TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦሮሚያ ለሲዳማ ክልል 100 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደሚያበረክት ገለፀ።

በዛሬው ዕለት በሀዋሳ "ጉዱማሌ" እየተካሄደ በሚገኘው የሲዳማ ክልል ይፋዊ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሚያ ክልል ለአዲሱ የሲዳማ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደሚያበረከት ገለፁ።

የክልሉ ፕሬዜዳንት በስነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ወቅት ነው ይህን ይፋ ያደረጉት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Koysha

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከአዲስ አበባ ውጭ መካሄድ ጀመረ።

የሚንስትሮች ም/ቤት የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ #በኮይሻ መካሄድ ጀምሯል።

ግመገማው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነው እየተመራ የሚገኘው።

ለ1 ቀን በሚቆይው በዚህ የስራ ግምገማ ሁሉም የካቢኔ አባላት እየተሳተፉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቅሬታ ያስነሳው የአምባሳደሩ ደብዳቤ ፦

ከሰሞኑን ሶማሊ-አሜሪካዊቷ የሚኒሶታ ተወካይ የምክር ቤት አባል ኢልሃን ዑመር “ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ በብዙ መልኩ እጅግ የሚያሳስብ ነው” ሲሉ መግለጫ አውጥተው ነበር፡፡

ኢልሃን በርሃብ አድማ ላይ ስለሚገኙ ፖለቲከኞች የአያያዝ ሁኔታና በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ አንስተው ጉድዩን “በቅርበት እየተከታተሉ” እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ለዚህ ምላሽ እንዲሆን ደግሞ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ፊርማ በአድራሻቸው የተጻፈው ደብዳቤ ይፋ ሆኗል።

“ሊያሳስብዎት የሚገባ ምንም ነገር እንደሌለ ላረጋግጥልዎት እወዳለሁ” ሲል የሚጀምረው ደብዳቤው በ “እውነታውኛ እና ተጨባጭ በሆነ ትክክለኛ መንገድ” ሁኔታዎችን መመርመሩ ስጋታቸውን ሊያቀል እና በሚዛናዊነት እንዲረዱ ሊያግዝ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሁሉም እስረኞች መብቶች እንዲከበሩ በሚያዙ ዓለም አቀፍ መርሆዎች እና ድንጋጌዎች መሰረት ሁሉም ታራሚዎች አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን ያለ ልዩነት በነጻ እንዲያገኙ ለማድረግ በመስራት ላይ ይገኛል ነው የሚለው፡፡

በምክር ቤት ተወካይዋ የተጠቀሱት እስረኞች በጦር ኃይሎች ሆስፒታል እየታከሙ እንደሚገኙና የርሃብ አድማውን እንዳቋረጡም ይጠቅሳል፡፡

በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉም ነው የሚለው ደብዳቤው፡፡

የአምባሳደሩን ደብዳቤ የተመለከቱት የኦሮሞ ፖለቲካ እስረኞች የጠበቆች ቡድን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኦሮሞ እስረኞችን አስመልክቶ የካቲት 20፣ 2021 እ.ኤ.አ ያወጣው መግለጫ አሳሳችና ትክክል ያልሆነ ብሎታል።

በአምባሳደር ፍጹም አረጋ ደብዳቤ በእጅጉ አዝነናልም ሲሉ ገልፀዋል።

https://telegra.ph/Ethiopia-02-22
በራስ አምባ ት/ቤት በኮቪድ-19 የተያዙ ተማሪዎች በመገኘታቸው ናሙና እየተወሰደ ነው !

በራስ አምባ ትምህርት ቤት ከኮቪድ - 19 በሽታ የተያዙ ተማሪዎች በመገኘታቸዉ ናሙና ከተማሪዎች እየተወሰደ መሆኑ አሀዱ ራድዮ 94.3 ዘገበ።

በራስ አምባ ትምህርት ቤት በኮቪድ 19 ያለባቸዉ 4 ተማሪዎች በመገኘታቸዉ በየክፍሉ ምርመራ መደረግ መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ርእሰ መመህር አቶ ስንታየዉ ገለታ ተናግረዋል፡፡

አሁን ናሙና ከተወሰደላቸዉ 22 ተማሪዎች በተጨማሪ በሁለተኛዉ ዙር በነገዉ እለት ማክሰኞ ከ3 ክፍሎች ናሙና እንደሚወሰድ አስታዉቀዋል፡፡

አራቱ ተማሪዎች ኮቪድ እንዳለባቸዉ የታወቀዉ ቤተሰቦቻቸዉ ናሙና ሰጥተዉ ነዉ ተብሏል፡፡

ተማሪዎቹ ከየክፍሉ አንድ አንድ 4 በመሆናቸዉ ከሁሉም ክፍሎች ናሙና ይወሰዳል ብለዋል፡፡

የመማር ማሰተማር ሂደቱ አሁንም ቀጥሏል ያሉ ሲሆን ለመምህራን ናሙና ለመዉሰድ መታሰቡን በተመከተ ምልክት ከታየ እንደሚወሰድ እና አሁን ላይ ከተማሪዎች ብቻ ለመዉሰድ መታቀዱን አቶ ስንታየዉ ገልፀዋል።

በራስ አምባ ትምህርት ቤት መመህር የሆኑ ግለሰብ እንደተናገሩት በትምህርት ቤቱ እስካሁን 6 ተማሪዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል፡፡ የታወቀዉም በጠና ስለታመሙ ነዉ ብለዋል፡፡ የሚያዙ ተማሪዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በትምህርት ቤቱ አሁን እየተደረገ ያለዉ የምርመራ ቁጥር በቂ አይደለምና ትኩረት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አሃዱ ሬድዮ 94.3
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የደረቅ ጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪና ተገልብጦ የሁለት ሠዎች ህይወት አለፈ!

በም/ጎጃም ዞን በአነደድ ወረዳ ሻፎ ጉዳልማ ቀበሌ ሰፈር አራት አካባቢ ላይ የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ዚባ ጫካ ከሰል የተጫነ የደረቅ ጭነት ኤፍ ኤስ አር የሠሌዳ ቁጥር 3 - አ .አ 17693 ከዚባ ከሰል ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ በመገልበጡ ሲያሽከረክር የነበረውና አንድ ሠው በድምሩ የሁለት/2/ሠዎች ህይወት አልፏል።

ስለአደጋው መንስኤ ፓሊስ ምርመራ እያደረገ ነው።

አሽከርካሪዎች በቂ የማሽከርከር ልምድ ሣይኖራቸው እንዲሁም በተለይ የአደጋ ቦታዎችን አውቀው በጥንቃቄ ባለማሽከርከር ውድ መተኪያ የሌለው ህይወት እየተቀጠፈ ስለሆነ ብርቱ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የወረዳው ፓሊስ ኮሙኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦሮሚያ ለሲዳማ ክልል 100 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደሚያበረክት ገለፀ። በዛሬው ዕለት በሀዋሳ "ጉዱማሌ" እየተካሄደ በሚገኘው የሲዳማ ክልል ይፋዊ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሚያ ክልል ለአዲሱ የሲዳማ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደሚያበረከት ገለፁ። የክልሉ ፕሬዜዳንት በስነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ወቅት ነው ይህን ይፋ ያደረጉት።…
ሲዳማ ለትግራይ ክልል የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ዛሬ በይፋ የምስረታ በዓሉን ያከናወነው የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ለትግራይ ክልል የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማደረጉ ተሰምቷል።

ሲዳማ ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ለትግራይ ክልል የፓትሮል እና የአምቡላስ ተሽከርካሪዎች ድጋፍ አድርጓል።

በሌላ በኩል ዛሬ በሀዋሳ "ጉዱማሌ" በነበረው የሲዳማ ክልል ምስረታ በዓል ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሲዳማ ክልል ስጦታ አበርክተዋል በዚህም ኦሮሚያ 100 ሚሊዮን፣ አዲስ አበባ 50 ሚሊዮን፣ አማራ 30 ሚሊዮን፣ ደቡብ 20 ሚሊዮን፣ ሶማሌ 10 ሚሊዮን፣ አፋር 7 ሚሊዮን፣ ሀረሪ 5 ሚሊዮን፣ ጋምቤላ 2 ሚሊዮን የገንዝበ ስጦታ አበርክተዋል።

በተጨማሪ ሻሸመኔ ከተማ 1.5 ሚሊዮን ፣ ምዕራብ አርሲ ዞን 1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሥጦታ እንዲሁም በርከታ የሰንጋዎችን አበርክተዋል።

ይህ መረጃ የአቶ ደስታ ዳንኤል ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Axum

Save the Children ዛሬ በላከልን መግለጫ በአክሱም ከ3 ወራት ወዲህ የመጀመሪያ እርዳታ ማከፋፈሉን አሳውቆናል።

በዕርዳታው በከተማው የሚገኙ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው ምግብ፣ መጠለያና የንፅህና መጠበቂያዎችን እንዳገኙ ገልጿል።

አክሱም በቅርብ ጊዜ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ በርካታ ተፈናቃዮችን ያስጠለለች ሲሆን ከ6 ሺህ የሚልቁ ተፈናቃዮች በተጣበቡ ትምህርት ቤቶች ፣ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችና በአከባቢው ነዋሪዎች ቤት ተጠልለው ይገኛሉ።

የSave the Children ልገሳ ለተፈናቃዮች መሰረታዊ የምግብ፣ መጠለያ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ያካተተ ነው።

Save the Children በአክሱም በየካቲት መባቻ እጅግ አስፈላጊ ድጋፍ ማቅረብ ከጀመረ አንስቶ ለቀናት እህል ያልቀመሱና በሆስፒታሎች ባለው እጅግ ውስን የህክምና አቅርቦቶች የተነሳ አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶች ማግኘት ያልቻሉ ቤተሰቦችን አግኝተዋል።

ድርጅቱ በእስካሁኑ የምግብ እና ሌሎች እርዳታ ለ1,063 ቤተሰቦች ወይም 4,368 ሰዎችም መድረስ እንደቻለ ቢገልፅም አሁብም ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

* ከSave the Children የተላከልን ዝርዝር መግለጫ ከላይ የያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ልዩ ክብር የሚሰጣቸው አርቲስት አዱኛ ዱሞ ሥጦታ ተበረከተላቸው !

በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ልዩ የሆነ ቦታ እና ክብር የሚሰጣቸው አርቲስት እንዲሁም የመብት ታጋይ አዱኛ ዱሞ ከሲዳማ ክልላዊ መንግስት የመኪና ስጦታ ተበረከተላቸው።

አርቲስት አዱኛ ዱሞ የተሰጣቸው የመኪና ስጦታ 12 ሰዎችን መያዝ የሚችል ዶልፊን መኪና መሆኑን ከአቶ ደስታ ዳንኤል የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ስጦታው የተበረከተላቸው ዛሬ በሀዋሳ በነበረው የሲዳማ ክልል ይፋዊ የምስረታ በዓል ላይ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ የኤርትራ ወታደሮች ጉዳይ ?

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች ንብረት ዘርፈው ወደ ኤርትራ መውሰዳቸውን /ድንበር ተሻግረው ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው መግባታቸውን ሲገልፁ ነበር።

በቅርቡ እንኳን የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ በርካታ የኮንስትራክሽን ማሽኖች፣ ንብረቶች ወደ ጎረቤት ሀገር ኤርትራ መሸጋገራቸውን ገልፆ የተወሰዱትን ንብረቶች ለማስመለስም ከፌዴራል መንግስት ጋር ንግግር እንደሚደረግ ገልፆ ነበር።

የትግራይ ነዋሪዎችም በርካታ ጊዜያት በተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ላይ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ትግራይ መግባቱን በመግለፅ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ እንዲደረግ ሲጠይቁ ነበር።

በዛሬው ዕለት ደግሞ በትግራይ ክልል የሰሜናዊ ዞን ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል አስተዳደር ሙሉብርሃን ኃይሉ የኤርትራን ወታደራዊ መለዮ ለብሰው የህዝቡን ንብረት የሚዘርፉና ሴቶችን የሚደፍሩት "ህወሓት" የፈጠራቸው ወንበዴዎች ናቸው ብለዋል።

ምክትል አስተዳዳሪው ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፦

- በውጭ አገር ያሉ እና በእግራቸው ጫካ ለጫካ የሚኳትኑ ቀሪ የህወሓት አባላት በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የትግራይን ህዝብ ለማታለል እየሞከሩ ነው ብለዋል።

- የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በአካል ተገኝቶ መዘገብ ለሚፈልግ የመገናኛ ብዙሃን በሩ ክፍት ነው ብለዋል።

- "ህወሓት" በክልሉ የፈጠራቸውን ስራ አጥ ወጣቶች መሳሪያ በማስታጠቅ እና የኤርትራን ወታደራዊ መለዮ በማልበስ ሴቶችን እንዲደፍሩ በማድረግ በኤርትራ ወታደሮች ላይ ለማሳበብ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ በ Instant View ያንብቡ።
https://telegra.ph/TigrayRegion-02-22
#Attention😷

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 14 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞቱ።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከተደረገው 5,960 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 735 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

ትላንት 347 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 153,541 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,293 ሰዎች ሞተዋል፤ 131,713 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 346 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Update

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ስርዓተ ቀብር ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን ይፈጸማል።

ዛሬ የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን የሎሬቱን ህልፈት የሚዘክር መርሃ ግብር አካሂዶ እንደነበር ኢዜአ ገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣የኮሚሽኑ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
13 ቀናት የቀሩት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና...

በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2012 ዓ/ም ሳይሰጥ የቀረው የ2012 የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከየካቲት 29 ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ኢቢስ ቲቪ ከቀናት በፊት ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወረቀቶች ማተም እንዲጀመር ትዕዛዝ ተሰጥቶ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ትዝእዛዝ የተሰጠው ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ሲሆን ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 የፈተና እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች በመላ ሀገሪቱ ባሉ ፈተና ጣቢያዎች ይሰራጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በፀጥታ በኩልም ከፈተናው ስርጭት ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሰላማዊ እንዲሆን ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ እየተሰማ ነው።

የ2012 ፈተናን 450 ሺህ ተማሪዎች እንደሚወስዱት ይጠበቃል።

ፈተናው ረጅም ጊዜ በመዘግየቱ በተማሪዎች ላይ እንዲሁም በወላጆች ላይ ከፍተኛ የስነልቦ ጫና መፍጠሩ ሲገለፅ ቆይቷል። አሁን ፈተናው ሊሰጥ 13 ቀናት ብቻ ነው የቀሩት።

ተፈታኝ ተማሪዎች እያደረጋችሁት ያለው ዝግጅት ምን ይመስላል ? ወላጆች ልጆቻችሁ ለፈተናው ብቁ ሆነው እንዲቀርቡ እያደጋችሁት ያለው የስነ ልቦና ዝግጅትስ እንዴት ይገለፃል ? ት/ ቤቶች ተማሪዎቻችሁ ፈተናውን በውጤት ያጠናቅቁ ዘንድ ምን አስተዋፅኦ እያደረጋችሁ ነው ?

ሀሳብ ያላችሁ በአስተያየት መስጫው ማካፈል ይቻላል።

@tikvahethiopia
ትላንት ለሊት 6 ሰዓት ገደማ በሚዛን ማረሚያ ተቋማ መዝናኛ ክበብ የተነሳው እሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያደረስ መቆጣጠር ተችሏል !

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ማረሚያ ተቋም መዝናኛ ክበብ ላይ ተከስቶ የነበረው ድንገተኛ እሳት አደጋ በፀጥታ ሃይል እና በሚዛን አካባቢ ማኅበረሠብ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በማረሚያ ተቋሙ መዝናኛ ክበብ ላይ ሲሆን ከታራሚዎች መኖሪያ ጋር ግንኙነት እንደሌለውም ተገልጿል።

ኮማንደር ዳዊት ጢሞቲዎስ የቤንች ሸኮ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ በስልክ የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ገደማ በሚዛን ማረሚያ ተቋም በመዝናኛ ክበብ ላይ የተከሠተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በፀጥታ ኃይሉና በሚዛን አካባቢ ነዋሪዎች ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።

የተከሠተው እሳት አደጋ ከታራሚዎች መኖሪያ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበረውና ብዙ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋል መቻሉን የገለፁት ኮማንደር ዳዊት የሚዛን አካባቢ ማኅበረሠብ የተከሠተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር የፀጥታ አካሉ ጎን በመቆም ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

የተፈጠረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በፀጥታ ኃይሉ እና በህዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለ በመሆኑ ማኅበረሠቡ ከስጋት ነፃ ሆኖ እንደወትሮው ሁሉ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ ኃላፊው ማሳሰባቸውን ከቤንች ሸኮ ዞን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መኢአድ በጎንደር ምርጫ ቅስቀሳ ችግር ገጥሞኝ ነበር አለ !

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ፥ ምርጫ ቦርድ የካቲት 8 ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲደረግ ቢፈቅድም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በፀጥታ አካሉ ክልከላ ደርሶብናል ሲሉ ከሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ በጎንደር የምርጫ ቅስቀሳ ችግር አጋጥሟቸው እንደነበር ገልፀዋል።

ችግሩ የተፈጠረው በጸጥታ አካሉ ከህግ የወጣ ድርጊት ነው ሲሉም ለኢትዮጵየ ፕሬስ ድርጅት አሳውቀዋል።

የጸጥታ አካሉ መኪና እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል፣ ፈቃድ አልተሰጣችሁም በሚል እገዳ አድርጓል ፣ የጸጥታ አካሉ ሥራ የህዝብ ጸጥታ ማስከበር እንጂ የተላለፈን ህግ መጣስ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

የጸጥታ አካሉ ከማንም በፊት በምርጫ ቦርድና በመንግስት በኩል መረጃው ደርሶታል።ይህ ሆኖ እያለ ደግሞ ይህንን መፈጸሙ ምርጫውን ከማደናቀፍና ጥላሸት ከመቀባት አይተናነስም ብለዋል።

ከዚህ በኋላ አልሰማንም አላየንም እንዳይሉ ፤ ይህንን ድርጊታቸውን ዳግም እንዳይፈጽሙ፤ ፓርቲው ህጋዊ ሆኖ እየተንቀሳቀሱ ድረስ ምንም አይነት እንግልት እንዳይገጥማቸና በየጊዜው የሚያስፈቅዱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ምርጫ ቦርድና መንግስት ወጥ መመሪያ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጸጥታ አካሉ እምዲሁም አመራሩ የማያገባው ውስጥ እንዳይገባ የሚመለከተው አካል አደብ ሊያስገባው እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ደረጃ ውጤታማ ቅስቀሳ ማድረጉን መኢአድ አሳውቋል። ከአዲስ አበባ ውጪ በደብረብረሃን፤ በባህርዳርና መሰል የአማራ ክልል ከተሞች ላይ የምርጫ ቅስቀሳው መካሄዱንም ጠቁሟል።

አብን እና ባልደራስ : telegra.ph/EPA-02-23

@TikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እሳት አደጋ በአ/አ ጀሞ ሚካኤል ታክሲ ማቆሚያ ፦

ትላንት ምሽት 3:30 አካባቢ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ስሙ "ጀሞ ሚካኤል ታክሲ ማቆሚያ" አካባቢ በደረሰ የእስት አደጋ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የደረሰው ጉዳት መጠን እንዲሁም የእሳት አደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ከወረዳ 02 ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጀ ይጠቁማል።

Photo : Tikvah - Family (Addis Ababa)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia