TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

አዲስ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለዓለም ሀገራት ስጋት እየሆነ ነው።

ከ40 በላይ አገራት ከUK ወደ አገራቸው የሚደረጉ በረራዎችን አግደዋል።

የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በዚህ ዙሪያ የጋራ ፖሊሲ ለማውጣት እየተወያዩ ነው።

ዴንማርክ ውስጥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመታየቱ ስዊድን ወደ ዴንማርክ የሚደረግ ጉዞ አግዳለች።

ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ ነው። በከፍተኛ ደረጃ ጎጂ ስለመሆኑ ግን እስካሁን የተገኘ መረጃ የለም።

የዓለም ጤና ድርጅቱ ማይክ ራየን ፥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በወረርሽኙ ዝግመተ ለውጥ ሂደት የሚጠበቅ ነው ብለዋል።

የUK የጤና ሚንስትር ጸሐፊ ማት ሀንኮክ አዲሱ ዝርያ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ቢሉም ማይክ ራይን አዲሱ ዝርያ "ከቁጥጥር አልወጣም" ብለዋል።

UK ከተገኘው የቫይረስ ዝርያ የተለየ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል። የደቡብ አፍሪካ ተጓዦች ላይ እገዳ እየተጣለም ነው።

እስካሁን የአዲሱ ቫይረስ ዝርያ በዴንማርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን እና ኔዘርላንድስም ተገኝቷል።

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ፤ የቫይረሱ ዝርያ ከተገኘባቸው ቦታዎች ውጪ ተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል።

UK የዘረ መል ቅንጣት ላይ ጥናት በማድረጓ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ እንደደረሰችበት አስረድተዋል።

በቤልጄም የሚሠሩት የቫይረስ አጥኚ ማርክ ቫን፤ "በቀጣይ ቀናት አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ በብዙ አገሮች ይገኛል ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN #ETHIOPIA ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት በሚቀጥለው #ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የሱዳን ጠ/ሚ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው ሐምዶክ እና ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው በመጪው ማክሰኞ ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለቱን አገሮች ድንበር ለማካለል የተቋቋመው ኮሚቴ በሚያደርገው ድርድር…
#ETHIOPIA #SUDAN

በም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴ ውይይት ላይ ለመታደም ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብቷል፡፡

በልዑኩ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ቀንዓ ያደታ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው መካተታቸውን አል ዓይን (AlAIN) ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MinistryOfEducation

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ተባለ።

በዚህ ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ መክረዋል።

ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ የተጀመረ ሲሆን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተነስቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አሳስበዋል።

ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላት እንዲሁም ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር "ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ" በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻም እንደሚጀመር አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #SUDAN በም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴ ውይይት ላይ ለመታደም ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብቷል፡፡ በልዑኩ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ቀንዓ ያደታ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው መካተታቸውን አል ዓይን (AlAIN) ዘግቧል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ሁለተኛው የኢትዮ - ሱዳን የድንበር ጉዳዮች የከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት በካርቱም ሱዳን እየተካሄደ ነው።

2ቱ ወገኖች በጋራ የድንበር አካባቢ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ይመክራሉ።

በማስቀጠልም የጋራ ድንበራቸውን በተመለከተ ያሉ ማናቸውንም ዓይነት ልዩነቶች ሁሉንም በሚያስማማ መንገድ ለመፍታት የወደፊት አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። (EPA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

ዛሬ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳታላይት አምጥቃለች።

' ET-SMART-RSS ' በስኬት መምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በይፋዊ ፌስቡክ ጉፁ ላይ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በዋናው ዳታ ቤዝ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት ለጊዜው ማቆሙን ገልጿል።

ደንበኞች የተቋረጠው አገልግሎት #በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈቶ ወደ ቀደመ አገልግሎቱ እንስኪመለስ በትእግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ኤጀንሲው ካጋጠመው የሰርቨር ችግር ውጪ በድረ-ገጽ አማካኝነት የሚሰጠው የፓስፖርት አገልግሎት አልተቋረጠም ብሏል።

በኤጀንሲው ዋና ሰርቨር ላይ ያጋጠመው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ በመግባት ቀጠሮ ማያዝ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ያጋጠመውን ችግር ዛሬ ወይንም ነገ አልያም በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እተየሰራ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #SUDAN

በሱዳን እየተካሔደ በሚገኘው 2ኛው የኢትዮ - ሱዳን ድንበር የጋራ ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ውይይት ላይ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን የተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡

ከጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት እየፈጸሙ ስለመሆናቸው አቶ ደመቀ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡

ይህም በትግራይ ክልል የተፈጠረው ቀውስ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ነው የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት መፈጸም የጀመረው፡፡

አቶ ደመቀ በንግግራቸው “ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የሱዳን ጦር የተደራጁ ጥቃቶችን እየፈጸመ መሆኑን እየተመለከትን ነው” ብለዋል፡፡

በዚህም “የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶች ተዘርፈዋል ፤ ካምፖቻቸው ወድመዋል እንዲሁም የራሳቸውን የእርሻ ምርት እንዳያጭዱ ተደርገዋል” ያሉት አቶ ደመቀ በርካታ ንጹሀን ስለመገደላቸው እና ስለመቁሰላቸውም ገልጸዋል፡፡

እናም በድንበር አከባቢዎች የተከሰተው የቅርብ ጊዜ ክስተት የኢትዮጵያን መንግስት ክፉኛ እንዳሳሰበው ነው በንግግራቸው ያካተቱት፡፡

ም/ጠ/ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ይህ ሁኔታ በሰሜን ዳግልሽ ተራራ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ባለበት ለማቆየት የደረስናቸውን ስምምነቶች አደጋ ላይ እየጣለ ነው” በማለት ስጋታቸውንም ገልጸዋል፡፡

More : https://telegra.ph/AlAin-12-22

ምንጭ፦ አል ዓይን (AlAIN)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ዛሬ ኢትዮጵያ ሳላመጠቀችው ሁለተኛዋ ሳተላይት ፦

• የሳተላይቷ ስም ET-Smart-RSS

• ET-Smart-RSS እንደ ETRSS-1 የመጠቀችው ከቻይና ነው።

• ሳተላይቷ ከቻይና የመጠቀችው ኢትዮጵያ ለዚህ የሚሆን መሠረተ-ልማት የሌላት በመሆኑ ነው።

• ET-Smart-RSS ሳተላይት ስትሠራ የመጀመሪያውን ዲዛይን ሠርቶ የላከው ESSI ነው።

• ET-Smart-RSS ተግባር የመሬት ምልከታ ሆኖ የምስል ጥራቷ ግን ከመጀመሪያዋ በእጅጉ የተሻለ ነው።

• ET-Smart-RSS ናኖ ሳተላይት እና የዘመኑን የረቀቀ ቴክኖሎጂ የያዘች ናት። የመጀመሪያዋ ETRSS-1 ማይክሮ ሳተላይት ናት።

• የመጀመሪያዋ እና የዛሬዋ ሳተላይት አንድ ላይ ሲጣመሩ የተሻለ የመሬት ምልከታ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል። ESSTI የሁለቱን ምስሎች በማቀናጀት ይቀበላል።

በሌላ መረጃ ፦

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካመጠቀቻቸው የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች በተጨማሪ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ሌሎች ሶስት ሳተላይቶች ለማምጠቅ ዕቅድ ይዛለች።

ከእነዚህ ሶስት ሳተላይቶች መካከል አንደኛው የኮሙዩኒኬሽን እና ብሮድካስቲግን ሳተላይት ነው።

ይህ ሳተላይት የስልክ ፣ የኢንተርኔት አገልግሎትን፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ጨምሮ ለመገናኛ አገልግሎት የሚውል ነው።

ሌላኛው ደግሞ እስከ 0.5 ሜትር የሚሆን የምስል ጥራቱ ከፍተኛ የሆነ የመሬት ምልከታ ሳተላይት እንደሚሆን ተገልጿል።

#DrYeshrunAlemayehu
#EthiopiaSpaceScienceandTechnology
#etv

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EFFORT

ዶ/ር አብርሃም በላይ ትእምት (ኢፈርት) ሥራው እንዲቀጥል መወሰኑን ተናግሩ።

የተቋሟቱ ሠራተኞች ደመወዝ እንዲከፈል እና ሠራተኞቹ ሥራ እንዲጀምሩ መንግሥት መወሰኑን አስታውቀዋል።

ዶክተር አብርሃም በላይ ይህን ያሳውቁት ዛሬ በመቐለ ከተማ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

ትእምት አመራሩ በባለአደራ እንዲመራ መንግሥት አምኖበት ለፍርድ ቤት ለውሳኔ አቅርቧል ብለዋል ዶ/ር አብርሃም።

የባለ አደራ ቦርድ አባላቱ 7 አባላት ያሉት እንደሆነ ከእነዚህም አምስቱ በትምህርት እና በተመሳሳይ ዘርፍ ልምድ ያላቸው መሆናቸው እና 2ቱ ደግሞ ከገንዘብ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተመረጡ መሆናቸው ገልፀዋል።

በተቋሙ (ትእምት) ላይ የተጀመረው የፍርድ ቤት ጉዳይ ጎን ከጎን የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል።

የትእምት ጉዳይ በፍርድ ቤት የተያዘ ቢሆንም የተወረሰ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። (EPA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,347
• በበሽታው የተያዙ - 290
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,137

አጠቃላይ 120,638 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,864 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 104,818 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

274 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #SUDAN በሱዳን እየተካሔደ በሚገኘው 2ኛው የኢትዮ - ሱዳን ድንበር የጋራ ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ውይይት ላይ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን የተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት እየፈጸሙ ስለመሆናቸው አቶ ደመቀ በንግግራቸው…
#SUDAN #ETHIOPIA

በም/ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከሱዳን ሉዐላዊ ምክር ቤት እና የሽግግር ወታደራዊ ም/ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሌተናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ትብብር እና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ርዕሶች ላይ መክረዋል።

በተጨማሪ ወቅታዊ የሁለቱ ሀገራት ጉዳዮች እና አከባቢያው ሰላም ላይ እንደተወያዩ ኤፍ ቢ ሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UNITED_NATION

በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች የአያያዝ ሁኔታ የሚገመግሙ 2 ቡድኖቹ ወደ ክልሉ መግባታቸውን የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ሃላፊ ሚሼል ባሸሌት የኢትዮጵያ መንግስት በተደረሰው ስምምነት መሰረት ያልተቆራረጡ ሰብዓዊ አቅርቦቶች እንዲኖሩ መፍቀዱን መቀበላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሆኖም ሰብዓዊ አቅርቦቶቹ በጦርነቱ የተጎዱ ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎች ሊያዳርሱ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡

ሚሼል ባሸሌት ከዓለም አቀፍ ህግጋት በተጣረሰ መልኩ በተሰባሰበ ህዝብ ላይ የመተኮስ፣ ሆን ብሎ ንጹሃንን ዒላማ የማድረግ፣ የግድያ እና ዝርፊያ ድርጊቶች ጭምር እንዳሉ የሚያለክቱ መረጃዎች ደርሰውናል ብለዋል፡፡

ይህም በ2ቱም ወገኖች ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ አለመቻላቸውን የሚያሳይ ነው ያሉም ሲሆን ጦርነቱ በክልሉ ሰሜናዊ ፣ ማዕከላዊ እና ደቡባዊ አካባቢዎች ቀጥሏል መባሉ ይበልጥ እንዳሳሰባቸውም ነው ኮሚሽነሯ የገለጹት፡፡ #AlAin

የተመድ OHCHR ሙሉ መረጃ 👇
https://www.ohchr.org/EN/NewsEvents/Pages/DisplayNews.aspx?NewsID=26623&LangID=E

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Mekelle

የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ ከንቲባ የሆኑት አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ በመቐለ ከተማ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት አጠቃላይ / የተሟላ የባንክ አገልግሎት መሰጠት እንደሚጀምር አሳውቀዋል።

አቶ አታኽልቲ ይህን ያሳወቁት ትላንት ከመቐለ የንግዱ ማህበረብ ጋር የመጀመሪያ ውይይታቸው ባደረጉበት ወቅት ነው።

ጊዜያዊ ከንቲባው በመቐለ ከባንክ ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ለማቃለል ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ያላቸው አካላት ወደ ባንክ ገንዘባቸውን እንዲያስገቡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ ሲሰራ እንደነር አስተውሰዋል።

በሌላ በኩል ፦

የትግራይ ክልልን ፖሊስ ለማደራጀት በኮሚሽን ደረጃ አመራሮች ተመድበው እየሰሩ እንደሆነ የመቐለ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ተናግረዋል።

የፖሊስ ኃይል አደራጅቶ ስራ በማስጀመሩ ሂደት መቐለ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ከተሞች አንዷ እንደሆነች አሳውቀዋል።

ከትላንት በስቲያ በመቐለ ከተማ ካሉ የፖሊስ አባላት እና ትራፊኮች ጋር ውይይት እንደተደረገ የገለፁት አቶ አታኽልቲ ከሁለት እና ከሶስት ቀን በኃላ በመቐለ መደበኛ የፖሊስ አገልግሎት መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SecurityAlert

www.tikvahethiopia.net

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የፀጥታ እና የደህንነት ችግር መኖሩን እያሳወቁን ይገኛሉ።

ታጣቂዎች በሰውና በንብረት ላይ ጥቃት እያደረሱ እንደሆነም ገልፀውልናል።

ጉዳዩ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግም አባላቶቻችን ጥሪ አቅርበዋል።

በየአካባቢው ያሉ የፀጥታ እንዲሁም የደህንነት ስጋቶችን በ www.tikvahethiopia.net በኩል ማሳወቅ ትችላላችሁ።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
ኢብራሂም ሀጂ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ጋዜጠኛ ፣ አርቲስት እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዕድገት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱት ኢብራሂም ሀጂ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኤፍ ቢ ሲ አሳወቀ።

ኢብራሂም ሀጂ አሊ ካለፈው ክረምት ጀምሮ ባጋጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ትናንት ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የቀብር ስነስርዓታቸው ዛሬ 9 ሰዓት ላይ በኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መቃብር ይፈጸማል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SecurityAlert www.tikvahethiopia.net በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የፀጥታ እና የደህንነት ችግር መኖሩን እያሳወቁን ይገኛሉ። ታጣቂዎች በሰውና በንብረት ላይ ጥቃት እያደረሱ እንደሆነም ገልፀውልናል። ጉዳዩ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግም አባላቶቻችን ጥሪ አቅርበዋል። በየአካባቢው ያሉ የፀጥታ…
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል "መተከል ዞን" ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በተፈፀመው ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች መቁሰላቸውን ፣ ንብረት መውደሙን የቲክቫህ አባላት በፎቶ አስደግፈው አሳውቀዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን የምንለዋወጥ ይሆናል።

www.tikvahethiopia.net ላይ በየአካባቢያቹ ያለውን ማንኛውም የፀጥታና የደህንነት ስጋት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia