TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.1K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወ/ሮ ኬሪያ ምስክርነታቸው ተነስቶ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የምስክርነት ጥበቃቸው ተነስቶ ዳግም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጸ።

ወ/ሮ ኬሪያ ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

የጠቅላይ አቃቤ ሕግ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን እንደገለጹት፤ ወ/ሮ ኬሪያ ከተከሳሽነት ወደ ምስክርነት ተቀይረው ነበር ብለዋል።

ወ/ሮ ኬሪያ በጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699 /2003 በገቡት ሥምምነት ዝርዝር የምስክርነት ቃላቸውን በፈቃዳቸው ሰጥተው ነበር።

በገዛ ፈቃዳቸው በጽሑፍና በሲዲ ምስክርነታቸውን ሰጥተው በኃላም በፍ/ቤት ውሳኔ ከእስር እንደተለቀቁና ጎን ለጎንም ለግለሰቧ አስፈላጊውን የምስክርነት ጥበቃ ሲደረግላቸው ነበር ብለዋል።

ይሁንና ወ/ሮ ኬሪያ ቆይተው ምስክር የመሆን ፍላጎት እንደሌላቸው እና ምስክርነት ሲሰጡ የቆዩት ተገደው እንደነበር በመግለፅ ምስክረነታቸው መቋረጡን አስረድተዋል።

በምስክሮች እና ጠቋሚዎች አዋጅ ቁጥር 699/2003 በአንቀፅ 11 መሰረት የጥበቃ ተጠቃሚው ሥምምነቱንና ግዴታውን የማያከብር ከሆነ የጥበቃ ስምምነት ውሉ ስለሚቋረጥ አቃቤ ሕግም ለወ/ሮ ኬሪያ ምስክር በመሆናቸው ይሰጣቸው የነበረውን ጥበቃ ለማንሳት መገደዱን ነው የተናገሩት።

"ከዚህም በኋላ ወይዘሮ ኬሪያ ከዚህ ቀደም በተጠረጠሩበት ወንጀል የቅድመ ምርመራ ስራ እንዲጀመር አቃቤ ሕግ ዛሬ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቧል" ብለዋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በጉዳዩ ላይ ለመከራከር አልተዘጋጀንም ብለዋል።

ፍ/ቤቱ ወ/ሮ ኬሪያ በመጪው ሰኞ ዳግም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አዟል።

ወ/ሮ ኬሪያ እስከ ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ መወሰኑን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጠዋት ውሎው የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትትን የመክፈቻ መልእክት ያዳመጠ ሲሆን፦ - ብጹዕ አቡነ ኤልያስ - ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ - ብጹዕ አቡነ ማርቆስ - ብጹዕ አቡነ አብርሃምን - ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ - ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ - ብጹዕ…
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የግንቦት 19/2013 ክንውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ፤ በመግለጫቸው ተከታዮቹ ነጥቦች ተነስተዋል ፦

- በትናንትናው ዕለት ውሳኔ የሰጠባቸውን 2 አጀንዳዎች ቃለ ጉባዔ ቀርቧል፡፡ በዚህም የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ ንግግር ቅዱስ ሲኖዶስ #አጽድቆታል፡፡

- ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሀገሪቱ በሚታዩት ወቅታዊ ችግሮች የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ስደትና መፈናቀል ዙርያ በሰፊው ተወያይቶ የመፍትሔ ሐሳብ የያዘ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ውሳኔው በዝርዝር በሚሰጠው መግለጫ ይገለፃል ብለዋል።

- የቤተክርስቲያን የአምልኮ ሥፍራ የሆኑት የመስቀል እና የጥምቀት ቦታዎች አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩ የሚፈታበት ውሳኔ አሳልፏል፤ የውሳኔው ዝርዝር በአጠቃላይ መግለጫው ይቀርባል ብለዋል።

- በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት እደረሱ ያሉ ችግሮችን አስመልክቶ ሦስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ መርጧል፡፡

- በመላው ሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በሙሉ ስለ ሀገሪቱ ሰላም ጸሎተ ምኅላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/EOTC-TV-05-27 #EOTCTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰሞነኛው የግብፅ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ዙሪያ : #Djibouti • የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡ - የፕሬዚዳንቱ የጅቡቲ ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል። - የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ታውቋል። በተለይም በፀጥታ…
#Update

ጎረቤታችን ጅቡቲን እየጎበኙ ያሉት የግብፁ ፕሬዜዳት ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ሲል አል አይን (Al AIN) በድህረ ገፁ አስነብቧል።

ውይይታቸው በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር የተባለ ሲሆን ፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን አንስተው ተነጋግረዋል።

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ፕሬዝዳንት ሲሲ ፍትሀዊ እና ግልጽ ስምምነት ሳይኖር ኢትዮጵያ ግድቡን ለሁለተኛ ጊዜ መሙላት የለባትም የሚል አቋም አንፀባርቀዋል ተብሏል።

የግብፅ ባለስልጣናት በግድቡ ዙሪያ በተለያየ ጊዜ የሚያነሷቸው ሃሳቦች እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ሙሌቱ አይቀሬ መሆኑን በተደጋጋሚ #አስረግጣ ተናግራለች።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,056 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 347 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 270,527 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 19 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,127 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,784,722 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹 #Anbesa🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ #Brand_Africa በ2021 በአፍሪካ እጅግ በጣም ከሚደነቁ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል ተካተተ።

አየር መንገዱ ኮቪድ - 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የህክምና ቁሳቁሶችንና የኮቪድ-19 ክትባትን በማማጓጓዝ ላስመዘገበው አስደናቂ ስራ የአምስተኛ ደረጃን አግኝቷል።

በተጨማሪ #አንበሳ_ጫማ ከምርጥ ብራንዶች / ምርጥ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል በ4ኛ ደረጃነት ተካቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ከአንድ ታካሚ ሆድ ውስጥ በርካታ የስለት መሳሪያዎች በቀዶ ጥገና ህክምና ወጣ !

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአንድ ታካሚ ሆድ ውስጥ በርካታ የተለያዩ የስለት መሳሪያዎች በቀዶ ጥገና ህክምና ሊወጣ እንደቻለ ወጣ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ለደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ገለጹ፡፡

የታካሚ የሕኪምና መረጃ መሠረት የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል እና በጨረር ምርመራ የተለያዩ ስለት ያላቸው ቁሳቁሶችና እስክሪቢቶ ጨምሮ ከሆዱ ሊገኝ ችሏል፡፡

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ፥ ግለሰቡ ታራሚ እና የአዕምሮ ህመምተኛ መሆኑን ገልጸው ከዕለታት አንድ ቀን እስክሪቢትቶ ሲውጥ ያየ ሌላ ግለሰብ በጠቆመው መረጃ መሠረት ነው ሊደረስበት የተቻለው።

በታካሚው ሆድ ውስጥ የነበሩ በርካታ ምስማሮች፤ እስክሪቢቶና ሌሎች የስለት ቁሳቁሶች በቀዶ ሕኪምና መውጣቸውን አቶ ተመስገን አስረድተዋል።

ከቀዶ ሕኪምና በኋላ ታካሚው በመልካም ጤንነት ላይ እንደምገኝ ተገልጿል።

ዶክተር በጋሻው መለሰ የቀዶ ሕኪምና ስፔሻሊስት ሐኪም ፥ ታካሚው መርፌንና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን በ4 ወራት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት መዋጡን ገልጸው ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን ልዩ ባህሪያትንና ጤናቸውን መከታተል ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

አክለው ፥ ግለሰቡ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ የስነ ልቦና ክትትል እየተደረገለት በመሆኑ መሻሻል እየታየበት መሆኑን ዶክተር በጋሻው አብራርተዋል።

ምንጭ፦ የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት
@tikvahethiopia
“...ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” - ሄኮ ማስ

ጀርመን ናሚቢያን ቅኝ በገዛችበት ወቅት ጅምላ ጭፍጨፋዎችን መፈጸሟን አመነች፡፡

ጀርመን እአአ ከ1904-08 ባሉት ዓመታት በናሚቢያ ዜጎች ላይ የፈጸመችውን ግድያ በጅምላ ጭፍጨፋነት ለመቀበል ስታቅማማ ቆይታለች፡፡

ነገር ግን 5 ዓመታትን በወሰደ ንግግር ጭፍጨፋውን ስለመፈጸሟ አምና ተቀብላለች።

ይህን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት መሰረት ለተለያዩ ልማቶች የሚውል የ1.3 ቢሊዬን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ተስማምታለች።

ጄኔራል ሎታር ቮን ትሮታ በሄሬሮ ጎሳዎች የተነሳውን የጸረ ቅኝ ግዛት ተቃውሞ ለማርገብ በማሰብ ሙሉ የጎሳው አባላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዝ 65 ሺ ገደማ የጎሳው አባላት መጨፍጨፋቸውን እና በትንሹ 1 ሺ የናማ ጎሳ አባላት መገደላቸውን የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄኮ ማስ “ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” ብለዋል ባወጡት መግለጫ፡፡

ማስ በመግለጫቸው “ዓላማችን ተጎጂዎቹ የሚታወሱበትን እውነተኛ የእርቅ መንገድ መፈለግ ነው” ብለዋል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ በዛሬዋ ናሚቢያ ቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶችን “በይፋ ጅምላ ጭፍጨፋ ብለን እንጠራቸዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

#አልዓይን #AP

@tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom #DrLiaTadesse

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የሀርቫርድ ቲ.ኤች.ቻን ህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የ2021 ጁሊየስ ቤንጃሚን ሪችመንድ ሽልማትን ተቀብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ የዶክተር ሪችመንድን ምሳሌነት በመከተል የዓለምን ህዝብ ጤና በተለይም አቅመ ደካሞች ጤና ለማሻሻል በቻልኩት ሁሉ ለመስራት ቁርጠኛ ነኝ ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የ2021 ኔክስት ጄኔሬሽን ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

ዶ/ር ሊያ ለሽልማቱ የበቁት በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በወሰዷቸው ወሳኝ እርምጃዎች መሆኑ ተገልጿል።

ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ የሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ለዚህ የከበረ ሽልማት የመረጣቸው በመሆኑ የተሰማቸውን ክብር ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#JanssenCOVID19Vaccine

በጃንሰን የተዘጋጀውና አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው የኮቪድ-19 ክትባት በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ እንዲውል የመድሃኒቶች ተቆጣጣሪ ፍቃድ መስጠቱን ቢቢሲ በ 'ሰበር ዜና' ዘግቧል።

በሙከራዎች ሂደት ኮቪድ-19 በመከላከል 85% ውጤታማ እንደሆነ የተገለፀው ክትባቱ የሚጠበቅበትን የደህንነት ደረጃዎች አሟልቶ ተገኝቷል ተብሏል።

ለዩናይትድ ኪንግደም 20 ሚሊዮን ዶዝ የታዘዘ ሲሆን በያዝነው ዓመት መጨረሻ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ክትባት ዩኬ ውስጥ ኮቪድ-19 ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውል 4ኛው ክትባት ይሆናል።

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር የስራ አመራር ቦርድ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ !

@tikvahethiopia