TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

ትላንት "በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ" የወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ቢሮ አስተባባሪነት በቢሮዉ ስር ባሉ 10 ወረዳና የኦሮሚያ ፣ አዲስ አበባ ፣ ደቡብ ፣ አማራ እና ትግራይ ወጣቶች አደረጃጀትን በማስተባበር በሰሚት የጋራ መኖርያ አከባቢ በመገኘት የጤፍ አጨዳ ፕሮግራም አድርገዋል።

ከፕሮግራሙ መልስ በጤፍ አጨዳዉ ላይ ለተሳተፉት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የለሚ ኩራ ክ/ከ የወጣቶችና በጎ ፍቃድ ቢሮ ሀላፊ አቶ ባጫ ጂሬኛ ምስጋና በማቅረብ የወጣቱ ሀይል በቀጣይ በክፍለ ከተማዉ ለሚሰሩ ስራዎች ለይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅረበዋል።

Via Amanuel Eticha (TikvahFamily)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ የብሔራዊ ስቴዲዬም ሁለተኛዉ እና የማጠቃለያ ምዕራፍ ግንባታ ፊርማ ተካሂዷል።

የሁለተኛ ምዕራፍ ስራዉ ዋና አካል የጣራ መሸከሚያ ምሶሶ ኮንክሪት ሙሊት ስራ መጀመሩን ስፖርት ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ሀሰተኛ የብር ኖት ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ተያዘ።

አበርገሌ ወረዳ 16, 900 #ሃሰተኛ የብር ኖቶች ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው ሃሰተኛ የብር ኖቶቹን ይዞ ትናንት በወረዳው ወርቃዲኑ ጥንስስ ከተማ ለመገበያየት ሲሞክር ተደርሶበት ነው።

በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው ምርመራ እየተደረገበት መሆኑም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EuropeanUnion

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት ሃገራት የ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የተደረገው ድጋፍ ሱዳን እና ኬንያን እንደሚያካትት ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ከ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ውስጥ 18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል መሆኑን ነው የጠቀሰው፡፡

እንዲሁም ሁለት ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለሱዳን የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዮሮ የሚሆነው ደግሞ በኬንያ የምግብ ዋስትና ለተጋረጠው አደጋ የሚውል መሆኑ ነው የገለጸው፡፡

የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ መድረሱን ገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot
#Mekelle

ዛሬ የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ በወቅታዊ ገዳዮች ዙሪያ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ አታኽልቲ በመግለጫቸው ተከታዩን ብለዋል ፦

- ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስና ከነዋሪዎች ጋር በቅንጅት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወነ ነው።

- የመደበኛ ፖሊስ አባላት በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ሥራ ገበታቸው ለመመለስ ሪፖርት እያደረጉ ነው።

- በጎ-ፈቃደኛ እና መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው ወጣቶች በከተማዋ ሰላምና መረጋጋት ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

- በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም ተገቢው ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው።

- ከሰባት ክፍለ ከተሞች መካከል በ5ቱ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት የሚሰጡ አመራሮች ተመድበዋል። በቀሪ 2 ክፍለ ከተሞች ላይ ምደባ ለማካሄድ ህዝባዊ ውይይት እየተደረገ ነው።

- ከ2 ሺህ 26 የመንግሥት ሠራተኞች መካከል እስካሁን 84 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሥራ ለመመለስ ሪፖርት አድርገዋል።

- በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ ምክር ቤቶች በነበሩበት እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጦ ጥሪ ቢደረግም ባለመምጣታቸው ምክር ቤቶቹ በህዝብ ምርጫ እንደ አዲስ እንዲቋቋሙ ተደርጓል።

- ምክር ቤቶችና አመራር የተመደበላቸው ክፍለ ከተሞች ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ገብተዋል።

- የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ችግሩ ተፈቷል።

- የዋጋ ንረት ችግር እንዲፈታ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው። (ena)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ሱዳን_ያስተናገደቻቸው_ሰልፎች

በዳቦ ዋጋ መናር ምክንያት ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን እንዲነሱ ያደረገው የሱዳን አብዮት 2ተኛ ዓመቱ በተለያዩ ስሜቶች እየታሰበ ነው፡፡

ከዛሬ 2 ዓመት ወዲህ ፕሬዝዳንት አልበሽርን በመጣል አዲስ የሽግግር መንግስት የተቋቋመ ሲሆን ወታደሩንና ሲቪሉን የሚወክሉ መሪዎች ሀገሪቱን እያስተዳደሩ ነው፡፡

ዛሬ ካርቱምን ጨምሮ በሱዳን የተለያዩ ከተሞች በተካሔዱ ሰልፎች በአንድ ወገን አብዮቱን የሚደግፉ አካላት በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎችም ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡

አብዮቱን በመደገፍ ሰልፍ የወጡ ሰልፈኞች የአብዮቱ ዓላማ ግን መስመሩን መሳቱን በመጥቀስ ቁጣቸውን አሰምተዋል፡፡

የኑሮ ውድነት እና የኢኮኖሚ ቀውስን በመቃወም ከሁለት ዓመት በፊት አብዮት ቢፈነዳም እነዚህን ችግሮች ከመቅረፍ አንጻር አብዮቱ ምንም አልፈየደም በሚል የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋብተዋል፡፡

በሱዳን ያለው የኑሮ ውድነት ፣ ከፍተኛ የዳቦ እጥረት እና የሀገሪሩ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

ከአብዮቱ በተቃራኒ በመቆም የፕሬዝዳንት አልበሽርን መንግሥት በመደገፍ አደባባይ የወጡም አሉ፡፡ እነዚህ አካላት የአልበሽር ስርዓት እንዲመለስ የሚፈልጉ ናቸው፡፡

ያም ሆነ ይህ ታዲያ የሀገሪቱ ሉኣላዊየሽግግር መንግስት ሊቀ መንበር በአብዮቱ 2ኛ ዓመት ላይ ትኩረት ያደረጉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ እና የሉኣላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን ፣ የአልበሽር አገዛዝ የተወገደበትን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ሰራዊቱ በአብዮቱ የተገኙ ውጤቶችን እንደሚያስጠብቅ ተናግረዋል።

አል ቡርሃን በትዊተር ሱዳናውያንን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን (AlAIN)

@titikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,313
• በበሽታው የተያዙ - 469
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,294

አጠቃላይ 119,494 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,846 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 102,153 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

258 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Djibouti #DrAbdelaHamdok #IGAD

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር አብደላ ሀምዶክ በ38ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ጅቡቲ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጅቡቲ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አቀባበል ተቀብለዋቸዋል።

የኢጋድ ስብሰባ ነገ ይጀምራል።

በኢጋድ ስብሰባ ላይ ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ለአባል ሀገራት መሪዎች ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያን ውስጣዊ ጉዳይ ጨምሮ የኬንያ እና ሶማሊያ አለመግባባት ዋነኛ የውይይት አጀንዳዎች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት የደረሰበትን ሁኔታ እንደሚዳሰስ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ኢጋድ እየሰጠ ያለውን የወረርሽኙ የሁለተኛ ዙር ምላሽ በማስመልከት ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ ፦ ኢጋድ፣ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ፣ አል ዓይን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19

የኤስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የኮቪድ-19 ክትባት (Pfizer/BioNTech) ተከተቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክትባቱን ሲወስዱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ታይተዋል።

ኔታንያሁ የኮቪድ-19 ክትባትን የወሰዱ የመጀመሪያው እስራኤላዊ ሲሆኑ በወሩ መጨረሻ በሚሊዮን የሚቆጠር የኮቪድ-19 ክትባት እንደሚደረስ ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎቻቸው ክትባቱን ይወስዱ ዘንድ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#WolaitaSodo

በወላይታ ሶዶ ከተማ "መርካቶ ገበያ" ዛሬ መንስኤ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የወ/ሶዶ ከተማ እሳት አደጋ መከላከያ ቡድን የበኩሉን ጥረት እያደረገ የሚገኝ ቢሆንም ካለው ከባድ ነፋስ የተነሳ እዘሳቱ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመት በመሆኑ ተጨማሪ ኃይል እንደሚያስፈልግ የከተማዋ ነዋሪዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

Via Wolaita Zone Communication
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TikvahFamilyWoalita

ዛሬ በወላይታ ሶዶ የደረሰውን የእሳት አደጋ የሚያሳዩ ተጨማሪ ምስሎች ከወላይታ ሶዶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ተልከዋል።

የእሳት አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አሳውቀዋል።

#Tariku #Natnael #Tikursew
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia