TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻችን'

በትግራይ ክልል የነበረውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎቻችን ቁጥር ወደ 50 ሺህ ይጠጋል።

የሱዳን ህዝብ እና መንግስት የተሰደዱ ዜጎቻችን ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል።

UNHCR ለስደተኞች የህይወት አድን ድጋፍ እያደረገ ነው።

ከUNHCR እንዳገኘነው መረጃ በሱዳን የሚገኙት የሀገራችን ዜጎች ወደሀገራቸው ፣ ወደቤታቸው መመለስ ፣ ህወታቸውን ዳግም መገንባት ይፈልጋሉ።

በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻችን የሚመለሱት ግን የሰላም ፣ የፀጥታ ደህንነት ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ ለUNHCR ተናግረዋል።

https://www.unhcr.org/news/press/2020/12/5fd3ab2d4/statement-attributable-un-high-commissioner-refugees-filippo-grandi-situation.html

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ወደ #ጎንደር ተቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት እንደገና ይጀምራል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Mekelle

በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የተዘጋጀ ድጋፍ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ደርሷል፡፡

ይህ ድጋፍ የአቅርቦት እጥረት ላጋጠማቸው የጤና ተቋማት መድኃኒቶችን እና ሌሎች የእርዳታ አቅርቦቶችን ያካተተ ነው፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Mekelle

ብዓለም ለኸ ኮሚቴ ቀይሕ መስቀልን ማሕበር - ICRC ኢትዮጵያን ዝተዳለወ ሓገዝ ኣብ ርእሰ ከተማ ክልል ትግራይ መቐለ በፂሑ አሎ፡፡ እቲ ሓገዝ ሕፅረት ቀረብ ንዘጋጠሞም ትካላት ጥዕና ዝዉዕሉ አፋውስን ካልኦት ናይ ረድኤት ቀረባትን ዘካተተ እዩ፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቤኔ ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ዶክተር ሙሉ ነጋ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ስራ ያቆሙ የመንግስት ሰራተኞች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በተጠቀሰው ቀን ወደ ስራ ገበታው የማይመለስ የመንግስት ሰራተኛ ካለ በገዛ ፈቃዱ ስራውን እንደለቀቀ ተደርጎ ይወሰዳል ተብሏል።

የንግድ ድርጅቶች ከነገ እሁድ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራቸው መመለስ አለባቸው ተብሏል።

ይህን በማያደርጉ የንግድ ድርጅቶች ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እርመጃ መውሰድ እንደሚጀምር ገልጿል።

በህጋዊም ሆነ በህገ-ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ሁሉ እስከ #ማክሰኞ ድረስ እንዲያስረክብ ጥሪ ቀርቧል።

ከማክሰኞ በኋላ "የቤት ለቤት ፍተሻ" ይደረጋል ፤ በፍተሻው ትጥቅ የተገኘበት ግለሰብ ሲያጋጥም ተጠያቂ እንደሚሆን ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,416
• በበሽታው የተያዙ - 515
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,240

አጠቃላይ 116,297 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,803 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 92,449 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

318 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthioTelecom

በመቐለ ከተማ እና በማይጨው የሞባይል ድምፅ አገልግሎት ማስጀመር እንደቻለ ኢትዮ ቴሌኮም ማምሻውን ገልጿል።

በመቐለ የሞባይል ድምፅ አገልግሎት የተጀመረው "አማራጭ ኃይል" በመጠቀም ከመሆኑ አንፃር የአገልግሎት መቆራረጥ ሊየጋጥም ይችላል፤ ደንበኞችም ይህን ይገንዘቡ ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም የጥገና እና የመሰረተ ልማቶች መልሶ የማቋቋም ስራዎች በማከናወን ከኃይል አቅርቦት ጋር በተገናኘ ከኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ጋር በመስራት የተሟላ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እያደረገ እንደሆነ አሳውቋል።

* ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።

@TikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbdallaHamdok 

ዛሬ ጥዋት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሃምኮድ ለ2 ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የሱዳን የደህንነትና የፀጥታ እንዲሁም ወታደራዊ ባለስልጣናት አብረዋቸው መጥተዋል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ዛሬ ጥዋት ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) የገቡት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ ከጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በጠ/ሚር ፅ/ቤት የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ግንኙነት ፣ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ምቹ መሠረት እንደሆነ ሁለቱም ወገኖች ገልጸዋል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ ኢትዮጵያ የምታካሂደውን የሕግ ማስከበር ሥራ አስመልክቶ ሱዳን አጋርነቷን ገልጣለች ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክም ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይም ደግሞ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለሱዳን እጅግ አስፈላጊ በሆነ ወቅት እንደደረሱላቸው አስታውሰዋል።

በሁለቱ ሀገራት መሪዎቹ መካከል የተካሄደው ውይይት በበርካታ የጋራ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
www.tikvahethiopia.net

Approve / Disapprove እነዚህ በወረዳ ያሉ መረጃዎች በዛው ወረዳ ነዋሪዎች ማረጋገጫ እንዲሰጥባቸው የተዘጋጁ ናቸው።

ለምሳሌ አንድ ወረዳ ውስጥ ያለውን ችግር የሚያረጋግጠው የዛው አባል ነው እንጂ ከሌላ ቦታ ያለብህን ችግር እኛ እናውቅልሃለን የሚል አካል አይደለም።

በድረገፁ ላይ በሀሰተኛ አካውንት / በዘመቻ ፣ በደቦ፣ በስሜት የሚሰራ ስራ ስለማይኖር መሬት ላይ ያለውን ችግር ለመረዳት ይጠቅማል።

በሌላ በኩል ሰዎች ፖስት ሲያደርጉ ማንነታቸው ለሌሎች አይታይም ፥ ይህም ሃሳባቸውን ፣ ችግራቸውን፣ መረጃዎቻቸውን በነፃነት ለቲክቫህ አባላት እንዲያጋሩ ይረዳቸዋል።

* ውድ አባላት ምዝገባው በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎች ስለሚያከናውኑ ችግሮች ሊያጋጥም ይችላል ፤ ይህንንም እንድትረዱን እንማፀናለን ፤ ያሉ ችግሮችን በሂደት እየፈታን እንሄዳለን።

በድረገፁ ላይ ችግር ሲያጋጥማችሁ በ @tikvahethhelpBOT አሳውቁ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia