አቶ ታገሰ ጫፎ ከሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ ጋር ተወያዩ።
ትላንት ኢትዮጵያ (አ/አ) የገቡት ሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ጋር ተወያይተዋል።
አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎና የአሜሪካ ኮንግረሰ ሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ በቀጠናዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
በውይይቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ፦
- በህዳሴ ግድብ ፣
- በህግ ማስከበር ፣
- በሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት፣
- ከሱዳን ድንበር ማስከበር ሥራ ጋር ተያይዞ ያለበት ደረጃና እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የሙሌት ሥራ ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኗን አብራርተዋል።
ሙሌቱ የተፋሰሱን ሃገራት ጥቅም በማይነካ መልኩ እንደሚፈፀምም ገልፀዋል፡፡
ከ "ህግ ማስከበር" ጋር ተያይዞ የተከሰቱ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እየተሠራ ነው ብለዋል። የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ በመደረግ ላይ ነው ብለዋቸዋል።
ኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበር ጋር ተያይዞ በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለሴናተሩ ተናግረዋል፡፡
ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ምን አሉ ?
በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የተሰጠው ማብራሪያ በኢትዮጵያ ውሥጥ እየተደረገ ያለውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለመረዳት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው ተግባራት ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ሴናተር ጀምስ አረጋግጠዋል፡፡ #FDRE_HoPR
@tikvahethiopia

#Tigray
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከ90 በመቶ በላይ ህዝብ አስቸኳይ የሆነ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ሲል አሳወቀ።
የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በመጋቢት ወር በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ዞኖች ስርጭት ከጀመረ ጀምሮ ለአንድ ሚሊዮን ሰዎች የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ መስጠቱን ገልጿል።
በጥቅምት ወር ላይ በተነሳው ግጭት ሳቢያ በአጠቃላይ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ (91 % የትግራይ ህዝብ ማለት ነው) አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው WFP አሳውቋል።
ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ምላሽ የ203 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።
የWFP ቃል አቃባይ ቶምሶን ፒሪ ፥ "በክልሉ ረሃብ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይሸጋገር ያሳስበናል" ሲሉ ተናግረዋል።
በትግራይ እስከ 2021 መጨረሻ በረሃብ ምክንያት የሰዎች ሕይወት እንዳይጠፋ እና የተጀመረውን የምግብ ድጋፍ አጠናክሮ ለማድረስ የተጠየቀው ገንዘብ በአስቸኳይ ሊቀርብ እንደሚገባ WFP አሳስቧል።
የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሪፖርት : www.wfp.org/news/wfp-reaches-over-1-million-people-emergency-food-assistance-tigray

TIKVAH-ETHIOPIA
"...ጠ/ሚኒስትሩ በተለያየ ግዜ የተናገሩትን በመቁረጥና በመቀጠል የተፈጠረ ሀሰተኛ መረጃ ነው" - የጠ/ሚ ፅ/ቤት ዛሬ ምሽት መቀመጫነታቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ጠ/ሚ ዐቢይ በብልፅግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ የተነናገሩት ንግግር ሾልኮ ወጣ በሚል አንድ የድምፅ ቅጂ አሰራጭተዋል። እነዚህ ውጭ ሀገር ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ያሰራጩት ምስጥራዊ ነው የተባለው የጠ/ሚ ዐቢይ የድምፅ ቅጂ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከፊል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር 👆
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ የተባለውና ከብልፅግና ስብሰባ ተደብቆ/ሾልኮ ወጣ ተብሎ ውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ በሚሰሩ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨው የድምፅ ፋይል የተቀነባበረ መሆኑን የጠ/ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ትላንት አሳውቋል።
ከድምፅ ፋይሉ ጋር በተያያዘ በርካቶች የራሳቸውን ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን አንዳንድ ጋዜጠኞች እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም በቻሉት አቅም ተቆራርጦ ተቀጥሏል ያሏቸውን ንግግሮች አንድ ላይ አቅርበው ግንዝቤ ለመፍጠር መሞከራቸውን ተመልከትናል።
ሾልኮ ወጣ የተባለው የድምፅ ፋይል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተሰራጨ በኃላ በሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ አክቲቪስቶች ፣ የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም የሚታወቁ የውጭ ሀገር ግለሰቦች ሲቀባበሉት አምሽተዋል።
አንዳንዶቹ ቆየት ብለው ባደረባቸው ጥርጣሬ ፋይሉን ከገፃቸው ላይ ለማንሳት መገደዳቸውን ፅፈዋል።
ከላይ የተያያዘው የ41 ሰከንድ ቪድዮ በከፊል ጠ/ሚ ተናገሩ የተባሉትን ቃላት እና አረፍተነገሮች የያዘ እና እንዴት ቃላት እንደተቆራረጡ ለማሳያነት JONA.G በተባለ ግለሰብ የቀረበ ነው።

የጠፋች ልጃቸውን በሕይወት ለማግኘት ተስፋ ያደረጉት ቤተሰቦች አስከሬኗን ተረክበዋል !
የ16 ዓመቷ ተማሪ ፌቨን ዳዊት ከጠፋች ከ4 ቀናት በሗላ አስክሬኗ በሀዋሳ ሀይቅ ተገኘ።
ፌቨንና ጓደኛዋ ትዕግስት ዘወትር እንደሚያደርጉት ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ እየተዝናኑ ነበር በድንገት 2 ወጣቶች ካልተቀላቀልናችሁ ብለው አብረዋቸው የሆኑት።
ጥቂት ደቂቃዎችን አብረዋቸው ከቆዩ በሗላ በጀልባ ሀይቁ ላይ እንዝናና የሚል ጥያቄን ወጣቶቹ ያነሳሉ። 2ቱ ታዳጊ ሴቶች አለመፈለጋቸውን ቢገልፁም የወጣቶቹ ጉትጎታ የሚቻል ስላልነበር እሺ ለማለት ተገደዱ።
ጏደኛዋ ትዕግስት እንደምትለው የታዳጊ ሴቶቹ ቀጣይ ፈተና የነበረው የጀልባ ጉዞው ለየብቻ ነው የሚል ትዛዝ አዘል መመሪያ ከወንዶቹ ሲመጣ ነው።
ብዙ አታስቡ ተከታትለን ስለምንሄድ የሚል የማሳመኛ ቃል ሲደጋገም እሺታን መርጠው ጉዞ ጀመሩ።
አላማቸው 2ቱን ታዳጊ ሴቶች መነጠል እንጂ መዝናናት ስላልነበር አንደኛው ወጣት ፌቨንን ይዞ ጉዞ ይጀምራል..ጥቂት እንደተጓዙ ፌቨን የነ ትዕግስትን ጀልባ መመልከት ስላልቻለች ከወዴት ናችሁ የሚል ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለጓደኛዋ ታደርጋለች።
ከቆይታ በሗላ የት ናችሁ የሚል ጥያቄ ሳይሆን ለጓደኛዋ የድረሽልኝ መማፀኛ መልዕክት መላክ ጀመረች።
አሳዛኙ እውነታ ግን ፌቨን ከሀይቁ ሰምጣለች። ወጣቶቹ ከአካባቢው ተሰውረዋል።
ከ4 አስጨናቂ ቀናት በኋላ ቤተሰብ የ16 አመት ልጃቸውን አስክሬን ተረክበዋል።
የፌቨን አስክሬን ሲገኝ እጇ መጠምዘዙን ዓይኗ በቦክስ የመመታት ምልክት እንደነበረው በቦታው ቤተሰቦቿ ይናገራሉ።
2ቱን ወጣቶች ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።
ህይወትን አይታ ያልጠገበችው የ16 ዓመቷ ፌቨን ቤተሰቦች ፈጣሪ እውነቱን ያሳየን የፍትህ ያለህ ይላሉ!
(#በጋዜጠኛ_አዳነ_አረጋ)

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪ በመምስል ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ 1 ሺ የሚጠጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ፖሊስ የምርመራ ስራ እየሰራ ይገኛል።
ተጠርጣሪዎቹ ከህዝብ በደረሰ መረጃ መነሻ በማድረግ በ7 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ግንቦት 22 ቀን 2013 በተከናወነ የኦፕሬሽ ስራ የተያዙ ናቸው።
አጠቃላይ ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በዋና ዋና አደባባዮች እና በምሽት በሰዋራ ቦታዎች የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 999 ግለሰቦች ናቸው የተያዙት።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ፦
- አብዛኞቹ ማስቲሽና ቤንዚን በመጠቀም እራሳቸውን በማደንዘዝ የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን ሲያውኩ እነደነበሩ
- የትራፊክ መብራት ካስቆመው ተሽከርካሪ ላይ ስፖኪዮ ገንጥለው እንደሚወስዱ፣
- ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ላይ ሞባይል ስልክ፣ የአንገት ሃብል፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን ቀምተው እንደሚሰወሩ
- በተለይ ሴት አሽከርካሪዎች አደጋ ሳያደረሱባቸው አደጋ እንዳደረሱባቸው በማስመሰልና በማዋከብ ገንዘብ እንደሚቀበሉ፣
- የትራፊክ አደጋ ሲያጋጥም ልዩ ልዩ ስልቶችን በመጠቀም ንብረቶችን እንደሚሰርቁ በጥቅሉ ትኩረታቸውን በዋና ዋና አደባባይ የትራፊክ መብራት በያዘው ተሽከርካሪ ላይ አድርገው ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር ተረጋጧል።
በሌላ በኩል ግለሰቦቹ በምሽት የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር የተረጋገጠ ሲሆን በተለይ ደግሞ የውጪ ሀገር ዜጎችንና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን በማዋከብና በማስጨነቅ በከተማዋ መልካም ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲፈጥሩ ነበር።
የተሰወኑት ግለሰቦች ደግሞ የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውን የአ/አ ፖሊስ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

#Ethiopia #COVID19
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,600 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 249 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 271,790 አድርሶታል።
በ24 ሰዓት 6 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,171 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,822,343 ደርሰዋል።

#ጥንቃቄ
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመረጃ መበርበር #ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል የተባለ ቡድን አሁን ላይ 37 ሺህ በሚደርሱ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።
ይህን ያሳወቀው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ነው።
ተቋሙ ባወጣው መረጃ "ሳይበር ሆርስ ግሩፕ" የተሰኘው የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት ማድረጉ እንደተደረሰበት ገልጿል።
ቫይረሱ "ብላክ ፒራሚድ ዋር" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 37 ሺህ በሚደርሱ የሀገራችን ኮምፒውተሮች ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሁሉም የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

በዋግኽምራና አካባቢዋ ከትላንት ጀምሮ መብራት ተቋርጧል። በዋግኽምራና አካባቢዋ ከትላንት ግንቦት 21/2013 ዓ.ም ምሳ ሰዓት አካባቢ ጀምሮ የመብራት ሀይል አገልግሎት መቋረጡን ተሰምቷል። መብራት ሀይል አገልግሎት የተቋረጠበት ምክንያት ? የመብራት ኃይል የተቋረጠበት ምክንያት በተመለከተ የ ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ስለሺ ወርቁና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰቆጣ አገልግሎት…
#Update
ከቀናት በፊት በዋግኽምራና አካባቢው ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጡን የሚገልፅ መረጃ ተለዋውጠን ነበር።
አካባቢው አሁንም ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳላገኘ ተሰምቷል።
በዋግ ኽምራ በሚገኙ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የተቋረጠው ኤሌክትሪክ አገልግሎት መልሶ ለማገናኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው በአካባቢው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ኤሌክትሪክ የተቋረጠው በ3 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ስርቆት በመፈፀሙና በመውደቃቸው ነው ብሏል።
ወደስፍራው ለጥገና የተንቀሳቀሰው ቡድን የወደቁትን ምሰሶዎች መልሶ ለመትከል ከእሁድ ጀምሮ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል።
ከአንድ ወር በፊት ከአላማጣ እስከ ሰቆጣ በሚገኙት 269 ምሰሶዎች ላይ የፍተሻ ስራ መከናወን መጀመሩን የተገለፀ ሲሆን በስምንት የብረት ምሰሶዎች ላይ የስርቆት ሙከራ መፈፀሙን በማረጋገጥ ምሰሶዎቹ ከመውደቃቸውና ኤሌክትሪክ ከመቋረጡ በፊት መስተካከሉ ተነግሯል።
በአሁኑ የተፈፀመው ስርቆት በመስመሩ ውስጥ በሚገኙትና የፍተሻ ስራ ባልተካሄደባቸው 47 ምሰሶዎች ውስጥ በሶስቱ ነው።
በምሰሶዎቹ መውደቅ ሰቆጣን ጨምሮ አምደወርቅ፣ ዳህና ፣ በአበርገለ፣ በሰሀላ፣በዝቋላና በአካባቢያቸው ኤሌክትሪክ ተቋርጧል።
የዋግ ኽምራ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ኃይል የሚያገኙት ከአላማጣ ባለ 66 ኪሎቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ከሚወጣ መስመር ነው።
#EthiopianElectricPower

የአሜሪካ የቪዛ እቀባ የሚመለከተው ማንን ነው ?
አሜሪካ በኢትዮጵያ "ትግራይ ክልል ግጭት" ሳቢያ በተለያዩ የግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ባለቻቸው አካላት ላይ የቪዛ እቀባ ማድረጓ አይዘነጋም።
አሜሪካ እገዳውን ለመጣል የወሰነችው የትግራዩ ጦርነት እንዲቆም፣ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል እንዲሁም ተፋላሚ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ ያቀረብኩት ሀሳብ ተቀባይነት አላገኘም በሚል እንደነበር ይታወሳል።
የቪዝ ክልከላ የተጣለባቸው አካላት በግልፅ የስም ዝርዝራቸው ይፋ ባይሆንም እቀባው ግን የሚመለከተው ፦
- የቀድሞ እና የአሁን የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት
- የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወታደራዊ እና የፀጥታ ሹማምንት
- የአማራ ክልል የፀጥታ አካላት
- የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (TPLF) አባላትን ነው።
ትላንት መግለጫ ያወጣው በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከላይ ከተገለፁት ውጭ ሌሎች ለትምህርት፣ ለስራ፣ ለሌላም ጉዳይ ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ሰዎችን የቪዛ ጥያቄ እንደሚያስተናግድ አሳውቋል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚሰጥ የአ/አ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።
በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 23-25/2013 ድረስ እንደሚሰጥ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 23-25/2013 ድረስ እንደሚሰጥ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ፦
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ዲና ፥ የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ፣ ከአሜሪካ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት የመግለጫቸው ዋነኛ አጀንዳ ነበር፡፡
ቃል አቀባዩ ምን አሉ ?
- አሜሪካ የጣለችውን እገዳ በማስመልከት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ ነው የሚቀርብን” ማለት ያሰሙትን ንግግር በተመለከተ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ “ግለሰቦች የመናገር መብት አላቸው ፤ ይህም የግል አስተያየትና ስሜታቸው ነው” ብለዋል፡፡
- የኦሮሚያ ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ” ሲሉ የተናገሩት ንግግር የመንግስት አቋም ሳይሆን የግላቸው አስተያየት መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልፀዋል።
- በውጭ ጉዳይ ደረጃ “ጉዳዩን የማጋጋል ፍላጎት የለንም” ብለዋል ፤ “የተፈጠረው ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ በጋራ ወዳጆቻችን በኩል እየተነጋገርን ነው ያለነው” ሲሉ አሳውቀዋል።
- የሴናተር ጂም ኢንሆፌ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል የተፈጠረውን ጉዳይ ለመፍታት እየተኬደ ያለበት የዴፕሎማሲ መንገድ አካል ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል ፤ "የአሜሪካ አቋም ይቀየራል ብለን ነው የምናምነው ፣ መቼና እንዴት የሚለው ግን እነሱን የሚመለከት ነው” ብለዋል።
- ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መገናኘታቸውን እና “ውጤታማ ጉብኝት” አድርገዋል ብለዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-06-02
#አልዓይን

ኢትዮጵያ በሁለት ቀን ብቻ 743 ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ አስወጥታለች።
ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን በስፋት ወደ ሀገራቸው መመለስ ከጀመረች ወራት ተቆጥረዋል።
አሁንም ዜጎችን ወደሀገራቸው የመመለስ ስራ ተጠባክሮ የቀጠለ ሲሆን በሁለት ቀን ብቻ 743 ዜጎቿን ወደሀገራቸው መልሳለች።
አገራቸው ከተመለሱት ከ 743 ኢትዮጵያውያን መካከል 334ቱ #ከሪያድ ትላንት የተመለሱ ሲሆኑ 409ኙ ደግሞ በዛሬው ዕለት #ከጅዳ የተመለሱ ናቸው።