TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር የስራ አመራር ቦርድ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ !

@tikvahethiopia
በታች አርማጭሆ ወረዳ ህገ-ወጥ ሽጉጥ ተያዘ።

ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ሲሆን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ከተማ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ የታርጋ ቁጥር አማ 31398 በሆነ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) 98 (ዘጠና ስምንት) ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ተጭኖ ከአብራሀጅራ ወደ ጎንደር ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ነው መሆኑን ሲሉ የታች አርማጭሆ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳውቋል።

መረጃው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ ሚድያ ዋና ክፍል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Shire የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ምሽት በትግራይ ሽረ ከተማ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት አራት ካምፖች ከ500 በላይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በግዳጅ ይዘው መወሰዳቸውን 3 የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶ/ር እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል። የእርዳታ ሰራተኞቹና ዶክተሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኪናዎች ላይ ተጭነው ተወስደዋል ሲሉ ፤ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል። ከእርዳታ…
#Update

በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ ከሚገኙ ካምፖች በወታደሮች ተወስደው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ዜጎች ውስጥ አብዛኞቹ ትላንት ሀሙስ ምሽት መለቀቃቸውን ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ምንጮች ነገሩኝ በማለት ሲኤንኤን ዘግቧል።

አንድ የእርዳታ ሰራተኛ ለሲኤንኤን እንደገለፁት ፥ ወታደሮቹ እስረኞቹን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላት ናችሁ በማለት እንደያዟቸው ተናግሯል።

የእርዳታ ሰራተኛው ወታደሮቹ ይህን ያደረግነው ሰዎቹ የህወሓት አባላት ስለነበሩ ነው ብለው ሲነግሩን ነበር በማለት ለሲኤንኤን አስረድተዋል።

ከእስር የተለቀቀ አንድ ተፈናቃይ ፥ ተይዘው በቆዩበት ወቅት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ወታደሮች አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልጿል።

UNHCR በትግራይ ከተፈናቃዮች መጠለያ ወታደሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወስደዋል መባሉ እጅግ እንዳሳሰበው ስጋቱን ዛሬ ገልጿል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ባባር ባሎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ "ሁሉም ወገኖች በኃይል የተፈናቀሉትን ጨምሮ የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት እንዲያረጋግጡ ከዚህ ቀደም ያቀረብንውን ጥሪ አሁንም እንደግማለን" ብለዋል። ቃል አቀባዩ በዛሬ መግለጫቸው ከተያዙት ውስጥ የተወሰኑት መለቀቃቸውን ቢናገሩም ቁጥራቸውን ግን አልጠቀሱም።

የተቀሩት ወጣቶች አሁንም በእስር ላይ ይሁኑ ይለቀቁ ግልጽ እንዳልሆነ አክለዋል። ባሎች ፥ "ለጠፉ ሰዎች ዘመዶች ብቻ ሳይሆን በሽረ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በሙሉ ሁኔታው አሳዛኝና አሳሳቢ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
"...ግብጽ ዛሬ ላይ እያደረገች ያለችው የጀርባ ሴራ ቀድሞ በግብጽ የነበሩ የተለያዩ መንግሥታት ሲያደርጉት የኖሩት ነው" - ብልፅግና ፓርቲ

ብልፅግና ፓርቲ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው ፅሁፍ የግብጽን ጠላትነት ጊዜና ዘመን ሊሽረው አልቻለም ብሏል።

ግብጽ እንድትኖር #ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር መጥፋት ወይም መፍረስ አለባት ብለው የሚያምኑ ሰዎች ያሉባት ሀገር ነች የሚለው ፓርቲው ፥ "ኢትዮጵያ አልደረሰችባቸውም፤ አልነካቻቸውም" ሲል ይገልፃል።

ብልፅግና ፓርቲ ፥ "ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ የጋራ የተፈጥሮ ስጦታችን ስለሆነ በፍትሃዊነት እና እኩልነት መንገድ ሁላችንም ተጠቃሚ መሆን እንችላለን የሚል የጸና ሰላማዊ እምነት ያላት ሀገር ናት ፤ ግብጽ ዛሬ ላይ እያደረገች ያለችው የጀርባ ሴራ ቀድሞ በግብጽ የነበሩ የተለያዩ መንግሥታት ሲያደርጉት የኖሩትን ነው" ብሏል።

የአባይን ወንዝ እና ውሃ በተመለከተ ያስቀመጡትን ኢትዮጵያን አቅም የማሳጣት ትኩረቷን ለልማትና ዕድገት እንዳታደርግ በተለይም በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ እንዳትሰራ በሀገሪቱ ውስጥ የተረጋጋ ሰላም ልማትና ዕድገት እንዳይኖር ቀውስና ትርምስ መፍጠርን አጀንዳቸው አድርገው ለዘመናት ኖረዋል፤ ዛሬም እየሰሩ ነው ሲልም ያስረዳል።

ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ ባወጣው ፅሁፍ ፥ "ታሪኩ ሰፊና ረጅም ቢሆንም ግብጽ በተለያዩ ዘመናት በኢትዮጵያ ላይ ያላሴረችው ያልሰራችው ደባና ተንኮል የለም" ብሏል።

በጥንቱ ዘመን ግብጽ ሠራዊትዋን ወደ ኢትዮጵያ አዝምታ የአባይን ውሃ ከምንጩ ለመቆጣጠር ባደረገችው ጦርነት በኢትዮጵያውያን ጀግኖች የውጊያ የበላይነት ጉንዳና ጉራእ ላይ ስለመደምሰሳቸው መዛግብት ያስረዳሉ ሲል አስታውሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PP ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ መጀመሩን ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው፥ "አያሌ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚከናወነው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴያችን ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል" ብለዋል። @tikvahethiopia
#Update

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በተለያዩ ሀገራዊ እና ፓርቲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሁለት ቀናት መክሯል።

አሁን የለው ሀገራዊ እንዲሁም አለም አቀፋዊ ሁኔታ የምርጫ ዝግጅት ፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ሂደት እና የቀጣይ ክረምት የግብርና ስራዎች ስራ አሥፈፃሚ ኮሚቴው ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።

አሁን እየተፈጠሩ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎች ከሀገራዊ ሉዓላዊነት እና የጂዮፖለቲካዊ ለውጦች ታይተው በምን መልኩ መመራት አለባቸው የሚለውን የስራ አፈፃሚ ኮሚቴው ትኩረት ተደርጎበታል።

ብልፅግና ስብሰባውን በተመለከተ ምን አለ ? ያንብቡ : telegra.ph/Prosperity-Party-05-28

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,772 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 417 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 270,944 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 12 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,139 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,798,140 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መቼ ነው የሚጠሩት ?

የ2012 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ካወቁ ሁለት ወር ገደማ ሆኖታል።

እስካሁን ተማሪዎቹ መቼ ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ አያውቁም። 

መቼ ትምህርት እንደሚጀምሩም አያውቁም።

ቃላቸውን ለ "ጀርመን ድምፅ ሬድዮ የወጣቶች አለም" የሰጡ ተማሪዎች ቀድሞውንም ሳይማሩ ጊዜያቸው እንደባከነ ገልፀው ያለፉትን የትምህርት ዘመኖቹን መለስ ብሎ ሲቃኝ ብዙ ቁጭት ያለበት መሆኑን ያስረዳሉ።

በፊትም ትልቅ በደል ነበረብን የሚሉት ተማሪዎቹ በሀገሪቱ የሰላም እጦት ምክንያት 12ኛ ክፍሎች ሳንማር ብዙ ጊዜ አልፏል። 11ኛ ክፍልም እንዲሁ ረብሻ ነበር። በመጨረሻም የኮሮና ወረርሽኝ ታክሎበት ብዙ ትምህርት እንዳመለጣቸው ተናግረዋል።

 ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ የ2012 ዓ/ም ፈተና ቢወስዱና ውጤታቸውን ካወቁ ወራት ቢቆጠሩም አሁንም ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚሄዱበትን ቀን አያውቁም፤ ይህም ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና ዳርጓቸዋል።

የሳይንስ እና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር ከሳምንት በፊት ሁሉም ዩንቨርስቲዎች አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እስከ ግንቦት 30/2013 ይቀበላሉ ሲል አሳውቆ ነበር። ሰኔ 1 ፤ 2013 የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ትምህርት ይጀመራልም ብሏል።

በእርግጥ ሰኔ 1 ሁሉም አዲስ የዩንቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች ትምህርት ይጀምራሉ ? ይህስ ዮንቨርስቲው በግሉ የሚወስነው ነው ወይስ ወጥ የሆነ አሰራር አለ ?  ተብለው የተጠየቁት የ ሚኒስቴሩ የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር ወ/ሮ አለምወርቅ ሕዝቅኤል «ምርጫውን ታሳቢ በማድረግ ከምርጫ በኋላ በአብዛኛው አዲስ ተማሪዎች ይገባሉ ብለን እናስባለን» ሲሉ መልሰዋል። ትክክለኛ ጊዜውም ሊለያይ እንደሚችል እና ሁሉም ዩንቨርስቲዎች በአንድ ጊዜ ላይጠሩ እንደሚችሉ አስረድተዋል።

#ዶቼቨለ
@tikvahethiopia
"አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመጪው ምርጫ በኋላ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የየሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

ከምርጫው በኋላ ሰኔ 21 ሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ነባር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመጪው ምርጫ ወደደቤተሰቦቻቸው በመሄድ በምርጫው ይሳተፋሉ ብለዋል።

"የተማሪዎቹ መሄድ ግዴታ አይደለም" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ፤ መምረጥ ለሚፈልጉ ነባር ተማሪዎች እንዲመች ከምርጫው በፊትና በኋላ ያሉ ቀናት የዕረፍት ጊዜ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

"ምርጫ ማድረግ መብት እንደመሆኑ፤ መምረጥ የማይፈልጉ ነባር ተማሪዎች በያሉበት ዩኒቨርሲቲ መቆየት ይችላሉ" ብለዋል።

ነባር ተማሪዎቹ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ባዘጋጀው የበይነ መረብ የመራጭነት መመዝገቢያ አማካኝነት በምርጫው ለመሳተፍ የመራጭነት ምዝገባ አድርገዋል።

ተማሪዎቹ ወደየመጡበት አካባቢ በመሄድ በምርጫው እንዲሳተፉ ምርጫ ቦርዱ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : https://t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity
“ድምፃችን ለነፃነታችን”

“ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል መሪ ቃል በመላው ሀገሪቱ ወጣቶችን ያሳተፈ ሰልፍ ነገ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

ሰልፉ የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና የሚያሳድሩትን ጫና በመቃወም የሚከናወን ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግስት ከሰሞኑ የጣለው የቪዛ ክልከላና በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረው ጫና ሀገሪቱ ከድህነት እንዳትላቀቅ ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ለሀገር እድገት የበኩላቸውን በመወጣት የውጭ ጫናን መቃወም ይገባቸዋል ተብሏል።

ይህ ወቅት ህዝቡ ይበልጥ አንድነቱን ሊያጠናክርበት እንጂ ህብረ ብሔራዊነቱን ሊያደበዝዝ እንደማይገባ ተገልጿል።

ከምዕራባውያን ጫና ለመላቀቅ መስራት በትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባም ነው የተገለፀው።

መርሐግብሩ ነገ እሑድ ግንቦት 22 በተመሳሳይ ሰአት በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

“ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ወጣቶች ንቅናቄ መድረክ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ይደረጋል፡፡

ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ንቅናቄው እስኪያልቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን አሳውቀዋል።

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ተገንዝበው ለፍተሻ እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

በአ/አ ስታዲዮም የሚደረገው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለጊዜው ዝግ የሚሆን መንገዶች ፦

• ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከከፍተኛው ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀልአደባባይ
• ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
• ከሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድርስ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት ተላልፏል።

ህብረተሰቡ ጥቆማ ለመስጠት ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ሲፈልግ በ011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopia
''...ለግድቡ የውሃ ሙሌት ከመደበኛ ዝናብ በተጨማሪ ደመናን የማበልፀግ ቴክኖሎጂን የመጠቀም ዕቅድ ተይዟል'' - የብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ

የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በመጪው ክረምት ይካሄዳል።

በክረምቱ የአየር ትንበያ በአባይ ተፋሰስ እና በምዕራብ ኢትዮጵያ አጋማሽ ከመደበኛና መደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራል ተብሎ ይገመታል።

በሙሌቱ ወቅት ከመደበኛ ዝናብ በተጨማሪ ውሃ የሚያስፈልግ ከሆነም ደመና የማበልፀግ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም እቅድ መያዙን የብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ ለኢዜአ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
የወላይታ ቡና የብራንድ ስያሜ አገኘ።

የቡና ሰብልን ለማምረት ምቹ የአየር ፀባይ ካላቸው አከባቢዎች አንዱ የሆነው የወላይታ አከባቢ በዓመት በአማካይ ከ1500-2000 ቶን ምርት ለዓለም ገበያ ያበረክታል።

የራሱ የሆነ የቡና ስያሜ ሳይሰጠው በሲዳማ “C” ቡና ዉስጥ ገብቶ ቆይቷል፡፡

በዛሬው ዕለት የወላይታ ቡና የራሱ የብራንድ ስያሜ ተሰጥቶታል።

በተጨማሪ መረጃ ለመጪው ክረምት ወቅት በዞኑ 19 ሚሊየን የቡና ችግኝ መዘጋጀቱ ተጠቅሷል።

@tikvahethmagazine
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,005 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 256 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 271,200 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 4 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,143 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,801,175 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia