#NewsAlert
በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ላይ በተለይም በወር አበባ ንዕህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና ታክስ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚህም መሰረት የሴቶች ወር አበባ መጠበቂያ ( ሞዴስ) እንዲሁም የህፃናት ንዕህና መጠበቂያ ( ዳይፐር) በሀገር ወስጥ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ከውጭ የሚያስገቡት ጥሬ እቃ ከታክስ ነጻ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
እነዚህ የተጠቀሱትን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ሲገቡ ደግሞ ቀድሞ ከነበረውን ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ከ30 በመቶ ዝቅ ተደርጎ ታክሱ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) አምራች ኢንዱስትሪዎች 8 መሆናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

#GERD #SUDAN
የሕዳሴው ግድብ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ !
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት ሊያካሂዱት ታስቦ የነበረው የበይነ-መረብ ስብሰባ ሱዳን ባለመገኘቷ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል።
የዕለቱ ሰብሳቢ የሆነችው ኢትዮጵያ ባስተላለፈችው ጥሪ መሰረት የግብጽ ልዑክ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች እና ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሙያዎች ባዘጋጁት ሰነድ ላይ ያሏትን የልዩነት ሃሳቦች ለአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር በማሳወቅ ሰነዱን ለሶስትዮሽ ድርድር እንደግብዓት ለመጠቀም መስማማቷ ይታወሳል፡፡
ሆኖም የልዩነት እና አንድነት ሃሳቦችን ለማጠናቀር የታሰበው የዛሬው ስብሰባ በሱዳን አለመገኘት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡
ይኸው ለአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር በኢትዮጵያ በኩል ተገልጿል፡፡
(የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ችሎት!
በ10 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ላይ መርማሪ ፖሊስ የ14 ሰዎችን የምስክርነት ቃል መቀበሉን ገለፀ።
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት "ከህወሃት ቡድን ተልዕኮ በመቀበል" ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ 10 የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችን ጉዳይ ተመልክቷል።
በዚህ መዝገብ ፦
• ኮሎኔል ሃረጎት በርሄ፤
• ሌተናል ኮሎኔል ሙሉ አለሙ፤
• ብርጋዴል ጄነራል ይልማ ከበደ ፤
• ኮሎኔል በረከት ወልደአብየዝጊ፤
• ሌቴናል ኮሎኔል ግደይ ገብረየሱስ፤
• ሻለቃ ሃሳቡ መሃመድ፤
• መቶ አለቃ ጸሃየ ሃይሉ፤
• ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ ይገኙበታል።
ተጠርጣሪዎቹ ለሕውሃት ቡድን ወታደራዊ ድጋፍ መስጠታቸውንና በመንግስት በጀትም በድብቅ ለትግራይ ልዩ ሃይል ስልጠና ሲሰጡ እንደነበር ፖሊስ ማስረጃ አግኝቻለሁ ብሏል።
እስካሁን የተጠርጣሪዎችን ቃል የመቀበል ስራ የተከናወነ ሲሆን በኤርፖርት የደረሰውን የጉዳት መጠን መረጃ ማምጣቱን አስታውቋል።
በውጭ ሀገር ላሉ የህወሓት ቡድን ደጋፊዎች ሃሰተኛ መረጃ በማቀበል ጭምር በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የተለያዩ የወንጀል ተግባራት ለመፈፀም መንቀሳቀሳቸውን ፖሊስ አረጋግጫለሁ ብሏል።
በተጨማሪም ቀሪ የምርመራ ስራ ለማከናወንና የተለያዩ የቴክኒክ፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ 14 ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል።
ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ”መርማሪ ፖሊስ የወንጀል ተሳትፏችንን ለይቶ ሊያቀርብ ይገባል፣ በጉዳዩ ላይ የሁላችንም ተጠያቂነትና የወንጀል ተጠርጣሪነት ተመሳሳይ ሆኖ መቅረብ የለበትም ” ሲሉ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኝ ክርክሩን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት 11 ቀን በመፍቀድ ለጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። ~ ENA

አዋዳ ካምፓስ ተማሪዎቹን አስመረቀ !
ዛሬ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ "አዋዳ ካምፓስ" ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ6ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 1,682 ተማሪዎች አስመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተመራቂ ቤተሰቦች የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ፣ የአዋዳ ካምፓስ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዛሬ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ "አዋዳ ካምፓስ" ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ6ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 1,682 ተማሪዎች አስመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተመራቂ ቤተሰቦች የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ፣ የአዋዳ ካምፓስ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Attention
የመተከል ተፈናቃዮች አሁንም የታጣቂዎች ጥቃት ስጋት አንዳለባቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ተናገሩ።
ከመተከል ዞን ተፈናቅለው ቻግኒ የሚገኙ ተፈናቃዮች ምሽት ላይ ማንነታቸውን የማናውቃቸው ሰዎች አይተውን ይሄዳሉ እዚህም መጥተው እንዳይጨርሱን ስጋት ላይ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ 22 ሺህ የሚደርሱ ተፈናቃዮቹ እየተጠበቁ ያሉት በጥቂት ሚሊሺያዎች ብቻ ነው፡፡
ካለው ስጋት አንጻር መንግስት መከላከያ ሰራዊት አልያም ፌደራል ፖሊስ ያምጣልን ሲሉ ተፈናቃዮቹ ጠይቀዋል፡፡
የጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ብርሀኑ መኮንን፥ ተፈናቃዮቹ ያሉበት አካባቢ ጫካ ያለበት በመሆኑ ያለባቸውን ስጋት እኛንም አሳስቦናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተፈናቃይ መስለው ተቀላቅለው የመጡ ሰዎችንም ይዘናል ሲሉ ገልፀዋል።
ቻግኒ አካባቢ 22 ሺህ ተፈናቃይ ያለ ሲሆን እስካሁን ድረስ በአዊ ዞን አጠቃላይ 47 ሺህ 996 ተፈናቃይ እንዳለ አቶ ብርሀኑ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

በህገወጥ ድርጊት ላይ ተሳተፉ የኢምግሬሽን አመራሮች እና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ !
ህጋዊ መንገድ ማሟላት ካልቻሉ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በመቀበል በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ሲልኩ የነበሩ የኢምግሬሽን አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም በህጋዊ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ስም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።
NISS እንዳስታወቀው ፤ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅርንጫፍ የሚሰሩ አመራሮችና ሰራተኞች ከአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ህጋዊ ሂደቶችን ያላሟሉ እና ከሀገር መውጣት የማይገባቸውን ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሲያስወጡ ነበር፡፡
የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ቡድን ጋር ባደረጉት ክትትል በህገወጥ ድርጊቱ ሲሳተፉ እንደነበር የተጠረጠሩ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል።
በሶስት ተጠርጣሪ የኢምግሬሽን ባለሙያዎች ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም ከ1 ሚልዮን ብር በላይ እና የተለያዩ የባንክ ደብተሮችና ሰነዶች ተገኝቷል።
በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ከተጠረጠሩ 3 በአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ስም ከሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ቤት የሌሎች ሰዎች ሰባት (7) ፓስፖርቶች ተይዘዋል፡፡
በአጠቃላይ በተደረገው ፍተሻ 37 የባንክ ደብተሮች እና ለህገ ወጥ ስራ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ቁሳቁስ የተገኙ ሲሆን፤ ተጨማሪ የማጣራት ስራዎች እየተከናወኑ ነው መሆኑን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

#AstraZeneca
ብሪታንያ በአስትራዜኔካ ኩባኒያ የተሰራውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠት ዛሬ ታህሳስ 26 ጀምራለች ፥ የኩላሊት እጥበት ታካሚ የሆኖ የሰማኒያ ሁለት ዓመት አረጋዊ ይህን ክትባት ለመከተብ የመጀመሪያ ሆነዋል።
ግማሽ ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ይሄኛው ክትባት በፋይዘር ባዮንቴክ ከተቀመመው ክትባት ዋጋው ረከስ እንደሚል ደግሞም እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ባለው ማቀዝቀዣ መቀመጥ ያለበት ባለመሆኑ ለማጓጓዣ ቀለል ያለ መሆኑ መገለፁን ቪኦኤ አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBot

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,157
• በበሽታው የተያዙ - 297
• ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ከበሽታው ያገገሙ - 243
አጠቃላይ 125,919 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,950 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 112,610 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
262 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለ2ኛ ጊዜ ከአፍሪካ 100 ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ውስጥ መካተታቸው ተገለፀ።
አቶ ተወልደ የላቀ ስኬት ባለቤት በመባል በቢዝነስ ፣ በፖለቲካና በስነ ጥበብ መስኮች ድንቅ ውጤት ካስመዘገቡ 100 ተፅእኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን መካከል ነው ለሁለተኛ ጊዜ የተካተቱት።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ለአቶ ተወልደ የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ተወልደ የላቀ ስኬት ባለቤት በመባል በቢዝነስ ፣ በፖለቲካና በስነ ጥበብ መስኮች ድንቅ ውጤት ካስመዘገቡ 100 ተፅእኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን መካከል ነው ለሁለተኛ ጊዜ የተካተቱት።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ለአቶ ተወልደ የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AlNejashiMosque
የ"ህወሓት ቡድን" ከኣል ነጃሺ መስጊድ በቅርብ ርቀት ላይ ምሽግ ቆፍሮ ውጊያ ሲያደርግ እንደነበር ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
ህወሓት ቆፈረው በተባለው ምሽግ አቅራቢያ የትግራይ ልዩ ኃይል ዩኒፎርም እና በኣካባቢው ውጊያ ሲደረግ እንደነበር የሚያሳዩ የጥይት ቀላሃዎች ተገኝተዋል ብሏል።
የመስጊዱ ሚናራ በከባድ መሳሪያ ተመቷል፤ የንጉስ አል ነጃሺ እና የነብዩ መሃመድ 12 ተከታዮች ያረፉበት መካነ መቃብር ያለበት ቦታም በከባድ መሳሪያ ጥቃት ተጎድቷል።
የእንግዳ መቀበያ አዳራሽ እና ሌሎች ክፍሎችም ተጎድተዋል።
የክልተ ኣውላሎ እስልምና ምክር ቤት እና የኣል ነጃሺ መስጊድ አስተዳዳሪ ሃጂ ሲራጅ መሃመድ ፥ የህወሓት ቡድን ከመስጊዱ አቅራቢያ ምሽግ መስራት ሲጀምር ድርጊቱን እንዲያቆም ቢጠየቅም ጥያቄውን እንዳልተቀበለ በቴሌቪዥን ቀርበው ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ሼህ አደም መሃመድ የኣል ነጃሺ መስጊድ ኢማም እና ኣስጎብኝ በተመሳሳይ በኣካባቢው አቅራቢያ ምሽግ እንዳይቆፈር መልዕክት ቢተላለፍም ሰሚ እንዳልተገኘ ገልፀዋል።
ሼህ ኣደም ፥ ከዚህ ቀደም በደርግ ሆነ በኃይለስላሴ ጊዜ በነበረው ሁኔታ ከተማ ውስጥ ምሽግ ታይቶ እንደይታወቅ ተናግረው በጥብታዊው እና ታሪካዊ ኣል ነጃሺ መስጊድ ኣቅራቢያ ይህ ሊደረግ እንደማይገባው ተናግረዋል፤ በመስጊዱ መጎዳት ሁሉም እንዳዘነ ገልፀዋል።
የሃይማኖት ኣባቶቹ መስጊዱ በቶሎ እንዲጠገን እና እንዲሰራ ጠይቀዋል።
ከኣል ነጃሺ መስጊድ በተጨማሪ የእንዳ ኣማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በመሳሪያ መመታቱን የኣል ነጃሺ መስጊድ አስተዳዳሪ ሃጂ ሲራጅ መሃመድ ተናግረዋል።
* በእምነት ተቋማቱ ላይ ስለደረሰው ጉዳት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሆነ የፌዴራል መንግስት እካሁን ያሉት ነገር የለም።
@tikvahethiopiaB

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* የቀጠለ ...
በኣል ነጃሺ መስጊድ ላይ ተፈፀመው ጥቃት ዛሬ እንዲህ በይፋ በሚዲያዎች ከመገለፁ በፊት በሶሻል ሚዲያ ላይ የተነገረ ቢሆንም የትኛውም የመንግስት ሆነ ለመንግስት ቅርብ የሆነ ሚዲያ ስለጉዳዩ ሲናገር አልተደመጠም።
ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም በግንኙነት አለመኖር ሳቢያ መረጃ ማግኘት ኣልቻሉም።
ከኣርብ ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨው የፎቶ ማስረጃ እና የእምነቱ ተከታዮች እያነሱት ባለው ጥያቄ እንዲሁም ጫና የመንግስት ሚዲያዎች ሊዘግቡት ችለዋል።
ኣካባቢው ላይ የግንኙነት መቋረጥ እንዲሁም ከመንግስት ሚዲያዎች ውጭ ያሉ ሚዲያዎች ወደ ስፍራው ሄደው ዘገባ እንዳይሰሩ ኣመቺ ሁኔታ አለመኖሩ ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት እጅግ ፈታኝ እንደሆነ ቀጥሏል።
በኣካባቢው ላይ መገኘት የሚችሉ ሚዲያዎች የሚመሩት በማህበራዊ ሚዲያው ጫና መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን ይበልጥ እያወሳሰበው ይገኛል።

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ጄይላን ከድር በኣል ነጃሺ መስጂድ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ከ2 ቀናት በኋላ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ይፋ እንደሚደረግ መናገራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።
ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ በስፋት የሰራው ዘገባ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማንበብ ይቻላል : https://www.bbc.com/amharic/news-55526508

#ሸገርደርቢ
በእጅግ በርካታ የኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቁት የሸገር ደርቢ ዛሬ ይካሄዳል።
የስድስተኛው ሳምንት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት ሲቀጥል #የሸገር_ደርቢ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ ቡና መካከል ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
https://t.me/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH

ወ/ሮ ህይወት እና ልጃቸው አጋዚ ስዩም በዋስ ከእስር እንዲወጡ ፍርድ ቤት ወሰነ !
የአምባሳደር ስዩም መስፍን ባለቤት ፈለገ ህይወት በርሔ እና ልጃቸው አጋዚ ስዩም የ50,000 ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ፍርድ ቤት መፍቀዱን ኤፍቢሲ / FBC ዘግቧል።
ይህ የፈቀደው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው፡፡
የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን በስዩም ባለቤት ፈለገህይወት በርሔ እና በልጃቸው አጋዚ ስዩም ላይ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ እና የምርመራ መዝገቡን ይዞ እንዲቀርብ ታዞ ነበር።
ፖሊስ ግን መዝገቡን በሌላ መርማሪ ቢሮው ስለተቆለፈ መዝገቡን ይዤ አልቀረብኩም የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።
ፖሊስ ለቀሪ ምርመራ ስራ ከኢንሳ የስልክ ልውውጥ መረጃ ለማምጣት ተጨማሪ 14 ቀን ጠይቋል።
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ይህን ማስረጃ ለማምጣት ብቻ ተጠርጣሪዎችን አስሮ ማቆየት ተገቢነት የለውም ሲል የዋስትና ጥያቄ አንስቷል፡፡
ችሎቱ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበው ምክንያት አልተቀበለውም ፤ የዋስትና ጥያቄያቸው ተገቢ ነው ሲልም የ50 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ፍቅዷል፡፡
ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣልም አዟል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia