውድቅ አድርገዋል።

ቻይና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውን ሙከራ ተቸች።
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ውይይት አድርገዋል።
በዚህ ውይይት ላይ አቶ ደመቀ ፥ መንግስት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች በተለይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላትን ለህግ እንዲቀርቡ፣ የሰብዓዊ ጥሰቶችን በተመለከ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት እንዲሰፋ መንግስት ተገቢ ምላሽ እየሰጠ ቢሆንም መሰረተ በመንግስት ላይ የሚሰነዘሩ መሰረተ ቢስ ትችቶች መቀጠላቸውን ለቻይናው አቻቸው አብራርተዋል።
ዋንግ ይ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያደርጋቸውን ጥረቶችን ማድነቃቸው ተነግሯል። በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውንም ሙከራ ተችተዋል።
አያይዘውም ቻይና በምትከተለው በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ መሆኑን ጠቅሰው ፣ አገራት የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው የመፍታት ልዑላዊ መብት ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በተደረገው ውይይት አቶ ደመቀ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እልባት እንደሚያገኝ ኢትዮጵያ እምነት ያላት መሆኑን ገልፀዋል።
ዋንግ ይ በበኩላቸው ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ አገራቸው ድጋፍ የምታደርግ መሆኑን ገልፀዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/Ethio-China-06-11
ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።
በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከጅቡቲው አቻቸው ጄኔራል ዘካሪያ ጋር በሁለቱ አገራት የመከላከያ ሰራዊት መካከል ትብብርን የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ሀገራቱ ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከጅቡቲው አቻቸው ጄኔራል ዘካሪያ ጋር በሁለቱ አገራት የመከላከያ ሰራዊት መካከል ትብብርን የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ሀገራቱ ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውስኔ መራዘም ቅሬታ አስነሳ።
የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ዉሳኔ የመራዘሙን ውሳኔ እንደማይቀበሉ የካፋ እና የዳውሮ ዞኖች ገለጹ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ዉሳኔ እንዲራዘም መወሰኑን ተከትሎ ከካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዉሳኔውን ተቃውሟል።
የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳሻው ከበደ በሰጡት መግለጫ ''ለህዝበ ውሳኔው አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ባለበት ወቅት እንዲራዘም መወሰኑ ከዞናችን አኳያ ምንም ዓይነት መሠረታዊ ምክንያት የሌለዉ'' ሲሉ ገልጸዋል።
ቦርዱ ጉዳዩን በድጋሚ በማጤን የህዝበ ዉሳኔዉ ቀደም ሲል በተያዘለት ሰኔ 14/2013 እንዲካሔድ እንዲያደርግ እንጠይቃለን ሲሉም አክለዋል።
የካፋ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይ ተሠማ በበኩላቸው ''ይህንን ህዝበ ውሳኔ የሚያስተባብሩ አመራሮች እንዲሁም የዞኖቹና የልዩ ወረዳው ከፍተኛ አመራሮች በጉዳዩ ላይ ሳይወያዩበት ብሄራዊ ምርጫ ቦርዱ በራሱና አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ህዝበ ውሳኔውን ማራዘሙ ተገቢነት እንደሌለው የዞኑ መንግሥት ያምናል'' ሲሉ ገልጸዋል።
የዳውሮ ዞን ደግሞ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የህዝበ ውሳኔው መራዘም ''የዞኑን ነባራዊ ሁኔታ ፈፅሞ ያላገናዘበ እንዲሁም ለሃገረ መንግስት ግንባታ የዜግነት ግዴታቸዉን ለመወጣት በሞራልም ሆነ በስነልቦና የተዘጋጁትን ህዝባችንን ቅሬታ ዉስጥ ያስገባቸዉ ሆኖ አግኝተነዋል'' ብሏል።
ዳውሮ ዞን ምርጫ ቦርድ ለጳጉሜ 1 ያዘዋወረውን የድምፅ መስጫ ቀን ቀድሞ በተያዘለት ቀን ሰኔ 14 እንዲያደርግ አሳስቧል።

Photo
#UPDATE #ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ ትላንት መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። ዛሬ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።
በዚህም በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14 ድምጽ መስጠት የማይቻልባቸው አካባቢዎችን ገልጿል። በእነዚህ አከባቢዎች ምርጫው ጳጉሜ 1 የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።
እነዚህም፦
- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - መተከል፣ ሺናሻ ልዩ፣ ካማሽ እና ዳለቲ
- በኦሮሚያ ክልል -ቤጊ፣ ሰኞ ገበያ፣ አያና፣ገሊላ፣አሊቦ፣ጊዳሚ፣ ኮምቦልቻ
- አማራ ክልል-ማጀቴ (ማኮይ)፣ አርጎባ ልዩ፣ ሸዋሮቢት፣ ኤፌሶን፣ ጭልጋ 1፣ ጭልጋ 2፣ ላይ አርማጭ፣ አንኮበር
- ደ/ብ/ብ/ህ ክልል - ሱርማ ልዩ ፣ ዲዚ ልዩ፣ ቀይ አፈር መደበኛ፣ ማጀት መደበኛ፣ ሸኮ ልዩ፣ ቴፒ
- ሐረሪ ክልል - ጀጎል ልዩ ፣ ጀጎል መደበኛ ናቸው።
በተጨማሪም የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ በፍጥነት ህትመት ሊከናወንባቸው የሚችልባቸውን መንገዶችን በመፈለግ ትላንት አስታውቆት የነበረውን 32 የምርጫ ክልሎች ወደ 27 ዝቅ ማለቱን ገልጿል።
በዚህም መሰረት በነዚህ 27 የክልል እና የተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ድምጽ የሚሰጠው ከላይ በተጠቀሰው ጷግሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ይሆናል።

ቦርዱ ከእውቅናው ውጪ የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ገለጸ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከእውቅናዬ ውጪ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ሁለት (2) ፤ በድሬደዋ ከተማ መስተዳድር ስድስት (6) እንዲሁም በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ሰባ አንድ (71) ምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተዋል ብሏል።
በእነዚህ ጣቢያዎች የተደረጉ የመራጮች ምዝገባዎች ህጋዊ አይደሉም ሲልም ቦርዱ ወስኗል።
ችግሩ የተፈጠረው የምርጫ አስፈጻሚዎች ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ የምርጫ ጣቢያዎችን በራሳቸው ስልጣን ከፍተው እንዲመዘገቡ በማድረጋቸው እንደሆነ ለማጣራት ችለናል። በደቡብ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን የተፈጠረው ችግር አስመልክቶም ምርጫ አስፈጻሚው ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል ተብሏል።
በትላንትናው ዕለት ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች የተረጋገጠ ቁጥር 37.4 ሚልዮን እንደሆነ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህ ቁጥር በሶማሌ ክልል በምርመራ የተነሳ የመራጮች ምዝገባ የታገደባቸው 14 ምርጫ ክልሎችን አይጨምርም ብሏል ቦርዱ።
በእነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ መራጮችን ድምፅ አሰጣጥ ሂደት አስመልክቶ ቦርዱ ከድምጽ አሰጣጥ ቀን በፊት ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

በተጠናቀቀው የህዳሴ-ደዴሳ የባለ 500 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተለያየ ምክንያት የተሰበሩትን ኢንሱሌተሮች በአዲስ የመተካት ስራ ተጀመረ።
የምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ቶማስ መለሰ እንደገለፁት ኢንሱሌተሮቹን የመተካት ሥራው የተጀመረው በቅርቡ የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መስመሩን ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡
ኢንሱሌተር የመቀየር ሥራው ከህዳሴ- ደዴሳ - ሆለታ ድረስ ከተዘረጋው መስመር መካከል እስከ ደደሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ ባለው በሁለቱም የማስተላለፊያ መስመሮች (ሎት1ና ሎት2 ) በተተከሉ ምሶሶዎች ላይ የሚከናወን መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
በመስመሩ ላይ በተካሄደለት የፍተሻ ስራ መሠረት በሁለቱ መስመሮች ላይ ከተተከሉት 1 ሺ 535 ምሶሶዎች መካከል በ3 መቶ 12 ምሶሶዎች ላይ የሚገኙ ኢንሱሌተሮችን በሌላ የመቀየር ስራ እንደሚከናወን ኃላፊው ጠቁመዋል።
በቀጣይ ከደደሳ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ሆለታ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው ባለ 500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በተመሳሳይ የመቀየር ሥራ እንደሚከናወን ተጠቁማል።
የደደሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ስምንት ባለ 33 እና ሁለት ባለ 132 እንዲሁም አንድ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ በአሁኑ ሠዓት ሁለት ባለ 33 እና አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ለነቀምቴ ከተማና አካባቢው ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል።
የህዳሴ ደደሳ ሆለታ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ቻይና ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጅ በተሰኘ ኩባንያ መገንባቱ ይታወሳል።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክኃይል